ባለፈው ጥቂት ወራት ውስጥ እንደዘገብነው የብዙ ሊቃውንት መፍለቂያ፣ የቅዱሳን ማረፊያ፣ እንዲሁም ለሃገራችን ኢትዮጵያ እና ለመላው ዓለም የሚማልዱ ገዳማውያን የጸሎት ቦታ እና የአምልኮ ቦታ የሆነው ጥንታዊው የዋልድባ ገዳም በገዛ ሀገራችን መንግስት ይልቁንም በቤተክህነት ውስጥ ባሉ የውስጥ የመናፍቃን ቅጥረኞች እና ሃይማቷን ለመበረዝ እና ታሪክን እና የታሪክ አሻራን ለማጥፋት የሚሯሯጡ ወገኖች በፈጠሩት ግልጽ ወረራ በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስቲያኒቷን ያለ ተተኪ ሊቃውንት እና መነኩሳት ለማስቀረት የሞት ሽረት ትግላቸውን እየታገሉ ነው። በመሠረቱ የቤተክነቱ ሰዎች ለቅዱስ ፓትሪያሪኩ ጀምሮ በሞላው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተከታታይ በተለያዩ በኢትዮጵያ ገዳማት ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ ወረራ፣ ዘረፋ፣ የእሳት ቃጠሎ፣ የተለያዩ የአብነት ት/ቤቶችን መዝጋት፣ አሁን ደግሞ ጭራሽ የገዳሙን ሕልውና ማሳጣት ይህ ሁሉ በደል ለቅድስት ቤተክርሲያናችን ተተኪ ጳጳሳትን፣ ፓትሪያሪክን እንዲሁም ባለ ብዙ ሙያ ሊቃውንትን የሚያፈሩት ገዳሞቻችን ሲፈተኑ ምነው ዝምታ አበዙ?
Monday, March 5, 2012
Friday, March 2, 2012
ጌታቸው ዶኒ እንደገና ወደ ዜና ብቅ ሲል
· ዳግመኛ በተሾመበት ደብር የተቀሰቀሰው የምእመናን ተቃውሞ
ተጠናክሯል።
· የደብሩ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እስርና ማስፈራሪያ
እየተፈጸመባቸው ነው።
(ደጀ ሰላም፣ የካቲት 21/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 29/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በግንቦት 2003 ዓ.ም የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ራሳቸውን “ወንጌላውያን” ብለው
ከሚጠሩ የፕሮቴስንታት አብያተ እምነት ጋር ያለው የዓላማ ግንኙነት በማስረጃ የተረጋገጠበት፣ በሕገ
ወጥ የማጥመቅ ሥርዐትና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ጉልሕ ሃይማኖታዊ ሕጸጽ የፈጸመው ሊቀ ካህናት ጌታቸው ዶኒ ቀደም ሲል
በአበው ካህናት እና ምእመናን ከፍተኛ ተቃውሞ ወደተባረረበት የቃሊቲ ደብረ ገነት ቁስቋም ማርያም እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ
ክርስቲያን ተመልሶ አጥቢያውን እንዲያስተዳደር በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ መሾሙ ተሰምቷል፡፡የአሰቦት ገዳም ለሁለተኛ ጊዜ ተቃጠለ . . .
