Wednesday, September 30, 2026

ሽምግልና ወይስ ድርድር?


 በቅድሚያ ሰላምታችን ይድረሳችሁ ውድ አንባቢያን፤ ይሄንን ደብዳቤ እና ይሄንን ጽሁፍ ከሰሜን አሜሪካ ከአንድ አንባቢያችን ተልኮልን በተለያየ ጊዜ የዋሺንግተን ሃገረ ስበክት አባ ፋኑኤል ላይ የተለያዩ ጽሁፎችን ማቅረባችን ይታወሳል፤ ሰውየው ከዚህ በፊት ባልተሰጣቸው ሥልጣን በአንድ አጥቢያ ላይ ላለ አንድ መነኮስ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብዳቤ መስጠታቸው ይታወሳል፤ አሁን ደግሞ በሌላ የሽምግልና ደብዳቤ ማውጣታቸውን ስንሰማ በጣም ግርምት ፈጥሮብናል፤ <<በአንድ ራስ፤ ሁለት ምላስ>> የሚሉት አይነት መሆኑ ነው፤ ጽሁፉን ሳንቀንስ ሳንጨምር እንደተላከልን አቅርበነዋል፤ ሃሳብ አስተያየታችሁን እንጠብቃለን እስከዚያው መልካም ጊዜ።

 

ሀገረ ስብከቱ ማሸማገል ነው ወይስ ማደራደር ነው የፈለገው? ሽምግልና የእርቅና የሰላም መሣሪያ እንጂ የግል ፍላጎት ማስፈጸሚያ አይደለም። ሽምግልና በኢትዮጵያ ታሪክ በሃይማኖትም በባህልም እጅግ የላቀ ስፍራ ያለው የተከበረ የማህበረሰብ ታላቅ እሴት እንጅ ለሽፍጥ የሚጠቀሙበት የጊዜ መግዣ ወይም ማደንዘዣ ስልት አይደለም ። የሽምግልናው ጉዳይ ከዚህ በፊት ተሞክሮ እንዳልተሳካ እየታወቀ አሁንም እዚያው አዙሪት ውስጥ ተመልሰን እንድንገባ ለምን ተፈለገ?

!!! የአሜሪካው መነኩሴ አባ ፍቅረማርያም አጣናው ጤንነቱ አጠራጣሪ እንደሆነ እየተነገረ ነው !!!

የቀብሮው መነኩስ "አባ ፍቅረ"
በቅድሚያ እንኳን ለጌታችን እና ለመድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ መስቀሉ በሰላም አደረሰዎ በማለት ለዛሬ ያሰናዳንውን ትታደሙልን ዘንድ በአክብሮት እንጋብዛለን።
 
አሁን በደረሰን መረጃ መሠረት ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ከአሜሪካ ከሚገኘው የምሥራቀ ጸሐይ ተክለሃማኖት ቤተክርስቲያን
አስተዳዳሪ  የሆኑት <<አባ ፍቅረ ማርያም አጣነው>> በደብሩ ላይ ብዙዎችን የቤተክርስቲያኒቱን አባላት በማገድ እና በማባረር ክፋታቸውን እና ጭካኔያቸውን ለብዙዎች እያስመሰከሩ እና እየተናገሩ ሥራቸወን ቀጥለዋል፡፡ ባለፈው ጥቂት ወራት ተደጋጋሚ መረጃዎችን ማድረሳችን ይታወሳል፤ ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹን ለመዘርዘር ያክል፤ 

1) የቀበሮ መነኩሴው አባ ፍቅረማርያም  

2) የሊቀ ጳጳሱ አቤቱታ እና የምዕመኑ መልስ  

Monday, September 14, 2026

የአሕመድ ግራኝ ጦርነትና ተጽዕኖዎቹ

በ 16ኛው ክፍለ ዘመን የተነሣው የአሕመድ ኢብን ኢብራሂም አል-ጋዚ (አሕመድ ግራኝ) ጦርነት በኢትዮጵያ ክርስትና ላይ ወደር የሌለውና ታሪክ የማይረሳው ጥፋት አምጥቷል። ይህ ጦርነት
ግራኝ መሀመድ አልጋዚ
ከግዛት መስፋፋት ባለፈ፤ ከፍተኛ የሰው ሕይወት መጥፋት፤ ለብዙዎች ከእምነት መፈናቀል (በግዴታ ሃይማኖት መቀየር) እንዲሁም ለዘመናት የተከማቹ በዋጋ የማይገመቱ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ቅርሶች መውደም ዋናኛ ምክንያት ሆኗል። የወረራው መጠን-ሰፊነትና አጥፊነት የኢትዮጵያን ማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ገጽታ ለዘለቄታው የለወጠው ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና በምእመናኗ ላይ ጥልቅ የታሪክ ጠባሳ ጥሎ አልፏል። ለአሕመድ ግራኝ ጦርነት መነሻ የሆኑ ምክንያቶች የአሕመድ ግራኝ ጦርነት ድንገት የተከሰተ ሳይሆን የዘመናት ቅራኔዎች ውጤት ነው። 

Saturday, September 12, 2026

የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሃገረ ስበከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፋኑኤል አደገኛ የቁልቁለት መንገድ

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል
በቅድሚያ እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገረዎ በማለት ፤ እንኳን ለአዲስ ዓመት 2019 በሰላም
በፍቅር ጠብቆ አደረሰን በማለት የመልካም ምኞታችንን ከዚህ ከዝግጅት ክፍላችን ለማስተላለፍ እንወዳለን።

