ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ከሺዎች በላይ ከሚቆጠሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ አንደኛው እና
ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አለኝታ በመሆነ እንደ አማኛም ወይንም እንደ ትክክለኛ ሕዝባዊ የፖለቲካ አደረጃጀት መንግሥት እያደረገ ያለውን እኩይ ተግባር በማውገዝ ይልቁንም በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደርሱትን ብዙ መጠነ ሰፊ አደጋዎች እንግልቶች አንድ አንድን ሃይማኖት ለማጥፋት፣ ለማሳነስ ወይንም character assassination እየተከታተለ ለአባላቱ ይልቁንም ለመላው ኢትዮጵያውያን በመግለጫ ከሚያሳውቁ እና ሕሊና ያላቸው የፖለቲካ መሪዎች ያሉበት ፓርቲ ነው ቢባል ስህተት ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም በአንድ ሃገር ላይ አንድ ሕዝባዊ ፓርቲ ማለት፤ ለተነሳበት የፖለቲካ ሥልጣን መያዝ ብቻ ሳይሆን በማሕበረሰቡ ውስጥ ያሉትን ችግሮች፣ የመንግሥትን አግባብ ያልሆኑ አካሄዶች፣ የፓርቲዎችን በሌላው ያላቸውን ጣልቃ ገብነት፣ እንዲሁም የሰውን ማሕበራዊ ኑሮ፣ የምጣኔ ሃብት፣ እና አንዱ ከሌላው ጋር ያለውን መስተጋብር ትክክለኛውን እንዲይዝ ማሳወቅ የሚመለክታቸውን የመንግሥት አካላት ማሳሰብ፣ ብሎም ለዚህ

የገዳማውያን ሞት የመንግሥት አልባነት ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ምልክት ነው!
(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰተ መግለጫ)
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን፣ አሰቦት ቅድስት ሥላሴ ገዳም አባት የኾኑት ባሕታዊ አባ ወልደሚካኤል ዘግተው በሚጸልዩበት በበዓታቸው ሳሉ በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም የጥይት ድምጽ ሰምተናል፣ ምን አልባት ያን ቀን ሳይገደሉ እንዳልቀሩ የሚናገሩት ምንጮች ጥርጣሬው እያየለ ሲመጣ በአባቶች ፍለጋ አስከሬናቸው ጥር 30 ተገኝቷል ብለዋል። በአራዊት የመበላትም ምልክት አለበት። ከዚኽ ቀደም በገዳማውያኑ ላይ ከደረሱ ጥቃቶችና ዛቻዎች አንጻር የድርጊቱ ፈጻሚ ለእርግጠኝንት በቀረበ በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው ራሱን ኦነሰ ብሎ የሚጠራው ኦነግ ሸኔ ነው።
ታጣቂው ኃይል በቅርብ ርቀት ይንቀሳቀሳል። ያንን ደግሞ መንግሥትም ያውቃል የሚሉት ምንጮች ዘላቂ መፍትሔ ካልተበጀ እንዲኹ እያዘናጉ አንድ በአንድ ይጨርሷቸዋል ይላሉ።
ፓርቲያችን በዓት ዘግተው፣ በዋሻና በገደል የሚጸልዩና ምድራዊ ፖለቲካና ሽኩቻ ፍጹም የማይገባቸው ባሕታውያንና ገዳማውያን ዒላማ ተደርገው መገደል የመንግሥት አልባነት ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ጉልህ ምልክት እንደኾነ ይረዳል።
ፓርቲያችን ድርጊቱን በጽኑ ያወግዛል፤ ለገዳማውያኑም መጽናናትን እየተመኘ ክስተቱ በዓለምአቀፍ መርማሪዎች ተጣርቶ እጃቸው ያለበት ተጠያቂ እንዲኾኑ የሚመለከታቸው አካላት እንዲሠሩ አበክሮ ይጠይቃል።
ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!
እናት ፓርቲ
የካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

No comments:
Post a Comment