Wednesday, November 5, 2025

በመላው ዓለም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያን፤ ሙስሊም፣ ፕሮቴስታንት፣ እና ካቶሊካውያን በእምነትም ያለእምነትም የምትኖሩ በሙሉ ኢትዮጵያውያን

የተወደዳችሁ የኢትዮጵያ ልጆች ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች፣ ፕሬቶስታንቶች፣ ካቶሊኮች፣ እንዲሁም እምነት ያላችሁ ወይም የሌላችሁ፤ ሁላችንንም አንድ የምታደርገን ሃገራችን ኢትዮጵያ በእጅጉ ሕመም ላይ ነች፤ ህመሟንም ሁላችንም ሳንረዳ አንቀርም እናውቀዋለን፤ እንረዳዋለን፤ ዛሬ በኢትዮጵያ የብዙ ኢትዮጵያውያን ደም በእብሪተኛው ዓብይ አሕመድ ጦር፣ በአክራሪ እስላማውያን፣ አክራሪ የሃይማኖት ሰዎች ብዙ ኢትዮጵያውያን በሚያውቁትም በማያውቁትም ክቡር ሕይወታቸው እየተቀጠፈ ይገኛል፤ ይሄንን ዜና ለማንችንም ዜና እንዳልሆነ እንረዳለን፤ ነገር ግን ማንኛውምይ የሃይማኖት ተቋም ይሄንን ግድያ እና ደም መፍሰስ በጎን ቁጭ ብለን ከመታዘብ ባሻገር ለማስቆም ወይም ለማስታገስ ጥረት ስናደርግ አንታይም፤ 

ባለፈው ሳምንት የእስምና መሪዎች አንድ መግለጫ አውጥተው ተመልክተናል፤ ነገር ግን ለበጣ በሚመስል መልኩ የእስልምና እምነት ተከታዮችም ተገድለዋል እና የእነሱንም ነፍስ ይማር በሚል ጩኸቴን ቀሙኝ በሚመስል መልኩ ሞታችንን ሲያቃልሉ ተመልክተናል ይሄ አያቀባብረንም፤ ኢትዮጵያ ለሁላችንም የምትበቃ ሃገር ሆና ሳለ አሁን በአሩሲ ያሉ ጂሃዲስት እጅግ በሚዘገንን መልኩ የክርስቲያኖችን ሕይወት ዘወትር ሲቀጥፉ እየታዩ ነው፤ ፦

A Cry for Justice: The Ongoing Massacre of Orthodox Christians in Oromia

The bloodshed in Eastern Arsi, Oromia, Ethiopia has not stopped — it grows worse each day. After the horrific slaughter of 25 Orthodox Christians in October 2025, the killing continues unchecked. The most vulnerable 
children, women, and the elderly are paying the highest price.

Little Tamrat, just four years old, was shot three times. Doctors now must amputate his leg to save his life. Sentayehu, only eight, still lies in a hospital bed after surviving both gunfire and a vicious machete blow to the head. Families are fleeing in terror, leaving behind their homes, churches, and memories.

On November 3, 2025,  six more innocent lives were taken in Abomsa Village. Yet the Zone Administrator, Ibrahim Kedir, denied the massacre in an interview with BBC Amharic — denying the pain, the bodies, the truth.

"አታልቅሽ ተመልሰው መጥተው ይገሉሻል..."የእናት ማሳሰቢያ ***


እንደ ህልም በእዛች በተረገመች ምሽት የተደረገውን አሰቃቂ ግድያ ታስታውሰዋለች። 

3 ወንድም እህቶቿን ፣እናቷን እና ሌሎች ቤተሰቦችን ጭምር ይዘው ከእነከብታቸው ስም አልባ የሞት አበጋዝ የሆኑ ታጣቂዎች
ልጇን የምትቀብር እናት እንዴት ትዘን?

