ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 25/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 1/
2012/ READ THIS
ARTICLE IN PDF)፦ በሰሜን አሜሪካ በኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ከርስቲያን በምዕራብ ስቴቶች የካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ሥር በሚተዳደሩ አቢያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚያገለግሉ ጥቂት ካህናት፤ ማኅበረ ቅዱሳንን፤ ማኅበረ በዓለ ወልድንና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤንና በጠቅላላው ለቤተ ክርስቲያናቸው የሚቀኑ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ካህናትን የሚቃወም ድብቅ ስብሰባ እየተካሔደ ነው። ድብቁ ስብሰባ ኦርቶዶክሳውያን የጡመራ መድረኮች የሆኑትን “ደጀ ሰላምን፣ አሐቲ ተዋሕዶን፣ አንድ አድርገንን፣ ገብር-ሔርንና ደቂቀ ናቡቴን” ከመናፍቃን ድረ-ገጽ ጋር በመደመር ይዘጋልን ማለታቸውን ጨምሮ በጠቅላላው ባለ ስምንት ነጥብ ደብዳቤ ጽፈው በመፈራረም ለቅዱስ ፓትርያርኩ ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ውስጠ አዋቂ ምንጮች በተለይ ለደጀ ሰላም ገልጸዋል።

“ሳይማሩ ተምረናል፣
ሳያውቁ አውቀናል”
እያሉ ሕዝቡን እየከፋፈሉት”
ነው
የሚሉት ድብቆቹ ካህናት “ማኅበራትም ሆኑ
ሰባክያነ ወንጌል ሀገረ ስብከቱ ሳያውቅና የፈቃድ ደብዳቤ ሳይዙ በየትኛውም ቤተ ክርስቲያን እንዳይሰብኩ
በቅዱስነትዎ በኩል ጥብቅ መመሪያ ለየአብያተ ክርስቲያናቱ እንዲተላለፍልን፤
ማንኛውም ሰው ወይም ማኅበር በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ምንም ዓይነት ፈቃድ እንዳይሰጥ በኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለአሜሪካን መንግሥት መመሪያ
እንዲተላለፍልን”
ሲሉ ቅዱስ ፓትርያርኩን በጥብቅ ማሳሰባችውን የተረቀቀው ደብዳቤ ይገልጣል። የዚህ
የድብቅ
ካህናቱ ስብሰባ ከተጀመረ አምስተኛ ሣምንቱን አስቆጥሯል።