Friday, October 31, 2025

በአርሲ የእልቂት ድግሱ እንደቀጠለ ነው፤ ለማን አቤት ይባል???

አርሲ በኦርቶክስት ደም ታጥባለች ፤ 

በምሥራቅ  አርሲ  ሽርካ  ወረዳ ሄላ  ዘባባ ቀበሌ  ከሚኖሩ ኦርቶዶክሳዊያን ሦስቱ መገደላቸው እና አራቱ መታገታቸው ተሰማ፡፡

በወረዳው ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ115 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውና ከ16 በላይ ዐብያተ ክርስቲያናት መዘጋታቸው ታውቋል።

ጥቅምት ፲፱/፳፻፲፰ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ 

ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በደረሰው መረጃ ጥቅምት  17 ቀን 2018  ዓ.ም ከለሊቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ሄላ ዘባባ ቀበሌ አርሴማ አጥቢያ የሚኖሩ ምእመናን በታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሦስቱ መገደላቸው እና አራቱ ደግሞ መታገታቸው ተገልጿል።

ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ የአንዱ ሟች አባትና ወንድም መታገታቸው በመረጃው የተገለጸ ሲሆን ታፍነው የተወሰዱት ምእመናን ስለሚገኙበት  ሁኔታ አይታወቅም ተብሏል፡፡

በመረጃው እንደተነገረው የሞቱት ሦስቱ ኦርቶዶክሳውያን በትላንትናው ዕለት ጥቅምት 18  ቀን  2018  ዓ.ም  ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታት ማለትም ከ2016 ዓ.ም መስከረም 02 ጀምሮ  እስከ  2017 ዓ.ም  ድረስ ያለማቋረጥ በወረዳው ከ115 በላይ ምእመናን የተገደሉ  ሲሆን  27  ኦርቶዶክሳዉያን  ደግሞ አሁንም  ድረስ  ታግተው  ያሉበት  እንደማይታወቅ  ነዋሪዎቹ  ለጣቢያችን  ገልጸዋል።

በግድያ  ያላበቃው  መከራና  ስቃይ  በሽርካ  ወረዳ  ብቻ  በዘጠኝ  ቀበሌዎች  በሺዎች የሚቆጠሩ  ኦርቶዶክሳዉያን  መፈናቀላቸውንም በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

Thursday, October 30, 2025

አትነሳም ወይ፤ ኦርቶዶክሳዊ አይደልህም ወይ?

የመጣብንን የአላውያን ጦር በመስቀሉ እንሰብራለን፤
"አትነሳም ወይ? " 

አንተ የተዋሕዶ ልጅ ሆይ
ማንቀላፋቱ አይበቃም ሆይ!
መዘናጋቱስ አይበቃም  ወይ
አይገድህም ወይ!
አትነሳም ወይ
እያለቀ ያለው ወገንህ አይደለም ወይ!

ወገን ሲታረድ እንደ በግ ጠቦት
ደሙ ሲፈስ እንደ ውኃ ጅረት
አየነው አየነው እረፉ ባይ ጠፋ
ሞት ታውጆብን ከምድር እንድንጠፋ

       አየገባህም ወይ
        አትነሳም ወይ
       በግፍ የሚገደለው ሕዝብህ አይደለም ወይ

       መንግሥት አለ ብለህ እንዳትጃጃል
አባት አለ ብለህ እንዳትጃጃል
እግዚአብሔርን ይዘህ ተነስ ለ ትግል
ወደ ፊት ሩጥ እንጂ ወደ ኋላ አትበል

           አይበቃም ወይ
            አያሳዝንም ወይ
            አትነሳም ወይ
      በግፍ የሚታረደው
       ሕዝብህ አይደለም ወይ
ወገን በሃይማኖቱ በግፍ ሲገደል
ሬሳው እንኳ  ሳይቀር በእሳት ሲቃጠል
አያሳዝንም ወይ እየሆነ ያለው
ተነሳ ወጣት ሆይ  መፍትሔው 
መነሳት ነው

ሌላው አጀንዳ በራሱ ድምፃችንን የሚያጎላ ሳይሆን ድምፅ የሚቀንስ ነው!

