Friday, December 14, 2012

የእርቀሰላሙ መጨረሻው እና የኢሳት ዘገባ

የኢሳት ዘገባ December 14, 2012 በፖትርያሪክ ምርጫውና በ1984 በተፈጠረው ታሪካዊ የቤተክርስቲያን ላይ በደረው ስህተት ዙሪያ ዘጋሚ የሆነ ሪፖርት።

በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ለለፉት ጥቂት ቀናት ተስፋ ተጥሎበት የነበረውን የሰምና አንድነት እንደተጠበቀው ውጤት ሳያመጣ ነገር ግን አስደሳች እና ተስፋ ሰጪ ሁናቴውችን ሰጥቶ ባለው ቅዳሜ በዳላስ ላይ አጠናቆ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለቱም ወገኖች ተማምነው የጋራ መግለጫ በሰላም እና አንድነቱ ጉባኤ ስም ለማውጣት መቻላቸው ትልቅ እመርታ እና ትልቅ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ቢገመትም፥ በኢትዮጵያ ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፮ኛውን ፖትርያሪክ እንመርጣለን በማለት እላይ እታች ማለታቸውን መላው ሰላም ወዳድ በሙሉ እንዳልደገፈው እና ይልቁንም ቤተክርስቲያኒቱን ወደበለጠ መከፋፈል ይወስዳታል የሚል ፍራቻ በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ እንዳለ

ባይገቡ የሁላችን ኦርቶዶክሳዊያን ምኞች ቢሆንም እንደሚሰማው ግን ምርጫውን ለማድረግ ብዙ ሥራዎችን እየሰሩ እንደሆነ ይነገራል። በሁሉም ቦታ ያሉትን አባቶች ማስተዋሉን ሰጥቷቸው ከራሳቸው በላይ ለመንጋቸው ተጨንቀው ለምዕመናኑ አንድነት ሲሉ በትዕግስት ጠብቀው መጨረሻውን ቢመለከቱ መልካም እንደሆነ የዝግጅት ክፍላችን ያምናል።
በመጨረሻ የሰላምና አንድነቱ ያወጣውን መሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
"በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን"
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

1 comment:

  1. ይገርማል እነማን ናቹ እንዴ ኢሳትን ምንጭ በአንድ ብሄር የበላይነት በማመን የሚሰብክ ሌላውን ብሄር ለማጥፋት የሚሰብክ(በተለይ የትግራይ ብሄር) የፖለቲካ ድርጅት ሚድያጋ ናቹ ምኑን የሃይማኖት ብሎግ ሆናቹሁት

    ReplyDelete