Thursday, October 11, 2012

ፓትርያርክ ምርጫ እስከ ሚከናወን ድረስ ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩና ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር አብረው የሚሠሩት አባላት በእርቀ ሰላሙ ጉዳይ ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋር ተወያዩ




ከጥቅምት 6-11 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ሠላሳ አንደኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ይካሔዳል፡፡
የጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋናው ስባሰባ ደግሞ ጥቅምት 12  እንደሚጀመር እየተጠበቀ ሲሆን በአሁን ሰዓት እንዱና አንገብጋቢው አጀንዳ የፓትርያርክ ምርጫ እና ተያያዥ ጉዳዮች እንደሚሆን እየተጠበቀ ነው ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከውጪው ሲኖዶስ ጋር ያለውን እርቀ ሰላም በተመለከተ ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው ከአቡነ መልከፄዴቅ ጋር ብቻ ውይይት ሲደረግ የቆየ ቢሆንም ሰሞኑን የዋናው ፓትርያርክ ምርጫ እስከ ሚከናወን ድረስ ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩና ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር አብረው የሚሠሩት ሰባቱ አባላት    ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋር ወይይት ማድረጋቸው ተነግሯል ፡፡

በውይይቱም አቡነ መርቆሬዎስ ከዚህ በፊት እንደሚገመተው ሁሉ በገዳም መኖርን እንደሚመርጡና አንድ  ጊዜ የተጣሰው ስርዓት እሳቸው በህይወት እያሉ ሌላ ፓትርያርክ እንዲመረጥ እንደማይፈቅዱና እሳችው እስኪያርፉ አሁን እንዳለው ቤተ ክርስቲያኗ በመንበረ ፓትርያርክ እየተመራች እንድትቆይ እንደሚሹ ማስታወቃቸውን ምንጮቻችን ዘግበውልናል፡፡
ልዑል እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት ይጠብቅልን፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፤  አሜን፡፡

Monday, October 8, 2012

“መሰናዘሪያ” የተባለ ጋዜጣ “አቡነ መርቆሬዎስ ኤርትራን ጎበኙ” ሲል መዘገቡ ለዕርቁ እንቅፋት ሊፈጥር ይችላል ተባለ

“አቡነ መቃርዮስ”


(ደጀ ሰላም መስከረም 28/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 8/2012; READ THIS NEWS IN PDF)፦ በሜላቢን ፕሮሞሽን ሓላ/የተ/የግ ማኅበር የሚታተመው “መሰናዘሪያ” የተሰኘ ሳምንታዊ ጋዜጣ መስከረም 22 ቀን 2005 ዓ.ም “አቡነ መርቆሬዎስ ኤርትራን ጎበኙ” ሲል በዜና ገጹ ላይ የተሣሣተ ዘገባ ማውጣቱ ለተጀመረው ዕርቅ እንቅፋት ሊፈጥር እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡ ጋዜጣው በስደት ላይ የሚገኙት አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ኤርትራ አምርተው ለቀናት ጉብኝት እንዳደረጉ፣ ከግንቦት ሰባት አመራሮች ጋራ አብረው እንደሚሠሩና ጉብኝታቸው ከዚሁ ጋራ የተያያዘ መኾኑን በመጥቀስ ያቀረበው ዘገባ “ትግራይ ኦንላይን” የተባለውን ድረ ገጽ በምንጭነት በመጥቀስ ነው። ድረ ገጹ “Why was Abune Mekariossent to Eritrea by Ginbot-7 after Prime Minister Meles died?” በሚል ርእስ ሴምቴፐር 27/ 2012 ባወጣው ዘገባው ኤርትራን ጎበኙ ሲል የጠቀሳቸው “አቡነ መቃርዮስ”ን ነው፡፡

