ኦርቶዶክሳዊነት ወዴት ገባ? አቦ አቦ መባልን መሽሽ ወዴት ገባ? ራስን ከክብር ከስልጣን ማራቅ ወዴት ገባ? ኸረ ወዴት ገባ? ስለልጆቹስ የሚገደው አባት ወዴት ጠፋ? ስለምእመናን ምቾትስ እድሜህን ሁሉ በጉስቁልና የኖርክ ዮሐንስ አፈወርቅ ሆይ እስኪ ተናገርና እንስማህ? ስለእርቅ ምን ያክል ዋጋ ትከፍል ነበር? ስለምዕመናንስ አንድነት ምን ያክል ዋጋ ትከፍል ነበር? ስለክርስትናስ ክብር ምን ያክል ዋጋ ትከፍል ነበር? አባታችን ተናገረንና እስኪ እንጽናና ፤ በእኛ ቤት ግን ከእርቅ ይልቅ የሥልጣን ጥማቱ አይሏል ፥ ከምዕመናን አንድነት ይልቅ የራስን ሹመት ማዳበር አይሏል ፥ ከክርስትናው ክብር ይልቅ የቤተ መንግሥቱ ክብር በልጧል ፤ በእኛ ቤት እንዲህ ሆኗል ፤ ያ ሥልጣንን ስለአለመፈለግ ወደገዳም ሽሽቱ ኦርቶዶክሳዊው ትህትና ቀርቷል ፥ ሁሉም ራሱን ይመርጣል ፥ ሁሉም ምረጡኝ ይላል ፥ ሁሉም ድጋፍን ይሻል ፤
Thursday, December 20, 2012
6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም የሚደረገውን ሩጫ ለማትደግፉ በሙሉ
መፈክራችን - “የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል” የሚል ነው።
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 11/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር20/2012/ PDF)፦ በጥቂት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፍላጎት በመዘወር ላይ ያለው የ6ኛው ፓትርያርክ ምርጫ ተጠናክሮ በመቀጠል አሁን “አስመራጭ ኮሚቴ” በማቋቋም ትልቅ ርምጃ ተስፈንጥሯል። ለዕርቅና ለሰላም ወደ አሜሪካ የላካቸውን ልዑካን መምጣት ሳይጠብቅ፣ ይዘው ለሚመጡት ምላሽ ቦታ ሳይሰጥ አዲስ ፓትርያርክ ወደ መምረጡ እየተጓዘ ነው።
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ በአገር ውስጥም፣ ከአገር ውጪም፣ በመላው ዓለም ያለው ኦርቶዶክሳዊ ድምጹን ማሰማት እንደሚፈልግ ይታወቃል። የአቅሙን የመፍትሔው አካል መሆን ይፈልጋል። ታዲያ ምን ይሻላል? ከጥቃቅን የጽዋ ማኅበራት እስከ ግዙፎቹ፣ ከማኅበረ ካህናት እስከ ማኅበረ ምዕመናን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን እንደሚገደን መናገር የሚገባን አሁን ነው። ስለዚህም ነው ይህንን የመወያያ ርዕስ የከፈትነው። መፍትሔ የምትሏቸውን ሐሳቦች በማቅረብ፣ በየአካባቢያችሁና በየአጥቢያችሁ በአካል በመሰባሰብና በመነጋገር ለእናት ቤተ ክርስቲያናችሁ ያላችሁ አለኝታነት እንድታሳዩ ይጠበቃል። እምነት በሥራ እንጂ በምን ይገለጻል? ለመነሻ እንዲሆን ይህንን እንጠቁም። እናንተም አክሉበት።
ሰበር ዜና - ሲኖዶሱ አስመራጭ ኮሚቴ ሠየመ - ቤተ ክርስቲያን በከፋ የመለያየት አደጋ ውስጥ ትገኛለች !!
- የፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ ረቂቁን አጽድቆ ተፈራርሟል
- ጠቅላላ ሂደቱ በመንግሥትና የመንግሥትን አቋም በሚደገፉ ጳጳሳት ቁጥጥር ሥር ገብቷል
- ለዕርቀ ሰላም ንግግር ወደ አሜሪካ ያመሩት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ‹‹መግለጫ እንሰጣለን፤ ከሲኖዶሱ ጋራ አብረን አንቀጥልም፤ ወደ ገዳም እንገባለን›› ማለታቸው እየተሰማ ነው
የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት ኾነው የተመረጡት ከሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ጢሞቴዎስ፣ አቡነ ቄርሎስ፣ አቡነ እስጢፋኖስ እና አቡነ ቀሌምንጦስ ናቸው፡፡ ከመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ መመሪያ ሓላፊዎች ውስጥ ደግሞ የዕቅድና ልማት መምሪያ ሓላፊው ሊቀ ትጉሃን ኀይለ ጊዮርጊስ ዳኜ፣ የሰበካ ጉባኤው መምሪያ ሓላፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ ይገኙበታል፡፡ አቶ ባያብል ሙላቴ (ከማኅበረ ቅዱሳን)፣ ከታዋቂ ምእመናን መካከል ደግሞ እንደ አቶ ዓለማየሁ ተስፋዬ (ከኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት) የመሳሰሉት ሰዎች እንደሚገኙበት ተጠቁሟል፡፡
ለዕርቀ ሰላሙ ሥምረት ሕዝበ ክርስቲያኑ የማንንም ተጽዕኖ ሳይፈራ በአንድነት እንዲንቀሳቀስ ጥሪ ቀረበ
- ‹‹ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት የመነኰሳት ብቻ አይደለችም፤ ምእመናን እንደ ምእመንነታቸው ሊደመጡ ይገባል፡፡››
- ‹‹ሁለቱም አካላት በደልንና ቅድመ ኹኔታን ትተው፣ ፍቅርን አስቀድመው፣ ለተጣሰው ቀኖና የጋራ ሓላፊነት ወስደው አንድነታቸውን ከመለሱ በኋላ ዐቃቤ መንበር መርጠው ፓትርያሪክ ለመሾም ምንም የሚያግዳቸው ነገር የለም፡፡››
በሰሜን አሜሪካ በስደት ላይ ከሚገኙት ብፁዓን አባቶች ጋራ ሲካሄድ የቆየው የዕርቀ ሰላም ንግግር ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በደረሰበት በአሁኑ ወቅት÷ የቤተ ክርስቲያን አንድ አካል የኾኑት በሀገር ውስጥም በውጭም የሚኖሩ ምእመናንና ምእመናን በጎ ተጽዕኖ ለመፍጠር
የሚያስችል፣ መግባባት የሰፈነበት የተግባር እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ፡፡ የቤተ ክርስቲያን አንድነትና
ሰላም የአባቶች ጉዳይ ብቻ አይደለም የሚል መልእክት የተላለፈበት ይኸው ጥሪ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ምእመናንና
ምእመናት በሚኖሩባቸው አካባቢዎችና በሚያገለግሉባቸው መድረኰች የዕርቀ ሰላሙ ሂደት ይሠምር ዘንድ ከጸሎት ባሻገር
ጠንካራ ተጽዕኖ ለመፍጠር በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች የማንንም አካል ጫና መስጋት እንደማይገባቸው ጠይቋል፡፡
Friday, December 14, 2012
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ ረቂቅ ላይ መወያየት ጀምሯል
- በረቂቅ ላይ ተጨማሪ የውይይት መድረኰች እንዲዘጋጁ ጠንካራ ፍላጎት እየታየ ነው
- ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያው የተሠየመው ኮሚቴ በሰው ኀይል ተጠናክሯል
- የገዳም መነኵሴ በፓትርያሪክ ዕጩነት ለማቅረብ የሚያስችል አንቀጽ ተካቷል
የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ እና በፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ ረቂቅ ዝግጅት ላይ ለመነጋገር ለኅዳር 30 ቀን 2005 ዓ.ም ተቀጥሮ የነበረውና ታኅሣሥ 2 ከቀትር በኋላ የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ልዩ ስብሰባ ታኅሣሥ 2 ቀንም 2005 ዓ.ም ቀጥሏል፡፡
