ሐሰተኛ አጥማቂው እራሱን "አባ ዮሐንስ" በማለት የሚጠራው አሳሳቹ አጭበርባሪው ራስታው በካሊፎርኒያ ግዛት በሚገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ
አባል የሆኑት ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሊዎስ እገዳ ደረሰበት፤ ከዚህ በፊት በቴክሳስ ግዛት በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ ገዝቶ የራሱን ገዳም ለማቋቋም በሚያደርገው ጥረት፤ በምዕመናን እና በአካባቢው ካህንት ከባድ ተቃውሞ ገጥሞት እንደነበረ ይታወሳል፤ የአካባቢው ሃገረ ስብከት ሠራተኞች ማለትም ሊቀ ጳጳሱን እና ዋና ሥራ አስኪያጁ ብቻ ፈቃዱን ሲሰጡ ፤ ሌሎቹ የሃገረ ስብከቱ ሰራተኞች እና ከ11 በላይ የሚሆኑ የዳላስ አካባቢ አጥቢያዎች ከፍተኛ ተቃውሞ በማቅረባቸው ምክንያት ሳይወድ በግዱ አካባቢው ለቆ ፤ "ጅብ በማያውቅበት ሃገር ሄዶ ፤ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ" እንደሚባለው በካሊፎርኒያ ግዛት በመሄድ ከዚህ በፊት በጥንቆላ እና በአጥማቂ ስም ከኢትዮጵያ ምዕመናን የዘረፈውን ገንዘብ በካሽ ይዞ አሜሪካን በመሄድ በተለያዩ ስቴቶች እየሄደ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን እያወጣ ቦታ መግዛቱን ተያይዞታል።
![]() |
| ሐሰተኛው አጥማቂ "አባ ዮሐንስ" |

| ሙሉውን ደብዳቤ ከታች ማስፈንጠሪያውን ይጠቀሙ |
ላላፉት በርከት ያሉ ወራት በተለያዩ የሚዲያ እና ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሰውየው የማያልቅ ብር ከኢትዮጵያ ዘርፎ ሄዶ በእዚያም ምዕመናንን በጥምቀት ሰበብ ሊበዘብዝ ስትራቴጂክ የሆኑ ቦታዎችን እየመረጠ ቦታ መግዛቱን ተያይዞታል፤ አሁንም በቅርቡ በካሊፎርኒያ ግዛት ቦታ ገዝቶ አድሶ ለጥምቀት እና ለጥንቆላው የሚያገለግለውን ማንኛውንም እቃዎች እና ንብረቶች በማሟላት ላይ እያለ የካሊፎርኒያ ግዛት እና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎዎስ የእግድ ደብዳቤ ማውጣታቸውን ስንሰማ ትልቅ እረፍት ተሰምቶናል፤ ሰውየው በኢትዮጵያ እያለ በጎጃም እና በጎንደር የተለያዩ ገዳማት እየተዘዋወረ ብዙዎችን ትዳራቸውን ያስጣለ፣ ብዙ መተት የሰራ እና ብዙዎችን ሕይወታቸውን የበጠበጠ ሰው መሆኑ እየታወቀ አንዳንድ የዋሕ ምዕመናን ይሄንን ጥቁር ራስ ራስታ "አባታችን" እያሉ ጉዳቸውን እና የሚኖሩበትን ከተማ እና ሃገር እየወሰዱ ለተጨማሪ ብዝበዛ ሰውየውን እያዘጋጁት ነው፤ በሃገረ ስብከቱ የተወሰደው እርምጃ እጅግ ወቅታዊ እና መልካም ጅምር በመሆኑ ሊበረታታ ይገባዋል እንልላለን፤
ሙሉ ደብዳቢውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

No comments:
Post a Comment