| በምንኩስና ቆብ ተደብቀው የሚደፍሩ እና ሆድ አደር የሆኑ |
ቆይቷል ብዙዎቹ ማስተካከል ያልቻሉና ለማስተካከልም ትንሽ ድካም ያልደከሙ ሰዎች ብዙዎች ናቸው።
በምንኵስና ሲቀለድበት ዝሙት ሲፈጸምበት በየግሮሰሪው ሲጨፈርበት እውነቱን ከመመስከር ይልቅ ለመወደድ የሚዳዱ ሰባኪ መሰል ሰው አምላኪዎች የተልከሰከሰውን ምንኩስና ሲያሽሞነምኑ እናያለን።
አነዚህ ደናቁርት ገንዘብ አምላኪ ሰባኪያን " ምንኵስናን ክህነትን ለማስጠላት ነው ቄስ ዲያቆን መነኩሴ እየመሰሉ ይህን የሚያደርጉ " በማለት አለባብሰው ለማለፍ እና ምእመኑን የማደንዘዣ መረፌ እየሰጡ የከተማ መነኩሴ ጥሩ እንደ ሆነ እንዲረዳ እየነቃ የነበረውንም ማደንዘዣ ለመውጋት የሚሞክሩ እና በመነኰሳት ላይ ተስፋ እንዲኖረው የሚያደርጉ አስመሳዮች ጸሓፊዎችን ሰባኪ ነን ባዮችን እያየነ ነው።
ከአጥፊዎቹ ይልቅ ይህ አይነት አረዳድ ይከፋል መፍትሔ ባንሆን እንኳን ማደንዘዣ መሆን ግን አላስፈላጊ ነው እንላለን እየነቃ ያለውን እያንዳንዱን የመነኰሳት እንቅስቃሴ በመረዳት ላይ ያለውን ምእመን በማደንዘዝና የቀደምት የአባቶቹን የምንኩስና ተግባር ለማስረሣት መሞከር ተገቢ አይደለም።
ቤተ ክርስቲያን ላይ አሁን ያለው ምንኵስና ምንኵስና እየሆነ ነው ወይ? መነኩሴ መሳይ በቀሚስ የተደበቁ የሌላ እምነት አራማጆች ናቸው ወይ? ወይስ ሁሉም ከሌላ ቤተ እምነት የመጣ ነው ወይ? ይህ ከሆነስ ማንም ሰባኪ ነኝ ባይ ጸሓፊ ነኝ ባይ ተቆርቋሪ ነኝ ባይ መሬት ላይ እየሠራ ነው ወይ? እሽ የሌላ ቤተ እምነቶች ከሆኑስ? በመነኰሳት ልብስ ሲጨፈርበት ዝሙት ሲፈጸምበት ሲዘርፉበት ሲያጭበረብሩበት ሰውን ሲገድሉ የሰው ሚሽት ሲያባልጉ ይህን አድራጊውን አካል ለፍርድ የሚያቀርብ አለ ወይ?።
ቤተ ክርስቲያን እንግዲህ መነኩሴ ሆኖ ይህን ማድረግ ይቻላል ማለት ነው? ቤተ ክርስቲያን ትፈቅዳለች?
ጉዳዩ እንዲህ ናቸው ከመባል አልፏል። ችግሩ ያለው እንዲህ አይነቶቹን አሰዳቢዎች ሳያክሙ የቤተ ክርስቲያን አካል ማድረግ ነው። ለምንስ ዝም እንላለን? ሌሎቹ እኮ ቀድመው አይተውታል እኛ እንዲህ አይነት መነኩሴ የቤተ ክርስቲያን አባል አይደለም ብለን ከመመስከር ወደ ኋላ አንልም።
ምንኵስና ስንል ገዳማውያንን እንደማይጨምር ብዙ ጊዜ እንናገራለን አዲስ የሚሆንበት እንዳይኖር።
ይቅርታ ወንጌል መሆንን፤ መኖርን እንጂ ማስመሰልን ሲናገሩባት አትወድም ከመነኰሳት ጋር የሥራ ጉዳይ ማኅበራዊ ኑሮ የሚያገናኛችሁ ልትኖሩ ትችላላችሁ ከቤተ ክርስቲያን የሚበልጥባችሁ ግን አይኑር።
ምንኵስና ታሟልና መድኃኒት እንፈልግለት!!
በሌላ በኩል ባለፈው ወር ከማዕረገ ምንኩስና የታገደው ደፋሪው መነኩሴ ብዙ ሥራዎችን እየሰራ እንደሆነ ተሰምቷል
ክፍሌ:-
1.ሥልጣነ ክህነቱ በሀገረ ስብከቱ ቢታገድም የካቲት 19/2018ዓ.ም በጉልበት በዕለተ ቅዱስ ገብርኤል በደብረ ዓባይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አውደ ምሕረት ተገኝቶ ጸሎት አድርጓል።በመስቀልም ኑ ! ልባርካችሁ እያለ ሲባርክ ውሏል።
2.ከሀገረ ስብከቱ ጋር የገጠመውን ያልተጠበቀ ተቃውሞ ለመቀልበስ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል በቃለ ዓዋዲው መሠረት ሥልጣኑ መታገድ ያለበት በሊቀ ጳጳሱ እንጂ በሥራ አሥኪያጅ ፊርማና ቴተር መሆን የለበትም የሚል መመሪያ የተሰጠ ሲሆን እሱ ግን የሀገረ ስብከቱን እግድ በይግባኝ አስነስቸዋለሁ እያለ ማስወራቱን ቀጥሏል ።በሌላ መልኩ ከሊቀ ጳጳሱ አቡነ አብርሃም ጋር ለማሸማገል ሲባል በሊቀ ጳጳስ ደረጃ አቡነ መቃርዮስ ፤በጠቅላይ ቤተ ክህነት ደረጃ እነ አባ ገብረ ሥላሴ ባሕር ዳር ከትመዋል።
3.ከእማሆይ ሐመልማል አግማስ ቤተ ሰቦች ጋር የመጨረሻው መጨረሻ የተባለለት ሽምግልና ለማካኼድ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ተሰብስቧል።
4.ባለሀብቶችና በክፍሌ እርዳታ የተቀጠሩ 60 ያህል አገልጋዮች ተሰብስበው "ለእንጀራ ያበቁን ቆሞስ አባ ክፍለ ማርያም አለማየሁ ናቸው" የሚል ምስክርነት ለአካባቢው ባለሀብቶችና ባለሥልጣናት እንዲሰማ ተደርጓል።
5.አቡነ አብርሃም ድርድሩን ወደጎን በማለት በክፍሌ ላይ ጠንከር ያለ ውሳኔ የሚያሳልፉ ከሆነ ነገሩን ሙሉ በሙሉ ወደ ጎጥ አጀንዳ በመውሰድ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን መተማ ለማስመደብ ሳምንት አይጨርስብንም በሚል ዛቻ ተጠናቋል።
ቀጣይ ምን እንደሚፈጠር?አድረን የምንሰማው ይሆናል።
ምንጭ፡
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
No comments:
Post a Comment