Saturday, July 11, 2026

ሥር እየሰደደ የሄደው የምሥራቅ ጎጃም “ቅብዓት” የክህደት አምልኮ ወደ ሰሜን አሜሪካ እየተዛመተ እንደሆነ ተነግሯል፤

የምሥራቅ ጎጃም ተሿሚው
ባላፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በተለያየ ጊዜ ስለ ምሥራቅ ጎጃም የቅብዓት እምነት አራማጆች የሚያደርጉትን የተለያዩ
እንቅስቃሴዎች በቅርበት ለተከታተለው፤ <<እንቁላል በቆይታ በእግሯ ትሄዳለች>> የሚለው አካሄድ በትክክል የሚያጠናክር አካሄድ እየሄዱ እንዳለ በደንብ መረዳት ይቻላል። በተለይ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ “ጳጳሳትን ሾመናል” ብለው ወደ ፊት ከመጡ በኃላ በበቤተክርስቲያን በኩል ምንም አይነት ምላሽ አልተሰጠም፣ ምንም አይነት እርምጃም አልተወሰደም፤ ይሄ ደግሞ የሚነግረን አንድ ጠንከር ያለ አካሄድ እንዳለ በትክክል የሚያስረዱ ሁኔታዎች እንዳሉ መረዳት የሚያዳግት አይመስለንም፤ በተለይ በኦሮሚያ ቤተክህነት፣ በአቡነ ሰላማ ቤተክህነት ምረታ ማግስት የተከሰቱ በርካታ ደም አፋሳሽ እውነታዎች ለምን በምሥራቅ ጎጃም እንደዚህ አይነት እርምጃም ሆነ አካሄድ መሄድ ተሳናቸው የሚለው ትልቁ እና ዋነኛው ጥያቄ እንደሆነ ብዙዎች የሚረዱት ይመስለናል።

“ቅብዓት” የሚለው እምነት ምን አይነት መሰረት አለው? የሚለውን በጥቂቱ ብንመለክት ምናልባት አካሄዳቸው እና መጥነው የሚረግጡት ብዙ ማሳያዎችን ብንመለከት ትንሽ ነገሮችን ሊያጠራልን ይችላል ብለን ስላሰብን ጥቂት የእምነቱን መሰረት የሆኑትን ነገሮች እናንሳ፤ በቅብዓት እምነት “ወልድን በሰውነቱ ከተዋሕዶ በኃላ ፍጡር አንለውም” ይሉናል፤ በሌላ በኩል “ፍጡር ሥጋን አልተዋኃደም” ይላሉ እስቲ እነዚህን እንተንትናቸው፤ ወልድን በሰውነቱ ከተዋሕዶ በኃላ ፍጡር አንለውም - በቅድስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ወልድ የምንነው የእግዚአብሔር አብ ድኅረ ዓለም ያለ እናት፤ በኃላም ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት የተወለደው እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በተለይ ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን፤ ነከፍሷ ነፍስን ነስቶ ፍፁም ሰው ፤ ፍፁም አምላክ ሆኖ መወለዱን የቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ይነግረናል፤ ነገር ግን እንደ “ቅብዓት” እምነት ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው እግዚአብሔር ወልድ ፍፁም ሰው የሚለውን አይቀበሉም ፤ የእመቤታችንን ንጽሕይተ ንፁሃን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከሰዎች ተለይታ እግዚአብሔር አብ ያዘጋጃት ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች መባልን አይቀብሉም፤ ለዚህም ይመስላል በታሕሣስ 28 የጌታ መወለድ የሚበሰርበት እለት ታዓምረ ማርያምን በፍፁም አያነቡም፤ ስለማይቀበሉት ማለት ነው።