የእርቀሰላሙ መጨረሻው እና የኢሳት ዘገባ
በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ለለፉት ጥቂት ቀናት ተስፋ ተጥሎበት የነበረውን የሰምና አንድነት እንደተጠበቀው ውጤት ሳያመጣ ነገር ግን አስደሳች እና ተስፋ ሰጪ ሁናቴውችን ሰጥቶ ባለው ቅዳሜ በዳላስ ላይ አጠናቆ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለቱም ወገኖች ተማምነው የጋራ መግለጫ በሰላም እና አንድነቱ ጉባኤ ስም ለማውጣት መቻላቸው ትልቅ እመርታ እና ትልቅ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ቢገመትም፥ በኢትዮጵያ ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ፮ኛውን ፖትርያሪክ እንመርጣለን በማለት እላይ እታች ማለታቸውን መላው ሰላም ወዳድ በሙሉ እንዳልደገፈው እና ይልቁንም ቤተክርስቲያኒቱን ወደበለጠ መከፋፈል ይወስዳታል የሚል ፍራቻ በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ዘንድ እንዳለ
ባይገቡ የሁላችን ኦርቶዶክሳዊያን ምኞች ቢሆንም እንደሚሰማው ግን ምርጫውን ለማድረግ ብዙ ሥራዎችን እየሰሩ እንደሆነ ይነገራል። በሁሉም ቦታ ያሉትን አባቶች ማስተዋሉን ሰጥቷቸው ከራሳቸው በላይ ለመንጋቸው ተጨንቀው ለምዕመናኑ አንድነት ሲሉ በትዕግስት ጠብቀው መጨረሻውን ቢመለከቱ መልካም እንደሆነ የዝግጅት ክፍላችን ያምናል።
በመጨረሻ የሰላምና አንድነቱ ያወጣውን መሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
"በእንተ ሰላም ቤተክርስቲያን"
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
Friday, December 7, 2012
የዕርቀ ሰላም ውይይቱ በመልካም ሁናቴ ቀጥሏል
(ደጀ ሰላም ኅዳር 27/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 6/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦በአሜሪካዋ የቴክሳስ ግዛት ዳላስ ከተማ በመካሔድ ላይ የአባቶች ዕርቀ ሰላም ውይይት በመልካም ሁናቴ በመካሔድ ላይ መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸውልናል። ትናንት የተጀመረው ጉባኤ በመጀመሪያ ቀን የጠዋት ውሎው በጸሎተ ኪዳን ጉባኤውን ጀምሯል። ጸሎተ ኪዳኑ በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ መሪነት ከተካሔደ በኋላ “ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት” በመልአከ መንክራት ቀሲስ አንዱዓለምይርዳው ተሰምቷል።
ጉባኤው ቀጥሎ ከዚህ ጉባኤ ምን እንደሚጠበቅ ባለ አምስት ነጥብ ማብራሪያ በአስታራቂ ኮሚቴው አባል በቆሞስ አባ ጽጌ ደገፋው የቀረበ ሲሆን የሰላምና አንድነት ጉባኤው አባላት ትውውቅ አድርገዋል። አስከትሎም ሁለት መልእክቶች በተከታታይ ቀርበዋል። ብፁዕ አቡነ ገሪማ ባቀረቡትየመግቢያ መልዕክት ስለ ኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ የተናገረውን በመዘርዘር ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር መሆኗን አብራርተው ቤተ ክርስቲያን ለአገር ያበረከተችውን አስተዋጽኦ ዘርዝረው በተለያዩ ጊዜዎች ፈተና እንደገጠማትና እንደተወጣችው አብራርተዋል:: ሰላም ማምጣት አስፈላጊ መሆኑንና ባፋጣኝ እንዲፈጸም እንደሚገባ አስረድተዋል:: ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅባቀረቡት ተመሳሳይ መልዕክት ታራቂዎችም አስታራቂዎችም እኛ ነን ብለዋል::
Thursday, December 6, 2012
የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ለብፁዕ ወቅዱስ እንዲመለሱ በደብዳቤ ፈቀዱ፤ ደብዳቤውን አጠፉ
- የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮን ዘገባና ቃለ ምልልስ አዳምጡ::
- ደብዳቤዎቹን ከዚህ ላይ ያገኟቸዋል።
ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ አቡነ ናትናኤል ጋር መነጋገራቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ በሊቀ ጳጳሱ መገሰጻቸውን አልሸሸጉም። “ይቅርታ አድርጌልኻለኹ” መባላቸውን አብራርተዋል። ስለዚህ ትህትናዎ፣ ክቡር ፕሬዚዳንት ግርማ፣ እናመሰግንዎታለን። ፕሬዚዳንት ግርማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 4ኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ሃገር ቤት ተመልሰው ከሁለት የተከፈለችው ቤተ ክርስቲያን አንድ እንድትሆን የሚያሳስብ ደብዳቤ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ እና ለብፁዕ አቡነ ናትናኤል መጻፋቸው፣ ምንም እንኳን ዘግይቶ “ቢስቡትም”፣ ሐሳቡ ግን አስደስቶናል። ይበል ብለናል ክቡር ፕሬዚዳንት። እንደ መንግሥት ኃላፊነትዎም ባይሆን እንደ አንድ በሥልጣን ወንበር እንደተቀመጠ ኦርቶዶክሳዊ ሐሳብዎን መግለጥዎ ተገቢም፣ ጥሩም ነው።
Wednesday, December 5, 2012
በጀርመን የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካህናት “ግልጽ ደብዳቤ” አወጡ
(ደጀ ሰላም ኅዳር 23/2005 ዓ.ም፤ዲሴምበር 1/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በጀርመን አገር ኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን ኃላፊ የሆኑት ሊቀ ካህናት ዶ/ርመርዓዊ ተበጀ “ ስለ ነገዋ ቤተክርስቲያን ስንል ዕድሉ ዛሬባያመልጠንስ? “ ሲሉ “ ግልጽ ደብዳቤ” አወጡ። የእናት ቤተክርስቲያን መካፋፈል የራስ ምታት፧ የሆድቁርጠት፧ የልብ ሕመም ወዘተ ሆኖ ለ21ዓመታት “ እኽ እኽ›› እያሰኘ መኖሩበውስጡ ላለፈበት ትውልድ ሁሉ ግልጽ” መሆኑን የጠቀሱት ሊቀ ካህናቱ እርሳቸውም የበኩላቸውን ሐሳብ ለመስጠት እንደፈለጉ ጠቅሰዋል። ይህንን ደብዳቤ አሁን መጻፍ የፈለጉት ጊዜው “የተመቸ” ነው በሚል ወይም በርሳቸው አገላለጽ“ሲመች በእጅ፣ ሲፈጅ በማንካ” ለማለት ሳይሆን ከዚህ አስቀድሞ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከመሾማቸው አስቀድሞም ተመሳሳይ ሐሳብ ማቅረባቸውን ማስረጃ ጠቅሰው አብራርተዋል።
ደጀ ሰላም ይህ መሠረታዊ ጽሑፍ ለአንባብያን ቢደርስ ያለውን ጥቅም በመረዳት፣ እንዲሁም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ይህንን አስተያየት ከግምት እንደሚያስገቡት በማመን አቅርበነዋል። መልካም ንባብ።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡
የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን አባቶች የእርቀ ሰላም ውይይት ዛሬ ይጀመራል
- ከኢትዮጵያ የመጣው ልዑክ ዳላስ የገቡት ትናንት ኅዳር 26/ ዲሴምበር 4 ነው።
(ደጀ ሰላም ኅዳር 26/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 5/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት የሚደረገው ሦስተኛ ዙርየዕርቅ ድርድር ዛሬ በሰሜን አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ ከተማ ይጀመራል:: ከዛሬ ኅዳር 26 እስከ 30(ዲሴምበር 5-9/2012) የሚካሄደው ስብሰባ ውጤታማ እንዲሆን በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ምኞታቸውን እየገለጡ ሲሆን በውጪው ዓለም የሚገኙ ካህናት፣ ምዕመናን እና መንፈሳውያን ማኅበራት በሁለቱም በኩል ላሉት አባቶች ችግሩ እልባት እንዲያገኝ የተማጽኖ ፊርማ እያሰባሰቡ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል::
