Saturday, June 16, 2012

ቅ/ሲኖዶስ በተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነት ያወገዛቸው 7 ድርጅቶችና 16 ግለሰቦች ውሳኔ ለአህጉረ ስብከት ተሰራጨ

·         መናፍቃኑ በማንኛውም የቤተ ክርስቲያናችን የክህነት፣ የክብርና የማዕርግ ስም አይጠሩም።
·         የቤተ ክርስቲያኒቱን የከበረ ስሟን በማጉደፍ ታሪኳንና ክብሯን በመዳፈራቸው በሕግ ይጠየቃሉ።
·         መናፍቃኑ እና ድርጅቶቹ ላሰራጯቸው ኅትመቶች የማስተባበያ ጽሑፎች ይዘጋጃሉ።
·         ሊቃውንት ጉባኤ ከማንኛውም አካል ለሚሰነዘረው ሃይማኖት የሚያጎድፍ ክብረ ነክ ጽሑፍ ምላሽ ለመስጠት በሚችልበት አኳኋን በጥራትና በስፋት ይጠናከራል።
·         ከተወገዙት ድርጅቶች መካከል የ”አንቀጸ ብርሃን” ድርጅት መሥራች በኾነውና በእጅጋየሁ በየነ አቅራቢነት የፓትርያርኩ መልእክቶች ጸሐፊ እስከመኾን ደርሶ በነበረው አሸናፊ መኰንን ላይ የተላለፈውን የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ለመቀሠጥ የተደረገው የሸፋጮች ሙከራ ከሽፏል (ሙከራውን የሰነዱን ገጽ 38 እና 39፣ ተ.ቁ 16ን በማነጻጸር ይመልከቱ)
·         “አሁን የተሐድሶ መናፍቃኑ ዝናራቸውን ጨርሰው የአገልጋዮችን ስም ማጥፋቱን ተያይዘውታል፤ ያወገዝናቸው ስለጠላናቸው ሳይሆን ስለካዱ ነው፤ ሰውን ማስታመም የሚቻለው በምግባር ድክመቱ እንጂ በሃይማኖት ክሕደት አይደለምና፡፡” /ብፁዕ አቡነ አብርሃም የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ለሀ/ስብከታቸው ሰባክያነ ወንጌል እና ምእመናን ይፋ ሲያደርጉ ከተናገሩት/
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 9/2004 ዓ.ም፤ ጁን 16/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያንና ለሃይማኖት ጉዳይ በተለይም ለምእመናን አንድነት ቅድሚያ በመስጠት፣ በጉዳዩ ላይ በስፋት በመነጋገር፣ ግንቦት 15 ቀን 2004 ዓ.ም፣ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች እና መጽሐፎቻቸው ላይ በአንድ ድምፅ ያስተላለፈውን የውግዘት ውሳኔ የያዘው ቃለ ጉባኤ ለመላው አህጉረ ስብከት ተሰራጨ፡፡
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሰኔ 7 ቀን 2004 ዓ.ምሰ ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ 48 አህጉረ ስብከት ባሰራጨው ቃለ ውግዘት የተካተቱት መናፍቃን ድርጅቶች ሰባት ሲኾኑ የግለሰቦቹ ብዛት ደግሞ 16 ነው፡፡

Friday, June 15, 2012

የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ካህናት፣ ሰበካ ጉባኤና ሰንበት ት/ቤት በ”ችግር ፈጣሪው” አስተዳዳሪ አባ ሚካኤል ታደሰ ታውከዋል


 READ THIS ARTICLE INPDF.
·        በአስተዳዳሪነት የተሾሙት ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንና ቃለ ዐዋዲውን በመጣስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች ተገዥ ባለመኾናቸው ማዕርገ ክህነታቸው ተሽሮ በሥልጣነ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ከተወገዙ በኋላ ነው።
·         ሀ/ስብከቱ የሀብት ቁጥጥርን ለማጠናከር ያስተላለፈውን መመሪያ በመጣስ ዘረፋን ያበረታታሉ።
·        ሰንበት ት/ቤቱን ‹ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው› በሚል አገልግሎቱን የሚያደናቅፉ ርምጃዎች ወስደዋል።
·        አስተዳዳሪው ከአባ ጳውሎስ የኤጲስ ቆጶስ ሢመት ተስፈኞች አንዱ ናቸው።

(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 8/2004 ዓ.ም፤ ጁን 15/ 2012/) በማዕርገ ዲቁናቸው በእቲሳ ደብረ ጽላልሽ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም በዐቃቢነት አገልግለዋል፡፡ ያን ጊዜ ስማቸው ዲያቆን ሙሉነህ ታደሰ ይባል ነበር፡፡ በገዳሙ ማዕርገ ምንኵስና ሲቀበሉ ስማቸው አባ ኀይለ ኢየሱስ ታደሰ መባሉን የገዳሙ አስተዳደር በቁጥር 79/05/98 በቀን 16/05/1998 ዓ.ም የሰሜን ኦሞ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የግለሰቡን ማንነት አስመልክቶ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሰጠበት ደብዳቤ ያስረዳል፡፡

Monday, June 11, 2012

ዝቋላን መልሰን እናልማ


“ይህን ቦታ ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ ሃላፊነት አለብን”
(አንድ አድርገን ሰኔ 4 ፤ 2004 ዓ.ም )፡- የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መጋቢት 9 ፤2004 ዓ.ም ለቀናት በዘለቀው እና ለማጥፋት አዳጋች የሆነው እሳት ደኑ ላይ ብዙ ጉዳት እንዳደረሰ ይታወቃል ፤በጊዜው እሳቱን ለማጥፋት በርካታ ምዕመናኖች ከአዲስ አበባ ፤ ከአዳማ እና ከደብረዘይት ወደ ቦታ አምርተውየተቻላቸውን ሁሉ አድርገው እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ እሳቱን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ይታወቃል ፤ይህን በእሳት ምክንያት ገዳሙ ያጣውን ደን መልሶ ለማልት የ‹‹ደጆችሽ አይዘጉ›› መንፈሳዊ ማህበር የመጀመሪያዙር የዛፍ ተከላ ፕሮግራም ሰኔ 24 እና ሰኔ 25 ቦታው ድረስ በመሄድ በሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናና የሚሳተፉበትየጉድጓድ ቁፋሮ እና ዛፎችን የመትከል መርሀ ግብር አውጥቷል በዚህ የተቀደሰ መንፈሳዊ አገልግሎት ገንዘብያላችሁ በገንዘባችሁ ጉልበት ያላችሁ በጉልበታችሁ ትሳተፉ ዘንድ ጥሪያቸውን ያስተላልፋሉ ፤ ይህን የዛፍ ተከላፕሮግራም ለመርዳት የምትፈልጉ ሰዎች ችግኞችን በመግዛት ፤ ብር በማዋጣት እና ቦታው ድረስ በመሄድ የጉልበትአገልግሎት መስጠት ይምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሐድሶ እንቅስቃሴ አለን? ዓላማውና ስልቱስ ምንድን ነው?


ሰኔ 11 ቀን 2003 ዓ.ም
/ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ግንቦት፣ 2003 ዓ.ም/ አትምኢሜይል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን “መታደስ አለባት” የሚሉ ድምፆችን     የሚያሰሙ አካላት አሳባቸውን በተለያዩ መንገዶች ማሰማት ከጀመሩ ውለው አድረዋል፡፡ እነዚህ አካላት በመጽሔቶች፣ በጋዜጦች፣ በመጻሕፍት፣ በበራሪ ወረቀቶች፣ በዓውደ ምሕረት ስብከቶችና በሚያገኟቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ይኸን ጩኸታቸውን ማስተጋባቱን       ተያይዘውታል፡፡ እንዲህ እያሉ ያሉትም “ኦርቶዶክሳውያን ነን” እያሉ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በተለያየ ቦታና ሓላፊነት ላይ ካሉና እንጀራዋን ከሚበሉ፣ ጥቂቶች እንዲሁም ደግሞ በኅቡእና በግልጽ በተለያየ መልክና ቅርጽ ራሳቸውን አደራጅተው ቤተ ክርስቲያኗ ሳትወክላቸው እርሷን ወክለው፣ “እኛም ኦርቶዶክስ ነን” በሚል ካባ ራሳቸውን ደብቀው እምነቷንና ሥርዓቷን “ይህ ሳይሆን ሌላ ነበር” እያሉ ፕሮቴስታንታዊ ትምህርትና መንፈስ የተዋረሳቸው ሰዎች ናቸው፡፡
 
ተሐድሶ የሚባል ነገር አለን? እነዚህ አካላት በአንድ በኩል ተሐድሶ የሚባል ነገር እንደሌለና ተሐድሶ የሚባለው ጉዳይ የሆነ አካል (እነርሱ እንደሚሉት ማኅበረ ቅዱሳን) ስም ለማጥፋት ሲል የፈጠረው የፈጠራ ወሬ እንጂ በሕይወት የሌለ ምናባዊ ነገር እንደሆነ ያስወራሉ፣ ይናገራሉ፡፡ ግን በእውነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዶግማዋ፣ ቀኖናዋና ትውፊቷ መታደስ አለበት በማለት የሚሠራ የተሐድሶ እቅስቃሴ የለምን?

ይህን ጉዳይ እነርሱው በይፋ ካወጧቸው የኅትመት ውጤቶቻቸው ለመመልከትና ለመታዘብ ይረዳ ዘንድ ራሳቸው በተለያዩ መጻሕፍቶቻቸው፣ መጽሔቶቻቸውና ጋዜጦቻቸው ካወጧቸው መካከል የተወሰኑትን ብቻ እንመልከት፡-
hohitebirhan.jpg
“እንደ እውነቱ ከሆነ በወንጌል እውነት ከታደሱ በኋላ በየጊዜው እየተመዘዙ የወጡት ምእመናኖቿና አገልጋዮቿ በውስጧ ቆይተው የተሐድሶን ሥራ እንዲሠሩ ቢደረግ ኖሮ፣ በወንጌል ተሐድሶ ያገኙ ክርስቲያኖች ለዓመታት የጸለዩበትንና የጓጉለትን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ በቅርብ ጊዜ ሊያዩ ይችሉ እንደ ነበር የሚያምኑ ጥቂቶች አይደሉም፡፡” (ኆኅተ ብርሃን፣ መጋቢት 2002፣ ገጽ 15)

ኢትዮጵያ ግብረሰዶምንና አራማጆቹ ምዕራባዊያንን አወገዘች!

ትናንት በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በ‹‹ግብረሰዶምና ተያያዥ ማኅበራዊ ቀውሶች›› ላይ ለመነጋገር በተጠራው አገራዊ ኮንፈረንስ የተገኙት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የፓርላማ አባላት፣ ወጣቶችና ሌሎች የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ‹‹ግብረሰዶምንና ግብረሰዶም የሚያስፋፉ ምዕራባዊያንን›› አወገዙ፡፡ በዚሁ ታሪካዊና አንገብጋቢ በተሰኘው አገራዊ ኮንፈረንስ ላይ ከ2,000 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ አምስቱ ዋና ዋና የሃይማኖት ተቋማት የኦርቶዶክት ተዋህዶ፣ የእስልምና፣ የካቶሊክ፣ የወንጌላዊት መካነ ኢየሱስና የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ያወጡትን የግብረሰዶማዊነት የተቃውሞ መግለጫ በአንድ ድምፅ እንደግፋለን ብለዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነትን ካልተቀበላችሁ በማለት የሰብዓዊ መብት ጥያቄ የሚያነሱና ዕርዳታ እንከለክላለን ለሚሉ የምዕራብ አገሮችም ‹‹ዕርዳታቸው በአፍንጫችን ይውጣ›› የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ 

