ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም )፦ በምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ከሸርካ ወረዳ ጋር አዋሳኝ በሆነችው እንደቶ ቀበሌ ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን
2019 ዓ.ም ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ከፍተኛ ጥቃት ከተከፈተ ወዲህ ብዙ ምዕመናን መገደላቸውን ከተለያዩ የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ለመረዳች ችለናል። ከተገደሉት ኦርቶዶክሳውያን መካከል እስካሁን የ34 ኦርቶዶክሳውያን አስክሬን መገኘቱን የዓይን ምስክሮች አረጋግጠዋል።
ሮቤ ወረዳ እንደቶ ቀበሌ ከሸርካ ወረዳ ጋር አዋሳኝ ስሆን ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በሸርካ ወረዳ እንደተፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት ሁሉ ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም በእንዳቶ ቀበሌ ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ ጥቃት መፈጸሙን ምእመናን ከጥቃት የተረፉ ምዕመናን ለማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን በስልክ አሳውቀዋል።
እንደመረጃ ሰጭዎች መረጃ ከሆነ ታጣቂዎች በፈጸሙት በዚህ ድንገተኛ ጥቃት ይህ ዜና እስከተዘገበበት ጊዜ ድረስ ከሟቾች መካከል የ34 ኦርቶዶክሳውያን አስክሬን በእንደቶ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሰብሰቡ ታውቋል። የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆንና ሊያሻቅብ እንደሚችል ተጠቁሟል።
ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ አደገና ጥቃት ቆስለው እና በስለት ተወግተው የተረፉ በርካታ ምዕመናን እና የአካባቢው ነዋሪዎች ፤ ወደ ሕክምና ማእከላት እና ጤና ጣቢያ ለመድረስ በበመንገድ መዘጋት ምክንያት እስካሁን በቂ የሕክምና እርዳታ ማግኘት እንዳልቻሉ ለመረዳት ችለናል፤ ከአደጋው ጋር ተያይዞ በዚህ ጥቃትየአይን ምሥክሮች እንደገለጹት እጅግ በርካታ የአካባቢው በተለይ ከክርስቲያኖች ናቸው ተብለው የሚገመቱትን የንግድ ተቋማትም መውደማቸውን እነዚህ የዓይን ምሥክሮች ገለጸውልናል።
በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት መፈጠሩን ለማወቅ ተችሏል። ባለፉት ዓመታት በምሥራቅ አርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በሚገኙ ንጹሐን ላይ በተደጋጋሚ ሲፈጸሙ የቆዩት መሰል ጥቃቶች አሁን ላይም አሳሳቢ መልክ ይዘው መቀጠላቸውን ለመረዳት ተችሏል።
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ እንዳቶ ቀበሌ የምእመናን ግድያ የጀመረው ከጥር 21ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን ዛሬም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ያሉ ምእመናን የዛሬውን ግድያ ከቀድሞው ጋር ወደ ኋላ መለስ ብለው ያስታውሳሉ።
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
No comments:
Post a Comment