·
ማኅበረ መነኮሳቱ አስቸኳይ ርዳታ ጠይቀዋል።
·
ከብት ዘራፊዎችና ከሰል አክሳዮች የቃጠሎ መንሥኤዎች ናቸው
ተብሏል።
·
‹‹ውኃ የለንም፤ የሚረዳን ሰውም የለንም፤ እሳቱ ወደ ትልቁ
ደንና ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን እየተቃረበ በመሆኑ ከፍተኛ ርዳታ ያስፈልገናል›› /የገዳሙ መነኮስ/
·
ገዳሙ በግራኝ ወረራ የመጥፋት፣ በኢጣልያ ወረራ የመዘረፍ
አደጋ ገጥሞት ነበር፤ ከ20 ዓመት በፊት ‹‹የኦሮሚያ ነጻነት እስላማዊ ግንባር/ጃራ/›› ገዳሙን ወርሮ
በአካባቢው የሚኖሩ 16 ክርስቲያን አባ ወራዎችን አርዶ ነበር።
(ደጀ ሰላም፣ የካቲት 21/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 29/2012/READ THIS NEWS
IN PDF)፦ እንደጥድ፣ ዝግባ፣ ወይራ፣ ግራር፣ ብሳና፣ ቀረሮ በመሳሰሉት
አገር በቀል እና ዕድሜ ጠገብ ዛፎች የተሞላውን በአጠቃላይ 13ሺሕ
ሄ/ር መሬት ያህል ይሸፍን እንደነበር የሚነገረው የአሰቦት ደብረ
ወገግ ቅድስት ሥላሴ እና አቡነ ሳሙኤል ገዳም በአራት ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በተቀሰቀሰ ሰደድ እሳት እየጋየ መኾኑ ተሰማ፡፡
Friday, February 24, 2012
ምክር
፩፦ ምክር
የሰው ልጅ ከልጅነት እስከ እውቀት፥ ከኲተት እስከ ሽበት ምክር ያስፈልገዋል። ጳጳስም ሆነ ካህን፥ ባዕለጸጋም ሆነ ደሀ፥ ባዕለ ሥልጣንም ሆነ ተርታ ሰው፥ ምክር የማያስፈልገው የለም። ማንም ይሁን ማን፥ በጎ ኅሊና ያለው መካሪ ከሌለው ከሚያለማው የሚያጠፋው ይበዛል። አበው፦ «መካሪ የሌለው ንጉሥ ያለ አንድ ዓመት አይነግሥ፤» ያሉት ለዚህ ነው። ከዚያ በላይ ቢነግሥ እንኳ በኃይል እንጂ በፍቅር ሊነግሥ አይችልም። እያሠረ፥ እየገረፈ፥ እያፈናቀለ፥ እየገደለ፥ ግፍ በግፍ ይሆናል።
በጎ ምክርን የሚሰማ እንዳለ ሁሉ፥ የማይሰማም አለ። ቅዱስ ዳዊት ከበጎ ኅሊና የሚመነጭ ምክር ለሰው ሕይወት እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ሲናገር «ለሚያደርጋት ሁሉ ምክር መልካም ናት፥ ምስጋናውም ለዘለዓለም ይኖራል።» ብሏል። መዝ ፩፻፲፥፲። ልጁ፥ ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞንም፦ «አስተዋይ ግን ምክርን ገንዘብ ያደርጋል። ምሳሌንና የተሸሸገውን ነገር፥ የጠቢባንን ቃልና ዕንቆቅልሾችን ያውቃል። . . . ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናትህንም ትእዛዝ ቸል አትበል፤ ለራስህ የክብር ዘውድ ለአንገትህም የወርቅ ድሪ ይሆንልሃል።» በማለት መስክሯል። ምሳ ፩፥፭-፱።
የቦረና ጉጂና ሊበን ዞነን ሃገረ ስብከት በኪዳነምህረት ዓመታዊ ክብረ በዓል ቀን በተነሳው ግጭት ከ40 በላይ ክርስትያኖች ታሰሩ
የቦረና ጉጂና ሊበን ዞነን ሃገረ ስብከት በኪዳነምህረት ዓመታዊ ክብረ በዓል ቀን በተነሳው ግጭት ከ40 በላይ ክርስትያኖች ታሰሩ
- በግጭቱ ምክንያት ንግስ አልነበረም ፤ ቅዳሴም ሳይቀደስ ቀርቷል
- የሚጠቡ ህፃናት ቤት አስቀምጠው በእስር የሚገኙ እህቶች አሉ
- አራት ሰዎች ያህል ከአንድ ቤት የታሰሩም ይገኛሉ
- ምሽቱን የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በእስር ላይ ከሚገኙት ምዕመናን ውስጥ የወረዳው ሊቀ ካህን መሪጌታ ልሳነወርቅ ወልዴ ፤ ቀሲስ ወርቁና የ80 ዓመት እድሜ አዛውንት አቶ ዘውዴ አበሩ በእስር ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል
(አንድ አድርገን የካቲት 16 ፤2004ዓ.ም)፡- የቦረና ጉጂና ሊበን ዞኖች ሃገረ ስብከት የክብረመንግስት ከተማ ህዝብ ትግል የተባረረውና ዛሬም የሃገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ነኝ የሚለው ተሾመ ሃይለማርያም አሁን መሽጎ በሚገኝበት በክብረመንግስት ከተማ ሌላ ቀውስ እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ሳይጠሩ አቤት ሳይላኩ ወዴት የሚሉ ሰዎች ቤተክርስትያንን ከበዋት ይገኛሉ፡፡ የተሀድሶያውያን ርዝራዦች በየቦታው ጊዜ ጠብቀው በማድባት ቤተክርስትያናችን ላይ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ ፤ ከበላይ ያለው አመራር ንዝህላልነት በጉዳዩ ዙሪያ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖበታል ፤ ችግሮች ሲፈጠሩ ለችግሮቹ ወቅታዊ መፍትሄ አለመስጠት ችግሮችን ሌላ ችግር እንዲፈጥሩ እድል እየሰጠ ይገኛል፡፡
Monday, February 20, 2012
በአሪዞና የተጀመረው እርቅ በመልካም ጅምር ተጠናቀቀ
በሀገር ውስጥ ባለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና በውጪ በሚገኘው ሲኖዶስ በካከል ባለፈው ሳምንት የተጀመረው ድርድር እግዚአብሔር በፈቀደው በጥሩ ሁኔታ መጠነቀቁ ከሥፍራው በደረሰን ዜና ለመረዳት ችለናል። ከባለፉት
ድርድሮች ሁለቱም ወገኖች በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው ንግግር አድርገው አያውቁም ነበር፣ ሌላው ቀርቶ ሰላምታ እንኳን መለዋወጥ የቻሉበት ጊዜ እንዳልነበረ ስናስታውስ የአሁኑ ዙር በእውነቱ ትልቅ እና ብዙ ጉዞዎችን ያደረጉበት ነው ብለን እናምናለን፣ በማንኛውም ቦታ እና ዓለም የሚገኙ የሰላም ወዳድ ሀይሎች ለዚህ ለሃያ ዓመታት የዘለቀው የጠላትነት ጊዜ አብቅቶ፣ ቃለ ውግዘቱ ተነስቶ አንድ የሚሆኑበት እና እንደገና በአንድ መቅደስ የምናገለግልበት ጊዜ እሩቅ እንደማይሆን እንገምታለን።
የተጀመረውንም የጾም ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ሰላም የናፈቀውን የተዋሕሶ ቤተሰብ እንደገና ሰለም እንዲያሳየን አብዝተን እንድንጸልይ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
የጋራ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
ድርድሮች ሁለቱም ወገኖች በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው ንግግር አድርገው አያውቁም ነበር፣ ሌላው ቀርቶ ሰላምታ እንኳን መለዋወጥ የቻሉበት ጊዜ እንዳልነበረ ስናስታውስ የአሁኑ ዙር በእውነቱ ትልቅ እና ብዙ ጉዞዎችን ያደረጉበት ነው ብለን እናምናለን፣ በማንኛውም ቦታ እና ዓለም የሚገኙ የሰላም ወዳድ ሀይሎች ለዚህ ለሃያ ዓመታት የዘለቀው የጠላትነት ጊዜ አብቅቶ፣ ቃለ ውግዘቱ ተነስቶ አንድ የሚሆኑበት እና እንደገና በአንድ መቅደስ የምናገለግልበት ጊዜ እሩቅ እንደማይሆን እንገምታለን።
የተጀመረውንም የጾም ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ሰላም የናፈቀውን የተዋሕሶ ቤተሰብ እንደገና ሰለም እንዲያሳየን አብዝተን እንድንጸልይ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
የጋራ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
እንኳን ለታላቁ ጾም፣ ጾመ ሁዳዴ አደረሳችሁ
ይህ ታላቅ ጻም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሞቶ ሕይወት ሊሆነን በገዳም ገብቶ የጾመው ጾም ስለሆነ፣ እኛም መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ ጾሙን የረደኤት የበረከት እንዲያደርግልን እና ለትንሳኤው በዓል በሰላም እንዲያደርሰን እንመኛለን።
ለቅድስት ቤተክርስቲያናችን አብዝተን እንጸልይ፣ የድህነታችን፣ የእኛነታችን መገለጫችን፣ የኢትዮጵያ ሀገራችን የስልጣኔ ምንጭ እና ኩራት የሆነችው የተዋሕዶ እምነታችንን ከአረያም ሆኖ በቃሉ ችግሮችን አስወግዶ አጽራረ ቤተክርስቲያንን አስታግሶ፣ የረቁትን አቅርቦ ያሉትን እንዲያጸናልን የዘወትር ምኞችን ነው።
መልካም ጾም
ቸር ያቆየን
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
Saturday, February 18, 2012
የአብነ ፋኑኤል ስብሰባ ለምን ይሆን?