ነድቷቸው ከአንድ ጫካ ላይ ወስደው አሳረፏቸው። 

ከመኖርያ ቤታቸው አርቀው ጫካ ላይ ከወሰዱ በኃላ  ሁሉም እንዲንበረከኩ አደረጉ። በያዙት መሣርያ ያለርህራሄ አርከፈኩባቸው ።ከተስማው የመሣርያ ጥይት ድምጽ በኃላ ሁሉም ጸጥ አሉ።

ከጸጥታው ውስጥ ግን የሚጣጣር እና የሚያቃስት ሰው ድምጽ በትንሽ በትንሹ ይሰማል። እንደ ቤተሰቧ ይህቺ የ8 ዓመት ህጻን በትከሻዋ አከባቢ እና በጎድኗ በኩል ሁለት ጥይት በስቷት አለፈ። 

በአፈሙዝ ያልሞቱትን በገጀራ ለመጨረስ ሁሉንም መከታተፍ ጀመሩ። ይህችንም ህጻን ልጅ መሃል አናቷን ሰነጠቁ። በጎድኗ እና ትከሻዋ በኩል ዘልቆ ከገባው የመሣርያ ቀለሀ በተጨማሪ ሰይፍ ለእዚህች ህጻን በአናቷ ታዘዘላት። 

ይህን ድርጊት ከፈጸሙ በኃላ ታጣቂዎች ከስፍራው ሄዱ።ይህች ህጻን ግን ከትንሽ ደቂቃ በኃላ ገላዋ በደም ረስርሶ ነቃች። ባልጠነከረ የስምንት ዓመት ገላዋ ላይ የገባው ቀለሃ እና ሰይፍ ድምጽ አውጥታ አስለቀሳት። 

Tuesday, November 4, 2025

ዛሬም በአርሲ ሌላ እልቂት ሌላ ግድያ 5 ክርስቲያኖች ታረዱ

 በትላንትናው እለት በክርስቲያኖች ደም በጨቀየችው በደም ምድሯ አርሲ ሌሎች አምስት ክርስቲያኖች ተጨፍጭፈዋል፤ የሚሰማም
ሲኖዶስ እና የንፁሐን ግድያ

መንግሥት የለም፤ የሚናገር አባትም የለም፤ የእምነቱ ተከታዮች እንኳን በትንሹ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው በአሁን ጊዜ፤ ነገር ግን ከቤተ መንግሥቱም ሆነ ከቤተ ክህነቱ በኩል ምንም አይነት ነገር እንዳልተፈጠረ በሰላም እና በመረጋጋት ላይ ናቸው ፤ ይሄ ደግሞ ለአንድ ሃገር ሰላምዊ የሆነ የሕዝቦች የኑሮ እና የቀን ተቀን ማኅበራዊ መስተጋብር ጭምር በእጅጉ ፈታኝ የሆነ ሁኔታ ተፈጥሮ እያለ ፤ ነገር ግን መንግሥታችንም ሆነ የቤተ ክህነቱ ተጠሪዎች የዶሮ ነፍስ እንኳን የጠፋ በማይመስል መልኩ ዝምታቸውን ቀጥለዋል፤ ክርስቲያኖችስ በዚህ መጠን እየተጨፈጨፉ ዝምታን መምረጥ ነገ ክርስቲያኖች አባቶቻችን ብለው ሊነሱ ወይም አብረዋቸው ሊቆሙ የሚችሉበት ሁኔታ ይኖራል? ግብረ መልሱ በእጅጉ አስደንጋጭ እና አስፈሪ እንደሚሆን ከወዲሁ መገመት አያዳግትም፤ 
የራሳችን የሚባሉ አብቶች ቢያንስ እኳን ዘለላ እንባ ማፍሰስ ቢያቅታቸው ወጥተው ማጽናናት ማንን ገደለ? ተነስተው ግደሉ እንዲሉ አንጠብቅም ነገር ግን በጸሎታቸው በአደባባይ ወጥተው ይሄ ግድያ ወደአልተፈለገ ነገር ውስጥ እንዳይወስደን በማለት ለምን አልተናገሩም፤ የነገው ሁኔታ በእጅጉ ያሳስባል አሁን ላይ እየሆነ ያለው ፤ እርግጥ ነው እያንዳንዱ ግድያ እና ጭፍጨፋ በመንግሥት በሚሰጡ መመሪያዎች እንደሆነ ብዙ ነገሮች ግልጽ እየሆኑ ነው፤ የሕዝበ ክርስቲያኑ ምላሽ ቆይቶ ጥሩ ላይሆን እንደሚችል የተገነዘቡት አልመሰለንም፤ ይሆነ ሆኖ ነገን የምናየው ነው፤ ነገር ግን ዛሬ ላይ እያለቅን ነው ብለን እንኳን እንድንጮች ጥሪያችንን እናቀባለን።