የሚያሳዝነኝ ዛሬ መሞታችን ብቻ ሳይሆን ሞታችን እንዳይቀጥል አንድ አይነት ድምፅ ማውጣት አለመቻላችን ነው ሌሎች እንኳን ሲሞቱ ይቅርና ሲታመሙ እንኳን የሚያወጡት ድምፅ አንድ አይነት ነው እኛ በሞታችን ሳይቀር ዥንጉርጉር ነን ድምፃችንን አንድ አድርገን መኖር ይፈቀድልን ለምን እንገደላለን ከሚል ጩኸት ይልቅ ሞታችንን እንከፋፈልበታለን እነ እገሌ አብረውን አልቅሰዋል እነ እገሌ በደንብ አልጮሁም የእነ እገሌ አለመጮህ ወዘተ እያልን ድምፅ መቀነሳችን ልዩነት መፍጠራችን ወደ ፊት እንኳን ለገዳዮቻችን አንድ ሆነን እንደማንቆም እየነገርናቸው ነው😭😭 ኦርቶዶክስ ናቸው ተብለን እየተገደልን ሞታችን ውስጥ ብዙ ነገር መሥራታችን ሞታችንን በልዩ ልዩ ምንዛሬ ማየታችን እጅግ ያሳዝናል መግደል ባይደክማችሁ እንኳን መሞት ደክሞናል ይበቃል እንበል የተከፋፈለ ሐሳብና የግል አመለካከት ከመሰንዘር ወጥተን ሞታችንን እናስቁም ገዳዮቻችንን እናውግዝ ዝምተኞችን እንቀስቅስ ተናጋሪዎች ንግግራቸው ትክክለኛ ሐሳብ ላይ ያነጣጠረ እንዲሆን እንምከር ሞታችንን ለልዩ ልዩ ፍጆታ የሚጎትቱትን በወንድምና እህት በልጅ በእናትና አባት ሞት ገብያ አትክፈቱ እንበል ያ ካልሆነ በስተቀር ለጊዜው ተነቃቅፈን ተወጋግዘንና ተነቋቁረን ተመልሰን ደግሞ ዝም እንላለን ሞቱም መቀጠሉ አይቀርምና አንድ ሆነን እንቁም ሞታችን ውስጥ በመከራችን የምድጃ እሳት ላይ የግል ነገራችንን ለማብሰል የግል ድስት አንጣድ!😭

በምሥራቅ አርሲ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በሚፈጸመው መንግሥት መር ኢስላማዊ ጅሃድ

ብፁዕ አቡነ ያሬድ የምሥራቅ አርሲ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ

በምሥራቅ አርሲ ኦርቶዶክሳውያን ላይ  በሚፈጸመው  መንግሥት መር ኢስላማዊ ጅሃድ የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ክፍል ሠራተኞች እልቂቱ ወደ ተፈጸመበት ወረዳ ደውለው ከአንድ ኦርቶዶክሳዊ መረጃ ይቀበላሉ።መረጃ ሰጪው ኦርቶዶክሳውያን ያሉበት አሳሳቢ መሆኑንና የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አባ ያሬድም ለ ጉዳዩ ትኩረት አለመስጠታቸውን ይናገራሉ።ማኅበሩም ድምፁን በሚዲያው ያወጠዋል።ይኽን የሰሙት አቡን ያሬድ ቪድዮው ከሚዲያው  እንዲወርድ በማስፈራሪያ ጭምር አዘዙ። በ ሞቱ ኦርቶዶክሳውያን ሥርዐተ ቀብር ላይ የሚገኙ የሀገረ ሰብከቱ ሠራተኞች ላይም ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደርግም ቀጭን ትእዛዝ ወጥቷል።ይኽ ብቻ አይደለም ከዚህን በፊት "በሀገረ ስብከትዎ ስለሚሞቱት ኦርቶዶክሳውያን ለምን ዝምታን መረጡ "ሲባሉ "ኦርቶዶክሳውያን መሞታቸውን እርግጠኛ አይደለሁም" እስከ ማለት የደፈሩ ሰው ናቸው።እንግዲህ ቤተ ክርስቲያን በእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እጅ ላይ ነው የወደቀችው።#EOTC  የገዳያችንን የብልጽግና ገጽታ የሚገነባ ስለ ኮሪደር ልማት ካልሆነ በቀር ሙሉ በሙሉ ስለ ኦርቶዶክሳውያን እልቂት አይዘግብም።ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የአዳነች አቤቤ የቅርብ ሰው የሆኑት አባ ሄኖክsilent mood ላይ ቢያስገቡትም አልፎ አልፎም ቢሆን መከራችንን ይዘግባል።#Mktv  ገዳዮቻችንን  በስም እንዳይጠሩአቸው  "ያልታወቁ ኀይሎች" እያሉ እንዲዘግቡ  የሚያደርጉት የ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ  እሾኾች ናቸው።

