በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን
የቅርብ ዘመን ታሪክ
ከተፈጠሩት ገጽታዎች አንዱ
‹‹የገለልተኛነት›› አቅጣጫ ነው፡፡
ገለልተኛነት በተግባር የታየው
በ1970ዎቹ
አጋማሽ በአሜሪካን ሀገር
ከቅዱስ ሲኖዶስ ተለይተው
የቀሩትን ሁለት ጳጳሳት
ተከትሎ ነው፡፡ እነዚህ
ሁለት ጳጳሳት
በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ
ተክለ ሃይማኖት
ከሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ
ራሳቸውን በማግለል በቅዱስ
ሲኖዶስ የማይመሩ አብያተ
ክርስቲያናትን መመሥረት ጀመሩ፡፡
በወቅቱ ይህንን ተግባር
የተቃወሙት በምዕራብ ንፍቀ
ክበብ የኢትዮጵያ
ቤተ ክርስቲያን
ሊቀ ጳጳስ
የነበሩት አቡነ ይስሐቅ
ነበሩ፡፡ አቡነ ይስሐቅ
ጉዳዩን ወደ ፍርድ
ቤት አድርሰው
እስከ ማስወሰን
በመድረሳቸው ሁለቱ ጳጳሳት
‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን››
የሚለውን የቤተ ክርስቲያኒቱን
ስም በመተው
‹‹የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተ
ክርስቲያን›› በማለት እስከ
ማቋቋም ተደርሶ ነበር፡፡
በርግጥ ታሪክ ራሱን
ስለ ሚደግም
አቡነ ይስሐቅም
በተራቸው ሌሎችን ገለልተኛ
አብያተ ክርስቲያናት አቋቁመው
ነበር፡፡







