Saturday, December 22, 2012

“ከፓትርያርክ ምርጫ - ዕርቅና አንድነት ይቅደም” ስንል ምን ማለታችን ነው?



(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 12/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 21/2012/PDF)፦ እንደሚታወቀው ቤተ ክርስቲያናችን በመስቀልያ መንገድ ላይ እንደምትገኝ ተደጋግሞ የተገለጸ ነው። ዋነኛዎቹ ርዕሰ ጉዳዮች ሁለት ናቸው። የመጀመሪያው ለ20 ዓመታት በውግዘት የተለያዩ አባቶች አንድ እንዲሆኑ፣ አንዲት ቤተ ክርስቲያን፣ አንድ አስተዳደር፣ አንድ ቅ/ሲኖዶስ እንዲኖረን ማድረግ ነው። ለዚህም “ተስፋ ሰጪ” ሁኔታ ላይ ተደርሷል። ይህ ዳር እንዲደርስ እናድርግ። ሁለተኛው ደግሞ 20 ዓመት ለቆየው መለያየት ዓምድና ምልክት የነበረው የፕትርክናው ሥልጣን አንዱ የመወያያ አጀንዳ ስለሆነ ከዕርቁ በፊት ሌላ እርምጃ አይደረግበት የሚለው ነው። ይህንን በሚጋፋ መልኩ በጥቂት የቅ/ሲኖዶስ አባላት ግፊትና በመንግሥት ተጽዕኖ 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም “አስመራጭ ኮሚቴ” ተቋቁሟል። ሁለቱ አጀንዳዎች የሚገናኙት እዚህ ላይ ነው።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ።



ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን።”
      (DEC. 21/2012ታኅሣስ 12/2005 ዓ/ም/PDF):- በዚህ ታሪካዊ የዕርቀ ሰላም ንግግር ላይ ከኢትዮጵያና ከአሜሪካ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተሰይመው የተላኩት ልዑካን በፍጹም መከባበር ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት በስፋት ተወያይተዋል።

በውይይቱም ወቅት ሁለቱም ወገኖች ከላካቸው አካል ይዘውት የመጡትን መሠረተ ሐሳብ በሰፊው የተነጋገሩበት ሲሆን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ አገራቸው መመለስ ለዕርቀ ሰላሙ ስኬታማነት ዋነኛ መሠረት መሆኑን በጋራ ተስማምተዋል። ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ልዑካን በኩል የቀረበው ዋና ሐሳብ “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ቅድስት አገራቸው ገብተው፣ ክብራቸው ተጠብቆና የሚያስፈልጋቸው ሁሉ ተሟልቶላቸው እርሳቸው በፈለጉት ቦታ ይኑሩ”፤ የሚል ሲሆን የዚህ ፍሬ ሐሳብ አመክንዮ ደግሞ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው ቢመለሱ ታሪክ ይፋለስብናል የሚል ነበር።  

ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ መነሻ በማድረግ በዋሸንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የተሰጠ መግለጫ



