(በምስራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ አካባቢዎች የ24 ሰዓት ሁኔታ)
ቀን፡ ጥቅምት 26/ 2017 ዓ.ም
ቀጠና፡ ምስራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች (ኪረሙ፣ አቤ ደንጎሮ፣ ጊዳ አያና ወረዳዎች)
1. የሁኔታዎች ማሳያ
በምስራቅ ወለጋ እና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች አወሳሳኝ ወረዳዎች ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓታት ከፍተኛ የፀጥታ መዛባት፣ የኃይል እርምጃ፣ የድሮን ቅኝቶች እና የሲቪል ህዝብ መጠነ-ሰፊ መፈናቀል ተከሰቷል። ኪረሙ፣ አቤ ደንጎሮ እና ጊዳ አያና ወረዳዎች የትግል እና የጥቃት አውድማ ሆነው የዋሉ ሲሆን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በጫካዎች እና በበረሃዎች ውስጥ ያለ መጠሊያና እርዳታ ይገኛሉ።
2. የየወረዳዎቹ የ24 ሰዓት ዝርዝር ሪፖርት
- ኪረሙ ወረዳ (ቦቃ፣ አገምሳ እና ሁዲት ቀጠናዎች)፦
- የቤት ቃጠሎ እና መፈናቀል፡ በቦቃ፣ አገምሳ እና ሁዲት (ሃሮ ሁዲት) አካባቢዎች በተፈጸመ የቤት ቃጠሎ እና የትቅስ ልውውጥ ምክንያት ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ከ40 ሺህ በላይ ህዝብ መኖሪያውን ትቶ ሰጂ እና ውፍጭ ወደሚባሉ የጫካ ቦታዎች ተፈናቅሏል።
- የመከላከያ ሰራዊት ስምሪት፡ ከመከላከያ ሰራዊት የተወሰነ አካል ከአሊ ወደ ሃሮ አዲስ አለም መሄጃ "ታንከር" በሚባል ቦታ (ከኪረሙ 2 ኪ/ሜ ወጣ ብሎ) መንገድ ዘግቶ ተቀምጧል። ነዋሪዎች ከላይ የሚወርደውን ጥቃት እንዲከላከሉላቸው ጥያቄ ቢያቀርቡም ምንም አይነት ምላሽ አለማገኘታቸውን ገልጸዋል።
- የአካባቢው የወደመ ሁኔታ፡ ጋምሳ ከተባለችው አካባቢ አቅራቢያ የሚገኙ ትንንሽ መንደሮች እና መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል።
- አቤ ደንጎሮ ወረዳ (ቱሉ ዋዮ፣ ጫሮ፣ ጋሊሳ)፦
- የኃይሎች እንቅስቃሴ እና የህይወት ጉዳት፡ የገዳ ኮማንዶ እና የመከላከያ መለዮ የለበሱ ኃይሎች በከተማዋ (ቱሉ ዋዮ) ገብተው እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ። በቱሉ ዋዮ በአንድ ቤተሰብ አባላት እና ጎረቤቶች (እስከ 10 በሚደርሱ ሰዎች) ላይ በገዳ ኮማንዶ የሞት ጥቃት ደርሷል።
- የንብረት ውድመት እና እስራት፡ ቱሉ ዋዮ የምትባለው ገጠር ከተማ ሙሉ በሙሉ የወደመች ሲሆን፣ የአማራ ተወላጅ የሆኑ በርካታ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች መኪኖቻቸው ተይዘው መታሰራቸው ተገልጿል።
ነዋሪዎችም ለከፍተኛ ስጋት ተዳርገዋል።
- ጊዳ አያና ወረዳ (ለሊሴ፣ ዋጃ እና አንገር ቀጠናዎች)፦
- ቅስቀሳ እና ዝግጅት፡ በለሊሴ፣ በዋጃ እና በለሊቱ አንገር በኩል በጊዳ አያና አማራ ላይ ሁለተኛ ዙር ቅስቀሳ ሲደረግ አድሯል።
- የነዋሪዎች አቋም፡ ቀደም ሲል ነሐሴ 12 እና 13 ቤታቸው ተቃጥሎባቸው የነበሩ አማራዎች ሦስተኛ ዙር ተፈናቅለዋል፡፡
- የአየር እና የድሮን እንቅስቃሴ (ኡኬ፣ ጭንጮ፣ ብጅት፣ ጨረቲ፣ ቦቃ)፦
- የድሮን ቅኝት እና ጥቃት፡ በኡኬ ኤርፖርት አካባቢ አጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ማረፋቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በጫንጮ፣ ብጅት፣ ጨረቲ እና እስከ ቦቃ በረሃ ባሉ ቦታዎች ከፍተኛ የድሮን አሰሳ ተካሂዷል።
- የደረሰ ጉዳት፡ በምሽት መብራት በመለኮሱ ምክንያት በደረሰ የድሮን ጥቃት 6 አማራ አርሶ አደሮች የተገደሉ ሲሆን፣ 11 ያህሉ ደግሞ ከባድ ጉዳት አስተናግደዋል። በበረሃ ውስጥ መውጫ አጥተው የተዘጋባቸው በርካታ 12 ሽህ ተፈናቃዮች ይገኛሉ።
3. አጣዳፊ የጥንቃቄ እና የቅድመ-መከላከል መልዕክቶች
- የአየር ጥቃት (የድሮን) ጥንቃቄ፦ በየትኛውም ሰዓት የድሮን ቅኝት ባለባቸው አካባቢዎች ስብሰባዎችን እና የቡድን እንቅስቃሴዎችን ማስወገድ።
- የመንገድ እና የጉዞ ጥንቃቄ፦ በሊሙ ገሌላ እና በለሊሴ በኩል ዞሮ ለመግባት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በመኖራቸው፣ በጊዳ አያና፣ በዋጃ እና በለሊቱ አንገር በኩል የሚገኙ ነዋሪዎች እና አካላት ከፍተኛ የቅኝት እና የጥንቃቄ አቋም እንዲይዙ።
- መረጃ የማጣራት እና ሚዲያ አጠቃቀም፦ በሶሻል ሚዲያ እና በጥቂት አክቲቪስቶች በኩል የሚሰራጩ የሃሰት መረጃዎችን ሳይከተሉ፣ ኢንተርኔት እና ስልክ በሚሰራባቸው አካባቢዎች ትክክለኛውን የመሬት ላይ መረጃ ብቻ በመከታተል መመራት።
- የሰብአዊ እርዳታ ጥሪ፦ በሰጂ፣ ውፍጭ እና በቦቃ በረሃዎች ውስጥ ለተጠለሉ ህፃናት፣ እናቶች እና አቅመ-ደካሞች አጣዳፊ የህክምና፣ የምግብ እና የመጠለያ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ ማስተላለፍ።
(ምስል የደንጎሮ ከተማ ተፈናቃይ አማሮች)
ምንጭ፡ ሞዐ ዘተዋሕዶ ቴሌግራም
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:
Post a Comment