Monday, October 19, 2026

ታከለ ኦማ ስጦታቸውን ተቀብለዋል

ኢ/ን ታከለ ዑማ እንደሚታወቀው የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው ከተሾሙ ጀምሮ በመቀጠል ደግሞ የኢትዮጵያ ማዕድን ሚኒስቴር ሆነው ለጥቂት ዓመታት ሰርተው ጥሪት ቋጥረው ወደ ሰሜን አሜሪካ ተጉዘው በዚያ ኢንቨስት እንዳደረጉት ብዙዎች የሚያውቁት እውነታ ነው፤ አሁንም ወደ ሃገራቸው ተመልሰው ለጠቅላዩ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ትንሽ ለኢንቨስትመንት የሚሆን አንድ 5 ቢሊዮን ስለጎደለኝ አንድ ሥራ ስጠኝ ብለው በጠየቁት መሠረት ኢትዮ ቴሌኮም እንደ ስጦታ ተሰጣቸው። 

 

ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ ተባለ

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ከንቲባና የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ሀዲድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ያገለገሉት ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣ ወ/ሮ ፍሬህይወት ታምሩን በመተካት ተሹመዋል።

ወ/ሮ ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው የኢፌዴሪ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸዉ አይዘነጋም።

ከዚህ በኋላ የ5 ብር ካርድ መበደር ሊቀር ነው  ተብሎ ተነግሯል አሉ።

 

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment