Monday, July 16, 2012

በጀርመን ስለ ዋልድባ ተጠርቶ የነበረ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ በፓትርያርኩ ታገደ


ስኬቱ በምን ይሆን?? በማፍረስ እና በመከፋፈል??
(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 9/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 16/ 2012/ READ NEWS IN PDF)፦ በዋልድባ ገዳም ክልል ውስጥ መንግሥት  እሠራዋለሁ ያለውን የስኳር ፋብሪካ ግንባታ በመቃወም በጀርመን ያሉ ማኅበረ ካህናት እና ማኅበረ ምእመናን በፍራንክፈርት ከተማ ሐሙስ ሐምሌ 12/2004 ዓ.ም (ጁላይ 19/2012) በኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ተገኝተው የተቃውሞ ድምፃቸውን እንዲያሰሙ በጀርመን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ኃላፊ ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርዓዊ ተበጀ  አስተላለፈውት የነበረው የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አግባብነት እንደሌለው እና ሕዝበ ክርስቲያኑ ወደ ሰልፉ እንዲወጣ የማድረጉ ጥረት እንዲገታ ቅዱስ ፓትርያርኩ  ጥብቅ መመሪያ አስተላለፉ።
ሊቀ ካህናት መርዓዊ
ከአምባሳደር ፍሥሓ ጋር

 በቅዱስነታቸው በተፈረውና ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርዓዊ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸውን የሚያወሳው ይኸው ደብዳቤ “ሁሎችም የዚሁ ሰላማዊ ሠልፍ ተባባሪዎች እንዲሆኑ በልዩ ልዩ መንገድ እያስገደዱ መሆንዎን ከደረሰን ሪፖርት መረዳት ችለናል፤ ይህም ኢ-ቀኖናዊ የአሠራር ሒደት ዲሞክራሲያዊ አሠራር እንዳልሆነ ልንገልጽልዎ እንወዳለን” በማለት ሌሎቹ ካህናት በነፃ ያሰቡበት ሳይሆን በሊቀ ካህናቱ አስገዳጅነት እየሆነ ያለ እንቅስቃሴ መሆኑን ፍራንክፈርት ከሚገኘው የቆንስላ ጀነራል ጽ/ቤቱ የደረሳቸው መረጃ እንዳለ አመልክቷል። 

Friday, July 13, 2012

የላስ ቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ከአቡነ ፋኑኤል ጋር እንደማይሠራ በድጋሚ አረጋገጠ



  • የደብሩ ማኅበረ ካህናት የፈረሙበትን ደብዳቤ ተመልከቱ፤

(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 14/2004 ዓ.ም፤ ጁን 21/ 2012/ READ THISARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በምዕራብ አሜሪካ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሥር የሚገኘው የላስ ቬጋስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን “ከብፁዕ አቡነ ፋኔኡል ጋር እንደማንሠራ እና የሸቱትንም ሾመት የማንቀበል መሆኑን” እንገልጻለን ባለበት መግለጫው አቡነ ፋኑኤል “ከዚህ በፊት ለአህጉረ ስብከቱ ተመድበው አባታዊ መመሪያ እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩት አባቶች በተለየ መልኩ በመጓዝ ካህናት እና ምዕመናንንን በማሳዘን ለመናፍቃን በር የሚከፍት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ሥርዓት ባልጠበቀ እና ባልተከተለ መንገድ መመሪያ በመስጠት እና በተግባርም በመፈፀም የግል ጥቅምን ብቻ በሚያስጠብቅ አካሄደ በመጓዛቸው በሚሠጡት የተሣሣተ እና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የወጣ አመራር ጋር አብሮ መጓዝ ተገቢ ባለመሆኑ ከዚህ በፊት ያለንን አቋም/ አቋማችንን እንገልጻለን” ብሏል።