Tuesday, October 28, 2025

ሁለተኛው አሳዛኝ የእልቂት ዜና





በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ። 

ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም [ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ] 

በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን መገዳላቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል። 

በደረሰን መረጃ መሠረት በቀበሌው የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ  ከተኙበት ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን ስድስቱ ከመገደላቸው ከአንድ ቀን በፈት ቀድመው ታፍነው ተወስደው ነበር ተብሏል። 

የተገደሉት ምእመናን የዕድሜ ክልላቸው ከ2 ዓመት ጀምሮ እስከ 76 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት መረጃው ይገልጻል። 

በተጨማሪም ሁለት ሰዎች በጥቃቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ለተሻለ ሕክምና ወደ አቦምሳ  ከተማ  ሪፈር  መሄዳቸውን በመረጃው ተያይዞ ተነግሯል፡፡ 

ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በቀበሌው ውስጥ የሚኖሩ 8 ኦርቶዶክሳውያን ሌሊት ላይ ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውን በደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል።  

የተነሳው አወዛጋቢው ነገር ምንድነው? መፍትሔውስ ምን ሊሆን ይችላል ከኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ

የምንሰውማ ጉድ ምንድነው? 

አዲስ የተገዛው የ8 ሚሊዮን የቅድስ ተ/ኃይማኖት ቤ/ክ አሜሪካ
በቨርጂኒያ ቅዱስ ተክለኃይማኖት ቤተክርስቲያን አጥቢያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከበድ ያለ ጭቅጭቅ እና ንትርክ የሚመስል ነገር ተነስቷል ፤ ከብዙ የብሎጎች እና የቴሌግራም ግሩፖች እንደተረዳነው፤ ይሄ ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረት ከአሥራ ሁለት ወይም ሦስት አመት በላይ በአገልግሎት እንደቆየ ይነገራል ፤ ነገር ግን ቦታው ከተገዛ ቅርብ ጊዜ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ ጣልቃ ገብነት በተለይ ከባሕርዳር ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ አብርሃም በቀጥታ ጣልቃ በመግባት በቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ እና በቤተክርስቲያኑ ምዕመናን ጋር የተነሳውን አለመግባባት ለማስማማት ሳይሆን ያልተፈጠረውን ታሪኩን በማጣመም ሌላ እንደሆነ አድርገው በማቅረብ በምዕመናኑ እና በቤተክስቲያኑ ምዕመናን መካከል ከፍተኛ አምባጓሮ አይነት መነሳቱን እና ፖሊስ ተጠርቶ እንደነበር የታሰሩ ምዕመናን እንዳሉ ግን የድረሰን መረጃ ባይኖርም፤ ፖሊሶች ግን በቦታው ላይ መጥተው ወደ ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ገብተው እንደነበር መረጃዎች ደርሰውናል፤ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ለመረዳት እንደቻልነው፤ የሚከተለውን መረጃ ለዚህ ሚዲያ ቤተሰቦች ለማድረስ ፤ ነው፤ 
በቀጣይነት ያሉትን እየተከታተልን እንዘግባለን፤ በዚህ አጥቢያ ያሉትንም ምዕመናን መረጃውን ብታደርሱን በሚዲያችን ለማስተናገድ እንደምንችል ከወዲሁ ለማስታወስ እንድወዳለን፤ 

📝የሚሰማው ምንድን ነው ? 

👉በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው  በቅርቡ ስምንት ሚሊዮን ዶላር (8Million $) ወጥቶበት  የተገዛው የምሥራቀ ጸሐይ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን  ቨርጅኒያ በመሀከላቸው ምንድን ነው የተፈጠረው ?

