- ፖሊስየ10 ቀንየምርመራጊዜጠይቆባቸዋል
በደቡብ ክልል የስልጤ ዞን ምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ፣ የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤና የደብሩ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላት “ሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጋጨት ተንቀሳቅሳችኋል”በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡
የወረዳው ፖሊስ፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ እና በዚኽ ሳምንት ሰኞ ስድስት የሰበካ ጉባኤውንና የቤተ ክርስቲያኒቱንየሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላት በቁጥጥር ሥር በማዋል በቂልጦ ወረዳ ፍርድ ቤት አቅርቧቸዋል፡፡ ግለሰቦቹ “የድረሱልኝ ጥሪ” በሚል “ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጭ ጽሑፍ ጽፈው በፌስቡክ አሰራጭተዋል”ሲል ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ግለሰቦቹ “የድረሱልኝ ጥሪ” በሚል ደብዳቤ መጻፋቸውን ቢያምኑምበፌስቡክ አለመልቀቃቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር በዋሉት ግለሰቦች ላይ የማጣራው ነገርአለ በሚል የ21 ቀን የምርመራ ጊዜ የጠየቀባቸው ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የ10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዶለታል፡፡
የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ሓላፊ አቶ ቶፊቅ ከድር፣ ስለ ጉዳዩ በስልክ ጠይቀናቸው፤ “በሕግ የተያዘ ጉዳይ በመሆኑአስተያየት ለመስጠት አልችልም” ብለዋል፡፡
በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኙት የቂልጦ ቅድስት ማርያም ሰበካ ጉባኤ እና ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላት÷ ሊቀመንበሩ መ/ር የማርያም ወርቅ ተሻገር፣ መ/ር ሀብታሙ ተካ፣ አቶ ሙሉጌታ አራጋው፣ ወ/ሪት ንጋት ለማ፣ አቶማስረሻ ሰይፈ እና አቶ ማሩ ለማ ሲሆኑ በወረዳው የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት፣ የፖሊስ፣ የጤና እናየግብርና ጽ/ቤቶች እንዲሁም የባንክ ቅርንጫፍ ሠራተኞች ናቸው፡፡
‹‹የድረሱልኝ ጥሪ›› በሚል ርእስ የተሰራጨውና የደብሩን የሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ማኅተም የያዘው ጽሑፍ÷ በስልጤዞን በምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመናን፣ በሃይማኖታዊማንነታቸው ላይ ባለሥልጣናት ይፈጽሙብናል ባሏቸው ግፎች መማረራቸውን፣ የአምልኮ ነጻነታቸው እና ሠርተውየመኖር ዋስትናቸውም አደጋ ላይ መውደቁን ያስረዳል፡፡
ኢትዮጵያ የሃይማኖት እኩልነት የተረጋገጠባት መሆኗን በፅሁፋቸው የጠቆሙት ምእመናኑ፣ ስለሚፈጸምባቸውግፍና ሥቃይ ለወረዳው የፖሊስ እና የሕግ አካላት በየደረጃው ቢያመለክቱም የአስተዳደሩ መዋቅር እና አሠራርያልተገባ “ሕጋዊ ሽፋን” በመስጠቱ የጥቃቱ ስልት ዐይነት እየጠነከረ መጣ እንጂ መፍትሔ አለማግኘታቸውንተናግረዋል፡፡
በየመኖሪያ አካባቢያችንና በሥራ ቦታዎች እየደረሰብን ነው ያሉት እስር፣ እንግልት፣ ዛቻ፣ እንዲሁም በመ/ቤትከደረጃ ዝቅ መደረግና መታገድ እና መባረር እየተጠናከረ መምጣቱን የገለጹት ምእምኑ፣ ድርጊቱ የተባባሰው፤ የቤተክርስቲያን መሥሪያ ቦታ ተረክበው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የመሠረት ድንጋይ ካስቀመጡበት ከጥቅምት 24 ቀን2007 ወዲህ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ለመንግሥት እና ለቤተ ክህነት አካላት አቤቱታቸውን ያሰሙበት “የድረሱልኝ ጥሪ” የሚለው ይኸው ጽሑፍ፣የሀገረ ስብከቱን ፈቃድ በመጠየቅ የተዘጋጀ መሆኑን የገለፁት ምእመናኑ በአንዳንድ ባለሥልጣናት የሚደርስባቸውንሥቃይ በመዘርዘር መፍትሔ የጠየቁበት እንደሆነ ጠቁመው፤ “ታምኑበታላችኹ ወይስ አታምኑበትም” እየተባለሃይማኖታዊ ግጭት እንደቀሰቀስንና የወረዳውን ስም እንዳጠፋን ተደርገን መታየታችን አሳዝኖናል ሲሉ ርምጃውንተቃውመዋል፡፡
ቀድሞ ያስቀድሱበትና የመካነ መቃብር አገልግሎት ያገኙበት የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከ20 ዓመትበፊት መቃጠሉን ያስታወሱት ምእመናኑ፣ በምትኩ የሚያሠሩት የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኒቱ መቃኞ በመጪው ሰኔ 21ቀን የሚመረቅ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የሃዲያ እና ስልጤ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች እንዲሁም የሰበካው ቤተክርስቲያን ምእመናን ከወረዳው አስተዳደር ጋር በጉዳዩ ላይ እየተነጋገሩበት እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በሌላበኩል ‹‹የድረሱልኝ ጥሪ›› በሚል በፌስቡክ ተሰራጭቷል ለተባለው ጽሑፍ የታሰሩት የሰበካ ጉባኤ አባላትማስተባበያ እንዲሰጡና መሳሳታቸውን አምነው ይቅርታ እንዲጠይቁ በማግባባት ከእስር ለማስፈታት ጥረትእየተደረገ መኾኑንም ምንጮቹ አክለው ገልፀዋል፡፡
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
No comments:
Post a Comment