ጠቅ/ቤተ ክህነት “ጉባኤ አርድእት” ነን ባዮች በመንበረ ፓትርያርኩ እንዳይሰበሰቡ አገደ


·         እገዳው የተላለፈው መንግሥት ለአባ ጳውሎስ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ ነው ተብሏል።
·         በአባ ጳውሎስ ቀጥተኛ ይኹንታ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ለቀናት በኅቡእ ሲሰበሰብ የቆየው ቡድኑ÷ ከፊል መሥራች አባላቱ ከሸሹትና የስብሰባ እገዳ ከተጣለበት በኋላ÷ ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት የ‹ዕወቀኝ› ጥያቄ ማቅረቡ ተነግሯል።
·   የቅ/ሲኖዶስ እና የጠቅ/ቤ/ክህነት ጽ/ቤቶች÷ ቤተ ክርስቲያን “ጉባኤ አርድእት” የተሰኘውን ኅቡእ ቡድን እንደማታውቀው ገልጸዋል።
·     የኅቡእ ቡድኑ አስተባባሪ ፕሮቴስታንታዊው ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን በአባ ጳውሎስ ትእዛዝ የያዘውን የጠ/ቤ/ክህነቱን መኪና እንዲያስረክብ ተደርጓል።
·   አባ ጳውሎስ የእምነት ንጽሕናቸውን በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ያላረጋገጡትንና ከቡድኑ ቀንደኛ አስተባባሪዎች አንዱ የኾኑትን አባ ሰረቀን በመንፈሳዊ ዘርፍ ም/ሥ/አስኪያጅነት ለመሾም ማሰባቸው ተሰምቷል።
·    “ለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ሲባል የቡድኑን ኅቡእ እንቅስቃሴ በጥብቅ እየተከታተልነው ነው” /የጠ/ቤ/ክ መመሪያ ሓላፊዎች/።
·     “ከጉባኤው አስተባባሪዎች አብዛኞቹ በሚሠሩባቸው ቦታዎች ተቀባይነት ያጡ ግለሰቦች ናቸው” /የቋሚ ሲኖዶስ ምንጮች/።
 (ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 4/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 11/ 2012/ READ IN PDF)፦ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ራሱን “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” በሚል መጠሪያ ሰይሞ ከቤተ ክርስቲያን ማእከላዊ አስተዳደር ዕውቅናና ፈቃድ ውጭ ከፓትርያርኩ ባገኘው ቀጥተኛ ይኹንታ የአባ ጳውሎስን ዐምባገነንት ለማጠናከር፣ መንፈሳውያን ማኅበራትን ለማፈራረስ፣ የግል እና የቡድን ጥቅሞቹን ለማስጠበቅ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ መሽጎ ሲዶልት የቆየው ቡድን በየትኛውም የመንበረ ፓትርያርኩ አዳራሾች እና ቢሮዎች ለመሰብሰብ እንደማይፈቀድለት አስታወቀ፡፡

Friday, July 6, 2012

በዋልድባ ውጥረቱ ቀጥሏል. . . ESAT Radio Interview

በዋልድባ ገዳም ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው፥ እስራቱ፣ እንግልቱ፣ ማሳደዱ፣ ድብደባው በፌደራል ወታደሮች እንደቀጠለ ነው ገዳማውያኑ አባቶቻችንም ጩኽታቸውን አቤቱታቸውን በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እያስተላለፉ ነው፥ ዝምታውም ቀጥሏል መንግሥትም መፍረሱን እንደቀጠለ ነው። ዝምታችን ይብቃ ገዳማውያኑን እና ታሪካዊ ገዳማችንን እንታደግ እንተባበር። 

Monday, July 2, 2012

ለዓውደ ምሕረት የተሰጠ መልስ


ይህንን ጽሁፍ አንድ የዘወትር አንባቢያችን በመልዕክት ያደረሰሱን መልዕክት ነው፣ በአንድ ወቅት እራሱን "ዓውደ ምሕረት" ብሎ የሚጠራው ብሎግ ባወጣው ጽሁፍ ላይ የሰጡት መልስ ይመስለናል። በጽሁፉ 
በርካታ መልዕክቶች ሰፍረውበታል በተለይ እነዚህ አጽራረ ቤተክርስቲያን የሆኑ ብሎጎች የሚያስተላልፉትን መልዕክት በተቻላቸው መጠን ጥሩ ነጥቦችን ለመጠቋቆም መክረዋል እኛም አንባቢያን ቢያነቡት መልካም ነው ብለን ስላመንን አቅርበነዋል መልካም ምንባብ::


ለዓውደ ምሕረት የተሰጠ መልስ
በጣም ይገርማል እንደው በዚህ ዘመን ስንት ዓይነት ሰዎች ወይም ክፍሎች ተነስተዋል? በእውነት ሁሉስ ለቤተክርስቲያን ቆምኩ ይላል እንዴ ለቤተክርስቲያኗ የቆመ ከሆነ፣ ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ግድ የሚለን ከሆነ እስቲ ምን አደረክ? እንደ ቤተክርስቲያን ልጅነትህ? ካንተ ብዙ ባይጠበቅም ግን እንደ አንድ ሰው ለነገሩ ግብራችን ይመሰክራል የምናደርገውን የምንሠራውን የምናስበውን ጨምሮ። ዛሬ እኮ ቤተክርስቲያን ውስጥ በተለይ በቤተክህነት ውስጥ ካሉት ሠራተኞች ውስጥ ወደ 30% የሚጠጋው ኦርቶዶክሳዊ አይደለም ለምን? አንተም ኦርቶዶክሳዊ አትሸትም (ማኅበረ ቅዱሳንን) ስለምትሰድብ አይደለም በአጠቃላይ የምታደርገው የምትጽፈው ጽሁፍ በሙሉ ስለቤተክርስቲያን ታስቦ ቢሆን  ጥሩ ነው ነገር ግን ማኅበረ ቅዱሳንን ከመስደብ ብዙ የማይገቡ ነገሮችን ከመናገር ይልቅ ይሁን አንተ እንዳልከው ማኅበረ ቅዱሳን ይጥፋ እንበል ከጠፋስ በኃላ ክፍተቶቹን ማን ይሞላል ገዳማቱን ማን ይረዳል፣ ምንዱባንን ማን  ይጦራል፣ የተቸገሩትን አብያተ ክርስቲያናት ማን ጧፍ ይገዛል፣ ዘቢቡን፣ ንዋየ ቅዱሳትን ማን ይሸፍናል። እርግጠኛ ነኝ እኔ ወይም እና "ዓውደ ምሕረቶች" እንደማትለኝ ነው። ምክንያቱም ጸሎቱም ይቁም ያልክ ሰው እንዴት ነው ጧፍና ዘቢብ ገዝተሕ ታጸልያለህ ብለን እምናስበው። ያለግብሩ ማቼም ማንንም መጠበቅ እና መገመት እኮ በደል ነው አንበሳ ሁልጊዜ አንበሳ ነው አህያ ልናደርገው አንችልም የርሱ ግብር በዱር በጫካው ተሰማርቶ ደካማ የሆኑትን ነፍሳት እነ ሚዳቆን፣ ተኩላን፣ የሜዳ አህያን የመሳሰሉትን አድብቶ ሰብሮ ቆራርጦ ይበላል እንጂ ና ዛሬ አህያ ነህ እና እንጫንህ ብንለው እኛንም ሰብሮ የዕለቱ ጉርሱ እንደሚያደርገን ሳይታለም የተፈታ ይመስለኛል። 

ሰበር ዜና - የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም በፌዴራል ፖሊስ ተከቧል


·        አራት መነኰሳት በፖሊስ ተይዘው ተወስደዋል፤ ሌሎቹ መነኰሳት እየተደበደቡ ተበታትነዋል።
·        የገዳሙ የሱባኤ ወቅት በፖሊስ የኀይል ርምጃ እየታወከ ነው።
የቤተክርስቲያን ተስፋዋ ወጣቱ ትውልድ ነው! እንሥራ በጋራ
·        በዛሬማ ወንዝ ላይ የሚገነባውን የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ግድብ የሚሠራው ሱር ኮንስትራክሽን  ለቆ መውጣቱ እየተነገረ ነው፤ በምትኩ የቻይና ተቋራጭ የገባ ቢኾንም በእርሱም ላይ ተቃውሞው መቀጠሉ ተሰምቷል።
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 24/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 1/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ዓዲ አርቃይ ወረዳ የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም ከማይ ፀብሪና ዓዲ አርቃይ ወረዳዎች በአምስት መኪና ተጭነው በመጡ የፌዴራል ፖሊስ ኀይሎች ሥምሪት ውስጥ እንደሚገኝ የስፍራው ምንጮች ለደጀ ሰላምገለጹ፡፡