Monday, November 3, 2025

An Urgent Appeal for the Orthodox Christians of the East Arsi Zone, Oromia, Ethiopia

=========

Your Excellencies, Distinguished Leaders, Human Rights Organizations, and People of Goodwill,

Priest Ephream Eshete Ephream

I, a priest of the Ethiopian Orthodox Tewahido Church, pleading on behalf of the beleaguered Orthodox Christian community in the East Arsi Zone of the Oromia Regional State in Ethiopia, write to you today with a heavy heart and a desperate plea for intervention. We are facing a systematic and brutal campaign of persecution that threatens our very existence, and our cries for help within our own country have gone unheeded.

The situation on the ground is not merely one of isolated incidents but a coordinated campaign of violence and terror. The most harrowing evidence of this is the chilling statistic that, on average, at least seven or eight of our faithful are killed in the region daily. These are not casualties of a generalized conflict; they are targeted assassinations, extrajudicial killings, and massacres aimed at cleansing the land of its ancient Orthodox Christian presence.

በመላው ዓለም የምንገኝ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ዘመቻውን እንድትቀላቀሉ በአክብሮት እንጠይቃለን!!


Crime Against Humanity led by Ethiopian Government Officials on Ethiopian Orthodox Christians.

https://www.aljazeera.com/wp-content/uploads/2023/02/2023-02-10T110825Z_1360883397_RC2HTY9LM5UG_RTRMADP_3_ETHIOPIA-CHURCH.jpg?resize=1920%2C1440
The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church (EOTC) is one of the oldest Christian institutions in the world, tracing its roots back to the early centuries of Christianity in Ethiopia and the Axumite Kingdom. It is a defining cultural and religious institution in Ethiopia: in addition to its spiritual role, it has historically been a central part of the country’s language, art, calendar, and identity.

Key features and significance

  • The EOTC holds a very large following: while exact percentages vary, it is reported to be the largest Christian church in Ethiopia. Ethiopia Insight+1

የማኅበራዊ ዘመቻው መካተት ያለባቸው ሐሳቦች 

፩. በኦርቶዶክሳውያን ላይ የጥቃት አድራሹ አካል ከመንግሥት ጋር በመናበብ የሚሠራው ጠቅላይ ቤተ ክህነት እና  ሲኖዶስ ስለሆነ 
ለችግራችን ምንጭ አድርጎ በመቁጠር ድምጽ ማሰማት። 

፪. የጠቅላይ ቤተ ክህነት ወይም ቋሚ ሲኖዶስ በአስቸኳይ ጉዳቱ ወደ ደረሰበት አካባቢ በመሄድ ወገኖቻችንን እንዲጎበኝና እንዲያጽናና መጠየቅ።

Calling the World Christian Society for help



A Call to Nations and the Oriental Orthodox Church

Stand With Persecuted Orthodox Christians  In Ethiopia

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

ዓለም  የዘነጋዉ  የ ኦርቶዶክሳዉያን  ጭፍጨፋ

በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ላይ ከመስከረም 2/2016ዓ.ም እስከ ኅዳር 20/2017 ብቻ (ከዚያ በኋላ የተገደሉትን አያካትትም)

የተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን  ስም ዝርዝር ።ለጊዜው የደረሰኝ መረጃ የነዚህ ብቻ ነው።የሌሎችም ሲደርሰኝ የማቀርብ ይሆናል።                 

ሀ)ጥቃቱን ከሌሎች ስፍራ ልዩ የሚያደርገው ሙሉ በሙሉ የኢኦተቤ አማኞች ላይ ያነጣጠረ ነው።ለምሳሌ በሌሎች የኦሮሚያ ክፍሎች አማራ የሆነ ሙስሊሙም ኦርቶዶክሱም ይገደላል  ከዚህ ግን ኦርቶዶክስን ለይቶ  ማጥፋት ነው እየተደረገ ያለው።

ለ) ጥቃቱን የሚፈጽሙት 100% የኦሮሞ አክራሪ የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው ።

ሐ) ከተገደሉት መካከል 45% የሚሆኑት  ከ2 እስከ 11 የሚደርሱ ቤተሰቦቻቸው ጋር  የተገደሉት ናቸው። 

Saturday, November 1, 2025

ገዳዮቻችን መቼ ይታወቁ ይሆን?