የቤተ ክርስቲያንን አንድነት መጠበቅ እና ማስጠበቅ መንፈሳዊ ግዴታችን ነው። 
(ታኅሳስ 13  2005 ዓ. ም/ PDF):- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የራሷ መንበረ ፕትርክና ከማግኘቷ በፊት ለ 1600 ዓመታት ከግብጽ በሚመጡ ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ማርቆስ ሥር ስትተዳደር መቆየቷ ይታወሳል ። በእነዚህ ባሳለፈቻችው ዘመናት የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲጠበቅ በነበራት ጽኑ አቋም ብዙ መስዋዕትነት ከፍላለች። ችግር በገጠማትም ጊዜ ከግብጽ የሚመጡ አባቶች ሲቀሩባት እንኳን  ስለ አንዲት ቤተ ክርስቲያን ምስክርነቷን እየሰጠች ፤ በርካታ ሊቃውንትን ፤ በቅድስና የከበሩ አባቶችን  ይዛ ፤ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ስትል ግን ከመንበረ ማርቆስ ሊቃነ ጳጳሳት እንዲላኩላት ስትማጸን ኖራለች።
በተለይም “ ወሰብአ ኢትዮጵያ ኢይሢሙ ላዕሌሆሙ  ሊቀ ጳጳሳት እማእምራኒሆሙ ወኢበሥምረተ ርእሶሙ” ኒቅያ   ፵፪፡ ፶  የሚለውን  ምንባብ በማንሳት  ፤ በሥርዋጽ የገባ መሆኑን ለማስረዳት አድካሚና ተደጋጋሚ ጉዞ ወደ ግብጽ በማድረግ  ፤ መጽሐፋዊና ታሪካዊ ማስረጃን በማቅረብ በመንበረ ማርቆስ ለሚገኙ አባቶች ችግሩን በማስረዳት በውይይት ለብዙ ዘመናት እንደ ተራራ ገዝፎ የተቀመጠውን ችግር በማቅለል  የቤ ክርስቲያን አንድነት እንደተጠበቀ የራሷ መንበረ ፕትርክና እንዲኖራት አድርገዋል ። የቀደሙት አባቶችቻን በተግባር ያስተማሩን ትምህርት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለመጠበቅ ሲባል የማይከፈል መስዋዕትነት አለመኖሩን ነው። ዛሬም የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚፈታተኑ፤ መዋቅራዊ አንድነቷን የሚያናጉ፤ አለመግባባትና መለያየትን የሚፈጥሩ ችግሮች  በተለይም  በሰሜን አሜሪካ  እየታዩ መምጣታቸው  ፤ ትክክለኛ ፍርድ እና ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮች መብዛታቸውን ስንመለከት፤ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ እና ሃይማኖታዊ አመራር መዋቅራዊ ተዋረዱን ጠብቆ መጠናከር እንዳለበት ያስገነዝበናል። እኛም በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት የምንገኝ አብያተ ክርስቲያናት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ይጠበቅ በማለት በተደጋጋሚ ለቅዱስ ሲኖዶስ በማሰማት ላይ የምንገኘው ይህንኑ ችግር ለማቃለል እገዛ እንዲያደርግ ነው።

Friday, December 21, 2012

የቅ/ሲኖዶሱ አባላት በውሳኔያቸው ተከፋፍለዋል


  • የዕርቀ ሰላሙ ልኡካን በሲኖዶሱ ውሳኔ ላይ የወሰዱት አቋም በመንሥኤነት ተጠቅሷል
  • ‹‹ይኾናል ብለን አንጠብቅም፤ ኾኖ ከተገኘ በጣም እንቃወማለን›› /አቡነ አትናቴዎስ/
  • ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ከሲኖዶሱ ስብሰባና ውሳኔዎች ራሳቸውን አግልለዋል
  • ዋና ጸሐፊው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ፈቃደኛ አልኾኑም
  • ማኅበረ ቅዱሳን በዕርቀ ሰላሙ እና በፓትርያሪክ ምርጫ አጣባቂኝ ውስጥ ገብቷል
የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ትላንት፣ ታኅሣሥ 10 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀትር በኋላ የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንብ አጽድቆ ምርጫውን የሚያስፈጽም 13 አባላት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ ሠይሟል፡፡ የኮሚቴው አባላት ከቅ/ሲኖዶስ አባላት፣ ከመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ መምሪያ ሓላፊዎች፣ ከገዳማት አበምኔቶች፣ ከሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፣ ከመንፈሳውያን ማኅበራት እና ከታዋቂ ምእመናን ‹‹የተውጣጡ ናቸው›› ተብሏል፡፡
የኮሚቴውን መቋቋም ተከትሎ ለዕርቀ ሰላሙ ንግግሩ ወደ አሜሪካ የተላኩትና በቅ/ሲኖዶሱ የተሰጣቸውን ተጨማሪ የሰላም ተልእኮ ለመፈጸም በዚያው ከሚገኙት ሦስት ብፁዓን አባቶች መካከል ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ÷ ትላንት ሌሊቱን ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ እና ከቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ጋራ በስልክ ተነጋግረዋል፡፡ በጥቅምት ቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት በደብዳቤ መላካቸውንና በዳላሱ የሰላም ጉባኤ በወጣው የጋራ መግለጫ መሠረት ዕርቀ ሰላሙን ከሚያደናቅፉ ተግባራት ለመቆጠብ ተስማምተው መፈረማቸውን ያስታወሱት ብፁዕነታቸው÷ ቅ/ሲኖዶሱ የልኡኩን ሪፖርት ሳያዳምጥና የሎሳንጀለሱን የሰላም ጉባኤ ውጤት ሳይጠብቅ አስመራጭ ኮሚቴ መሠየሙን እንደማይቀበሉት ማስታወቃቸው ተዘግቧል፡፡
ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ እና ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ
ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ እና ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ

Thursday, December 20, 2012

ምን እንበል ? “በጎች ሆይ የእረኞቻችሁን ምክር ስሙ” ወይንስ “እረኞች ሆይ ፦ የበጎቻችሁን ምክር ስሙ”??


ኦርቶዶክሳዊነት ወዴት ገባ? አቦ አቦ መባልን መሽሽ ወዴት ገባ? ራስን ከክብር ከስልጣን ማራቅ ወዴት ገባ? ኸረ ወዴት ገባ? ስለልጆቹስ የሚገደው አባት ወዴት ጠፋ? ስለምእመናን ምቾትስ እድሜህን ሁሉ በጉስቁልና የኖርክ ዮሐንስ አፈወርቅ ሆይ እስኪ ተናገርና እንስማህ? ስለእርቅ ምን ያክል ዋጋ ትከፍል ነበር? ስለምዕመናንስ አንድነት ምን ያክል ዋጋ ትከፍል ነበር? ስለክርስትናስ ክብር ምን ያክል ዋጋ ትከፍል ነበር? አባታችን ተናገረንና እስኪ እንጽናና ፤ በእኛ ቤት ግን ከእርቅ ይልቅ የሥልጣን ጥማቱ አይሏል ፥ ከምዕመናን አንድነት ይልቅ የራስን ሹመት ማዳበር አይሏል ፥ ከክርስትናው ክብር ይልቅ የቤተ መንግሥቱ ክብር በልጧል ፤ በእኛ ቤት እንዲህ ሆኗል ፤ ያ ሥልጣንን ስለአለመፈለግ ወደገዳም ሽሽቱ ኦርቶዶክሳዊው ትህትና ቀርቷል ፥ ሁሉም ራሱን ይመርጣል ፥ ሁሉም ምረጡኝ ይላል ፥ ሁሉም ድጋፍን ይሻል ፤

6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም የሚደረገውን ሩጫ ለማትደግፉ በሙሉ



መፈክራችን - “የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል” የሚል ነው።

(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 11/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር20/2012/ PDF)፦ በጥቂት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፍላጎት በመዘወር ላይ ያለው የ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ተጠናክሮ በመቀጠል አሁን “አስመራጭ ኮሚቴ” በማቋቋም ትልቅ ርምጃ ተስፈንጥሯል። ለዕርቅና ለሰላም ወደ አሜሪካ የላካቸውን ልዑካን መምጣት ሳይጠብቅ፣ ይዘው ለሚመጡት ምላሽ ቦታ ሳይሰጥ አዲስ ፓትርያርክ ወደ መምረጡ እየተጓዘ ነው።


ይህንን ጉዳይ በተመለከተ በአገር ውስጥም፣ ከአገር ውጪም፣ በመላው ዓለም ያለው ኦርቶዶክሳዊ ድምጹን ማሰማት እንደሚፈልግ ይታወቃል። የአቅሙን የመፍትሔው አካል መሆን ይፈልጋል። ታዲያ ምን ይሻላል?  ከጥቃቅን የጽዋ ማኅበራት እስከ ግዙፎቹ፣ ከማኅበረ ካህናት እስከ ማኅበረ ምዕመናን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን እንደሚገደን መናገር የሚገባን አሁን ነው። ስለዚህም ነው ይህንን የመወያያ ርዕስ የከፈትነው። መፍትሔ የምትሏቸውን ሐሳቦች በማቅረብ፣ በየአካባቢያችሁና በየአጥቢያችሁ በአካል በመሰባሰብና በመነጋገር ለእናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያላችሁ አለኝታነት እንድታሳዩ ይጠበቃል። እምነት በሥራ እንጂ በምን ይገለጻል? ለመነሻ እንዲሆን ይህንን እንጠቁም። እናንተም አክሉበት።

ሰበር ዜና - ሲኖዶሱ አስመራጭ ኮሚቴ ሠየመ - ቤተ ክርስቲያን በከፋ የመለያየት አደጋ ውስጥ ትገኛለች !!

  • የፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ ረቂቁን አጽድቆ ተፈራርሟል
  • ጠቅላላ ሂደቱ በመንግሥትና የመንግሥትን አቋም በሚደገፉ ጳጳሳት ቁጥጥር ሥር ገብቷል
  • ለዕርቀ ሰላም ንግግር ወደ አሜሪካ ያመሩት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ‹‹መግለጫ እንሰጣለን፤ ከሲኖዶሱ ጋራ አብረን አንቀጥልም፤ ወደ ገዳም እንገባለን›› ማለታቸው እየተሰማ ነው
ከታኅሣሥ 1 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ለዘጠኝ ቀናት ያህል በፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ ረቂቅ ላይ ሲወያይ የቆየው የቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ የሕጉን ረቂቅ አሻሽሎ አጽድቋል፤ ለዕርቀ ሰላሙ ዕንቅፋት እንዳይኾን ትዕግሥት እንዲደረግበት ብርቱ ክርክር የተካሄደበትን አስመራጭ ኮሚቴም ሠይሟል፤ እንደ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ያሉት አባቶች ከሂደቱ ራሳቸውን ማግለላቸው እየተነገረ ነው፡፡
የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት ኾነው የተመረጡት ከሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ጢሞቴዎስ፣ አቡነ ቄርሎስ፣ አቡነ እስጢፋኖስ እና አቡነ ቀሌምንጦስ ናቸው፡፡ ከመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ መመሪያ ሓላፊዎች ውስጥ ደግሞ የዕቅድና ልማት መምሪያ ሓላፊው ሊቀ ትጉሃን ኀይለ ጊዮርጊስ ዳኜ፣ የሰበካ ጉባኤው መምሪያ ሓላፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ ይገኙበታል፡፡ አቶ ባያብል ሙላቴ (ከማኅበረ ቅዱሳን)፣ ከታዋቂ ምእመናን መካከል ደግሞ እንደ አቶ ዓለማየሁ ተስፋዬ (ከኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት) የመሳሰሉት ሰዎች እንደሚገኙበት ተጠቁሟል፡፡

ለዕርቀ ሰላሙ ሥምረት ሕዝበ ክርስቲያኑ የማንንም ተጽዕኖ ሳይፈራ በአንድነት እንዲንቀሳቀስ ጥሪ ቀረበ

  • ‹‹ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት የመነኰሳት ብቻ አይደለችም፤ ምእመናን እንደ ምእመንነታቸው ሊደመጡ ይገባል፡፡››
  • ‹‹ሁለቱም አካላት በደልንና ቅድመ ኹኔታን ትተው፣ ፍቅርን አስቀድመው፣ ለተጣሰው ቀኖና የጋራ ሓላፊነት ወስደው አንድነታቸውን ከመለሱ በኋላ ዐቃቤ መንበር መርጠው ፓትርያሪክ ለመሾም ምንም የሚያግዳቸው ነገር የለም፡፡››
በሰሜን አሜሪካ በስደት ላይ ከሚገኙት ብፁዓን አባቶች ጋራ ሲካሄድ የቆየው የዕርቀ ሰላም ንግግር ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በደረሰበት በአሁኑ ወቅት÷ የቤተ ክርስቲያን አንድ አካል የኾኑት በሀገር ውስጥም በውጭም የሚኖሩ ምእመናንና ምእመናን በጎ ተጽዕኖ ለመፍጠር የሚያስችል፣ መግባባት የሰፈነበት የተግባር እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ፡፡ የቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሰላም የአባቶች ጉዳይ ብቻ አይደለም የሚል መልእክት የተላለፈበት ይኸው ጥሪ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ምእመናንና ምእመናት በሚኖሩባቸው አካባቢዎችና በሚያገለግሉባቸው መድረኰች የዕርቀ ሰላሙ ሂደት ይሠምር ዘንድ ከጸሎት ባሻገር ጠንካራ ተጽዕኖ ለመፍጠር በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች የማንንም አካል ጫና መስጋት እንደማይገባቸው ጠይቋል፡፡