ቤተ ክርስቲያን “ተራሮችን አንቀጠቀጥኩ” በሚለው ወይም በ“ያ ትውልድ” ቁጥጥር ሥር፦ የዳላስ ተሞክሮ


(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 20/2010)፦ ይህ ጽሑፍ በቅርቡ በተከታታይ ስናስነብባችሁ እና በዩ-ቲዩብም ስናሳያችሁ የቆየነው “የዳላስ ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ተከታታይ” ሳይሆን ከዳላሱ ጉዳይ በመነሣት የቀረበ አጠቃላይ ምልከታ ነው። ርዕሱን የበለጠ ለመረዳት ግን ሁለት መሠረታዊ አባባሎችን መገንዘብ ያስፈልጋል። እነዚህም “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ” እና “ያ ትውልድ” የሚሉት ሐረጎች ናቸው። እነዚህ ሁለት ወካይ ሐረጎች አሁን ኢትዮጵያን በመምራት ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ እና የኢህአፓ መታወቂያዎች ናቸው። ኢሕአዴግ ስለ ራሱ ገድል ያወጣቸው የነበሩት (የነተስፋዬ ገብረ አብ) መጻሕፍት የሚታወቁት “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” በሚል ሲሆን ስለ ኢሕአፓ ታሪክ በሰፊው ያተተው የፓርቲው መሥራች ክፍሉ ታደሰ የጻፋቸው መጻሕፍት ደግሞ “ያ ትውልድ” ይባላሉ። ይህ ጽሑፍ እነዚህ ሁለት ትውልዶች ከቤተ ክርስቲያን ላይ እጃቸውን እስካላነሱ ድረስ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነጻነት እንደሌላት ለማጠየቅ ይሞክራል።

Friday, June 29, 2012

በባቦጋያ መድሃኒአለም የቦታ ጉዳይ 13 ሰዎች ላይ እያንዳንዳቸው ሰባት ወር ተፈረደባቸው

  • ከ400 በላይ ምዕመናን በእንባ ወደ እስር ቤት ሸኝተዋቸዋል፡፡
  • የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የበላይ አካል ተጽህኖ አለበት ፤

(አንድ አድርገን ሰኔ 22 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በፍርድ ቤቱ ውሳኔ በጣም አዝነናል ፤ ሲጀመር አንስቶ በባቦጋያ መድሃኒዓለም ቦታ እና በኩሪፍቱ ሪዞርት መካከል ያለው የቦታ ውዝግብ በየጊዜው ማቅረባችን ይታወቃል፤ አቅማችን በፈቀደው መጠን ጉዳዩን ሰዎች ዘንድ እንዲደርስ የመፍትሄ አካላት እንዲሆኑ ያላሰለሰ ጥረት አድርገናል ፤ ከወራት በፊት የቤተክርስትያኑን ቦታ በአካባቢው ምዕመናን ጉዳዩን ዳር እዲያደርሱ የተወከሉ ሰዎች በፍርድ ቤት “እናንተ መጠየቅ አትችሉም ቤተክርስትያኒቱ የወከለቻችሁ አካላት አይደላችሁም” በማለት ለኩሪፍቱ ሪዞርት ባለቤት እንደተወሰነለት ገልጸን ፅፈን ነበር ፤ 

