Friday, January 4, 2013

‘ እዚህ የተገኘነው ላንተ ክብር ነው!’ እነ ‘ ሊቀ ትጉሃን’ መኩሪያ ጉግሳ



ዳንኪራው በከበሮ ሲቀልጥ እንዴት ያሳዝናል
ይህ አነጋገር ሲሰማ በአንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ነኝ በሚል ሰው የተነገረ በመሆኑ ክብር ለሚገባው ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፣ አልያም ቅዱስ ጳውሎስ “ክብር ለሚገባቸው ክብርን ስጡ” ብሎ ለመሰከረላቸው ለቅዱሳን የተነገረ እንዳይመስለን። ይልቁንም በአንድ አሜሪካን ውስጥ በሚገኝ ሬስቶራንት ውስጥ በመገኘት የጫጉላ ሽርሽር በማድረግ ላይ ለሚገኘው ለድምጻዊው ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ለተሰኘው ዘፋኝ የተነገረ ነው።

በእርግጥ በዘመናችን ላሉ አገልጋይ ነን ባዮች ብዙ ነገር ግራ የገባቸው ይመስለናል። ዓለማዊው ከመንፈሳዊው፣ ምድራዊው ከሰማያዊው፣ ሥጋዊው ከነፍሳዊው፣ ጊዜያዊው ከዘላለማዊው ነገር ጋር የተምታታባቸው ይመስለናል። ይህ ባይሆን ኖሮማ ‘ቴዲ ላንተ ክብር ነው እዚህ የተገኘነው’ በማለት በ’ሊቀ ትጉሃን’ መኩሪያ ጉግሳ ፕሮግራም መሪነት፣ በ’ቀሲስ’ ተስፋዬ መቆያ ባራኪነት፣ ‘በዘማሪ’ ቸርነት ሰናይ ዘማሪነት ለአንድ ዓለማዊ ዘፋኝ ያውም የዓለም ዳንኪራ ሲደለቅ በሚያመሽበት ሬስቶራንት ውስጥ በመገኘት እንዲህ አይነት ዝላይ እና ድሪያ ባልተደረገ ነበር።
ለነገሩ ያልተማሩትን ያልዋሉበትን ወንጌል እናስተምራለን በማለት ከመናፍቃኑ ስብከት እየለቃቀሙና እየቃረሙ በሚያመጡት ‘ስብከት’ ፤ ‘ወንጌል ምዕመኑ አልገባውም’ በሚል ያልበሰለ ንግግር ታጅበው በመድረክ ላይ ከወጡ መምህራን እና ዘማሪያን ነን ባዮች ከዚህ ሌላ ምን ሊጠበቅ ኖሯል። ወንጌል የሚለው ትርጉም ምንድነው ተብለው ሲጠየቁ እንኳን መልስ የሌላቸው፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናንን ልብ አማርኛ በማራባት እና በእንቶ ፈንቶ ልቡን ይዘው የተናገሯትን እንዱን እንኳን በተግባር ከማያውሉ ‘ወንበዴዎች’ ከዚህ ሌላ ምን ይጠበቃል።



'ቅሱስ ጋብቻ' ትምህት 
አይ ተስፋዬ መቆያ! ከዚህ ቀደም ‘ተሐድሶ የለም!’ በሚለው ንግግርህ ሳትፀፀት እና ንስሐ ሳትገባ ቀረህ “አይ ረስቼው ነው” በሌላ ጊዜ የሰው ስም የሚያጠፉ ናቸው በማለት ስትኮንን ተሰምተሃል እሁን እንጂ በየመድረኩ እና በየለቅሶ ቤቱ ሳይቀር እኔ አላልኩም ስትል ሰነበትህ። እንደውም እነ ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው እያልክ የስድብ መዓት ታወርደው ጀመር፣ ምነው በየለቅሶ ቤቱ ለማጽናናት በሚል ሰበብ ከምትሳደብ አንዳንዴም ከምታስለቅስ ከክፉ ድርጊትህ አትቆጠብም ነበር። አሁን ደግሞ ክብር ለእግዚአብሔር መስጠቱን ዘንግተህ ለእነ ቴዲ አፍሮ ክብር ስትሰጥ ማመሸትህ አይብስም። ‘ተሐድሶ የለም አላልኩም’ ብለህ ሽምጥጥ አድርገህ የካድከው በሰኔ ፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የሰበከውን ስብከት ዘንግተህው ከሆነ አሁንም መለስ በልና፥ ከአርካይቭ ውስጥ ብትሰማው ግጥም አድርገህ መናገርህን ታስታውሰዋለህ። ለነገሩ አይፈረድብህም መድረክ ላይ ስትቆም ምን እንደምትናገር በደንብ ስለማታስተውለው ይሆናል ለዚህም ምስክሩ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ለእርቀ የመጡ የሰላም ልዑካን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በደብረ ሰላም ቅድስተ ማርያም እንደተናገርከው ‘እኛ የማናፍርበት፣ በኩራት የምንናገረው ገለልተኛነታችንን ነው’ በማለት በሊቃነ ጳጳሳቱ ፊት የመለያየት፣ የመገነጣጠል መንፈስ ያለበት ንግግር ስትናገር መስማቱ በቂ ምስክር ነው።

