![]() |
| ኦቦ በላይ መኮንን (ዋቄ ፈና) |
ኦቦ በላይ ከእሥር መፈታታቸው እየተነገረ ነው፤
የቀሲስ በላይ ቀጣይ ሁኔታ ምን ሊሆን ይችላል?
ቀሲስ በላይ እደምናስታውሰው የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ እና ሃላፊ ሆነው ይሰሩ እንደነበር የሚታወስ ነው፤ ይሄንንም ተከትሎ በተለያየ ጊዜ ከሚሰጡ መግለጫዎች ጋር እና አቡነ ሣዊሮስ እና እነ አቡነ ኤዎስጣቲዎስ እነ አቡነ ዜና ማርቆስ በተደጋጋሚ አብረዋቸው ይታዩ እንደነበር ይታወሣል፤ በመሆኑም በቀጣይነት ለቀሲስ በላይ ከእሥር በፊት የነበራቸውን የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊነትን ይሰጧቸው ይሆን?
አቡነ ሣዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በመሆን እየሰሩ እንዳለ ይታወቃል፤ ነገር ግን ቀሲስ በላይ በእሥር በነበሩበት ወቅት አንድም ቀን በእሥር ቤት ተገኝተው ባለማጽናናታቸው እና ባለመጠየቃቸው በቀሲስ በላይ እና በአቡነ ሣዊሮስ መካከል ልዩነቶች እንዳሉም ይታወቃል፤ ነገር ግን ልዩነትም ቢኖር እና እርስ በእርስ መናናቅ ቢኖርም ለእርቅ ይሆን ዘንድ የቀደመ ቦታቸው ይሰጧቸዋል የሚሉ አንዳንድ የውስጥ አዋቂዎችም እየተናገሩ ነው፤ እውን ኦቦ በላይ መኮንን ይቀደመ ቦታቸውን የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አኪያጅነታቸውን ይይዙ ይሆን? ብዙዎች በጉጉት የሚጠብቁጥ እውነታ ነው፤
በሌላ በኩል ኦቦ በላይን የዋቄፈናው ክፍልም በጉጉት እየጠበቀ እንደሆነም እየተነገረ ነው፤ ሰውየው በፖለቲካውም ሰዎችን በማወቅም በርከት ላሉ አመታት ልምድ ስላላቸው ኦቦ በላይን የዋቄ ፈናው አመራር ሥልጣንም ገንዘብም ደጎስ አድርጎ ለእነሱ እንዲሰሩ በማግባባት ላይ እንዳሉ እየተወራም እንዳለ ልብ ይሏል፤ ለሁሉም በቀጣይ ቀናት የትኛውን መንገድ እንደሚከተሉ ተከታትለን እንደምናቀርብ ቃል እንገባለን።
ይቆየን፤
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:
Post a Comment