![]() |
| የምሥራቅ ጎጃም ተሿሚው |
እንቅስቃሴዎች በቅርበት ለተከታተለው፤ <<እንቁላል በቆይታ በእግሯ ትሄዳለች>> የሚለው አካሄድ በትክክል የሚያጠናክር አካሄድ እየሄዱ እንዳለ በደንብ መረዳት ይቻላል። በተለይ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ “ጳጳሳትን ሾመናል” ብለው ወደ ፊት ከመጡ በኃላ በበቤተክርስቲያን በኩል ምንም አይነት ምላሽ አልተሰጠም፣ ምንም አይነት እርምጃም አልተወሰደም፤ ይሄ ደግሞ የሚነግረን አንድ ጠንከር ያለ አካሄድ እንዳለ በትክክል የሚያስረዱ ሁኔታዎች እንዳሉ መረዳት የሚያዳግት አይመስለንም፤ በተለይ በኦሮሚያ ቤተክህነት፣ በአቡነ ሰላማ ቤተክህነት ምረታ ማግስት የተከሰቱ በርካታ ደም አፋሳሽ እውነታዎች ለምን በምሥራቅ ጎጃም እንደዚህ አይነት እርምጃም ሆነ አካሄድ መሄድ ተሳናቸው የሚለው ትልቁ እና ዋነኛው ጥያቄ እንደሆነ ብዙዎች የሚረዱት ይመስለናል።
“ቅብዓት” የሚለው እምነት ምን አይነት መሰረት አለው? የሚለውን በጥቂቱ ብንመለክት ምናልባት አካሄዳቸው እና መጥነው የሚረግጡት ብዙ ማሳያዎችን ብንመለከት ትንሽ ነገሮችን ሊያጠራልን ይችላል ብለን ስላሰብን ጥቂት የእምነቱን መሰረት የሆኑትን ነገሮች እናንሳ፤ በቅብዓት እምነት “ወልድን በሰውነቱ ከተዋሕዶ በኃላ ፍጡር አንለውም” ይሉናል፤ በሌላ በኩል “ፍጡር ሥጋን አልተዋኃደም” ይላሉ እስቲ እነዚህን እንተንትናቸው፤ ወልድን በሰውነቱ ከተዋሕዶ በኃላ ፍጡር አንለውም - በቅድስ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ወልድ የምንነው የእግዚአብሔር አብ ድኅረ ዓለም ያለ እናት፤ በኃላም ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለ አባት የተወለደው እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በተለይ ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን፤ ነከፍሷ ነፍስን ነስቶ ፍፁም ሰው ፤ ፍፁም አምላክ ሆኖ መወለዱን የቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ይነግረናል፤ ነገር ግን እንደ “ቅብዓት” እምነት ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው እግዚአብሔር ወልድ ፍፁም ሰው የሚለውን አይቀበሉም ፤ የእመቤታችንን ንጽሕይተ ንፁሃን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከሰዎች ተለይታ እግዚአብሔር አብ ያዘጋጃት ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች መባልን አይቀብሉም፤ ለዚህም ይመስላል በታሕሣስ 28 የጌታ መወለድ የሚበሰርበት እለት ታዓምረ ማርያምን በፍፁም አያነቡም፤ ስለማይቀበሉት ማለት ነው።
ፍጡር ሥጋን አልተዋሃደም ማለታቸው እከላይ እንዳብራራነው
፤ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ ቤዛ ሊሆን ወደ ምድር መምጣቱን ያምናሉ ነገር ግን ፍፁም አምላክ ሆኖ እንጂ
ፍፁም ሰው ሆኖ መምጣቱን አይቀበሉም፤ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንደምታስተምረው፤ እግዚብሔር አምላክ ዓለምን ከፈጠረበት ድንቅ ሥራው
ይልቅ የሚረቀው እና የሚያስደንቀው እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሰው ሆኖ መፈጠሩን
ነገር ለሰው ልጅ አዕምሮ እጅግ የሚረቅ ነው፤ በመጀመሪያ ነብዩ ኢሣያስ በትንቢቱ “ድንግል ወንድ ልጅን ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል
ትለዋለች” ትንቢተ ኢሣያስ 7፡14 የተናገረው መፈጸሙን በቅብዓት እምነት ከእውነት የራቀ እንደሆነ ይነገራል፤ አምላክ ከእመቤታችን