ከዚህ በኋላ ምዕመኑን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተስፋ ለማስቆረጥ ወደፊት ምንም ጥያቄ እንዳይጠይቁ ለማሸማቀቅ አቶ ጌታቸው ዶኒ ፤ የሪዞርቱ ባለቤትና የፍርድ ቤት ጠበቃቸው ከባቦጋያ መድኃኔዓለም ቤተክርስትያ አስተዳዳሪ ጋር በመሆን የሀሰት ክስ ማቅረባቸውን ይታወሳል ፤ ይህ በእንዲህ እያለ አቶ ጌታቸው ዶኒ የሀሰት ምስክሮችን አስመጥቶ ፍርድ ቤት በማቆም ማስመስከሩ ይታወቃል ፤ በዚህ የፍርድ ቤት የምስክር ሂደት የቤተክርስትያኒቱ አስተዳዳሪ ፍርድ ቤት ውስጥ የሚሰሙትን ምስክርነት ለሶስተኛው ምስክር አሳልፈው ሲናገሩ በመያዛቸው ለ24 ሰዓት ታስረው በ2000 ብር ዋስ መፈታታቸው ይታወቃል ፤ ፍርድ ቤቱ እኝህን አስተዳዳሪ  አቃቢ ህግ ክስ እንዲመሰርት ቢያዝም አቃቢ ህግ ልብ አግኝቶ ይህን ሲያደርግ መመልት አልተቻለም ፤ ፍርድ ቤቱ የተቀመጠው ህግ ከባለስልጣናት ትዕዛዝ ሲበልጥበት መመልከት አልቻልንም ፤ አስተዳዳሪው ምስክሮቹ ቃላቸው አንድ አንዲሆን በማሰብ የውስጡን ለውጩ ምስክር አሳልፈው ምስክርነቱን ሲናገሩ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በዝምታ መታለፋቸው ሁሉን አስደምሟል ፤ በመሰረቱ ምስክርነት እየተሰማ ሳለ አይደለም መስካሪ የችት ታዳሚው ችሎቱን አቋርጦ መውጣት እንደሌለበት ያስቀምጣል ፤ ዳኛው  “ችሎትን በማወክ” በሚል አንቀጽ እዚያው ሌላ ፋይል ሳይከፍት የቅጣተኝነት ፍርድ ማስተላለፍ ይችል ነበር ፤

Saturday, June 23, 2012

በሙስና የሚታሙት የላፍቶ ደ/ትጉሃን ቅ/ሚካኤል አስተዳዳሪ አባ አእምሮ ሥላሴ ታከለ የአ/አ ሀ/ስብከት ም/ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ



·         የደብሩ ሰበካ ጉባኤ በአስተዳዳሪው ላይ ያቀረበው የሙስናክስ በመጣራት ላይ ነበር::
·         ወርቅ፣ የውጭ ምንዛሬና የሌሎች ነዋያት ግምት ሳይጨምር በጥሬ ብር ከ200,000 በላይ መዝብረዋል::
·         የአስተዳዳሪውን ሹመት በማስፈጸም የእጅጋየሁ በየነ ሚናአለበት::
·         የሀ/ስብከቱን ገዳማትና አድባራት ሓላፊዎች ለዐመፅ ለማዘጋጀት አባ ጳውሎስ ያሰቡት ዕቅድ አካል ይኾን?
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 15/2004 ዓ.ም፤ ጁን 22/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF):- ሰባኬ ወንጌል ከነበሩበት የመርካቶ ደብረ ኀይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን ወደ ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንተዘዋውረው በአስተዳዳሪነት ከተሾሙ ሁለት ዓመታትን  ብቻ ነው ያስቆጠሩት - አባ አእምሮ ሥላሴ ታከለ፡፡በሁለት ዓመት የደብሩ ቆይታቸው ግን ካራታቸው በመዝገብ ላይ ያልሰፈረ የወርቅ እና የውጭ ምንዛሬ ስርቆትንጨምሮ ለተፈጸሙ ሕገ ወጥ የነዋየ ቅድሳት ሽያጭ እና የሙዳይ ምጽዋት ቆጠራ እንዲሁም ያለ ደረሰኝ ገቢየመሰብሰብ ድርጊቶች ዋነኛ ተጠያቂ መኾናቸው በሰፊው ይነገራል። በደብሩ የአንድ ወገን የጎጠኝነትአስተሳሰብ እንዲስፋፋና ሌሎች በርካታ አስተዳደራዊ ችግሮችም እንዲከሠቱ ምክንያት የመኾናቸው ጉዳይአደባባይ የወጣ ምስጢር መኾኑን ብዙዎች ይመሰክራሉ።

Friday, June 22, 2012

በጀርመን የቅ/ሚካኤል በዓለ ንግሥ በመናፍቁ “ቄስ” በገዳሙ ደምሳሽ ምክንያት በውዝግብ አበቃ



(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 15/2004 ዓ.ም፤ ጁን 22/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF):- በደመቀ ሁኔታ ተጀምሮ የነበረው የቅዱስ ሚካኤል በዓለ ንግሥ ሆን ብለው ከረፈደ በቦታው በተገኙት መናፍቁ «ቄስ» ገዳሙ ደምሳሽ ምክንያት በውዝግብ አበቃ። በሀገረ ጀርመን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በኑፋቄያቸው ምክንያት በምእመናን ዘንድ ትልቅ ቁጣን እያስነሱ ያሉት መናፍቁ “ቄስ” በገዳሙ ደምሳሽ “ከልካይ የለኝም” በሚል መንፈስ በአካባቢያቸው የሚገኙ ደጋፊዎቻቸውን በአውቶብስ ጭነው ከአካባቢያቸው ወጥተው በአገልግሎት እንዳይስተፉ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ የጣሉባቸውን እግድ በመተላለፍ እሑድ ሰኔ ፲ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ በመገኘት ብጥብጥ እንዲነሳ ምክንያት ሆነዋል።