"ደብር ወገዳም"

ደብር ወገዳም 

 መልካም ቃላት የሚበዙት ክፉት ሲበዛ ነው። ሰው መልካም ሥራ ሲርቀው ክፋቱን ሊደብቅ ሲል መልካም ስም ማዕረግ ይደረድራል። መልካም ቃላት ጋጋታ ይጠቀማል። የዘንድሮን የመንፈስ እርቃንነት መቋቋም ያልቻለ ስው ግማሹ በስም ግማሹ ባሸበረቀ ካባና ቀሚስ እንደ ሞዴል በሚቀያየር አልባሳት ያጌጣል። 

ቀደም ባለው ጊዜ የቆየው ባሕል ሊቃውንት ብቻ የሚጠሩበት ሥም አለ። እንደየ ትምህርታቸው እንደ ደብሩ ትልቅነት የአለቃ ስም ይሰጣል። ዛሬ ግን ስም ያልወሰደ የለም። የማይንቆለጳጰስ የለም። 
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባሕርዳር እና የምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስበከት ሊቀ ጳጳስ

ሰላም በሌለበት ደብር የመልአከ ሰላም አበዛዙ፣ የተማረው የተመገበው ሳይኖር የመጋቤ ሐዶስና ብሉይ አበዛዙ ግርም ይላል። 

መልአከ ከዋክብት፣ መልአከ ጨረቃ፣ መምህረ መምህራን፣ ርዕሰ ርዑሳን፣ ርዕሰ ባሕታውያን፣ ቆሞስ ሞቆሳት …..ሊቀ ሐዋርያት፣ መጋቤ ሰማእታት… ምኑ ቅጡ። አምፓል ለቀጠለ ኹሉ መልአከ ብርሃን። 

አቡነ አብርሃም ደግሞ ሰሞኑን አንዲት ስም አስተዋውቀዋል። ደብር ወገዳም የምትል። የዶላር ስም ናት መሰለኝ። መቼስ ለብር ቤተ ክርስቲያን እንዲኽ ያለ ስም አይወጣም። 

Wednesday, August 19, 2015

ልብ ያለው ልብ ይበል


ሰሞኑን በአንድ የፌስ ቡክ ግድግዳ ላይ ተለጥፎ ያየነው ነገር ዓይናችንን ስቦት ትንሽ ነበብ ስናደርገው እንዲህ ይላልኢየሱስ ሳያቆስል የማረካቸውይላል ዝርዝሩን ለመመልከት ጓጓን እና ወደ ውስጥ ገባ ብለን ማንበብ ቀጠልን እንዲህ ይላል
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብርቅዬ ልጆች የወንጌል ዘማቾች ሰባኪያን ባንድ ዝርዝር ዘማርያን በሌላ ዝርዝር ተዘርዝረው ተመለከትን እንደእውነቱ ከሆነ ሰውየው ጥሩ መረጃዎችን ለኦርቶዶክሳውያኑ የሰጠን ይመስለናል ምክንያቱም ሰውየው ሲዘረዝር ዋናዋናዎቹን ብቻ ነበር የምናውቃቸውብርቅዬዎቹንማለታችን እንደሆነ እንዲሰመርልን እንፈልጋለን ነገር ግን አብዛኛው ኦርቶዶክሳዊ ጋሻ ጃግሬዎቹን ወይንም ተከታዮቹን እንደ ግንባረ ቀደሞቹ ለመሆን የሚጣጣሩን እታች ያሉትን እስከ ዛሬ አናውቃቸውም ነበር ነገር ግን ሰፋ የለ መረጃ ስለሰጠን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን እያልን እነዚህን ዝርዝሮች ጎላ አድርገን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ምዕመናን ለማሳወቅ ወደድን በዚህም ይህንን ትንሽ ክታብ ጨምረን ለማቅረብ ተዘጋጀን እነሆ ጋበዝናችሁ ዝርዝሩን ይመልከቱን

Thursday, July 16, 2015

የስልጤ – ቂልጦ ቅድስት ማርያም አስተዳደር እና ምእመናን: ‹‹የድረሱልን ጥሪ››ው በድረ ገጽ መሰራጨቱ ‹‹ከፍላጎታችን ውጭ ነው፤ አውግዘነዋል›› አሉ