Tuesday, December 4, 2012
ስለ “አባቶች እርቅ” ጉዳይ ፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ
- ምእመናን ፊርማቸውን በኢንተርኔትም ሆነ በየአጥቢያቸው በወረቀት እንዲያሰባስቡ ተጠይቀዋል፤
(ደጀ ሰላም ኅዳር 25/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር4/2012/ READ THIS NEWS IN PDF):- የቤተ ክርስቲያን አባቶችን እርቀ ሰላም ለማገዝና የምዕመናን ሙሉ ድጋፍ ለማሳየት “የተማኅጽኖ ፊርማ” (ፔቲሽን) ማሰባሰብ ተጀምሯል። ምእመናን የዳር ተመልካች ሆነው ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ችግር ወደ ሌላ ችግር ስትሸጋገር መመልከት ብቻ ሳይሆን እነርሱም በፈንታቸው “የእርቁ አካል” በመሆን አባቶችን መርዳት እንደሚገባ የሁሉም እምነት ነው። ደጀ ሰላምም ለረዥም ዓመታት ስታደርግ እንደነበረው አሁንም ምእመኑ ይህንን የፊርማ ዘመቻ በመካፈል ድምጹን ማሰማት አለበት። በኢንተርኔት መፈረም ለምትፈልጉ (ይህንን በመጫን) ፊርማውን ማከናወን ይቻላል። የ “ፌስቡክ ተጠቃሚዎች” በፌስቡክ አማካይነት በቀላሉ መፈረም ያስችላችኋል።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
Friday, November 9, 2012
በጋሻው ደሳለኝና አሰግድ ሣህሉ
(ደጀ ሰላም ጥቅምት 30/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 9/2012, READ THE NEWS IN PDF)፦በሃይማኖት ጉዳይ በተነሣባቸው ጥያቄ ምእመኑ ዓይናችሁን ላፈር ያላቸው ብዙ ሰዎች ቢኖሩም በተለይ በበጋሻውና በባልንጀሮቹ ላይ ጠበቅ ያለ አጀንዳ እንደተከፈተባቸው ለረዥም ጊዜ ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል። ጉዳዩ በቅዱስነታቸው እረፍት እና በመከካሉ በመጣው ጊዜ ክፍተት ተረሣ ቢመስልም “ይደር” ተባለ እንጂ “ይዘጋ” ስላልተባለ እነሆ ርዕሳችን አድርገነዋል። በድጋሚ። ከበጋሻው እንጀምር።
በጋሻው በሊቃውንት ጉባኤ የተያዘበት ጉዳይ ካለፈው ዓመት ግንቦት የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ያደረለት የአንዳንድ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ሐዘኔታ በማትረፍ በአቋራጭ የቅ/ሲኖዶሱን ይቅርታ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ እንዳልሠራለት ታውቋል፡፡ የበጋሻው የኑፋቄ ንግግሮች የተሰራጨባቸውን ቪሲዲዎች እና መጻሕፍት መርምሮ ለምልአተ ጉባኤው የውሳኔ ሐሳብ ለማቅረብ የተቋቋመው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እና የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ኮሚቴ “ግለሰቡ ለጥያቄ ተፈልጎ ስላልተገኘ ወደፊት ቀርቦ እንዲጠየቅና በሚሰጠው መልስ ጉዳዩ እንዲታይ በሚል አስተያየት ታልፏል” በማለቱ ጉዳዩ ሳይወሰንበት ለዚህ ዓመት ድኅረ አቡነ ጳውሎስ ምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ተላልፎ የነበረ ቢኾንም ምልአተ ጉባኤው በሥራ ላይ በቆየባቸው ዐሥር ቀናት ከጥምር ኮሚቴው የቀረበለት ነገር አልነበረም፡፡
Wednesday, October 31, 2012
የቅዱስ ሲኖዶስ ጋዜጣዊ መግለጫ አንዳንድ ሐሳቦች
- READ THIS NEWS IN PDF.
- የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ “ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ እያለ ራሱን የሚጠራው” የሚለው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ተ.ቁ (2) “እኛንም አላስደሰተንም፤ እንዲስተካከል እናደርጋለን”ሲሉ ሌላው የቅዱስ ሲኖዶሱ አባል ደግሞ እንዲህ ያለው ቃል ከጋዜጠኞች በፊት ምልአተ ጉባኤው በተናበበው የመግለጫው ክፍል ላይ እንዳልነበረ ተናግረዋል፤
- “ስድስተኛውን ፓትርያርክ በመንበሩ ላይ ለማስቀመጥ እየተዘጋጀን ነው ያለነው፤ ሕጉን ካጸደቅን በኋላ ወደ ምርጫው ነው የምንገባው፤ በውጭም ያሉት ተቀብለውን፣ በውስጥም ያለነው ተቀብለናቸው ከእኛው ጋራ ምርጫውን እንዲያካሂዱ ፈቃደኞች ነን፡፡” /ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል/
- “ጳጳስ ንብረት የለውም - ጎመን የሚዘራበት፣ ሽንኵርት የሚተክልበት፤ ንብረቶቹ ምእመናን ናቸው፡፡” /ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያው ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄ የመለሱት/
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ መግለጫም በማውጣት ተጠናቀቀ
- ምልአተ ጉባኤው የዕርቀ ሰላሙንአምስት የመነጋገሪያ ነጥቦች ለይቷል፤
- ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ደቡብ እና ምዕራብ አዲስ አበባን፣ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ሰሜንና ምሥራቅ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከትን ይመራሉ፤
- “የመነኰሳት መተዳደሪያ ደንብ” ይወጣል፤ የገዳማት ተወካዮች በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉና ሪፖርት እንዲያቀርቡ ይደረጋል፤
- ለአኵስም ጽዮን ማርያም አዲስ ንቡረእድ ይሾማል፤
- ለካህናት ማሠልጠኛ፣ ለገዳማት፣ ለአብነት ት/ቤቶች (ብር 10 ሚልዮን+) እና ለሌሎችም የልማት ዕቅዶች ማስፈጸሚያ ከብር 128 ሚልዮን በላይ በጀት ተመድቧል፤
Monday, October 29, 2012
የቅ/ሲኖዶስ የቅዳሜ ውሎና ውሳኔዎች፤ ስብሰባው አልተጠናቀቀም
- READ THIS NEWS IN PDF.