Friday, December 14, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ ረቂቅ ላይ መወያየት ጀምሯል



  • በረቂቅ ላይ ተጨማሪ የውይይት መድረኰች እንዲዘጋጁ ጠንካራ ፍላጎት እየታየ ነው
  • ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያው የተሠየመው ኮሚቴ በሰው ኀይል ተጠናክሯል
  • የገዳም መነኵሴ በፓትርያሪክ ዕጩነት ለማቅረብ የሚያስችል አንቀጽ ተካቷል

የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ እና በፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ ረቂቅ ዝግጅት ላይ ለመነጋገር ለኅዳር 30 ቀን 2005 ዓ.ም ተቀጥሮ የነበረውና ታኅሣሥ 2 ከቀትር በኋላ የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ልዩ ስብሰባ ታኅሣሥ 2 ቀንም 2005 ዓ.ም ቀጥሏል፡፡

የእርቀሰላሙ መጨረሻው እና የኢሳት ዘገባ

የኢሳት ዘገባ December 14, 2012 በፖትርያሪክ ምርጫውና በ1984 በተፈጠረው ታሪካዊ የቤተክርስቲያን ላይ በደረው ስህተት ዙሪያ ዘጋሚ የሆነ ሪፖርት።

በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ለለፉት ጥቂት ቀናት ተስፋ ተጥሎበት የነበረውን የሰምና አንድነት እንደተጠበቀው ውጤት ሳያመጣ ነገር ግን አስደሳች እና ተስፋ ሰጪ ሁናቴውችን ሰጥቶ ባለው ቅዳሜ በዳላስ ላይ አጠናቆ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለቱም ወገኖች ተማምነው የጋራ መግለጫ በሰላም እና አንድነቱ ጉባኤ ስም ለማውጣት መቻላቸው ትልቅ እመርታ እና ትልቅ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ቢገመትም፥ በኢትዮጵያ ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፮ኛውን ፖትርያሪክ እንመርጣለን በማለት እላይ እታች ማለታቸውን መላው ሰላም ወዳድ በሙሉ እንዳልደገፈው እና ይልቁንም ቤተክርስቲያኒቱን ወደበለጠ መከፋፈል ይወስዳታል የሚል ፍራቻ በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ እንዳለ

ባይገቡ የሁላችን ኦርቶዶክሳዊያን ምኞች ቢሆንም እንደሚሰማው ግን ምርጫውን ለማድረግ ብዙ ሥራዎችን እየሰሩ እንደሆነ ይነገራል። በሁሉም ቦታ ያሉትን አባቶች ማስተዋሉን ሰጥቷቸው ከራሳቸው በላይ ለመንጋቸው ተጨንቀው ለምዕመናኑ አንድነት ሲሉ በትዕግስት ጠብቀው መጨረሻውን ቢመለከቱ መልካም እንደሆነ የዝግጅት ክፍላችን ያምናል።
በመጨረሻ የሰላምና አንድነቱ ያወጣውን መሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
"በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን"
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

Friday, December 7, 2012

የዕርቀ ሰላም ውይይቱ በመልካም ሁናቴ ቀጥሏል


(ደጀ ሰላም ኅዳር 27/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 6/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦በአሜሪካዋ የቴክሳስ ግዛት ዳላስ ከተማ በመካሔድ ላይ የአባቶች ዕርቀ ሰላም ውይይት በመልካም ሁናቴ በመካሔድ ላይ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸውልናል። ትናንት የተጀመረው ጉባኤ በመጀመሪያ ቀን የጠዋት ውሎው በጸሎተ ኪዳን ጉባኤውን ጀምሯል።  ጸሎተ ኪዳኑ በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ መሪነት ከተካሔደ በኋላ “ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት” በመልአከ መንክራት ቀሲስ አንዱዓለምይርዳው ተሰምቷል።