Who is killing us?
በታቀደና በስልት ኦርቶዶክሳውያንን እያጸዳ ያለው አክራሪው ክንፍ ተደጋጋሚ ተግባር እየፈጸመ ‹‹በማይታወቁ ታጣቂዎች›› የሚል ዘገባ ተደጋግሞ ሲነገር ስንሰማ ጥያቄ እናነሳለን መቼ  ነው ‹‹ገዳዮቻችን የሚታወቁት››?  የሚለው የሚመለከታችሁ የቤተ ክህነትና
የቤተ መንግሥት ሹሞች ምላሽ የምንጠይቀው፡፡ 

👉ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በሚል የተዘገቡ የቤተ ክርስቲያን ዘገባዎችን እንደ ማሳያ እንመልከት፡፡
በኦሮሚያ ክልል ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ቤተክርስቲያንን እና ምዕመናንን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን በተመለከተ የተለያዩ የዜና እና የቤተክርስቲያን ምንጮች ዘገባዎች አውጥተዋል። ዋና ዋናዎቹ ዘገባዎች እና የሚመለከቷቸው አካባቢዎች የሚከተሉት ናቸው፡ 


ከጥምረት ለቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ ኦርቶዶክሳዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

ከጥምረት ለቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ ኦርቶዶክሳዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ
“ስለ አንተ ዘወትር ይገድሉናል፤ እንደሚታረዱ በጎችም ሆነናል።” ሮሜ ፰ ÷ ፴፮

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በታቀደና በተጠና መልኩ ከሃገር ለማጥፋት ካልሆነም አናሳ ሆና እንድትቀጥል

ሥርዓታዊ ጥቃት እየደረሰባት ትገኛለች። በተለይም ከ ፳፻፲ ዓ.ም. ጀምሮ ከሰሜን አስከ ደቡብ፤ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ በአራቱም መዓዘን ካህናቱ ምእመናኑ ይገደላሉ፤ ይፈናቀላሉ አብያተ ክርስቲያናት ይቃጠላሉ። “ኦርቶዶክስን ከኦሮሚያ ማጽዳት” የሚለው የቆየ የመንግሥት እቅድ የመተግበር አካል ነው።
ሰሞኑን ጥቅምት ፲፭ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም. በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሥር ባሉ የተለያዩ አካባቢዎች “ማንነታቸው ያልታወቁ” በሚባሉ ነገር ግን አገዛዙ እና ሌሎች አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ኃይላት በሚያሰማሯቸው ታጣቂዎች ሃያ አምስት ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች መገደላቸውን እና ከሞት የተረፉትም ለከባድ የአካል ጉዳት መዳረጋቸውን በተለያዩ ሚዲያዎች መዘገቡ ይታወቃል።
በእነዚህ ጥቃቶች የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ወንድማማቾች እና እህታማቾች እንዲሁም ከሁለት ዓመት ሕፃን እስከ ሰባ ስድስት ዓመት አረጋዊ ሽማግሌ የግፍ ግድያው ሰለባ መሆናቸው ታውቋል። በያዝነው ዓመት መስከረም ፯፣ ጥቅምት ፲፬፣ እና ጥቅምት ፲፰ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በጉናና መርቲ ወረዳዎች፤ በሸርካ ወረዳ፤ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች ከሃያ አምስት በላይ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ተገድለዋል። በዚሁ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ ፻፲፭ (አንድ መቶ አራ አምስት) ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ከአሥራ ስድስት በላይ አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተዋል።

What would the world say about Arsi mass killing on Orthodox Christians?

Here is a summary report of publicly-documented information regarding attacks on Christians — especially members of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church (EOTC) — in the Arsi Zone (Oromia Region,


Ethiopia). Please note that there are serious gaps, conflicting claims, limited independent verification, and some of the details you asked about (e.g., “mutilated, stoned, burned alive inside the church”, perpetration by a named individual “Mr. Ibrahim Kadir”, a figure labelled “government-led Muslim fanatics”, exact counts like 1,850 victims) do not appear in credible independent sources. Hence, the account that follows is carefully qualified.