  • የሰበካ ጉባኤው እና የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው 6 አባላት የሐሰት ወሬ ማሰራጨት በሚል ተከሠዋል
  • ከ11-14 ቀናት እስር በኋላ በዋስ ቢወጡም ሊቀ መንበሩ የማርያም ወርቅ ተሻገር እንደታሰረ ነው
  • ‹‹ችግሩን ከሥሩ ለማድረቅ›› በቤተ ክህነት እና በመንግሥት አካላት ‹‹ጥረት እየተደረገ ነው››
  • የሰላም ጉባኤ በማካሔድ የቤተ ክርስቲያኑን ቅዳሴ ቤት ለማክበር መዘጋጀቱን ሀ/ስብከቱ አስታውቋል
*          *          *Silte01
  • ‹‹ድረሱልኝ ጥሪ››ው፣ የጥንቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሏል መባሉ ያልተረጋገጠ ነው
  • የስልጤ ዞን የምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ፤ ዜጎች በመግባባት እና በፍቅር የሚኖሩባት ናት፤ በጽሑፉ ሊቢያን እንደ ንጽጽር መጠቀማችን ተገቢ አልነበረም፤
  • የወረዳ፣ የዞን እና የክልል አመራሮች ከሀገረ ስብከቱ፣ ከወረዳ ቤተ ክህነቱ፣ ከሃይማኖት ፎረም እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ችግሩን ከሥሩ ለማድረቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው፤
  • ‹‹ድረሱልኝ ጥሪ›› ከደብሩ ምእመናን፣ ከሰበካ ጉባኤው እና ከሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው ዓላማ እና ፍላጎት ውጭ ሐራ ዘተዋሕዶ በተባለው ድረ ገጽ በመለቀቁ ድርጊቱን አውግዘነዋል፡፡

Tuesday, June 16, 2015

ሰበር ዜና - ከእዚህ በፊት በሰጣቸው ትምህርቶቹ በርካታ ጥያቄዎች የተነሱበት በጋሻው ደሳለኝ ሉንድ፣ስዊድን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሌላ ትልቅ ውዝግብ ፈጠረ።።''በጋሻው ስዊድን የገባው በአውሮፓ የምትገኘውን፣በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ አባቶች የምትመራውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለማወክ ያለመ ተልኮ ይዞ ነው'' አውሮፓ የሚኖሩ አባቶች እና ምዕመናን።(የደብዳቤ እና የፎቶ ቅጅዎች ተያይዘዋል)



           አቶ በጋሻው ዛሬም የውዝግብ ማዕከል ሆኗል
 


  • ወደ ሉንድ፣ስዊድን የገባበት ሰነድ በራሱ አወዛጋቢ ሆኗል፣
  • ሉንድ፣ስዊድን የሚገኘው ቴዎሎጂ ዩንቨርስቲ የግለሰቡን ወደ ስዊድን መምጣት እንደሚያውቅ ተደርጎ የተገለፀውን ደብዳቤ ሐሰት መሆኑ እየተነገረ ነው፣
  • ዩንቨርስቲው ስለጉዳዩ እንደማያውቅ ለማወቅ ተችሏል፣
  • በአውሮፓ የሚኖሩ በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ አባቶች ስር የሚገኙ አጥብያ አብያተ ክርስቲያናት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የበጋሻውን አወዛጋቢ የሀገር ቤት ታሪክ የሚያውቁ አባቶች እና ምዕመናን በብርቱ እያስጠነቀቁ ነው፣
  •  ''ከሀገር ቤት አቡነ ማትያስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ እና ቋሚ ሲኖዶስ እንዳስተምራችሁ ፍቃድ ሰጥተውኛል'' በጋሻው ለሉንድ፣ስዊድን ምዕመናን የነገራቸው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በበርካታ የቤተክርስቲያኒቱ ጉባኤያት ላይ ሁከት በመፍጠር፣በአደባባይ የቤተ ክርስቲያኒቱን አባቶች በማጥላላት እና በአስተማራቸው ትምህርቶች አፅራረ ቤተ ክርስቲያን ይዘት ከሐዋሳ እስከ ጎንደር ከአዲስ አበባ እስከ ሐረር ባሉ አያሌ አጥብያ አብያተ ክርስቲያናት በሚገኙ  አባቶች ከመድረክ ላይ እንዳያስተምር በሀገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት፣የደብር አለቆች እና ምዕመናን የታገደው በጋሻው ደሳለኝ ስዊድን፣ሉንድ አንድ ሰንበት በተጭበረበረ መንገድ መድረክ በግድ ነጥቆ ማስተማሩ ምእመናንን በእጅጉ አስቆጥቷል።