ገዳሙ ከግብር አበሮቻቸው ጋር
በጀርመን በአራቱም አቅጣጫ ካሉት የኢ/ኦ/ተ አብያተ ክርስቲያናት በኮሎኝ ከተማ የሚከበረውን ዓመታዊውን የሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልን የንግሥ በዓል ለማክበር ከዋዜማው ጀምሮ በታላቅ ቁጥር ተገኝተው የነበሩት ምእመናን በዓሉን በደመቀ ሁኔታ በማክበር ላይ ሳሉ ግለሰቡ እሑድ ጠዋት ግብር አበሮቻቸውን ይዘው በአገልግሎት ላይ ያሉ በሚመስል መልኩ ፈረጅያቸውን ለብሰው፤ ቆባቸውን አጥልቀው በቤተ ክርስቲያኑቱ የተገኙ ሲሆን ታቦተ ሕጉ ወጥቶ፤ ዑደቱ አብቅቶ፤ ምእመናኑ ቃለ ምእዳን የሚሰጥበት ቦታ በመሰባሰብ ላይ ሳሉ እኚሁ ግለሰብ ከካህናቱ ጋር ለመቆም ወደፊት ለመቅረብ በሚሞክሩበት ጊዜ በግለሰቡ በቦታው መገኘት በተለይም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በግለሰቡ ላይ የጣሉት የእንቅስቃሴ እግድ አለመከበሩ ያቃጠላቸው ምእመናን በንዴት “፤ወደ ታቦተ ሕጉ አይቀርቡም አልተፈቀዶለትም” ብለው መንገድ ዘግተውባቸዋል። በዚህ ጊዜ በዋነኝነት መንገዱን ዘግተው ወደፊት አይሄዱም ብለው ከፊታቸው የከለከልዋቸውን ጎበዝ ምእመን ገፍትረው ለመሄድ በመሞከራቸው ረብሻ እንዲነሳ ምክንያት ሆነዋል።

የላስ ቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ከአቡነ ፋኑኤል ጋር አልሠራም አለ

ከላስ ቤጋስ ሐመረ ኖህ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተጻፈው ደብዳቤ
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 14/2004 ዓ.ም፤ ጁን 21/ 2012/ READ THISARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በምዕራብ አሜሪካ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሥር የሚገኘው የላስ ቬጋስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን “ከብፁዕ አቡነ ፋኔኡል ጋር እንደማንሠራ እና የሸሙትንም ሹመት የማንቀበል መሆኑን” እንገልጻለን ባለበት መግለጫው አቡነ ፋኑኤል “ከዚህ በፊት ለአህጉረ ስብከቱ ተመድበው አባታዊ መመሪያ እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩት አባቶች በተለየ ምልኩ በመጓዝ ካህናት እና ምዕመናንን በማሳዘን ለመናፍቃን በር የሚከፍት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ሥርዓት ባልጠበቀ እና ባልተከተለ መንገድ መመሪያ በመስጠት እና በተግባርም በመፈፀም የግል ጥቅምን ብቻ በሚያስጠብቅ አካሄደ በመጓዛቸው በሚሠጡት የተሣሣተ እና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የወጣ አመራር ጋር አብሮ መጓዝ ተገቢ ባለመሆኑ ከዚህ በፊት ያለንን አቋም/ አቋማችንን እንገልጻለን” ብሏል።

