በስዊዲኗ
የስቴክሆልም ከተማ በመጪው እሑድ “ይከፈታል” የተባለ ቤተ ክርስቲያንን አስመልክቶ ምእመናን ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው።
የተቃውሟቸውን እና ምክንይቱን ዝርዝር እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
ቸር
ወሬ ያሰማን፤ አሜን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ለሥጋዊ ጥቅምና ለበቀል ብቻ ሲባል ቤተክርስቲያን ”የመክፈት” እንቅስቃሴ፣ በስቶክሆልም ስዊድን
![]() |
| በስቶክሆልም ስዊድን የሚገኘው የደብረ ሰላም መድኅኔዓለም ቤተክርስቲያን |
ውድ አንባቢያን በቅድሚያ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ እያልን:- የዚህ ጽሑፍ ዓላማ የግለሰቦችን
ስም እያነሱ ማሳጣት ሳይሆን እያካሄዱት ያሉትን ሥጋዊ እና ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ እኛ የተረዳነውን ያክል ለሌሎች ምእመናን
እንዲሁም ለአባቶቻችን ካህናት አሳውቀን በአንድነት ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ለማስከበር እንድንነሳ መሆኑን እንድትረዱልን
በአክብሮት እንጠይቃችኋለን።
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነን ”ኢትዮጵያ ዛሬ” በሚባል ድረ ገጽ ላይ አንድ ”መንፈሳዊ” ጥሪ መመልከታችን ነው
(አወዛጋቢውን ደብዳቤ ለማንበብ ይጫኑ )። ማስታወቂያው ”ታላቅ የምስራች ለሁሉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ለሆናችሁ በሙሉ”
በማለት ይጀምራል:: ከዚያም ወደ ዉስጡ ሲገባ የሚነበብዉ ነገር ለህሊና የሚከብድ፤ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ የሆነ፤ የቤተክርስቲያንን
ሥርዓት፣ ከዚያም አልፎ የምእመናንን አንድነት የሚንድ እኩይ ተግባር ሆኖ እናገኘዋለን:: ማስታወቂያው ሲነበብ “...
በስቶክሆልም ስዊድን ሶላንቱና ሴንትሩም አካባቢ በዓይነቱ ልዩ የሆነና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማና
ቀኖና መሠረት የሚመራ፤ በካህናት አባቶች የተመሠረተ፤ ንብረትነቱም ሆነ ባለቤቱ በግልጽ በስቶክሆልም ስዊድን በስደት የሚኖረው
ኢትዮጵያዊ ሕዝብ የሆነ ቤተክርስቲያኑ የሚገኝበት የቦታው አቀማመጥ በዓይነ ሕሊናችን ወደ ሀገራችን ታላላቅ የእምነት ገዳማት
የሚያስጉዝ በውስጥ አደረጃጀቱ ብቃት ያለዉ... ወዘተ” በማለት ጸሐፊዉ ”በአይነቱ ልዩ የሆነ ቤተክርስቲያን
” ”እንደሚከፈት” ያትትና በዕለቱ የቅድስት ድንግል
ማርያምን ፤ የአቡነ ተክለሐይማኖትንና የአቡነ አረጋዊን የቃል ኪዲን ታቦታት አካትቶ የያዘ አዲስ
ቤተክርስቲያን የፊታችን ሚያዝያ 21/ 2004 ዓ.ም ወይም እ.ኤ.አ. ኤፕሪሌ 29/ 2012፤ እሁድ በብፁዕ አቡነ
ኤልያስ ጸሎትና ቡራኬ ተመርቆ ”ይከፈታል” ብሎ ጥሪዉን ያጠናቅቃል::











