![]() |
| የቀብሮው መነኩስ "አባ ፍቅረ" |
አስተዳዳሪ የሆኑት <<አባ ፍቅረ ማርያም አጣነው>> በደብሩ ላይ ብዙዎችን የቤተክርስቲያኒቱን አባላት በማገድ እና በማባረር ክፋታቸውን እና ጭካኔያቸውን ለብዙዎች እያስመሰከሩ እና እየተናገሩ ሥራቸወን ቀጥለዋል፡፡ ባለፈው ጥቂት ወራት ተደጋጋሚ መረጃዎችን ማድረሳችን ይታወሳል፤ ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹን ለመዘርዘር ያክል፤
እነዚህ መልእክቶች ሁሉ የሚያሳዩት ከዚህ በፊት በተመሳሳይ መልኩ የተለያዩ መረጃዎችን ማሰራጨታችን ይታወቃል፤ አሁንም ሰውየው የጭቃ ጅራፋቸውን ማንሳት ቀጥለውበት ምዕመናንን ከእግዚአብሔር ጉባኤ የመለየት እና የማሳደድ ሥራቸውን ቀጥለዋል፤ ባለፈው እንደገለጽነው የተወሰኑ ካህናትን ማገዳቸውን ቀጥለውም ምዕመናንን በፖሊስ አስጠርተው እንዲባረሩ ማድረጋቸው እና በተመሳሳይ መልኩ ከጥቂት ቀናት በፊት በድረሰን መረጃ መሰረት <<ሰውየው በጣም ጤንነታቸውን እንጠራጠራለን>> ነበር ያሉን መረጃውን ያደረሱን የደብሩ አባላት የማስፈራሪያ እና በንብረቴ እና በቦታዬ እንዳትደርሱ የሚል ማስፈራሪያ በሰውየው ተፈርሞ መድረሱን ነገረውናል፤
እንደ መረጃ አቀባይችን ከሆነ ሰውየው ፈርመው በቦታዬ አትድረሱ ማስፈራሪያውን ያደረሷቸው ሰዎች እንደነገሩን ከሆነ ፤ የግል ንብረት ሲሆን መከልከያ የሚሆን ማገጃን ተጠቅመው እንደሆነ ነው የድረሰን መረጃ የሚያሳየው፤ ደብዳቤውም በመነኩሴው መፈረሙን ተመልክተናል፤ ብዙዎች እንደሚናገሩት አንድ መነኩስ እንዴት በዚህ ደረጃ ቤተክርስቲያንን ሲከፋፍል እና ሲያምስ ይኖራል ብለው ይጠዩቃሉ፤ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እንደሆኑ ልክ በሐዋሳ ሲያደርጉ እንደነበረው ተመሳሳይ ውንብድናቸውን እየሰሩ እንዳሉ ለመረዳት ችለናል፤ ከምንጮቻችን እንደተረዳነው፤ ሰውየው ከባድ የሆነ ወጪዎችን በማውጣት ሊቀ ጳጳሱን እና የሀገረ ስብከቱን የሥራ ሃላፊዎች በሙሉ በብራቸው እንደተቆጣጠሯቸው ነው የደረሰን መረጃ የሚያመለክተው፤
የብዙዎች ምዕመናን አስተያየት እንደሚነግረን ከሆነ፤ ሊቀ ጳጳሱ ተመሳሳይ ደብዳቤ ለሌሎች አጥቢያዎች ሰጥተዋል (ሸጠዋል) የሚል ግምት አለ፤ ስለዚህ በተለያዩ አጥቢያ ያሉ በተለይ በዚህ ሃገረ ስብከት ያሉ ምዕመናን በሙሉ የቤተክርስቲያናቸውን የባለቤትነት ማረጋገጫ በአጭበርባሪ መነኮሳት እና ካህናት እጅ እንዳይወድቅ ከባድ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ጥሩ የሆነ ማገናዘቢያ መረጃ በመሆኑ በሁሉም አጥቢያዎች መረጃዎችን እንዲደርሱ ሁላችንም የበኩላችንን እንድናደርግ ከዝግጅት ክፍላችን እንጠይቃለን።
በሌላ በኩል በዚሁ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ላይ የሚሰሩት ቀሲስ ብርሃኑ ጎበና የሊቀ ጳጳሱ ቀኝ እጅ እንደሆኑ እና ቤተክርስቲያናችንውን ሲገዙ በተለይ በ16 እና 17 ሚሊዮን ብር የተገዛ የገበያ አዳራሽ ለቤተክርስቲያን ለማድረግ መገዛቱን መረጃ አቀባያችን ገልጸውልናል፤ አስተዳዳሪው በወቅቱ ያለ አንዳች እማኝ ወይም ተጨማሪ የቤተክርስቲያኒቱ ሰበካ ጉባኤ አባላት እንኳን ሳይፈርሙ ብቻቸውን መፈረማቸውን ሰምተናል፤ ይህ ማለት ደግሞ የቤተክርስቲያኒቱን ምዕመን ከባድ የሆነ ችግር ውስጥ የሚጥል አካሄድ መሆኑን ከወዲሁ ለመተንበይ ነብይ መሆን አይጠይቅም፤ በሃገራችን የፍትሐብሄር ሕግ የባል ንብረት የሚስት ንብረት እንደሆነ ይደነግጋል፤ በተመሳሳይ ህግ በአሜሪካም ተመሳሳይ ከሆነ እንደሚሆን ይጠብቀል፤ የንብረቱ ባለቤት ቀሲስ ብርሃኑ እና ባለቤታቸው መሆናቸውን ይነግረናል፤ ይህ ማለት የቤተክርስቲያኒቱ ምዕመናን ገንዘባቸውን ሲከፍሉ እና እዳ ሲገፈግፉ የሚኖሩት ምስኪን ምዕመናን በሙሉ ፤ የሆነ ነገር ቢፈጠር ከሰዎች ንብርት በመሆኑ በሕግ እና በፖሊስ ሃይል ምዕመናን አሁን በተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን እየሆነ እንዳለው እንደሚሆን ግልጽ እና ግልጽ ነው፤ በተለይ ሊቀ ጳጳሱ ተመሳሳይ ደብዳቤ ለተለያዩ አስተዳዳሪዎች እየሰጡ እንደሆነ በግልጽ የሚያሳየው መረጃ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ማንኛውም በሰሜን አሜሪካ የሚገኝ አጥቢያ ከእነዚህ ስግብግብ እና ቅንቅናም መነኮሳት እና ካህናት ልትጠበቁ እና ጥንቃቄ እንድታደርጉ የዝግጅት ክፍላችን ማሳሰቢያውን በማስተላለፍ ሃላፊነታችን ለመወጣት ጥረታችንን እንቀጥላለን።
በአካባቢው ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ እየሆነ እንዳለ በቀላሉ ለመረዳት ችለናል፤ ሊቀ ጳጳሱ እንደ ሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ችግሮችን ከመቆጣጠር እና ነገሮችን ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዳይሄድ እንደ አባት ጥረት ከማድረግ እና ሃላፊነታቸውን ከምወጣት ፤ የችግሮቹ ዋነኛው ጠንሳሽ እና አቀጣጣይ መሆናቸውንም ለመረዳት ችለናል፤ በዚህ አጥቢያ ላይ ችግሮች ሲፈጠሩ ችግሩን ብዙ ቦታ ሳይደርስ ከመቆጣጠር እና ሃላፊነትን እንደ መወጣት፤ ይባስ ብለው ለአጥቢያ አለቃ የበለጠ ከባድ እና ይልቁንም የወንጀለኛ አሰራር በሚመስል መልኩ በድብቅ ባለቤት እንደሆኑ የሚያሳይ ደብዳቤ መስጠታቸው ሰውየው ምን ያክል የችግሩ ጠንሳሽ እና አቀጣጣይ እንደሆኑ በቀላሉ መረዳት ይቻላል። በተለይ ችግሮች በአጥቢያው እንዳሉ እየተረዱ፣ የአጥቢያው ምዕመናን ተደጋጋሚ ደብዳቤ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም እና ቢወተውቱም ይባስ ብለው ተጨማሪ አቀጣጣይ ደብዳቤ በሌላቸው ሥልጣን እና ሃላፊነት በጎደለው መልኩ እንደዚህ አይነት እጅግ በጣም አደገኛ የክፋት እና የሰይጣን ሥራን በድብቅ በማድረጋቸው ዛሬ ላይ ይሄ አጥቢያ በችግር ላይ ሌላ ችግር ውስጥ በግባቱን ሰምተናል፤ ለዚህም ማሳያ በቅርቡ በዘመዴ ቲቪ ላይ የቀረበውን ማዳመጥ እና መስማት የችግሩን ክብደት እና ጥልቀት ይበልጥ የሚያሳይ ነው፤ የሆነ ሆኖ እኛም ነገሮችን እየተከታተልን ለማቀረብ ቃል እየገባን፤ ለዛሬ እዚሁ ላይ እናጠቃልላለን፤
በሚቀጥለው የምሥራቀ ጸሐይ ችግሮች እና የመነኩሴው አደገኛ አካሄድ በብዙ ጥልቅ ትንታኔ እንመለሳለን፤ እስከዚያ መልካም እንመኛለን።
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:
Post a Comment