ዘፈኑም ቀልጧል! 
በመድረክ ላይ የምትናገረውን ብታስተውለውና ብትገነዘበው ኖሮ ‘ ዘፈን ኃጢያት ነው’ ብለህ ባስተማርክበት አፍህ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው ክብር ለአንድ ዘፋኝ ሲሰጥ እየሰማህ ዝም ባላልክ አልፎም ተባባሪ ባልሆንክ ነበር። ደግሞ ይኽንንም በለመደ አፍህ ስለምትዋሽ ከነመረጃው ቀርቦላችኃል። ምናልባት መምህር ለመቼነው? መገኘትህ ካልቀረ ስለንስሐ ሕይወት፣ ስለሥጋ ወደሙ፣ ያለ ሥርዓተ ተክሊል ማግባቱን ወቅሰህና ገስፀህ ቀጣይ ሕይወቱን የሚስተካከልበትን ብትነግረው መልካም በነበረ። ያደረከው ድርጊት መልካም እንደሆነ ቆጥረህ እንደ አንድ አለማዊ ሰው አድናቆትህን ገልጸህ የተመለስከው አንተ እውነተኛ መምህር ከሆንክ የዘፋኝ አድናቂ እንዴት ትሆናለህ? ለነገሩማ ይሄንን የቀፀልከው ከአባትህ ከአባ መልአኩ ይሆናል። እሳቸው በመክረክ ላይ ልክ እንደ ክብር ‘40 ሺህ ብር የሚከራይ ቤት አለኝ’ ብለው አይደል። ለመነኮሴ ጾም፣ ፀሎት ትርጉም መሆኑ ቀርቶ ፎቅ ቤት እንዳላቸው ሲነግሩን አይደል የሰነበቱት፥ ወይ ጊዜ! ወይ የቤተክርስቲያን አምላክ!
ሌላው በጣም የሚደንቀው ነገር፤ በወቅቱ የተሰጠው የትምህርት ርዕስ ነው ‘ቅዱስ ጋብቻ’ ይላል . . . ለመሆኑ የተቀደሰ ጋብቻ የሚባለው ምንድነው? ነው በአንተና በተሐድሶ ቡድኖች የተሰጠው ስያሜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታስተምረው ውጪ ነው? ወይስ እንደሁሌ ድፍረትህ ገለልተኛ ስለሆንን ሥርዓቱንም፣ ቀኖናውንም ገለል ያለ ለማድረግ አስበህ ነው ለማንኛውም የቤተክርስቲያን አምላክ ፍርዱን ይስጥ። አንድን ጋብቻ የተቀደሰ የሚያደርገው እንደ ተጋቢዎቹ ዝግጅት በተክሊል (ለደናግላን)፣ በቀለበት ተክሊል (ለመዓስባን) ደናግላን ላልሆኑ ካልሆነም በሥጋ ወደሙ ብቻ (ሁሉም ላይ በሥጋ ወደሙ) መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ሥርዓተ ጋብቻው ሲፈጸም ነው። ያንተና የመሳዮችህ ቅዱስ ጋብቻ ደግሞ በዳንኪራና በሆታ ሲፈጸም ሆኗል ማለት ነው። ለዚህም አፍህን ሞልተህ ዓለማዊውን ጋብቻ ቅዱስ ብለህ በኃላም ባንተ ባራኪነት በጀሌዎችህ ዘማሪነት የተጀመረው የእነ ቴዲን የመልስ ሥነ-ሥርዓት ፍፃሜው በሬጌ ሙዚቃ ማጠቃለያ የማታምነውን መስቀል እያወዛወዝክ በልብህ ስትዘፍን አመሸህ፥ የለበስከው ፈረጅያ እና የለበስከው ቆብ ባይኖር ኖሮ እንደጓደኞችህ አብረህ ለመናጥ ዳድቶህ እንደነበር ማስተዋል ይቻላል። ይገርማል እንግሊዝኛ ሊዘፍኑ የተነሱ ወጣቶች የተናገሩትን አስተውለኽለዋል ‘ቴዲ መጣም ስለምወድህ እንዘምርልሃለን!’ ሲሉ ቤቱ በሙሉ በሳቅ፤ ምን ሊዘምሩ ነው ሲባል የፈረንጅኛውን ዳንኪራ ማውረድ ጀመሩ። ምን ያድርጉ ከእናንተ አስቀድመው የተማሩትን ነዋ (ይኼንን ሊንክ ይመልከቱ ) ቤተክርስቲያንን በአደባባዩ አዋርደው ለአዋራጆች ዳረጓት።

