ብዙዎች ታላላቅ ሃገራትን ሲያስተዳድሩ፣ ሲመሩም ሕዝባቸውን ከድኅነት አረንቋ አውጥተው ወደ ተሻለ ኑሮ ደረጃ እና ወደ ኢንዱስትሪያል ሪቮሊሽን የቀየሩ ብዙ የዓለም መሪዎች እናውቃልን፣ አንብበናል፣ ሰምተናል፣ በዓይናችንም አይተናል፤ ዛሬ ላይ ግን በእኛ ሃገር ይልቁንም በሃገራችን ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት የተባለችው እማማ ኢትዮጵያን ካለችበት ከፍታ አውርዶ ወርዶ ተዋርዶ ሃገራችንን ለውርደት የዳረጋት፤ በታሪክም በትውልድም እስከ ወዲያኛው ድረስ ሞቶ እንኳን አጽሙን በሃገራን ምድር ሊያሳድድ የሚስችል ሥራ እየሠራ ያለውን አቶ ዐብይ መሐመድን እግዚአብሔር የሥራህን ይስጥህ ከማለት ውጪ ምን ሊባል ይችላል፤ ነገር ግን መጪው ትውልድ ስሙንም ማንነቱንም ሲያወግዝ እና ሲረግመው ይኖራል ለውርደት የዳረጋትን ሃገራችንን፣ ሕዝቦቿል ለረሃብ እና ለቸነፈር የዳረጋትን፣ እንዲህም ማቆሚያ ወደ ሌለው ጦርነት ውስጥ የሚከተን ይሄ የዛሬው ሂትለር ሃገሪቷን ከመኖር ወደ አለመኖር እየወሰዳት እንደሆነ ለማንም ግልጽ ነው፤ በተለይ ለኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በግራኝ መሐመድ እና በዮዲት ጉዲት ከደረሰባት መጠነ ሰፊ ጥቃት ባልተናነሰ በዚህ በእኛ ዘመን ሲደርስ ማየታችን እና መስማታችን ይበልጥ ያሳምማል፤ የእሥራኤል አምላክ ይሄንን ክፉ ጊዜ አሳጥርልን፤ በጎን ጊዜ አምጣልን በለን ከመጸለይ መቦዘን የለብንም።
ይህ ሁሉ መዋረድ ለኢትዮጵያ አይደለም። ይህ ሁሉ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን #መግደያ ለማግኘትና ሥልጣን ላይ ለመቆየት ነው። ከዚህ ውጭ ለሆነ ዓላማ ቢሆን ኖሮ
- እልቂት ይገታል
- ፍትሕ ይሰፍናል
- የተፈናቀሉ ወደ ቀያቸው ተመልሰው ይቋቋማሉ
- የተቃጠሉና የፈረሱ አቢያተ ክርስቲያናት ይሰራሉ
- ጽንፈኝነትና ዘረኝነትን የሚያስፋፉ ሰዎች ለሕግ ይቀርባሉ፣ ሕጎችና አስተምህሮዎች በሕግ ይታገዳሉ----
አሁን ያለው ስደትና ሞት፣ ዲስኩርና ጭብጨባ ብቻ ነው። ወገኔ ከእነዚህ ሰው መሳይ የደም ዋናተኞች ራስህን አድን‼️
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
No comments:
Post a Comment