ጉባኤው ቀጥሎ  ከዚህ ጉባኤ ምን እንደሚጠበቅ ባለ አምስት ነጥብ ማብራሪያ  በአስታራቂ ኮሚቴው አባል በቆሞስ አባ ጽጌ ደገፋው የቀረበ ሲሆን  የሰላምና  አንድነት ጉባኤው አባላት ትውውቅ አድርገዋል። አስከትሎም ሁለት መልእክቶች በተከታታይ ቀርበዋል።  ብፁዕ አቡነ ገሪማ ባቀረቡትየመግቢያ መልዕክት ስለ ኢትዮጵያ  መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረውን በመዘርዘር ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር መሆኗን አብራርተው ቤተ ክርስቲያን ለአገር ያበረከተችውን አስተዋጽኦ ዘርዝረው በተለያዩ ጊዜዎች ፈተና  እንደገጠማትና እንደተወጣችው  አብራርተዋል:: ሰላም ማምጣት  አስፈላጊ መሆኑንና ባፋጣኝ እንዲፈጸም እንደሚገባ አስረድተዋል::  ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅባቀረቡት ተመሳሳይ መልዕክት ታራቂዎችም አስታራቂዎችም እኛ ነን ብለዋል::

Thursday, December 6, 2012

የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ለብፁዕ ወቅዱስ እንዲመለሱ በደብዳቤ ፈቀዱ፤ ደብዳቤውን አጠፉ



  • የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮን ዘገባና ቃለ ምልልስ አዳምጡ::
  •  ደብዳቤዎቹን ከዚህ ላይ ያገኟቸዋል።
(ደጀ ሰላም ኅዳር 27/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 6/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊት ሪፓብሊክ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ደብዳቤ ከጻፉ በኋላ ሐሳቡን ማጠፋቸውን ገልጸዋል::በችኮላና የሚያስከትለውን “ጣጣና መዘዝ” ባለማገናዘብ በቀናነት የጻፉት ደብዳቤ መሆኑን ያብራሩት ክቡር ፕሬዚዳንቱ “መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ እንደማይገባ” በማስታወስ ደብዳቤያቸው መሳባቸውን አስታውቀዋል።


ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ አቡነ ናትናኤል ጋር መነጋገራቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ በሊቀ ጳጳሱ መገሰጻቸውን አልሸሸጉም። “ይቅርታ አድርጌልኻለኹ” መባላቸውን አብራርተዋል። ስለዚህ ትህትናዎ፣ ክቡር ፕሬዚዳንት ግርማ፣ እናመሰግንዎታለን። ፕሬዚዳንት ግርማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 4ኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ሃገር ቤት ተመልሰው ከሁለት የተከፈለችው ቤተ ክርስቲያን አንድ እንድትሆን የሚያሳስብ ደብዳቤ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ እና ለብፁዕ አቡነ ናትናኤል መጻፋቸው፣ ምንም እንኳን ዘግይቶ “ቢስቡትም”፣ ሐሳቡ ግን አስደስቶናል። ይበል ብለናል ክቡር ፕሬዚዳንት። እንደ መንግሥት ኃላፊነትዎም ባይሆን እንደ አንድ በሥልጣን ወንበር እንደተቀመጠ ኦርቶዶክሳዊ ሐሳብዎን መግለጥዎ ተገቢም፣ ጥሩም ነው።

Wednesday, December 5, 2012

በጀርመን የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካህናት “ግልጽ ደብዳቤ” አወጡ


(ደጀ ሰላም ኅዳር 23/2005 ዓ.ም፤ዲሴምበር 1/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በጀርመን አገር ኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን ኃላፊ የሆኑት ሊቀ ካህናት ዶ/ርመርዓዊ ተበጀ “  ስለ  ነገዋ ቤተክርስቲያን ስንል ዕድሉ ዛሬባያመልጠንስ? “   ሲሉ “  ግልጽ ደብዳቤ”   አወጡ። የእናት ቤተክርስቲያን መካፋፈል የራስ ምታት፧ የሆድቁርጠት፧ የልብ ሕመም ወዘተ ሆኖ ለ21ዓመታት  “   እኽ እኽ››  እያሰኘ መኖሩበውስጡ ላለፈበት ትውልድ ሁሉ ግልጽ”   መሆኑን የጠቀሱት ሊቀ ካህናቱ እርሳቸውም የበኩላቸውን ሐሳብ ለመስጠት እንደፈለጉ ጠቅሰዋል። ይህንን ደብዳቤ አሁን መጻፍ የፈለጉት ጊዜው “የተመቸ” ነው በሚል ወይም በርሳቸው አገላለጽ“ሲመች በእጅ፣ ሲፈጅ በማንካ” ለማለት ሳይሆን ከዚህ አስቀድሞ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከመሾማቸው አስቀድሞም ተመሳሳይ ሐሳብ ማቅረባቸውን ማስረጃ ጠቅሰው አብራርተዋል።