'ቴዲ እኛ እዚህ ቦታ የተገኘነው ላንተ ክብር ነው'
እኛ መቼም የሚገርመን የ’ሊቀ ትጉሃን’ መኩሪያ አፍ የሚታረመው፣ ምላሱ የሚገረዘው መቼ ይሆን? በየመድረኩ የሚወረውራቸው ያልበሰሉ እና ያልታረሙ ታላቅ እንኳንስ አንድ ኦርቶዶክሳዊ መምህር ነኝ የሚል ቀርቶ በአንድ ፕሮቴስታንት አዳራሽ ውስጥ ያለ ፖስተር የማይናገረውን ንግግር የሚተፋ ሰው መቼ ይሆን የሚታረመው። ለነገሩ አንዳንድ የገባቸው መምህራን እጁን ወደላይ ዘርግቶ ዓይኑን ጨፍኖ ሲያስተምር አይተው ‘መኩሪያ ሲያስተምር ፕሮቴስታንት አዳራሽ ያለሁ ይመስለኛል’ ይላሉ። ሚስቱም ለጓደኛዋ ስትናገር ‘መኩዬ የቅዱሳንን ስዕል ቤት ውስጥ አትስቀይ፣ ስትጸልዪም ለጌታ ብቻ ጸልዪ፣ ወዳሴ ማርያም፣ ሰኔ ጎልጎታ፣ . . . ወዘተ የማያስፈልጉ ተረቶች ናቸው እና አትጸልዪ ይለኛል ብላ ከነገረቻት ጋር አብሮ ሲታይ ነገሩ እንዴት ነው? ያሰኛል። በተለይም ሲሰብክ ለተከታተለው ሰው በቅርቡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዘውን የአሸናፊ መኮንን መጽሐፍ በመሆኑ የሰውየውን ማንነት ለመገመት ምንም አያጠራጥርም።

