- ከኢትዮጵያ የመጀመሪያው ግዙፍነት የሌለው ዓለም አቀፍ ቅርስ የመኾን ዕድሉን ካገኘ በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጥበቃና ክብካቤ ይደረግለታል፤
- የአ/አ ሀ/ስብከት አንዳንድ ሓላፊዎች ለዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል የሰጡትትኩረት አከባበሩን በማዳከም የወቅቱን የቅ/ሲኖዶስ አመራር የማስነቀፍ ዓላማእንደነበረው ተጋልጧል፤
- በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ፖሊስ በማኅበረ ቅዱሳን መዘምራንና አባላትላይ ያካሄደው ፍተሻና በኅትመቶች ሽያጭ ላይ የተደረገው እገዳ ተቃውሞገጥሞታል፤
- የአቶ መለስ ዜናዊ 40ኛ ቀን ተዝካር በታላቁ ቤተ መንግሥትና በጠ/ቤ/ክህነትይደረጋል፤
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 14/2004 ዓ.ም፤ ሰምቴፕር 24/2012/ READ IN PDF):- የመስቀል - ደመራ በዓልአከባበር በዓለም ግዙፍነት ከሌላቸው ቅርሶች መካከል አንዱ ኾኖ እንዲመዘገብ ሲደረግ የቆየው ጥረት“በመልካምና ቅደም ተከተሉን በጠበቀ መንገድ ላይ እንደሚገኝ”፣ በመጪው ዓመት ኅዳር ወርምኢትዮጵያ ለዩኔስኮ ያቀረበቻቸው ማስረጃዎች ተቀባይነት አግኝተው የመስቀል - ደመራ በዓልየመጀመሪያው ግዙፍነት የሌለው ዓለም አቀፍ ኢትዮጵያዊ ቅርስ (World Intangible Heritage) ኾኖ እንደሚመዘገብ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣንአስታወቀ፡፡