መወለዱን መጻሕፍትም ፤ መጽሐፍ ቅዱስም በመጠቀሱ እርሱን ቢቀበሉም፤ የእግዚአብሔር ወልድ በተዋሕዶ ሁለቱንም ባሕሪያት ይዞ መፈጠሩን
አይቀበሉትም ማለት ነው፤ “ፍጹም አምላክ” ብቻ ነው በለው የሚቀበሉት ይሄ ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሰረታዊ
እምነት የካደ ይሆናል ማለት ነው።
አስተምህሮው በዚህ መልኩ ከሆነ ለምን ቤተክርስቲያን
ዝምታን መረጠች፤ ዛሬ ላይ እስከ ፓትርያርክ ሹመት ድረስ ተደርሶ ምንም አይነት ነገር ተብሎም አያውቅም፤ ይልቁንም ሽምግልና እና
ተመሣሳይ ነገሮች እንጂ በኦሮሚያ ቤተክህነት እንደሆነው፤ ወይንም በትግራይ በአቡነ ሰላማ ቤተክህነት እንደሆነው አይነት ግርግር
አልተፈጠረም፤ የተለያዩ መላ ምቶችን ማንሳት ይቻላል፤ ከነዚህም ውስጥ ዛሬ ላይ ግዛታቸውን እያጠናከሩ ከምሥራቅ ጎጃም ብቻ ከ16
ያላነሱ አጥቢያዎች ላይ የቅብዓትን መሠረት ያላቸው ሰዎችን ሹመው በራሳቸው መስተዳደር ላይ ይገኛሉ፤ በመቀጠል ወደ ሰሜን አሜሪካ
ተሻግረው የራሳቸውን የእመነት መሠረት ለመትከል ትልቅ መሠረት እየጣሉ እንደሆነ ይነገራል፤ የቅብዓትን የእምነት መሠረት ወደ ምእራብ
አገሮች መውሰድ ብዙ ጥቅሞች አሉት፤ ከሁሉም በላይ የማይቋረጥ የፋይናንስ ምንጭ እጅግ በጣም አስፈላጊ እና ወደፊት ለሚያቅዷቸው
ሥራዎች መሠረት እንደመሆኑ መጠን፤ ወደ ምእራቡ ክፍልዓለም መሄድ በጣም ወሣኝ እና ከሁሉም በላይ ከፍተኛ ፕራዮሪቲ ተሰጥቶት የሚሠራ
እንደሆነ መገመት አያዳግትም፤ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ መሠረቱን እስከምንናገኝ እረፍት ሊኖረን እንደማይችል እናውቃለን፤ ለጊዜው
ግን እንዴት እና የት የሚለውን መረጃዎችን አጠናክረን እንመለሳለን፤ ለዛሬ ግን የተለያዩ መሠረታዊ እውነታዎችን እንነጋገራለን፤
የቅብዓት እምነት በምሥራቅ ጎጃም ማለትም ምስካበ ቅዱሳን ቆጋ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ፣ በደብረ ወርቅ፣ በግንደ ወርቅ እና ጎንጃ አካባቢ በከፍተኛ ሁኔታ የእመነቱ መሰረት የሆኑት
አባቶች እና በርከት ያሉ ሊቃውንት ያሉበት ቦታ ነው፤ በቅዱስ ሲኖዶስም ይሄንን እምነት የሚደግፉ እና የሚያራምዱ ጥቂት የማይባሉ
የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እንዳሉ ይታወቃል፤ እነዚህን አባቶች ይዘን እነርሱ ለተለያየ አግልግሎት በማለት በተለያዩ ዓለማት ወይም
ሃገረ ስብከት የሚመድቧቸው እና የሚሾሟቸው መነኮሳት ያንን እምነት እና አስተምህሮ በመያዝ እምነታቸው በጉያቸው ይዘው መሰረት ለመጣል
እና ምዕመናንንም የክህደት አስተምህሯቸውን ለማሰራጨት የተለያዩ መንገዶችን እና አካሄዶችን እንዳሉ የተለያዩ መላምቶችም፤ እውነታዎችም
እንዳሉ ልብ ይሏል፤ ከነዚህ መሠረት ሊጣልባቸው ከሚታቀዱት ጥቂቶቹ ሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ ጥቂቶቹ እንደሆኑ ለማወቅ ነብይ መሆን
አይጠይቅም፤ ከላይ እንደጠቀስንው ዋነኛውም ለዚህ ምክንያት የሚሆነው የማይቋረጥ የፋይናንሥ ምንጭ ማግኘት ዋነኛው እና በጣም አንገብጋቢው
እንደሆነ ይታወቃል።
ብፁዕ አቡነ ዘካሪያስ በጥር አካባቢ ለቅዱስ ፓትሪያሪኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የልመና ደብዳቤ ጽፈው ነበር፤ ደብዳቤውም እንሚነበበው በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት እየተስፋፋ የመጣው የክህደት አስተምህሮ (ቅብዓት) እጅግ አሳሳቢ ደረጃ እንደደረሰ እና ቅዱስ ፓትርያሪኩም ታሪካዊ ሃላፊነት እንዳለባቸው ይሄንን ቤተ ክርስቲያንን የማፍረስ አካሄድ በእጅጉ እንዲቃወሙ እና እንዲያስቆሙ የሚጠይቅ ደብዳቤ ነበር፤ ከወራት