ሕይወት በንስሐ መመለስ መልካም ነበር እውነት ነው?
 በነገራችን ላይ ዘፋኞችን በሙሉ እየሰበሰበ ከመናፍቃን ካሴቶች የኮረጃቸውን ዳንኪራዎች እያስጠና ዘማሪ ማስባሉ ሲታይ በሁለት መንገድ ይታያል። አንደኛው ዘፋኞችን አሳምኖ ንስሐ እንዲገቡ አስደርጎ ተመልሰው ኃጢአት ነው ተብሎ (ገላ: 5 ፥ 19) ወደ ተነገረለት ዘፈን እንዳይመለሱ ማድረግ በጎ ነገር ቢሆንም፤ ሁለተኛው በመኩሪያው የሚደረገው ዘፋኝነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ዛሬ ማታ ዘማሪ በሚቀጥለው ቀን በሙዚቃ ኮንሰርት አቅራቢ ሆኖ መስቀጠል ግን የጤና እንደማይሆን የሁሉም ኦርቶዶክሳዊ አዕምሮ ይመረምረዋል። ይህ ተየሐድሶ ‘ማዘናጋት’ ስትራቴጂ አንዱ አካል ነው። መንፈሳዊ ዘማርያንን እና መንፈሳዊነት የተላበሱ መዝሙሮችን አስወጥቶ ዓለማዊነት በተላበሱ መዝሙር መሰል ዘፈኖች መተካት በየትኛውም መመዘኛ ለዘፋኞቹ ሁለንተናዊ እድገት ታስቦም አይደለም፣ ወይንም እነሱን ወደንስሐ ለመመለስም ሊሆን አይችልም። አባቶቻችንን ብሂል ለማስረሳት እና የቅዱስ ያሬድ ውብ አመስጋኝ ዜማዎች ለማስተው እና የዘመኑን የዘፋኝ እና የመናፍቃን ዜማዎች ለምዕመናን ለማስተዋወቅ የሚያደርጉት ዘማቻዎች ናቸው እንጂ።
ለነገሩ የ’ሊቀ ትጉሃኑን’ ግብር ለተመለከተ ይህ የሚያስደንቅ አይደለም፥ ከታክሲ ተራ ጓደኞቹ ጋር በየቀኑ ሲጣላ የሚውለው ዐርብና ረቡዕ ሳይቀር በሚበላው ክትፎ አይደለም? ከዚህ በተጨማሪ እስቲ በየትኛው ቤተ ክርስቲያን ነው መኩሪያ በኪዳንና በቅዳሴ ላይ ተገኝቶ የሚያውቀው? ቅዳሴ ሲያልቅም አይደል መጋረጃ ገለጥ አድርጎ የሚገባው፤ በየትኛው ኮሌጅ ተመርቆ እንዳሰፋው የማይታወቀውን ቀሚሱን አንጠልጥሎ የሚመጣው።የሚገርመው ደግሞ የሚሰጠው የማሳሳቻ ምክንያት ‘አይ ዛሬ እኮ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካልመጣህልን ብለውኝ ነው’ ሌላ ጊዜ ደግሞ ‘ትላንት ማታ ጨጓራዬ ተነስቶብኝ ሲያሰቃየኝ አደርኩ፣ እንቅልፍ አጥቼ አደርኩኝ’ ወዘተ የመሳሰሉትን ምክንያቶች በመደርደር ኪዳኑን ሆነ ቅዳሴውን ከተወው ሰንብቷል። ‘ሊቀ ትሁሃን’ ይሉታል እንዲህ ነው፥ ለነገሩ የቤተክርስቲያን አባቶች ሙልጭ ላለው ሰነፍ የሚሰጡት ስም ‘ሊቀ ትጉሃን’ ነው። ምናልባት ትጉህ ነህ ሲባል በቀጣይ ቀን ተሻሽሎ ይመጣል በሚል እሳቤ ነው። ይኼኛው ‘ሊቀ ትጉሃን’ ግን የሚገባው ሆኖ አልተገኘም አሁንም እንደተኛ ነው፤ ለዚህ አይደል ሹራብ እንደለበሰ ድምጽ ማጉሊያውን ጨብጦ ‘ቴዲ እኛ በዚህ ቦታ የተገኘነው ላንተ ክብር ነው!’ ያለው ያስለቅሳል! ያሳፍራል! ኸረ የቤተክርስቲያን አምላክ ተመልከት . . .

'አገልጋዮቹ' በቅዳሴ ሰዓት የሉም፣ በኪዳን ሰዓት የሉም . . .
ስለ ቸርነት እንኳን መናገር የሚያስፈልግ አይመስለንም በየሄደበት በሚፈታው ቀበቶው እና ያገኘውን ሁሉ ‘አገባሻለው’ በሚለው ንግግሩ ሁሉም ምዕመናን ጠንቅቀው ያውቁታል፥ በዚህ ቦታ ቀሚሱን እንደለበሰ ተገኝቶ ከሙዚቃው ቃና ማንቆርቆሩ የሚገርም አይሆንም ። እንግዲህ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዓይናችን እያየ የወንበዴዎች እና የመናፍቃን መሰብሰቢያ ሆናልናለች፤ ምዕመናኑም ቅዱስ ጳውሎስ ‘እንደ ጥበበኞች እንጂ፥ ጥበብ እንደሌላቸው አትሁኑ ቀኖቹ ክፎዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ!’ ኤፌ. 5 ፥ 15 የሚለውን ቃል ያስተዋልን አይመስለንም። እውነትን ከሐሰት፣ ጽድቁን ከኃጢያት፣ ብርሃንን ከጨለማ፣ መዝሙርን ከዘፈን፣ መናፍቁን ከአማኒው የምንለይበት ጥበቡን እና እውቀቱን አድሎናል። እኛ ግን በተሰጠን አልተጠቀምንም ስለዚህም እንደነዚህ አይነት የሐሰት መምህራንንና ዘማሪያንን ምናለበት መንነታቸውን ተረድተን ለይተን ብናርማቸው እና እሺ ቢሉ፣ ለንስሐ እንዲበቁ እምቢ ካሉ ደግሞ መንገዳቸውን እንዲያስተካክሉ ማድረግ ሲገባን የገዛ ጠላቶቻችንን በጉያችን ይዘን በሁለት ቢላ እየበሉ የጠላቶቻችን ተላላኪ እንዲሆኑ ፈቅደንላቸው እኛን መስለው፣ የእኛን አባቶች ፈረጅያ ለብሰው፣ ቆቡን አጥልቀው፣ መስቀሉን ተሸክመው በመካከላችን እየተመላለሱ እንሲ ከውጥ ሲያባርሩ ቀጣሪዎቻችው መናፍቃኑም ከውጪ እጃቸውን ዘርግተው እየተቀበሉ እስከ መቼ እንዝለቅ? ኸረ የቤተክርስቲያን አምላክ ተመክከት ወደኛ . . .  መርከቢቱ ልትሰጥም ስትቃረብ የእስራኤል አምላክ ወደኛ ተመክከት. . .
ለማንኛውም ቸሩ እግዚአብሔር የፀጋው ግምጃ ቤት የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን አይተዋትም፤ እኛ ዝም ብንል እንኳ እርሱ ዝም አይልምና በጊዜው ሁሉንም ይፈታዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ነገ በሬ ሰርቀው ሲመጡ ከመደናገጥ ዛሬ በእንቁላሉ ማረሙ የተሻለ ነበር። እንደ አበው ብሂል ‘ሳይርቅ በቅርቡ፥ ሳይደርቅ በእርጥቡ’ ብለው እንዳስተማሩን ማረሙ የተሻለና ተገቢ ነው እንላለን ለሙሉም ለእነርሱም፣ ለእኛ ለምዕመናኑም ማስተዋሉን ያድለን እንላለን።
በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን!  

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

8 comments:

  1. ቴዲን ከነሱ ጋር አትደምሩት መቶ በመቶ እሱ ይሻላል አምላክ አንድ ቀን ይመልሰው ይሆናል፡፡ እነዚህ አጭበርባሪዎች ግን ከቤተክርስቲያን ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ የሚከለክላቸው ሕግ የለም እንዴ የቤተክርስቲያን አምላክ ፍርዱን ይሰጣል እሾህ ወይን አያፈራም እባካችሁ አዳራሻችሁ ግቡ ምዕመኑን አትረብሹት

    ReplyDelete
  2. Egziabher mastewalun yest.....ke Egziabher gare metalat terfu ke kebir lemanes naw yetagese Amlake leferde sinesa yemiaktew yelem

    ReplyDelete
  3. የሊቃዉንት መሪ የሆኑት የኔታ ወልደ ጊወርጊስ መች ተለመደና ከተኪላ ዝምድና በሚል አስቀምጠውልናል

    ReplyDelete
    Replies
    1. Aleka Ayalew Tamiru enji Aleka Wolde-Giorgis aydelum. Sinitekis betkikil bihon melkam new.

      Delete
  4. betam new yemysazenew .libe yestachew kemalet wiche minem malet aychalem EGZEABEHR betkirsetyanene yetbkat..!!!!

    ReplyDelete
  5. Alubalta kemitisifu kal egxiabher atisifum geta eko yalew hatiat yelelebet binor yiwigerat new ...

    ReplyDelete
  6. wendimochihin kenitwokis min alebet and legna yemitekim yegziabher kal bitnegren
    Ebakachihu egziabhern atasazinu!!! Yihe leantem hone legna hiwot minim aytekmenim!!!

    ReplyDelete