በስብሰባው ላይ የተገኙት የሃይማኖት ተቋማትን በሙሉ ወክለው ጉባዔውን በፀሎት የከፈቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት ሕግ ሳይጻፍ ጊዜ ጀምሮ ከእግዚአብሔር ጋር ትውውቅ ነበራቸው፤ የዛሬ ሳይንቲስቶችም ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ መሆንዋን ይናገራሉ፤›› በማለት በዓለም ላይ ያሉ ሕዝቦች በሙሉ እርስ በርስ ተረጋግጠዋል፤ ብቸኛ ነፃ አገር ኢትዮጵያ ነች ብለዋል፡፡ ‹‹አሁንም የተረገጡትና የማንነት ቀውስ ያለባቸው ወገኖች ተናገሩ ብላ የምትሰማ አይደለችም፡፡ ባህላችን አልተለወጠም፣ ታሪካችን አልተቀነሰም፣ ማንነታችን አልተበረዘም፤ እንዲሁ ዝም ብለን የምንለወጥ አይደለንም፤›› ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ 

Sunday, June 10, 2012

በዋልድባ ጉዳይ ከ20 በላይ ወጣቶች ታስረዋል

(አንድ አድርገን ግንቦት 2 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የዋልድባ ገዳም ጉዳይ አሁን ወደ ሌላ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል ፤ የመወያያ መድረኮች ውጤት እያመጡ አይደሉም ፤ መንግስት ዘነዘና የዋጠ ይመስል የአቋም ለውጥ ማድረግ ተስኖታል ፤ የሚሰራውን ስራ አሁንም ገዳሙ ላይ ተጽህኖ የለውም ብሎ አምኗል ፤ ባሳለፍነው ሳምንት ከ3ሺህ የሚበልጥ የአካባቢው ነዋሪ ተቃውሞውን በቦታው ላይ መግለጹን ገልጸን ነበር ፤ ከዚህ ተቃውሞ በኋላ 10 የሚሆኑ የገዳሙ አባቶችን የአካባቢው ባለስልጣናት ሰብስበው አነጋረዋቸው እንደነበረ ለማወቅ ችለናል ፤ በቀጣይ ሰኔ 7 ፤ 2004 ዓ.ም ተጨማሪ የስብሰባ ፕሮግራም መያዛቸውን ጭምር ፤ ከዚህ በፊት የተደረጉት የስብሰባ ውጤቶች መስማት ባንችልም አሁንም ስብሰባዎች እየተደረጉ ናቸው ፤ ከእነዚህ ስብሰባዎች በተጨማሪ ባሳለፍነው ረቡዕ የአካባቢውን ወጣቶች በመሰብሰብ ስለ ግድቡ ለማወያየትም ባለስጣናቱ ሞክረው ነበር ፤ በስብሰባው ላይ የተገኙት በርካታ ወጣቶች ስብሰባውን አድርገው ከጨረሱ በኋላ በያዙት አቋምና ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ አማካኝነት ከየቤታቸው እና በተገኙበት እየተለቀሙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው  ወደ እስር ቤት ገብተዋል  ፤ ለእስር የሚፈለጉ ሰዎች ወሬው እንደደረሳቸው ግማሾቹ ጎንደርና ሌሎች ቦታዎች ሲሸሹ ብዙዎች ደግሞ “ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?” ወደ ሮሜ ሰዎች 8 ፤ 35 በማለት መታሰርን መርጠው እዚያው አሳሪዎቻቸው ይጠባበቃሉ ፡፡ ጉዳዩ የእምነትና በእምነት ስለሆነ የሚመጣውን ነገር ሁሉ ለመቀበል ተዘጋጅተዋል ፤  ወንጌሉ እንዲህ ይላል “ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ” ማቴዎስ ወንጌል 10፤28

Friday, June 8, 2012

እውን የማኅበረ ቅዱሳንና የኦርቶዶክስ "ተሐድሶ" ፍልሚያ ወይስ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ህልውና ጉዳይ?


(አዲሱ ተስፋዬ/ READ IN PDF):- ከትላልቆቹ ያገራችን ባለስልጣናት ጀምሮ ታች እስካለው ሕዝብ ድረስ  ማኅበረቅዱሳን  የበርካቶች መነጋገርያ ከሆነ ከራርሟል:: የሰሞኑን ግን ለየት የሚያደርገው ራሱን " ኦርቶዶክስ “ተሐድሶ” "በማለት የሚጠራው ድርጅት በማኅበሩና በተዋሕዶ እምነታቸው ላይ ጽኑ አቋም ባላቸው  የኦርቶዶክስ ሃይማኖትአባቶች ላይ ለማንበብ የሚዘገንኑ (character assassinating) ጽሑፎችን እያስነበበ ነው ። ከዚህም አልፎ የ”ተሐድሶ”  ቡድኖችንና አቡነ ጳውሎስን የተቃወሙ አባቶች ላይ ስማቸውን የሚያጠፋ በርካታ መጽሀፍትእስከመታተም ተደርሷል (አቡነ ሳሙአልን አቡነ አብርሃምን አቡነ ሚካኤል እና ሌሎች ጳጳሳትን ስም እያጠፉ የወጡትመጻህፍትን ያስታወሷል) አንዳንድ ሃላፊነት የጎደላቸውና የድረገጻቸውን traffic rank ከመጨመር የዘለለ አርቀውማሰብ የተሳናቸው የፖለቲካ ዌብሳይቶችም እነዚህኑ ጽሑፎች በየድረ ገጻቸው ላይ በመለጠፍ ለብዙዎች አስነብበዋል።
ጽሑፎቹን ያነበቡ በርካቶች የዋሀንም የችግሩን መሰረታዊ ምክንያት ባለመረዳት "የ”ተሐድሶ” ና የማኅበረ ቅዱሳንጦርነት"በማለት እንደዘበት ሲመለከቱትና ሲገረሙበት ይስተዋላል። ውስጠ ሚስጥሩን ያወቁና ውዝግቡ "የውክልናጦርነት " መሆኑን የተገነዘቡ ጥቂቶችም የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን “ህልውናዋን ጥያቄ ውስጥ ያስገባ”  ችግርውስጥ መግባቷን ይተነትናሉ። ለመሆኑ ግን የማኅበረ ቅዱሳንና የ”ተሐድሶ”  ገመና ምን ይመስላል? ። ከሁለቱምበስተጀርባ ያለው አካል ማነው? የሁለቱ አካላት መሰረታዊ አለመግባባትስ ምክንያቱ  ምንድነው?

ስኳር



clik here for pdf 
አንድ መምህር ሁለት ትልልቅ የመስተዋት ገንቦዎች ይዞ ወደ ክፍል መጣ፡፡ ሦስት   ተማሪዎች ደግሞበካርቶን ሌሎች ሦስት ነገሮችን ተሸክመውለታል፡፡ ተማሪዎቹ ከመቀመጫ ተነሥተው ተቀበሉት፡፡
መምህሩ ትልልቁን የመስተዋት ገንቦዎች በተማሪዎቹ ፊት ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው፡፡ ሦስቱንካርቶኖቹን ደግሞ በጎን አደረጋቸው፡፡ መጀመርያ ትልልቅ ድንጋዮች አነሳና በአንደኛው የመስተዋትገንቦ ውስጥ እስካፉ ድረስ ከተታቸው፡፡ ከዚያም ተማሪዎቹን አንድ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡
 «ይህ የመስተዋት ገንቦ ሙሉ ነውን?´
ተማሪዎቹም በአዎንታ ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡
ከዚያም ቀጠለና ትንንሽ የከበሩ ድንጋዮችን አንሥቶ ወደ መስተዋቱ ገንቦ ውስጥ ከተታቸው፡፡በድንጋዮችና በድንጋዮቹ መካከል በሚገኙ ባዶ ቦታዎች ወስጥ እየገቡ የከበሩት ድንጋዮች ገንቦውንሞሉት፡፡ መምህሩም ተማሪዎቹን በድጋሚ ጠየቃቸው፡፡
«አሁንስ የመስተዋቱ ገንቦ ሙሉ ነውን?´
ተማሪዎቹም ሙሉ መሆኑን ተናገሩ፡፡