በኃላ የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ነው በሚል ያለ የግርጌ እና እራስጌ የሚያሳይ ደብዳቤ ባይኖረውም በሌጣ ደብዳቤ ጽፎ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ያለ ሃገረ ስብከታቸው ገብተው በምን አግባብ ነው የሚፈተፍቱት፤ በራሳቸው ሃገረ ስብከት ስንት ብዙ አይነት ወንጀል እየተሰራ እንዲሁም እራሳቸው ብፁዕነታቸው ብዙ ገንዘብ እንደወሰዱ እና ግማሹን እንደከፈሉ፤ በተጨማሪ መክፈል ያለባቸው ብዙ ብር ከምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት እንደወሰዱ እና ያንን ማስመለስ እንደሚፈልጉ የሚያትት ደብዳቤ አወጡ፤ ይሄንን ስንመለከተው ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ (ቅብዓት) የሚባል አደገኛ አስተምህሮ በምሥራቅ ጎጃም እየተስፋፋ እንደሆነ እና ያንን ለማስቆም ደግሞ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ታሪካዊ ሃላፊነት እንዳለባቸው ይጠይቃል፤ የምሥራቅ ጎጃም በጻፈው ደብዳቤ ብፁዕነታቸው የወሰዱት ገንዘብ አለ እና ያንን እንዲመልሱ የሚል ፍጹም እርስ በራሱ የማይገናኝ ሁለት ነገር የሆነ እንደሆነ መገዘብ ያስችላል፤ <ፍየል ወዲያ፤ ቅዝምዝም ወዲህ>> የሚሉት አይነት መሆኑ ነው፤ ለነገሩ ነገሩን ለማድበስበስ እና እየተካሄደ ያለውን ዘመጃ ለማደናቀፍ የመጣባቸውን ከባድ የሆነ ቁጣ ለማስቆም ያደረጉት እንደሆነ ማየት ይቻላል፤ በተነሳው ችግር ላይ ምንም አይነት አስተያየት ሳይሰጡ ተነስተው ገንዘብ መልሱ ማለት ፈጽሞ ከጉዳዩ ጋር ባይገናኝም ፤ ያንን በሃገረ ስብከትም በጠቅላይ ቤ/ክህነትም ወይም በሕግም መጠየቅ እየቻሉ ለተነሳው ጥያቄ ገንዘብ ስላለባቸው ይመልሱልን ብሎ መልስ መጻፉ እራሱ የችግሩን ክፋት የሚያሳይ ይመስለናል።
በሚቀጥለው ጽሁፋችን የምሥራቅ ጎጃም ያሉትን በተለይ በሰሜን አሜሪካ ተሰራጭተው የሚገኙትን የምሥራቅ ጎጃም (ቅብዓት) ቫይረስ ተሸካሚዎች በመረጃ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኞች በሙሉ ለማሳወቅ እንወዳለን፤ መረጃዎች እየመጡልን ነው፤ ነገር ግን በግብታዊነት እጃችን ላይ ያሉንን መረጃዎች ከማጋራት በጥንቃቄ ተመልክተን መረጃዎችን አረጋግጠን ሙሉውን ለማጋራት በዝግጅት ላይ እንዳለን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን፤ ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥር ባሉ አህጉረ ስብከቶች በሙሉ መሠል ከሥር የሚነሱ የባእድ እምነቶችን በመከታተል መምህራን በትምህርት፤ ካህናት አባቶች ቀናዊት የሆነችውን የኦርቶዶክሳዊት እምነት ከሐዋርያት እንደተረክባናት በተመሳሳይ መልኩ ለቀጣዩ ትውልድ ማስረከብ እንዲቻል እቅበተ እምነት፤ ስብከተ ወንጌል ተስፋፍቶ እንዲቀጥል ብዙዎች ይስማሙበታል። ቤተክርስቲያን በተለያዩ ቦታዎች በመንግሥት፣ በአጽራረ ቤተክርስቲያን፣ አክራሪ እስልምና እንዲሁም የተለያዩ ችግሮች እያሉብን በተጨማሪ እንደ ቅብዓት እና ጸጋ ያሉ የተተከሉ እሾህ መሰል ጋሬጣዎች ቤተክርስቲያንን ከውስጥ ሆነው እያደሙ ነው እና በተለያዩ ደረጃዎች ያሉ ከሊቀ ጳጳስ ጀምሮ እስከ ምዕመናን ባሉ የቤተክርቲያኒቱ ደረጃዎች እነዚህን መከላከል እና በጥብዓት ትምህርቶችን እና ግንዛቤዎችን እንደሚያስፈልግ ሳይተለም የተፈታ እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል፤ ቅድስት፣ ንጽሕይት እና ርትዕይት የሆነችውን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን እግዚአብሔር አምላክ ይጠብልን አሜን።

No comments:
Post a Comment