Wednesday, October 3, 2012

የመስቀል በዓል “ግዙፍነት ከሌላቸው የዓለም መንፈሳውያን ሀብቶች” ተርታ ሊመዘገብ ይችላል



  • ከኢትዮጵያ የመጀመሪያው ግዙፍነት የሌለው ዓለም አቀፍ ቅርስ የመኾን ዕድሉን ካገኘ በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጥበቃና ክብካቤ ይደረግለታል፤
  • የአ/አ ሀ/ስብከት አንዳንድ ሓላፊዎች ለዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል የሰጡትትኩረት አከባበሩን በማዳከም የወቅቱን የቅ/ሲኖዶስ አመራር የማስነቀፍ ዓላማእንደነበረው ተጋልጧል፤
  • በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ፖሊስ በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራንና አባላትላይ ያካሄደው ፍተሻና በኅትመቶች ሽያጭ ላይ የተደረገው እገዳ ተቃውሞገጥሞታል፤ 
  • የአቶ መለስ ዜናዊ 40ኛ ቀን ተዝካር በታላቁ ቤተ መንግሥትና በጠ/ቤ/ክህነትይደረጋል፤ 
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 14/2004 ዓ.ም፤ ሰምቴፕር 24/2012/ READ IN PDF):- የመስቀል - ደመራ በዓልአከባበር በዓለም ግዙፍነት ከሌላቸው ቅርሶች መካከል አንዱ ኾኖ እንዲመዘገብ ሲደረግ የቆየው ጥረት“በመልካምና ቅደም ተከተሉን በጠበቀ መንገድ ላይ እንደሚገኝ”፣ በመጪው ዓመት ኅዳር ወርምኢትዮጵያ ለዩኔስኮ ያቀረበቻቸው ማስረጃዎች ተቀባይነት አግኝተው የመስቀል - ደመራ በዓልየመጀመሪያው ግዙፍነት የሌለው ዓለም አቀፍ ኢትዮጵያዊ ቅርስ (World Intangible Heritage) ኾኖ እንደሚመዘገብ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣንአስታወቀ፡፡

Sunday, September 30, 2012

እንዲህም አለ ለካ?



ስሙ ቀሲስ ቸርነት ኅይለሥላሴ ይባላል በፍኖተ ጽድቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ቨርጂኒያ በሚገኘው ቤተክርስቲያን አገልጋይ ነኝ ይላል የክህነት ሥነ ምግባር የሌለው፣ የክህነት ለዛ የሌለው፣ ሃይማኖትን ከፖለቲካ ጋር ሊያገናኝ የሞከረ ተራ አሳሳች ካድሬ በኢትዮጵያ ኤምባሲ በተደረገው የአቶ መለሰ ዜናዊ ለቅሶ ላይ ተገኝቶ የበላበትን በደንብ የጮኽ የጌታው አገልጋይ ሰው ነው
አሳፋሪ እና የብዙ ኦርቶዶክሳዊያንን አንገት ያስደፋ ተራ ንግግር ስለሆነ ተናጋሪው ካህን ተብየው በመጪው ዘመኑ ንሰሐ ገብቶ ከዓለም መድኅኒት ስርየት እንዲሰጠው ቢለምን ይሻለዋል
ልቦናውን ይስጠው

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

Thursday, September 20, 2012

ቀጣዩን ፓትርያርክ በተመለከተ …



ትጉህ እና ቅን ለበጎቹ አሳቢ መሪ ይስጠን
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 9/2004 ዓ.ም፤ ሰምቴፕር 19/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፡- ከአምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ማለፍ በኋላ በመንበረ ተክለ ሃይማኖት መቀመጥ የሚገባውን ቀጣይ አባት ከመሾም አስቀድሞ የአራተኛውን ፓትርያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ዕጣ ፈንታ መወሰን፣ ከዚህም ጋራ የቤተ ክርስቲያንን ሰላምና አንድነት እንዲሁም የመዋቅር ማሻሻያ የሚመለከቱ ርምጃዎች መውሰድ የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ ኾኖ ወጥቷል፡፡ በአሜሪካው የሰላምና አንድነት ጉባኤ ከተጀመረው የዕርቀ ሰላም ሂደት በተጨማሪ በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሥሓቅ የሚመራውና ከዐሥር ያላነሱ ልሂቃንን የያዘው የአገር ሽማግሌዎች ቡድን ሰሞኑን ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ጋራ በመወያየት በቅርቡ ቡድኑ በቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ተገኝቶ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ የሚነጋገርበት ኹኔታ እንዲመቻች መደረጉ ተዘግቧል፡፡