በአርሲ ዞን ለደረሰው ጭፍጨፋ እነዚህ ሃገረ ስብከቶች የሃዘን እና የአጋርነት መግለጫዎችን ልከዋል

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሁለት ወረዳዎች በታጣቂዎች ከተገደሉት ምዕመናን መካከል አምስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት እንደሆኑና
ጥቂቅ ሃገረ ስብከቶች ሃዘናቸውን እና ከአርሲ ክርስቲያኖች ጋር ቆመዋል


ከዚህ ቀደምም በጀጁ ወረዳ በታጣቂዎች የታገቱ ሰዎች እንዳልተመለሱ የዞኑ ሀገረ ስብከት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ምሽት ገልጿል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሀገረ ስብከት በሰጠን ቃል፣ በሰሞንኛው ጥቃት መርቲ እና ጉና ወይም አባጀማ በተሰኙት ሁለት ወረዳዎች ላይ የሟቾች ቀብር መፈጸሙን ገልጿል። 


የኖላዊው አባት ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ አርአያነት ያለው ሥራ በምሥራቅ አርሲ

የብፁዕ አቡነ ይስሐቅ አርአያነት ያለው ተግባር
=========
ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ  በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ  ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉት ውስጥ በእግዚአብሔር
የኖላዊው አባት ብፁዕ አቡነ ይሥሐቅ አርአያነት ያለው ሥራ

ቸርነት ለተረፈው ሕፃን 70,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ ።

(EOTCMK TV ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም)

ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ከሰሙበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ ማዘናቸውን እና ለሞቱት እረፍተ መንግሥተ ሰማያት፤ ቤተሰባቸውን ላጡ መጽናናትን እንዲሰጥ ተመኝተዋል ።


ብፁዕነታቸው የሰው ልጅ ሰው ሆኖ ከመኖር ይልቅ አውሬ እየሆነ ያስቸገረበት ዘመን ላይ መድረሳችን እጅግ የሚያሳዝን ነው ብለዋል። 





ከሻሸመኔ እስከ አርሲ ጭፍጭፋ ተጠያቂው ሰው አቶ ኢብራሂም ከድር ለፍርድ መቅረብ አለበት

ግፉዓን ይትመሐፀንዋ ለመንግስተ ሰማያት 😭😭😭
ገዳይም አስገዳይም ኢብራሂም ከድር ነው
አቶ ኢብራሂም ከድር ለፍድ ይቅረብ
በመጀመሪያ በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን ነፍስ ይማር እንላለን 🤔
ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን እንመኛለን 😭
ነገሩ የትናንቱ እንደ አዲስ መሰለን እንጂ ስንቱ ነው በሰማይ በድሮን 
በታች በምድር በታንክ 
በዲሽቃ እየተጨፈጨፈ ያለው?
እየተፈናቀለ ያለው ማነው ብለን ከጠየቅን መንግሥት ነው፤
መንግሥት ሲባል ደግሞ በስም ዝርዝር 
በሻሸመኔ ከተፈጸመው ጭፍጨፋ እስከ አርሲ በተደረጉት ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖችን ከማጽዳት ጋር በተያያዘ ብዙ ሰዎች ስማቸው ሲነሳ
ቆይቷል በተለይ በአሁን ሰዓት በአርሲ በተፈጸመው ጭፍጭፋ ክርስቲያኖችን የማጽዳቱን ሥራ በዋናነት ከሚመሩት ሰዎች ሥምሪት ከሚሰጡት ስዎች ግንባር ቀደሙ አቶ ኢብራሂም ከድር ዋነኛው ነው፤ 

Friday, October 31, 2025

በአርሲ የእልቂት ድግሱ እንደቀጠለ ነው፤ ለማን አቤት ይባል???