ደጀ ሰላም ይህ መሠረታዊ ጽሑፍ ለአንባብያን ቢደርስ ያለውን ጥቅም በመረዳት፣ እንዲሁም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ይህንን አስተያየት ከግምት እንደሚያስገቡት በማመን አቅርበነዋል። መልካም ንባብ።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን አባቶች የእርቀ ሰላም ውይይት ዛሬ ይጀመራል



  • ከኢትዮጵያ የመጣው ልዑክ ዳላስ የገቡት ትናንት ኅዳር 26/ ዲሴምበር 4 ነው።

ሁለቱም ታራቂ አባቶች ከውይይታቸው በፊት በጋራ ተቀምጠው
 
(ደጀ ሰላም ኅዳር 26/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 5/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት የሚደረገው ሦስተኛ ዙርየዕርቅ ድርድር ዛሬ በሰሜን አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ ከተማ ይጀመራል:: ከዛሬ ኅዳር 26 እስከ 30(ዲሴምበር 5-9/2012) የሚካሄደው ስብሰባ ውጤታማ እንዲሆን በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ምኞታቸውን እየገለጡ ሲሆን በውጪው ዓለም የሚገኙ ካህናት፣ ምዕመናን እና መንፈሳውያን ማኅበራት በሁለቱም በኩል ላሉት አባቶች ችግሩ እልባት እንዲያገኝ የተማጽኖ ፊርማ እያሰባሰቡ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል::

Tuesday, December 4, 2012

ስለ “አባቶች እርቅ” ጉዳይ ፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ



  •    ምእመናን ፊርማቸውን በኢንተርኔትም ሆነ በየአጥቢያቸው በወረቀት እንዲያሰባስቡ ተጠይቀዋል፤
(ደጀ ሰላም ኅዳር 25/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር4/2012/ READ THIS NEWS IN PDF):- የቤተ ክርስቲያን አባቶችን እርቀ ሰላም ለማገዝና የምዕመናን ሙሉ ድጋፍ ለማሳየት “የተማኅጽኖ ፊርማ” (ፔቲሽን) ማሰባሰብ ተጀምሯል። ምእመናን የዳር ተመልካች ሆነው ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ችግር ወደ ሌላ ችግር ስትሸጋገር መመልከት ብቻ ሳይሆን እነርሱም በፈንታቸው “የእርቁ አካል” በመሆን አባቶችን መርዳት እንደሚገባ የሁሉም እምነት ነው። ደጀ ሰላምም ለረዥም ዓመታት ስታደርግ እንደነበረው አሁንም ምእመኑ ይህንን የፊርማ ዘመቻ በመካፈል ድምጹን ማሰማት አለበት።  በኢንተርኔት መፈረም ለምትፈልጉ (ይህንን በመጫን) ፊርማውን ማከናወን ይቻላል። የ “ፌስቡክ ተጠቃሚዎች” በፌስቡክ አማካይነት በቀላሉ መፈረም ያስችላችኋል።

በየአጥቢያችሁ ፊርማውን በመፈረም ሌሎችንም እንዲፈርሙ ማድረግ ለምትፈልጉ ደግሞ (ይህንን ፒ.ዲ.ኤፍ) “ዳውንሎድ” በማድረግ መጠቀም ትችላላችሁ።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ



 
......«ሐምሌ 22 ቀን 1928  ስምንት ወታደሮች በስተጀርባቸው ሃያ እርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተንጠቀቅ ቆሙ። ወዲያው አዛዡ «ተኩስ» በማለት ትእዛዝ ሲሰጥ ስምንቱም ተኩሰው መቷቸው። ግን በስምንት ጥይት ሳይሞቱ ቀሩ። መሞታቸውንና አለመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ። ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ። ከዚያም ሌላ ወታደር በሦስት የሽጉጥ ጥይት ራስ ቅላቸውን መትቶ ገደላቸው። .........