መጪውም ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የፍሠሀ፣ እንዲሁም የንሥሃ ዘመን እንዲሆንልን ልባዊ ምኞታችንን ለመግለጽ እንወዳለን፤ በዚህ ሣምንት መጀመሪያ አካባቢ የደረሰንን ዜና ይዘን በዚህ በዓዲስ አመት ለመምጣት ያስገደደን ነገሩ ትንሽ አስደንጋጭ እና አሳሳቢም በመሆኑ ይሄንኑ ከወዲሁ ለማስታወስ እንወዳለን።  

በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ፋኑኤል ለአንድ አጥቢያ ምሥራቀ ጸሐይ አቡነ ተክለሃማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ፍቅረ ማርያም አስተራይ ለተባሉ መነኩስ እጅግ አደገኛ የሆነ ፤ እና የምዕመናንና የሰበካ ጉባኤ አባላትን ሃላፊነት እና ቦታ ያላገናዘበ እጅግ በጣም ከፋፋይ እና መሰሪ የሆነ ደበዳቤ በድብቅ ጽፈው ለአስተዳዳሪው በመስጠት፤ አስተዳዳሪውም ባለፍው ሣምንት ውስጥ ለአካባቢው ፖሊስ ጠርተው የማይፈልጓቸውን ሰዎች ከቤተክርስቲያን ቅጽር እንዲባረሩ እና በድጋሚ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይመለሱ በማድረግ እጅግ በጣም ከባድ እና አደገኛ አካሄድ መጀመራቸውን የሰማንው በዚህ ሣምንት መጀመሪያ አካባቢ ነበር፤  

Wednesday, September 9, 2026

የቃሊቲ ክፍለ ከተማ አገልጋይ መልአከ ሕይወት ተስፋዬ ጀንበሬ እግድ ተነሳ

May be an image of ticket stub and text
No photo description available.
May be an image of text
መልአከ ሕይወት ተስፋዬ ጀንበሬ
በሊቀ ካሕናት ዕዝራ ንዋይ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቤ/ክ ሥራ አስኪያጅ አማካኝነት ከሥራ ታግደው የነበሩት ታላቁ ሊቅ መልአከ ሕይወት 
ተስፋዬ ጀንበር ትወናው ሲያልቅ እግዳቸው ነተሳ።
"በታች ሆኖ መወርወር ወደ ላይ ማሳየት ነው" እንዲሉ አስተዳደራቸው አልተመጣጠነም የተማረው ባልተማረው ሲመራ የሚፈፀም ድርጊት መሆኑ ቢታወቅም በአቃቂ ቃሊቲ በክፍለ ከተማ ሰራተኞች ከሥራ አስኪያጁ ውጪ በሥራቸው በምግባራቸው በማኔጅመንታዊ ጥበባቸው የሚወደዱት በመልአከ ሕይወት ተስፋዬ ጀንበሬ እግዳቸው የተነሳው በቀን 2/13/2018 ዓ.ም በተጻፈ ይፋዊ ደብዳቤ ነው ።
መልአከ ሕይወት ከሥራ ታግደው በነበረበት ወቅት ሲስተጓጎሉ የነበሩ የሥራ እንቅስቃሴዎችና አገልግሎቶች ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው እንደሚመለሱ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ህገ ቤተክርስቲያን መከበር አለበት በማለታቸው በሥራ አስኪያጁ እንዲጠሉ እንዲታገዱ የተደረገ ይታወሳል ።

 

 

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

Wednesday, September 2, 2026

ኦቦ በላይ መኮንን ከእሥር መፈታታቸው ተነገረ

No photo description available.
ኦቦ በላይ መኮንን (ዋቄ ፈና)

 

 ኦቦ በላይ ከእሥር መፈታታቸው እየተነገረ ነው፤ 

 ከሦስት ዓመታት በፊት በሐሰተኛ ሰነድ ከአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ከ7 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማዘዋወር ሞክረዋል በሚል የተከሰሱት ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በአመክሮ ከእሥር መለቀቃቸው ተዘግቧል። ቀሲስ በላይ በመጀመሪያ የ5 ዓመት እሥራት እና የ10 ሺሕ ብር ቅጣት ተወስኖባቸው የነበረ ቢሆንም፣ በይግባኝ ቅጣታቸው ወደ 3 ዓመት ከ7 ወር ዝቅ ብሎ ነበር። የእሥር ጊዜያቸውን ባጠናቀቁበት ማረሚያ ቤት ባሳዩት መልካም ሥነ-ምግባር ምክንያት በአመክሮ ከእሥር እንዲለቀቁ በመወሰኑ የእሥር ጊዜያቸውን አጠናቀው መውጣታቸውን ዘ-ሃበሻ ዘግቧል።

 የቀሲስ በላይ ቀጣይ ሁኔታ ምን ሊሆን ይችላል? 

ቀሲስ በላይ እደምናስታውሰው የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ እና ሃላፊ ሆነው ይሰሩ እንደነበር የሚታወስ ነው፤ ይሄንንም ተከትሎ በተለያየ ጊዜ ከሚሰጡ መግለጫዎች ጋር እና አቡነ ሣዊሮስ እና እነ አቡነ ኤዎስጣቲዎስ እነ አቡነ ዜና ማርቆስ በተደጋጋሚ አብረዋቸው ይታዩ እንደነበር ይታወሣል፤ በመሆኑም በቀጣይነት ለቀሲስ በላይ ከእሥር በፊት የነበራቸውን የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊነትን ይሰጧቸው ይሆን?