አርሲ በኦርቶክስት ደም ታጥባለች ፤ 

በምሥራቅ  አርሲ  ሽርካ  ወረዳ ሄላ  ዘባባ ቀበሌ  ከሚኖሩ ኦርቶዶክሳዊያን ሦስቱ መገደላቸው እና አራቱ መታገታቸው ተሰማ፡፡

በወረዳው ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ115 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውና ከ16 በላይ ዐብያተ ክርስቲያናት መዘጋታቸው ታውቋል።

ጥቅምት ፲፱/፳፻፲፰ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ 

ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በደረሰው መረጃ ጥቅምት  17 ቀን 2018  ዓ.ም ከለሊቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ሄላ ዘባባ ቀበሌ አርሴማ አጥቢያ የሚኖሩ ምእመናን በታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሦስቱ መገደላቸው እና አራቱ ደግሞ መታገታቸው ተገልጿል።

ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ የአንዱ ሟች አባትና ወንድም መታገታቸው በመረጃው የተገለጸ ሲሆን ታፍነው የተወሰዱት ምእመናን ስለሚገኙበት  ሁኔታ አይታወቅም ተብሏል፡፡

በመረጃው እንደተነገረው የሞቱት ሦስቱ ኦርቶዶክሳውያን በትላንትናው ዕለት ጥቅምት 18  ቀን  2018  ዓ.ም  ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታት ማለትም ከ2016 ዓ.ም መስከረም 02 ጀምሮ  እስከ  2017 ዓ.ም  ድረስ ያለማቋረጥ በወረዳው ከ115 በላይ ምእመናን የተገደሉ  ሲሆን  27  ኦርቶዶክሳዉያን  ደግሞ አሁንም  ድረስ  ታግተው  ያሉበት  እንደማይታወቅ  ነዋሪዎቹ  ለጣቢያችን  ገልጸዋል።

በግድያ  ያላበቃው  መከራና  ስቃይ  በሽርካ  ወረዳ  ብቻ  በዘጠኝ  ቀበሌዎች  በሺዎች የሚቆጠሩ  ኦርቶዶክሳዉያን  መፈናቀላቸውንም በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

Thursday, October 30, 2025

አትነሳም ወይ፤ ኦርቶዶክሳዊ አይደልህም ወይ?

የመጣብንን የአላውያን ጦር በመስቀሉ እንሰብራለን፤
"አትነሳም ወይ? " 

አንተ የተዋሕዶ ልጅ ሆይ
ማንቀላፋቱ አይበቃም ሆይ!
መዘናጋቱስ አይበቃም  ወይ
አይገድህም ወይ!
አትነሳም ወይ
እያለቀ ያለው ወገንህ አይደለም ወይ!

ወገን ሲታረድ እንደ በግ ጠቦት
ደሙ ሲፈስ እንደ ውኃ ጅረት
አየነው አየነው እረፉ ባይ ጠፋ
ሞት ታውጆብን ከምድር እንድንጠፋ

       አየገባህም ወይ
        አትነሳም ወይ
       በግፍ የሚገደለው ሕዝብህ አይደለም ወይ

       መንግሥት አለ ብለህ እንዳትጃጃል
አባት አለ ብለህ እንዳትጃጃል
እግዚአብሔርን ይዘህ ተነስ ለ ትግል
ወደ ፊት ሩጥ እንጂ ወደ ኋላ አትበል

           አይበቃም ወይ
            አያሳዝንም ወይ
            አትነሳም ወይ
      በግፍ የሚታረደው
       ሕዝብህ አይደለም ወይ
ወገን በሃይማኖቱ በግፍ ሲገደል
ሬሳው እንኳ  ሳይቀር በእሳት ሲቃጠል
አያሳዝንም ወይ እየሆነ ያለው
ተነሳ ወጣት ሆይ  መፍትሔው 
መነሳት ነው

ሌላው አጀንዳ በራሱ ድምፃችንን የሚያጎላ ሳይሆን ድምፅ የሚቀንስ ነው!