- ቤተ ክህነታችን ለመጀመሪያ ጊዜ የአጭር እና የመካከለኛ ጊዜ ስትራቴጂያዊ ዕቅድያዘጋጃል፤
- ለአዳሪ እና አብነት ት/ቤቶች ማጠናከርያ 10 ሚልዮን ብር በጀት ተመድቧል፤
- የካህናት ማሠልጠኛዎች በየክልሉ ይቋቋማሉ፤ በየቋንቋዎቹ የመጽሔቶችና ጋዜጦች ኅትመት ይጀመራል፤
- የሥርዐተ ምንኵስና አፈጻጸም በየገዳማቱ ሕግ መሠረት ጠብቆ “ልማት እንዲጠናከርባቸው” ይደረጋል፤
- የጋዜጠኛ መ/ር ካህሳይ ገብረ እግዚአብሔር “ብፁዓን እነማን ናቸው?” መጽሐፍ በሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮ የውሳኔ ሐሳብ እንዲቀርብበት ተወስኗል፤
- የአቡነ ጳውሎስ “ንብረት” ተሰብስቦ ወደ ሙዝየም እንዲገባ ተወስኗል፡፡ ሐውልታቸውስ?
- ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ጸሐፊ የኾኑትን ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝን ከሥልጣነ ክህነት በማገድ የወሰዱት ርምጃ “በግል ጥላቻ የተገፋ ነው”ያለው ምልአተ ጉባኤው ካህኑም ሊቀ ጳጳሱም ለዕርቀ ሰላሙ በሚያመሩት ብፁዓን አባቶች አቀራራቢነት ተነጋግረው መፍትሔ እንዲሹ ትእዛዝ ሰጠ
- በሕገ ወጡ የዋሽግተን ዲሲ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት ላይ አስቀድሞ የተላለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ ኾኖ “የጽ/ቤቱ ባለሙሉ ሥልጣን” በሚል በአህጉረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅነት ተሹሞ የነበረው ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን በአቡነ ጳውሎስ ቀጥተኛ ትእዛዝ ከተሰጠው ሓላፊነት ተወግዶ በቃለ ዐዋዲው መሠረት አዲስ ሥራ አስኪያጅ እንዲሾም ተወስኗል
- የአቡነ መቃርዮስ የኤርትራ ጉብኝት እንደማይወክላቸው በስደት የሚገኙት አባቶች ገለጹ፤
- በድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሙስናና የሀ/ስብከቱን የአስተዳደር ችግር የሚያጠራው የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ልኡክ ነገ ወደ ስፍራው ያመራል፡፡
Saturday, October 27, 2012
የቅ/ሲኖዶስ የሰሞኑ ውሎ ሪፖርታዥ
- በግብጹ የፓትርያርክ ምርጫ ቤተ ክርስቲያናችን በአምስት ብፁዓን አባቶች ትወከላለች
- የጠ/ቤ/ክህነቱ የመዋቅር ማሻሻያ እንዲጠና ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ሰጠ::
- የውጭ ግንኙነት መምሪያ በክፍለ አህጉር ዴስኮች ይደራጃል፤ የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የሚዳስስ መጽሔት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ይጀምራል::
- “አዲስ አበባ በአራት አህጉረ ስብከት መከፈሉ አስተዳደራዊ ችግሮችን በዘላቂነት ይቀርፋል፡፡” /የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/
- ሢመተ ፓትርያርክ በምርጫ ወይስ በዕጣ? ከግብጽ ምን እንማራለን?
