- የሰበካ ጉባኤው እና የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው 6 አባላት የሐሰት ወሬ ማሰራጨት በሚል ተከሠዋል
- ከ11-14 ቀናት እስር በኋላ በዋስ ቢወጡም ሊቀ መንበሩ የማርያም ወርቅ ተሻገር እንደታሰረ ነው
- ‹‹ችግሩን ከሥሩ ለማድረቅ›› በቤተ ክህነት እና በመንግሥት አካላት ‹‹ጥረት እየተደረገ ነው››
- የሰላም ጉባኤ በማካሔድ የቤተ ክርስቲያኑን ቅዳሴ ቤት ለማክበር መዘጋጀቱን ሀ/ስብከቱ አስታውቋል
- በ‹‹ድረሱልኝ ጥሪ››ው፣ የጥንቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተቃጥሏል መባሉ ያልተረጋገጠ ነው
- የስልጤ ዞን የምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ፤ ዜጎች በመግባባት እና በፍቅር የሚኖሩባት ናት፤ በጽሑፉ ሊቢያን እንደ ንጽጽር መጠቀማችን ተገቢ አልነበረም፤
- የወረዳ፣ የዞን እና የክልል አመራሮች ከሀገረ ስብከቱ፣ ከወረዳ ቤተ ክህነቱ፣ ከሃይማኖት ፎረም እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ችግሩን ከሥሩ ለማድረቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው፤
- የ‹‹ድረሱልኝ ጥሪ››ው፤ ከደብሩ ምእመናን፣ ከሰበካ ጉባኤው እና ከሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው ዓላማ እና ፍላጎት ውጭ ሐራ ዘተዋሕዶ በተባለው ድረ ገጽ በመለቀቁ ድርጊቱን አውግዘነዋል፡፡
ከቤተ ክህነቱ ምንጮች የተገኘው የምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የስልጤ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ‹‹ማስተካከያ››ደብዳቤ
Source: https://haratewahido.wordpress.comየተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
No comments:
Post a Comment