Monday, March 9, 2026

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ በመምህር ዘለዓለም ወንድሙ ሕልፈተ ሕይወት የሐዘን መልዕክት አስተላለፉ።

የቅዱስ  ፓትርያርኩ ሙሉ መልእክት ነው። 

“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ”
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን !!
‹‹ወነአምር ከመ ለእመሂ ተነሥተ ቤተ ማኅደርነ ዘበምድር ዘውእቱ ሥጋ ብነ ሕንጻ በኀበ እግዚአብሔር በሰማያት ዘኢገብሮ እደሰብእ፡-
በምድር ያለው ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰው እጅ ያልሠራው ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናውቃለን፡፡›› (2ቆሮ. 5፡1)

በልዩ ልዩ ጊዜያት ዐረፍተ ዘመን የገታቸውን ወገኖች ልንሸኝ እንችላለን፤ የአንዳንድ ሰዎች ሞት ግን ከልብ ቶሎ የማይወጣ፤ ለዘመናትም በህሊና መዝገብ ላይ የሚቆይ ነው፡፡

በመሆኑም የሚከተሉት ሃይማኖት ወይም መርጠው ያልተወለዱበት አካባቢ እንደበደል ተቆጥሮባቸው ከየአቅጣጫው በሚሰነዘረው ጥቃት በሚገደሉ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ ምእመናን በአጠቃላይ የሰው ልጆች ኀዘን ልባችን በትካዜ ውስጥ በሚገኝበት በዚህ ወቅት በመንፈሳዊ ሕይወቱ እና በትጋቱ ለቤተ ክርስቲያን ተስፋ የነበረው፤ ለበርካታ ዓመታትም በገጠር፣ በከተማ፣ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ እየተዘዋወረ ወንጌለ መንግሥትን ሲያስተምር የቆየው የመንፈስ ቅዱስ ልጃችን መ/ር ዘለዓለም ወንድሙ ለመንፈሳዊ አገልግሎት በተጓዘባት ሰሜን አሜሪካ ባጋጠመው ሕመም ከዚህ ዓለም ድካም በሥጋ ማረፉን ስንሰማ ታላቅ ድንጋጤ ፈጥሮብናል፡፡

Monday, March 2, 2026

‎ምንኵስና ታሟልና መድኃኒት እንፈልግለት!!

በምንኩስና ቆብ ተደብቀው የሚደፍሩ እና ሆድ አደር የሆኑ
‎አሁን ያለው ምንኵስና የአባቶቻችንም የታሪካቸውም አሰር የለውም። ምናልባት ከሆነ ልብሱ ብቻ ነው የሚሆነው። ምንኵስና መስመሩን ከሳተ
ቆይቷል ብዙዎቹ ማስተካከል ያልቻሉና ለማስተካከልም ትንሽ ድካም ያልደከሙ ሰዎች ብዙዎች ናቸው።
‎በምንኵስና ሲቀለድበት ዝሙት ሲፈጸምበት በየግሮሰሪው ሲጨፈርበት እውነቱን ከመመስከር ይልቅ ለመወደድ የሚዳዱ ሰባኪ መሰል ሰው አምላኪዎች የተልከሰከሰውን ምንኩስና ሲያሽሞነምኑ እናያለን።
‎አነዚህ ደናቁርት ገንዘብ አምላኪ ሰባኪያን " ምንኵስናን ክህነትን ለማስጠላት ነው ቄስ ዲያቆን መነኩሴ እየመሰሉ ይህን የሚያደርጉ " በማለት አለባብሰው ለማለፍ እና ምእመኑን የማደንዘዣ መረፌ እየሰጡ የከተማ መነኩሴ ጥሩ እንደ ሆነ እንዲረዳ እየነቃ የነበረውንም ማደንዘዣ ለመውጋት የሚሞክሩ እና በመነኰሳት ላይ ተስፋ እንዲኖረው የሚያደርጉ አስመሳዮች ጸሓፊዎችን ሰባኪ ነን ባዮችን እያየነ ነው።