Thursday, June 7, 2012

በአንድ አይናችን በቤተክርስትያን በአንዲት እምነታችን በተዋህዶ አትምጡብን!


(አንድ አድርገን ግንቦት 30 ፤ 2004ዓ.ም)፡- በቤተል ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን በቦታ ጉዳይ በተነሳው ግጭት በርካቶች ተጎድተዋል ፤ በዚህ ቦታ ይገባኛል በማለት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማው ህጋዊ ካርታ ሲኖረው ቤተክርስትያኒቱም ህጋዊ ካርታ እጇ ላይ ይገኛል ፤ የአካባቢው ሰው በቦታው አማካኝነት ክፉኛ ስለተበሳጨ የሚሆነውን ነገር ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በአትኩሮት ሲከታተል ነበር ፤ ማክሰኞ እለት በልበ ሙሉነት ምንም እንደማይሆኑ ከክፍለከተማ የተወከሉ ሰዎች እና ጥቂት ፖሊሶች ስራቸውን ቦታው ላይ ሲጀምሩ ተቃውሞ ከምዕመኑ ማስተናገድ ጀመሩ ፤ የነበረውን ሰው ለመበተን  ሲሞክሩ በያዙት የፖሊስ ሀይል ስላቻሉ ተጨማሪ የፖሊስ ኋይል ከአካባቢው  ጣቢያ እንዲመደብላቸው በመጠየቅ ከ40 የሚበልጡ ፖሊሶች በአካባቢው ላይ ከደቂቃዎች በኋላ መምጣት ችለው ነበር ፤ እነዚህ ፖሊሶች የመጡት ከአንድ መሳሪያ እና ከፖሊስ ዱላ ጋር ብቻ ስለነበረ ከህዝቡ የሚወረወረውን ድንጋይ መቋቋም ሲያቅታቸው ለፌደራል ፖሊስ አድማ በታኝ ልዩ ኋይል በመገናኛ ሬዲዮ በመነጋገር የችግሩን ጥልቀት በማስረዳት ኋይል እንዲጨመርላቸው ጥያቄ አቀረቡ ፤ በዚህ ጊዜ በቦታው ላይ የነበረው ፖሊስ ወደ አርባ ቢጠጋም የህዝቡን ተቃውሞ ግን መመከት አልቻሉም ነበር ፤ ይህ የሚያሳየው ከ40 በላይ ፖሊሶች መቆጣጠር ያልቻሉት የህዝብ ተቃውሞ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ነው፡፡  

Wednesday, June 6, 2012

በደብረ ይድራስ ቅ/ጊዮርጊስ ተቃዋሚዎችን ለመበተን የተሰማራው ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ ይዞ ቤተ መቅደስ ገባ


  • በአስለቃሽ ጢሱ ጸሎተ ቅዳሴው ታጉሏል፤ ሕፃናት፣ ምእመናንና አገልጋዮች ታፍነዋል::
  • ለውዝግቡ መፍትሔ ያፈላልጋል የተባለ ጥምር ኮሚቴ ተቋቁሟል::
  • ከ70 - 80 የሚደርሱ የደብሩ ሠራተኞችና ምእመናን እንደታሰሩ ናቸው::
  • ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ሊቀ ጳጳሱን በስልክ አነጋግረዋል::