በሌላ በኩል የወቅቱ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባናል፤ የቅ/ሲኖዶስን የሰላምና የተቋማዊ ማሻሻያ ርምጃዎች በማገዝ ረገድ የበኩላችንንም ለማበርከት ተዘጋጅተናል የሚሉ የአገልጋዮችና ምእመናን ስብስቦችም ይበጃል በሚሏቸው ሐሳቦች ዙሪያ የሚመለከታቸውን አካላትና ሰፊውን ምእመን በተደራጀ መንገድ እያወያዩ ናቸው፤ ለውይይትና ግንዛቤ የሚረዱ ጽሑፎችም በተለያዩ መድረኮች እየቀረቡና እየተሠራጩ ይገኛሉ፡፡ ከእኒህም መካከል ውሉደ አበው ዘተዋሕዶ የተሰኘውና በዋናነት ለመረጃ፣ ለግንዛቤና ለውይይት የሚረዱ ጽሑፎችን መዘርጋት የጀመረው የአገልጋዮች መድረክ አንዱ ነው፡፡

መድረኩ ባዘጋጀውና ለደጀ ሰላም መድረስ በጀመረው በዛሬው ሁለተኛ ጽሑፉ ከቀጣዩ ፓትርያሪክ ምርጫ አስቀድሞ መከናወን በሚገባቸውና ‹‹መንገድ ጠራጊዎች ናቸው›› በሚላቸው መሠረታዊ ሥራዎች ላይ ሐሳቡን በዝርዝር አቅርቧል፤ እኒህ መሠረታዊ የቅድመ ሢመተ ፓትርያሪክ ተግባራት ለቤተ ክርስቲያናችን፣ ለአገራችንና ለዓለም ሁሉ ያላቸውን በረከት በማመላከትም ተገቢው ጊዜ እንዲሰጣቸው ይከራከራል፡፡ ደጀ ሰላማውያን ሁሉ በመድረኩ የጽሑፍ አበርክቶዎች ላይ ሐሳባቸውን በማቅረብ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ በባለቤትነት ለመወያየት እንችል ዘንድ ደጀ ሰላም ጥሪዋን ታቀርባለች፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።
 +++

Wednesday, September 19, 2012

የደብረ ምጥማቅ መግባቢያ


የደብረ ምጥማቅ መግባቢያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆነች ትልቋ ተቋም ናት፡፡ በሕዝቡሃይማታኖዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ታሪካዊ ጉዞ ውስጥ የማይተካና ወሳኝ የሆነ ሚናም አላት፡፡ ዕድገቷ ለሀገሪቱ ዕድገት፣ ሥልጣኔዋ ለሀገሪቱ ሥልጣኔ፣ አሠራርዋ ለሀገሪቱ አሠራር፣ የችግር አፈታቷም ለሀገሪቱ የችግር አፈታት ወሳኝ ነው::
በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግሮች ለመፍታትና አንዲት፣ ጠንካራ፣ በአሠራርዋ ዘመናዊ፣ በእምነቷ ጥንታዊ፣ በሀገሪቱ ጉዞ ውስጥ ተደማጭና ወሳኝ የሆነ ሚና ያላት፣ ሌሎች ችግሮቻችንን በመፍታት ረገድ ሀገራዊ መንፈሳዊና ተልእኮዋን የምትወጣ ቤተ ክርስቲያን እንድትሆን በማድረጉ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ ይመለከተናል፡፡
በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያኒቱ ከገጠሟት ፈተናዎች አንዱ የመለያየት ዕጣ ፈንታ ነው፡፡ ይህ ዕጣ በተለይም በሀገር ቤትና በውጭ በሚባል ሲኖዶስ፣ በማይግባቡና በማይቀራረቡ አባቶች እነርሱም በተከተሉት ሁለት ዓይነት የችግር አፈታት ምክንያት የተከሰተ ነው፡፡