የሚያሳዝነኝ ዛሬ መሞታችን ብቻ ሳይሆን ሞታችን እንዳይቀጥል አንድ አይነት ድምፅ ማውጣት አለመቻላችን ነው ሌሎች እንኳን ሲሞቱ ይቅርና ሲታመሙ እንኳን የሚያወጡት ድምፅ አንድ አይነት ነው እኛ በሞታችን ሳይቀር ዥንጉርጉር ነን ድምፃችንን አንድ አድርገን መኖር ይፈቀድልን ለምን እንገደላለን ከሚል ጩኸት ይልቅ ሞታችንን እንከፋፈልበታለን እነ እገሌ አብረውን አልቅሰዋል እነ እገሌ በደንብ አልጮሁም የእነ እገሌ አለመጮህ ወዘተ እያልን ድምፅ መቀነሳችን ልዩነት መፍጠራችን ወደ ፊት እንኳን ለገዳዮቻችን አንድ ሆነን እንደማንቆም እየነገርናቸው ነው😭😭 ኦርቶዶክስ ናቸው ተብለን እየተገደልን ሞታችን ውስጥ ብዙ ነገር መሥራታችን ሞታችንን በልዩ ልዩ ምንዛሬ ማየታችን እጅግ ያሳዝናል መግደል ባይደክማችሁ እንኳን መሞት ደክሞናል ይበቃል እንበል የተከፋፈለ ሐሳብና የግል አመለካከት ከመሰንዘር ወጥተን ሞታችንን እናስቁም ገዳዮቻችንን እናውግዝ ዝምተኞችን እንቀስቅስ ተናጋሪዎች ንግግራቸው ትክክለኛ ሐሳብ ላይ ያነጣጠረ እንዲሆን እንምከር ሞታችንን ለልዩ ልዩ ፍጆታ የሚጎትቱትን በወንድምና እህት በልጅ በእናትና አባት ሞት ገብያ አትክፈቱ እንበል ያ ካልሆነ በስተቀር ለጊዜው ተነቃቅፈን ተወጋግዘንና ተነቋቁረን ተመልሰን ደግሞ ዝም እንላለን ሞቱም መቀጠሉ አይቀርምና አንድ ሆነን እንቁም ሞታችን ውስጥ በመከራችን የምድጃ እሳት ላይ የግል ነገራችንን ለማብሰል የግል ድስት አንጣድ!😭

በምሥራቅ አርሲ ኦርቶዶክሳውያን ላይ በሚፈጸመው መንግሥት መር ኢስላማዊ ጅሃድ

ብፁዕ አቡነ ያሬድ የምሥራቅ አርሲ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ

በምሥራቅ አርሲ ኦርቶዶክሳውያን ላይ  በሚፈጸመው  መንግሥት መር ኢስላማዊ ጅሃድ የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ክፍል ሠራተኞች እልቂቱ ወደ ተፈጸመበት ወረዳ ደውለው ከአንድ ኦርቶዶክሳዊ መረጃ ይቀበላሉ።መረጃ ሰጪው ኦርቶዶክሳውያን ያሉበት አሳሳቢ መሆኑንና የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አባ ያሬድም ለ ጉዳዩ ትኩረት አለመስጠታቸውን ይናገራሉ።ማኅበሩም ድምፁን በሚዲያው ያወጠዋል።ይኽን የሰሙት አቡን ያሬድ ቪድዮው ከሚዲያው  እንዲወርድ በማስፈራሪያ ጭምር አዘዙ። በ ሞቱ ኦርቶዶክሳውያን ሥርዐተ ቀብር ላይ የሚገኙ የሀገረ ሰብከቱ ሠራተኞች ላይም ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደርግም ቀጭን ትእዛዝ ወጥቷል።ይኽ ብቻ አይደለም ከዚህን በፊት "በሀገረ ስብከትዎ ስለሚሞቱት ኦርቶዶክሳውያን ለምን ዝምታን መረጡ "ሲባሉ "ኦርቶዶክሳውያን መሞታቸውን እርግጠኛ አይደለሁም" እስከ ማለት የደፈሩ ሰው ናቸው።እንግዲህ ቤተ ክርስቲያን በእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እጅ ላይ ነው የወደቀችው።#EOTC  የገዳያችንን የብልጽግና ገጽታ የሚገነባ ስለ ኮሪደር ልማት ካልሆነ በቀር ሙሉ በሙሉ ስለ ኦርቶዶክሳውያን እልቂት አይዘግብም።ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የአዳነች አቤቤ የቅርብ ሰው የሆኑት አባ ሄኖክsilent mood ላይ ቢያስገቡትም አልፎ አልፎም ቢሆን መከራችንን ይዘግባል።#Mktv  ገዳዮቻችንን  በስም እንዳይጠሩአቸው  "ያልታወቁ ኀይሎች" እያሉ እንዲዘግቡ  የሚያደርጉት የ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ  እሾኾች ናቸው።