Saturday, November 7, 2026

አምባሳደር ማሲንጋ የሚሰመኮ ኮሚሽነር የሆኑትን አቶ ብርሃኑ አዴሎ በአርሲ ጉዳይ የአሜሪካንን መንግሥት እንዳሳሳበቸው ገልጸውላቸዋል

 

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ፣  በቀድሞው አርሲ ዞን በተፈጸሙ ጥሰቶች ምርመራ ፣ የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ እና የኮሚሽኑን አቅም በማጎልበት ዙሪያ በኢሰመኮ ዋና መ/ቤት ተወያይተዋል።

 በቅርቡ የአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ፣ በቀድሞ አርሲ ዞን የተፈጸመውን የሲቪሎች ጥቃት፣ በሃይማኖት፣ በብሔር ወይም በፖለቲካ ምክንያት የሚፈጸም ጥቃትን ሀገራቸው አሜሪካ እንደምታወግዘው ገልጸው ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ጉዳዩን እንዲያጣራና ጥቃቱን የፈጸሙ አካላትን ለሕግ እንዲያቀርብም ጥሪ አቅርበው ነበር።

ኢሰመኮ በበኩሉ በቀድሞ አርሲ ዞን ሲቪሎችን ፣ የቀበሌ ጸጥታ አካላትን ፣ ሚሊሻዎችን ጨምሮ 48 ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርት አድርጓል።

ዛሬ በነበረው ውይይት አቶ ብርሃኑ አዴሎ በዚሁ የምርመራ ጉዳይ ለአምባሳደሩ ገለጻ አድርገዋል።  

እንደሚታወቀው አቶ ብርሃኑ አዴሎ በዐብይ አሕመድ ጥቆማ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽነርነት ባለፈው መስከረም 2018 ከመመረታቸው በፊት፤ ከሲቪል ሰርቪስ የባችለር ዲግሪያቸውን፤ በመቀጠል ከሕንድ ቬጊው የሰብዓብዊ መብት አያያዝ የማስተርስ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን፤ ከመስከረም 2018 በፊት በፓርላማ አባልነት፣ የካቢኔት ሚኒስቴር አማካሪ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኢንቴሌክቹዋል ፕሮፕርቲ ዳይሬክተር በመሆን እንዳገለገለሉ ይታወቃል። 

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም                                                                                                                                                                    


ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ/ም  

 

 


No comments:

Post a Comment