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 16/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶ. 26/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥቅምት 25 ቀን 2005 (እ.አ.አ ኖቬምበር 4 ቀን 2012) በሚካሄደው የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 118ኛ ፓትርያርክ ምርጫ ላይ የሚገኙ አምስት ብፁዓን አባቶችን በልኡክነት መሠየሙን የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት መመሪያ አስታወቀ፡፡
የፓትርያርክ ምርጫ ሕግን በሚመለከት ቅዱስ ሲኖዶሱ በኅዳር ወር መጨረሻ ልዩ ስብሰባ ይጠራል
አርእስተ ጉዳይ፡-
- READ THIS ARTICLE IN PDF
- የግብጹ ፓትርያርክ ምርጫ ልኡክ ዛሬ ማምሻውን ወደ ካይሮ ያመራል፤ በምርጫው ይሳተፋል፤
- የጠ/ቤ/ክህነቱ ‹የጨለማ ቡድን› የተቋማዊ ለውጡን አመራር ለመቀልበስ ያደረገው ሙከራ ከሸፈ፤
- በወኅኒ ቤት የሚገኙ መነኰሳት ቁጥር መጨመር አሳሳቢ ኾኗል፤ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብቻ በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው የተፈረደባቸው ከ70 ያላነሱ ‹መነኰሳት› ይገኛሉ፤
- ገዳማት የመነኮሳታቸውን ቁጥር ጨምሮ ዝርዝር መረጃዎቻቸውን ለአህጉረ ስብከትያሳውቃሉ፤ መነኰሳት መታወቂያ እንዲኖራቸውና ከቦታ ወደ ቦታም ያለደብዳቤ እንዳይንቀሳቀሱ ይደረጋል፤
- ከአብነት ት/ቤቶች ጋራ የተያያዘው የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ በልዩ ትኩረት ክትትል ይካሄድበታል፤ የአብነት ትምህርት መለኪያ ተበጅቶለትና በየቋንቋው መምህራን ተመድበው መምህራን በየጊዜው የሚስመርቋቸው ደቀ መዛሙርት በምደባ በየአህጉረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እንዲመደቡ ይደረጋል፤
- ምልአተ ጉባኤው በድሬዳዋ ሀ/ስብከትና በድሬዳዋ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር የሚያጣራው ልኡክ በአስቸኳይ ወደ ስፍራው እንዲያመራ አዘዘ፤ የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አባ አረጋዊ ነሞምሳ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ስም በማጥፋት የኮሚቴውን ተልእኮ የሚያደናቅፉ ሕገ ወጥ ቡድኖችን እያደራጁ ነው፤
- የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፤
Wednesday, October 24, 2012
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባጸደቃቸው በ20 አጀንዳዎች ላይ እየተወያየ ነው
- ዕርቀ ሰላሙ የምልአተ ጉባኤው ግንባር ቀደም አጀንዳ ነው::
- በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ማሻሻያ ላይ የሚሠራ ኮሚቴ ተቋቁሟል::
- ንቡረእድ ኤልያስ ኣብርሃ ከሓላፊነታቸው ሊነሡ ይችላሉ::
- በአቡነ ጳውሎስ ዕረፍት የታሸገው መንበረ ፓትርያርክ ጉዳይ ውሳኔ ያገኛል::
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 14/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 24/2012/ READ THIS
NEWS IN PDF)፦ ሰኞ
ጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም ጠዋት የተጀመረው የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ
20
የመወያያ አጀንዳዎችን በማጽደቅ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ነው፡፡
መግባባት በተመላበት መንፈስ እየተካሄደ የሚገኘውና በአጭር ቀናት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀው ይኸው የምልአተ
ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በሁለቱ ቀናት ውሎው ከአምስት በላይ አጀንዳዎች የተመለከተ መኾኑ ተጠቁሟል፡፡ የስብሰባው ምንጮች
እንደተናገሩት “ሰላምን በተመለከተ” እና “ሕገጋትን በተመለከተ” በሚል የዕርቀ ሰላሙን ሂደት፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን
ማሻሻልና የቃለ ዐዋዲው የማሻሻያ ሂደት የሚገመግምበት ኹኔታ በመነጋገሪያነት ከተቀረጹት አጀንዳዎች ዋነኞቹ ሲኾኑ
“የፓትርያርክ ምርጫ ሕግ ማውጣት” በሚል ቀጣዩን ፓትርያርክ
ስለመምረጥ የተመለከተው አጀንዳ ደግሞ በመጨረሻው ተራ ቁጥር ገደማ ከተያዙት ጉዳዮች መካከል ይገኝበታል፡፡ ከእኒህም ጋራ
“የዐቃቤ መንበሩን መተዳደርያ ሕግ ማውጣት” በሚል የተያዘ አጀንዳ
መኖሩን ለመረዳት ተችሏል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)









