የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በገጠር በከተማ የሚገኙ ካህናት መናኞች፣ ሞት ዛሬም ቀጥሏል። በተለይ ባለፈው
በኢሃዴግ ዘምን ብዙ ፈተናዎች እና ብዙ ቤተክርስቲያንን የመግፋት እና ምዕመናንን የምግደል የማሳደድ ታሪክ እንደ ብልጽግና ዘመን ሆኖም ተሰምቶም አይታወቅም፤ በተለይ ባላፉት 7 ዓመታት የተገደሉት እና በግፍ ሕይወታቸውን የተነጠቁ ክርስቲያኖች፣ የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናት፣ እንዲሁም ሕይወታቸውን የሰዉት ካህናት በኢትዮጵያ ላለፉት 3 ወይም 4 የአገዛዝ ዘመናት ማለትም ፤ በአፄ ኃይለሥላሴ፣ በመንግሥቱ ሃይለማርያም፣ በመለሰ ዜናዊ እና ኃይለማርያም በድምሩ የተገደሉ፣ የተሰዉ፣ የተቃጠሉት ቤተክርስቲያናት በድምሩ የሦስቱም ዘመናት ፤ ዛሬ በአብይ አሕመድ ጊዜ የሞቱት፣ የተቃጠሉት ቤተክርስቲያናት አንድ የተሰዉ ካህናት ቁጥር ሁለት እጥፍ በአሁኑ ማለትም ባለፉት 7 ዓመታት የሆነው በእጅጉ ብዙ ቁጥር ነው እጅግ ዘግናኝም ነው፤

ጠቅላዩም ከዚህ በፊት ቤተክርስቲያናት ሲቃጠሉ "አኔ አብይ መቼም አቃጠልክ አትሉኝም" በሚል የእብሪት ንግግሩ ይታወቃል፤ በእጅጉ በጣም የወረድንበት እና ሰው ሞሆናችን ሁሉ አጠራጣሪ እስኪሆን ድረስ የሰው ልጅ ድም እንደ ጎርፍ የሚፈስባት፣ አብያተ ክርስቲያናት በብዙ ቁጥር የሚቃጠሉበት ከባድ ዘመን እንደሆነ በብዙዎች ይነገራል፤
እንደምናስታውሰው ባለፈው ዓመት በዝቋላ አቦ ገዳም እጅግ ዘግናኝ በሆነ መልኩ መነኮሳት እራሳቸውን ለእግዚአብሔር የሰጡ፤ ዓለም በቃን ብለው በገዳም የሚኖሩ አባቶች እጅግ ሰቅጣጭ በሆነ መልኩ አንገታቸው ተቀልቶ ሕይወታቸው አልፏል፣ በአብይ አህመድ የሚመራው መንግሥታችን ገዳማትን በመድፍ እና በከባድ ወታደራዊ መሣሪያዎችን በመጠቀም ድብደባ ፈጽመዋል፤ ደብረ ኤልያስ ገዳም አንደኛውም ማሳያ ሲሆን በዚያም ከ570 በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ክቡር ሕይወታቸውን ሰጥተዋል፤ በሃገራችን ኢትዮጵያ ከትግራይ አክሱም ጀምሮ እስከ ሲዳሞ እና አርባ ምንጭ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናት እጅግ በከፋ ሁኔታ ግድያ እየተፈጸመ ይገኛል፤ ቤተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ ይገኛሉ፤ ዋነኛው ምክንያት ደግሞ "ብልጽና/ ብልግና ፓርቲ" ፕሮቴስታንታዊ መንግሥት በመሆኑ በተቻለው መጠን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት የማይሸረብ ሴራ መንግሥታዊ እና ግለሰባዊ ሴራዎች ብዙ ናቸው ፤ ጊዜም ያልፋል ዘመንም ይተካል በሌላ ነገር ግን ማንም ሰው ከተጠያቂነት እና ለፍርድ እንደሚቀርብ ሊያውቅ ይገባዋል፤ ማንም ሰው ከፍርድ አያመልጥም፤
ይህ በእንዲህ እንዳለ እጅግ ልብ የሚሰብር የሆነ አሰቃቂ ግድያ በደብረ ወገግ ተፈጽሟል፤ ግድያው የተፈጸመው ጥር 28 ቀን 2018 ዓም በደብረ ወገግ አባ ሣሙኤል አሰቦት ገዳም፤ ገዳማዊው በዓታቸው ውስጥ ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገለው ተገኝተዋል ባሕታዊ አባ መብራቱ፤ ፤ በዓታቸውን ለብቻቸው ዘግተው የሚኖሩ ባሕታዊ ነበሩ፤ በመሣርያ ተገድለው ነው የተገኙት የመረጃ ምንጮች ከቦታው አድርሰውናል፤ ይህን ድርጊት ማን ፈጸመው? ግድያው በር ዘግተው ለቤተ ክርስቲያን እና ለሀገረ በሚጸልይ መናንያን ላይ መሆኑ ልብ ይሰብራል፤
መንግሥት የሕግ የበላይነት የሌለበት ሃገር ስላደረጋት ይልቁንም በኦቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ላይ እየተፈጸመ ያሉትን ግድያ፣ ማሳደድ፣ ቤተ ክርስቲያን መቃጠል የመሣሰሉት በሙሉ መንግሥት መር ግድያዎች ናቸው አለያም የክልል እና የዞን ባለ ሥልጣናት የማያውቁት ግድያ የለም ፤ ለዚህም ምሣሌ ይሆንን ዘንድ በምሥራቅ አርሲ የሚፈጸሙትን ግድያዎች በሙሉ በዞኑ እና በቀበሌው ባለሥልጣናት የተቀነባበረ እና በሴራ የሚገደሉትን ሊስት በመስጠት እና ቦታቸውን እና የግድያውን ሁኔታ ሁሉ አቀነባብረው ነው ግድያው የዘር ማጥፋቱ እየተፈጸመ የሚገኘው አሁንም በደብረ ወገግ በአካባቢው የሚገኙ ጽንፈኛ የሙስሊም ቡድኖች በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ እንዳሉ ይታወቃል፤ ከዚህ በፊትም ገዳማዉያኑን በተለያየ ምክንያት የሚገፉ፣ በገዳሙ የተጠለሉ ሕጻናት የአብነት ተማሪዎችን በመግደል እና የመሣሰሉት ወንጀሎችን ሲፈጽሙ መንግሥትም ሆነ የክልል የጸጥታ ቢሮ ምንም አይነት ከለላም ሆነ ጥበቃ ለማድረግ ፈቃደኞች አልሆኑም።
የሰማዕቱ የአባታችን በረከት በሁላችንም ላይ ይደርብን አሜን።

No comments:
Post a Comment