በጋሻው መድረኩን በጉልበት ከነጠቀ በኃላ መድረክ ላይ ቆሞ 

ሉንድ፣ስዊድን ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሁለት ሳምንታት በፊት የግንቦት 21 የደብረ ምጥማቅ የቅድስት ድንግል ማርያምን በዓል ለማክበር ዝግጅት ይጀምራሉ።በእዚህ መሰረት ከስዊድን እና ኖርዌይ የሚገኙ አባቶች በአቡነ ኤልያስ ተመድበው ለአገልግሎት ይሄዳሉ።ጉባኤው ሲካሄድ ቀደም ብሎ በጋሻው በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ በማገልገል ላይ በሚገኘው ዲ/ን ያሬድ አማካይነት የግብዣ ደብዳቤ ተልኮለት ስዊድን ገብቶ ነበር።ሆኖም ግን ምእመኑን በመፍራት በዕለቱ በቦታው ዝር ሳይል ይቆያል።

በሳምንቱ ግን በቦታው የዶክትሬት ዲግሪውን በመስራት ላይ በሚገኘው እና ያለውን ትርፍ ጊዜ በሙሉ በቤተ ክርስቲያኒቱን በነፃ በቅዳሴ፣በማስተማር እና ምዕመናንን በመምከር የሚያገለግለው ቀሲስ መንግሥቱ በቦታው የዕለቱን ትምህርት ለመስጠት ሲዘጋጅ ከበጋሻው በኩል ትዕቢት በተሞላበት እና የቤተ ክርስቲያንን ስርዓት ፈፅሞ በተፃረረ መልክ ካህኑን እላፊ ንግግሮችን ከመናገሩም በላይ መርሃ ግብሩን የሚመራው እና ቀደም ብሎ በጋሻውን ለማስመጣት ደብዳቤዎችን መላኩ የተነገረለት ዲ/ን ያሬድ የድምፅ መናገርያውን ከካህኑ ነጥቆ ለበጋሻው ሲሰጥ እና ቀሲስ መንግስቱ እና ምዕመናን ቤተ ክርስቲያኑን ጥለው እያለቀሱ ሲወጡ ተስተውሏል።ይህ ጉዳይ የበርካታ ምእመናንን ልብ ያሳዘነ ከመሆኑም በላይ ጉዳዩ በእዚህ ሳይቆም  ለቅዳሜ ሰኔ 6/2007 ዓም አሁንም በድጋሚ ምእመናንን የሚጠራ ፖስተር ተዘጋጅቶ እንዲሰራጭ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።

Sunday, June 14, 2015

“ሃይማኖታዊ ግጭት ለማስነሣት ተንቀሳቅሳችኋል” የተባሉ የሰበካ ጉባኤ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ





  •   ፖሊስ10 ቀንየምርመራጊዜጠይቆባቸዋል

    
በደቡብ ክልል የስልጤ ዞን ምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ፣ የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤና የደብሩ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላት “ሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጋጨት ተንቀሳቅሳችኋልበሚል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

በቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላት በዋና ሥራ አስኪያጅ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ጥያቄ እየታሰሩ ነው