(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 29/2004 ዓ.ም፤ ጁን 6/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከይዞታ ማስከበር ጋራ በተያያዘ ትናንት፣ ግንቦት 27 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት በአጥቢያው ምእመናን መካከል ግጭት ተቀስቅሷል፤ በግጭቱ የአንድ ፖሊስ ሕይወት አልፏል፤ ስድስት ፖሊሶችና በርካታ ምእመናንም ተጎድተዋል፤ ብዙዎቹን የደብሩ ሰበካ ጉባኤ አባላትንና ሌሎች ሠራተኞችን ጨምሮ በቁጥር ከ70 - 80 የሚሆኑ የአጥቢያው ወጣት እና አዛውንት ምእመናን ከየመንደሩ በፌዴራል ፖሊስ አባላት እየተሰበሰቡ መታሰራቸው ነው የተነገረው፡፡

ግጭቱ እየቀጠለ በነበረበት ኹኔታ ለጸሎተ ቅዳሴ የተሰበሰበውን ሕዝብ ለመበተን በሚል ፖሊስ ወደ ቤተ መቅደሱ ዘልቆ በመግባት አስለቃሽ ጭስ መጠቀሙ ተመልክቷል፤ በዚህም በመካሄድ ላይ የነበረው ጸሎተ ቅዳሴ ታጉሏል፤ ለቍርባን የተዘጋጁ ሕፃናት፣ ሌሎች ምእመናንና አገልጋዮችም በጭስ የመታፈን አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡ የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ በሮችና መስኰቶች መንሥኤው ለጊዜው ባልታወቀ ኹኔታ የተበሳሱና የተሰባበሩ ሲሆን የደብሩ አስተዳደር ቢሮዎች፣ የጥምቀተ ክርስትና ቤትና ሌሎችም በሮች “የተደበቁ ሰዎችን ለማሰስ” በሚል መዝጊያዎቻቸው እየተሰበረ ፍተሻ እንደተካሄደባቸው ተገልጧል፡፡

Tuesday, June 5, 2012

የዋልድባን ገዳም እናድን የሚሉ ሰላማዊ ሰልፎች በዓለም ዙርያ ሲካሄዱ ውለዋል




 Addisu Abebe | Washington From VOA news

ሙሉውን ዘገባ ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ፡

ዛሬ ማለዳ ከዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ተነስቶ ወደ ውጪ ጉዳይ መሥራ ቤት የተጓዘውን የዋሽንግተኑን ሰልፍ ተከታትለን ነበር

Saturday, June 2, 2012

ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የአሜሪካ 3ቱ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆነ


(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 24/2004 ዓ.ም፤ ጁን 1/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በተሐድሶነቱ የሚታወቀውና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወ/ሮ እጅጋየሁን ተክቶ የፓትርያርኩ ቀኝ እጅነትን የተረከበው ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን በአቡነ ጳውሎስ ፈቃድ በአሜሪካ የሚገኙት የሦስቱም አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ መሾሙን ምንጮቻችን እየገለፁ ነው። ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በአሜሪካ ሥራ አስኪያጅነትን ሥልጣን ተረክቦ እንዲሠራ የተሾመው ኃ/ጊዮርጊስ በተሐድሶ እምነት አራማጅነቱ በግልጽ የሚታወቅና ዓላማዎቹን እና እምነቶቹን በተለያዩ የተሐድሶ ብሎጎቸ በይፋ በማስተላለፍ የሚታወቅ፣ ከዚያም አልፎ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ከተሐድሶዎቹ ብሎጎች ጋር በማገናኘት ደብዳቤዎቻቸው በዚያ እንዲስተናገዱ እና ምእመኑ ከንጽሕት እምነቱ ተናውጾ በኑፋቄ ትምህርት እንዲበከል ከፍተኛውን እንቅስቃሴ የሚያድርግ ግለሰብ መሆኑ ይታወቃል።