Monday, June 18, 2012

አቡነ ጳውሎስ በእነ ኀይለ ጊዮርጊስ አስተባባሪነት “ጉባኤ አርድእት” የተሰኘ ቡድን እያደራጁ ነው


አርእስተ ጉዳዮች፡- (READ THIS ARTICLE IN PDF)
  • ·    አቡነ ጳውሎስ በግንቦቱ ቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መናጋቱ የተረጋገጠውን የዐምባገነንት ሥልጣናቸውን ያድሱልኛል ያሏቸውን ሦስት ቡድኖችን አቋቁመዋል፤ “ጉባኤ አርድእት” አንዱ ነው።
  • ·         የ”ጉባኤ አርድእት” መተዳደርያ ደንብ ከሰሞኑበአቡነ ጳውሎስ ፊርማ እንደሚጸድቅ እየተነገረ ነው፤ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ቢሮ ተሰጥቶታል፤ ምንጩ ያልታወቀ በጀትም ተመድቦለታል፤ 25 መሥራች አባላት እና 180 ተባባሪ አባላት እንዳሉት ተገልጧል፡፡ ቋሚ ሲኖዶሱ እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሂደቱን በትኩረት እየተከታተሉት ነው።
  • ·       ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁንን ጨምሮ በአእመረ አሸብር፣ ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ ንቡረ እድ ተስፋይ ተወልደ እና ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ የሚመራ ነው የተባለው “ጉባኤ አርድእት” የአቡነ ጳውሎስን የጠቅላይነት ሥልጣን የሚያጠናክር የሕገ ቤተ ክርስቲያን ‹ማሻሻያ› ረቂቅ አዘጋጅቷል፤
  • ·      “ቤተ ክርስቲያን ራሷ ማኅበር ስለሆነች በተቋም የተደራጀ ሌላ ማኅበር አያስፈልጋትም” በሚል እንደ ማኅበረ ቅዱሳን እና የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበርያሉትን ማኅበራት ለማዳከምና ለማፍረስ ይሠራል፤ ይህም ካልተሳካ ራሱን ወደ “ማኅበረ አርድእት” ለውጦ በማኅበራቱ ላይ የማያባራ ቀውስ ለመፍጠር ይንቀሳቀሳል፤ “ከማኅበረ ቅዱሳን ያኮረፉ” የሚባሉ ሰዎችን ሰብስቦ ማኅበረ ቅዱሳንን ማጥቃት አንዱ ስልቱ ነው፤
  • ·   በሰላም፣ ልማትና ሰብአዊ ተራድኦ ዙሪያ ከተደራጁ የወጣት ማኅበራት ጋራ እሠራለኹ በሚል አባላትን በአፈሳ ለመመልመልና መንግሥትን በማወናበድ የፖለቲካ ድጋፍ ለመሸመት ይጠቀምበታል፤
  • · በቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጠንካራ አቋም የያዙ ብፁዓን አባቶችን በፖለቲከኛነት በመወንጀል፣ በአሉባልታዎች ስማቸውን በማጥፋት፣ በየአህጉረ ስብከታቸው ሁከት በመፍጠር የተቀናጀ የማሸማቀቅ ዘመቻ ይከፍታል፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ፊልጶስ፣ አቡነ ሕዝቅኤል፣ አቡነ ቄርሎስ፣ አቡነ ናትናኤል፣ አቡነ ቀውስጦስ፣ አቡነ አብርሃም፣ አቡነ ዲዮስቆሮስ እና አቡነ ገብርኤል የወቅቱ ዒላማዎች ናቸው፤
  • ·   አቡነ ጳውሎስ የግንቦቱ ቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች በአራቱ ቃለ ጉባኤአልፈረሙም፤ ቋሚ ሲኖዶስ ፓትርያርኩ አራቱንም ቃለ ጉባኤ ካልፈረሙ በእርሳቸው ርእሰ መንበርነት እንደማይሰበሰብ በመግለጽ አቡነ ጳውሎስን አስጠንቅቋል፤
  • ·    በአቡነ ጳውሎስ ደብዳቤ “በጄነራል ዳይሬክተር ማዕርግ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግሥት ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት” እንደተሰጠው የሚነገርለት የ”ጉባኤ አርድእት” ቀንደኛ አስተባባሪ ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን “ጉባኤ እግዚአብሔር” (Ethiopia Assemblies of God) የተሰኘ የፕሮቴስታንት ቤተ እምነት እንደሚያዘወትር፤ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነቱ ተወግ የተባረረውን የሃይማኖተ አበው አባላት በጎጠኝነት ስሜት እያነሣሣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመመለስ እየዶለተ መኾኑ ተገልጧል፣