  •   በጥያቄአቸው፣ በአስተዳደር ይኹን በልማት ሥራ ምንም ችግር የለም ብለዋል በሌለ ልማት!
  • ምእመናኑንም ‹‹ምንም ዓይነት ድርሻ የሌላቸውና ማንነታቸው የማይታወቅ›› ሲሉ ገልጸዋቸዋል
  • የታሰሩት ምእመናን በፖሊስ ጣቢያ ‹‹ማዕተባችኹን በጥሱ መስቀላችኹን አውልቁ›› ተብለዋል
  • የቀድሞው የደብሩ አለቃ ዘካርያስ ሓዲስና ኃይሌ ኣብርሃ ከውዝግቡ ለማትረፍ እያሰሉ ነው
bole bulbula medየቤተ ክርስቲያን ይዞታ ከቤተ ክርስቲያን አቋም ጋር በሚስማማ እና ሀብቷን በሚያስጠብቅ አኳኋን እንዲለማ በመጠየቅ በቅንጅት የተንቀሳቀሱ የቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ደብር ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላትበሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጥያቄ እየታሰሩ እና ለእንግልት እየተዳረጉ ነው፡፡
ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ለቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በክፍለ ከተማው ለወረዳ 12 ፖሊስ ጣቢያ በጻፉት ደብዳቤ፣ በምእመናኑ እና የሰንበት ት/ቤት አባላቱ ተበይዶ የታሸገው የደብሩ ቢሮዎች በፖሊስ ርምጃ እንዲከፈቱ ምእመናኑም በወንጀል ድርጊት እንዲጠየቁ አመልክተዋል፡፡
ጥያቄአቸውን ተከትሎ ባለፉት ኹለት ቀናት ከኻያ የማያንሱ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላት መታሰራቸው ታውቋል፡፡ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ ታስረው ከተለቀቁት ውጭ እስከ አኹን በእስር የሚገኙ ስምንት ምእመናን (አራት ምእመናን እና አራት የሰንበት ት/ቤት አባላት) በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተገልጧል፡፡ ከታሳሪዎቹ መካከል ደብሩን በስብከተ ወንጌል ሲያገልግሉ ቆይተው በጡረታ የተገለሉ የ70 ዓመት ሕመምተኛ አዛውንት ይገኙበታል፡፡ ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሲገቡ በአዛዡ ‹‹ማዕተባችኹን በጥሱ፤ መስቀላችኹን አውልቁ›› መባላቸውን ከእስር የተፈቱት ምእመናን ተናግረዋል፡፡
በደብሩ የልማት እና የመካነ መቃብር ይዞታዎች የሚገኙ የንግድ ቦታዎች እና ሱቆች ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ግለሰቦችን በሚጠቅም አኳኋን በከፍተኛ ዋጋ እየተከራዩ ባለበት ኹኔታ የደብሩ ገቢ እና ልማት እየተዳከመ መምጣቱ በምእመናን እየተገለጸ እና ይኸውም በጠቅላይ ቤተ ክህነት የአስተዳደር ጉባኤ በተሠየመ አጥኚ ቡድን ተረጋግጦ እርምት እንዲደረግ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ቢሰጥም፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ በደብሩ የአስተዳደር ይኹን የልማት ሥራዎች ምንም ዐይነት ችግር እንደሌለ ነው በደብዳቤአቸው የጠቀሱት፡፡

በአ/አበባ ሀ/ስብከት: ከብር 113 ሚልዮን በላይ የፈሰስ ዕዳ እንዲሰረዝ መጠየቁ እርምት ያስፈልገዋል፤ ‹‹የአየር ባየር የዘረፋ ስልቱን ለመሸፈን የተቀመረ ነው›› /ሠራተኞች/

Lique Tebebit Elias Techane
የአጥቢያዎች ፈሰስ፣ የሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪዎች እና የአበል ክፍያዎች ቀበኛ የጥንቆላ እስረኛሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ: ከግሮሰሪ(አ.አ) እስከ ባለአምስት ፎቅ ሕንፃ(መቐለ) ባለቤት
  • የቁጥጥር እና የፋይናንስ ሓላፊዎች የትምህርት ዝግጅት እና ልምድ ዝቅተኛ ነው
  • በቆጠራዎች የሚዘረፈው የሙዳይ ምጽዋት ገንዘብ ቢሯቸው ድረስ ይመጣላቸዋል
  • የቤተሰብ ጉባኤ በሚመስለው የቁጥጥር ክፍሉ ስብሰባ የዘረፋ ስልቶች ይቀመራሉ
  • ትኩረቱን ወደ ከፍተኛ ግዥዎችና ፕሮጀክቶች ለማዞር እስከ መምከር ተደርሷል
  • እነኃይሌ ኣብርሃ እንዳሉት፣ ‹‹ንቡረ እድ ኤልያስን የተማመነ ምን ይኾናል!››
/ከሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች/
‹‹ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ውጪ ታሳድራለች›› እንዲሉ በአኹኑ ወቅት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሒሳብ እና በጀት እንዲኹም በቁጥጥር አገልግሎት ዋና ክፍሎች በኩል ከሕግ፣ ከመርሕ እና ከሥነ አመክንዮ ውጭ ብዙ ሕገ ወጥ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ፡- በአድባራት የደመወዝ እና የአበል ክፍያ ጭማሪ፤ በክብረ በዓል እና በወርኃዊ የአብያተ ክርስቲያን የሙዳይ ምጽዋት ቆጠራ እና የንብረት ሽያጭ ጨረታ ወቅት የሚሠሩ ሙስናዎች ልክ እንደ ሕጋዊ መብት በግልጽ እተፈጸሙ ይገኛሉ፡፡ ለዛሬው፣ ለቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎት ወሳኝ ስለኾነው የፈሰስ(ፐርሰንት) ጉዳይ እንመልከት፡፡