| የስብሰባው ቦታ |
በዚህ በጨረስነው ሳምንት ውስጥ በአሪዞና የተጀመረው ጥቂት እንደሄደ ያለምንም ስኬት ተጠናቋል፣ በብዙ ተንታኞች ከበፊተኛው በበለጠ መቀራረብ ቢኖርም እስከ አሁን ብዙ መፈታት ያለባቸው ችግሮች ግን ሊፈቱ እንዳልቻሉ ይነገራል። እንደ ተንታኞቹ በተለይ ከአስታሪቂዎቹ ውስጥ ሌላ ስውር የሆነ መንገድ ይዘው እሚንቀሳቀሱ ሰዎች እንዳሉ ታውቋል፥ እውነታው ግን ጊዜው ሲደረስ ይታወቃል ብለን እናምናለን፥ ለሁሉም የእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ጸሎት እንደሚሆን እናምናለን፣ ሰላሙ ወርዶ ቤተክርስቲያን ወደ አንድ ሥርዓት የምትመጣበት ጊዜ እሩቅ የሚሆን አይመስለንም፣ ለዛ እንዲያበቃን እንመኛለን። ይህ በእንዲህ እንዳለ አቡነ ፋኑኤል ለእርቅ የመጡትን አባቶች ይዘው በዋሽንግተን አካባቢ ተከታይ አለኝ፣ ሥራ እየሰራሁ ነው ለማለት ይመስላል ከእላይ ታች እየተባለ ነው። ከአካባቢው ምንጮች እንደተረዳነው በመጪው እሁድ የካቲት ፲፩ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. (Feb. 19, 2012) በፎልስ ቸርች አካባቢ በሚገኘው የሜቶዲስት ቸርች ውስጥ ስብሰባ ለማድረግ እየተጣደፉ እንደሆነ ከአምንጮቻችን ተገልጾልናል። እንደምንጮቻችን ገለጻ በዋሽንግተን ዲሲ ቅዱስ ሚካኤል ያላደረጉት ለምንድነው ብለው ሲጠየቁ፣ የተለያዩ ምክንያቶች እንዳላቸው ይነገራል ከነዚህም ጥቂቶቹ እንደሚከተለው ነው፡
Thursday, February 16, 2012
ስድስት አብያተክርስትያናት በጧፍና እጣን እጦት የመዘጋት አደጋ አንዣቦባቸዋል
ስድስት አብያተክርስትያናት በጧፍና እጣን እጦት የመዘጋት አደጋ አንዣቦባቸዋል
(አንድ አድርገን የካቲት 08 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የገሀነም ደጆች የማይችሏት ቀዳማዊት ንፅሂት እመቤት ቅድስተ ቤተክርስትያን ዙሪያዋን በጠላት ጦር እየደማች ትገኛለች፡፡ አረማውያን ቤተመቅደስ እያፈረሱ መናፍቃን ቅጥሯን እየጣሱ ፤ ተሀድሶዎች የራሷ ያልሆነውን እያቀረቡ ወላጅ እንደሌለው ልጅ እያስጨነቋት ይገኛሉ ፡፡ ከጠላቶቿ በላይ እየጎዳት የሚገኝው የቤተክርስትያን አስተዳደር የተማከለ አለመሆኑ ነው፡፡
የሰሜን ሸዋ ህዝብ ሙሉ ለሙሉ ለማለት በሚያስደፍር መልኩ የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እምነት ተከታይ ነው ፡፡ ሀገረ ስብከቱ ወደ ማዕከላዊ ቤተክህነት ፈሰስ የሚያደርገው ገንዘብ ቀዳሚ ከሆኑት ሀገረ ስብከቶች ውስጥ ይመደባል፡፡ ሆኖም ግን ሀገረ ስብከቱ ሲዳሰስ ከዝናውና ከክብሩ የማይስተካከል ገጽታ ይነበብበታል ፡፡ በሀገረ ስብከቱ የሚንቀሳቀሰው የደብረ ብርሀን ማህበረ ቅዱሳን ማዕከል ከሌሎች ማዕከሎቹ የተሻለ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ቢወራለትም በተግባር ግን የሚሰማውን ያህል ሆኖ እየሰራ አይደለም፡፡ በአሁኑ ሰአት በሀገረ ስብከቱ ስር ያሉ አብያተክርስትያናት በንዋየ ቅዱሳን እጦት የመዘጋት አደጋ አጋርጦባቸው ይገኛሉ፤ አብዛኞቹ መቀደሻ ጧፍ ፤ ማጠኛ እጣን ማግኝት አገልግሎቱን እያደናቀፈ እና እየተፈታተነ የሚገኝበት ጊዜ ላይ ደርሰዋል፡፡ ይህ እንዲህ ሆኖ ሳለ ሀገረ ስብከቱ ያለባቸውን ችግር አጥንቶ የመፍታት አቅጣጫ ሲከተል ለማየት አልቻልንም ፤ ቤተክርስትያናቱ አካባቢው ላይ የሚኖረው ምዕመን ቁጥር አነስተኛ መሆኑ ቤተክርስትያናቱ የሚያስፈልጋቸውን ንዋየ ቅዱሳት ለማሟላት የአቅም እጥረት መኖሩ አንዱ ምክንያት ነው ፤ ሀገረ ስብከቱ ዓመታዊ ፈሰስ የሚደርገው ብር እነዚህን የመሰሉ ችግሮች ፈተው መሆን ያለባቸው ይመስለናል፡፡ ቤተክርስትያናቱ እየተቸገሩ ፈሰስ ማድረግ ተገቢ ነው ብለን አናምንም፡፡
Tuesday, February 14, 2012
ተስፋዬ መቆያ እና ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን የአገልጋዮች ጉባኤ ተጠሪ ነን አሉ
![]() |
| ተስፋዬ መቆያ እና ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን |
ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በአሜሪካን መዲና በሆነችው ዋሽንግተን ዲሲ ላይ "የአገልጋዮች ጉባኤ" በሚል ከተቋቋመ ሦስት ዓመታትን ያስቆጠረው ጉባኤ ጉባኤውን እንደተለመደው በዋሽንግተን ዲሲ ላይ ርዕሰ አድባራት ቅድስተ ማሪያም ቤተክርስቲያን ማድረጉን ሰምተን ነበር፣ ከተለያየ ቦታ የመጡ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች፣ ካሕናት፣ ዘማሪያን፣ እንዲሁም ቅዱስ ሲኖዶስ ሕገወጥ ሰባኪያን እና ዘማሪያን ብሎ በማንኛውም ዓውደ ምሕረት ላይ ቆመው እንዳይሰብኩ ወይም እንዳይዘምሩ የተለዩትም ዘማሪያን በቦታው በተጋባዥነት ተገኝተው ነበር።
በፊኒክስ አሪዞና እርቀ ሰላም ተጀመረ
፩ኛ/ ብፁዕ አቡነ መልከፄዲቅ የስደተኛው ሲኖዶስ ጸሐፊ
፪ኛ/ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስደተኛው ሲኖዶስ ተወካይ
፫ኛ/ ሌቀ ካህናት ምሣሌ
፬ኛ/ መልአገ ገነት ገዛህኝ ከስደተኛው ሲኖዶስ በኩል በተወካይነት ተወክለው በተጠቀሰው ቦታ ተገናኝተው እርቀ ድርድሩን ለማድረግ ትላንት ጀምረው ተወካዮቹ በፊኒክስ ተገኝተው ዛሬ ረፋዱ ላይ ስብሰባው እንደሚጀመር ይጠበቃል።
![]() |
| እርቁ እውነት ይሆን? እርቁን የማይፈልግ ክፍል ይኖር ይሆን? |
ዛሬ የካቲት ፮ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በፊኒክስ አሪዞና የኢትዮጵያው ቅዱስ ሲኖዶስ ተወካዮች
፩ኛ/ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የመንበረ ፓትሪያሪክ ልዩ ጸሐፊና የድሬደዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
፪ኛ/ ብፁዕ አቡነ አትናቲዮስ የወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
፫ኛ/ ብፁዕ አብነ ቀወስጦስ የኣዲስ አበባ እና የምዕራብ ሸዋ ሊቀ ጳጳስ (በህመም ምክንያት መምጣት አልቻሉም)
፫ኛ/ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ
እንዲሁም ከስደተኛው ሲኖዶስ የተወከሉ ደግሞ ፩ኛ/ ብፁዕ አቡነ መልከፄዲቅ የስደተኛው ሲኖዶስ ጸሐፊ
፪ኛ/ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የስደተኛው ሲኖዶስ ተወካይ
፫ኛ/ ሌቀ ካህናት ምሣሌ
፬ኛ/ መልአገ ገነት ገዛህኝ ከስደተኛው ሲኖዶስ በኩል በተወካይነት ተወክለው በተጠቀሰው ቦታ ተገናኝተው እርቀ ድርድሩን ለማድረግ ትላንት ጀምረው ተወካዮቹ በፊኒክስ ተገኝተው ዛሬ ረፋዱ ላይ ስብሰባው እንደሚጀመር ይጠበቃል።
Saturday, February 11, 2012
የአቡነ ፋኑኤል ማስፈራሪያ
አባ ፋኑኤል እና የአባ ሰላማ ግንኙነት
በወርሃ ጥቅምት በተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በስተ መጨረሻ ሹመታቸውን አረጋግጠው ወደዋሽንግተን ዲሲ በድብቅ የገቡት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የእስከ አሁኑ ሕገ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ አካሄዳቸው ብዙዎችን አስደምሟል፣ እንደ አንድ መንፈሳዊ መሪ በተቻለ መጠን ልዩነትን ወደ ጎን ትቶ ለመሥራት እንደ መሞከር ይባስ ብለው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማስፈራሪያዎችን የአባ ፋኑኤል አፈ ቀላጤ በሆነው አባ ሰላማ በተሰኘው የመናፍቃኑ አንደበት በሆነው የብሎግ መድረክ ማስፈራሪያዎችን ጨምሮ ለዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥራ አስፈፃሚ ሥራ አስኪያጅ ለሆኑት ለቀሲስ ዶ/ር መስፍን ልከውላቸዋል።
በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው አቡነ ፋኑኤል ቀሲስ ዶ/ር መስፍን የጀመሩትን ሥራ ካላቆሙ እርምጃ እወስዳለው በማለት ማስፈራሪያን ጨምረው በደብዳቤው ገልጸዋል የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ያገኙታል እንደ አቡነ ፋኑኤል ከሆነ ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ቤተክርስቲያን ፣ በሀገረ ስብከቱ ሥር ያሉት አጥቢያዎች፣ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ እንዲሁም ሕዝበ ክርስቲያኑ የጣለችባቸውን ሃላፊነት ባስቸኳይ ካላቆሙ እርምጃ እንደሚወስዱ ዝተዋል። እረ ለመሆኑ የሚሰሩት መንፈሳዊ ሥራ ነው ወይስ ሌላ የፓለቲካ ሥራ ነው? አቡነ ፋኑኤል ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ከመጡ ጊዜ ጀምሮ በሀገረ ስብከቱ ታቅፈው ከነበሩት አጥቢያዎች ወደ አንደኛው እንኳን በመሄድ ለማግባባት አለመሞከራቸው፣ የነበረውንም ሥራ አስፈጻሚ እንደ ቤተክርስቲን መዋቅር እኔ አላውቅህም ከማለት የፍትህ መንፈሳዊ በሚያዘው መሠረት ሰብስቦ ሥርዓት ባለው መንገድ መሥራት አለበለዚያም በሌላ መተካት ሲቻል፥ ጭራሽ መኖሩንም አላውቅም ሲሉት የነበሩትን ሥራ አስፈጻሚ ማስፈራራት ምን የሚሉት አካሄድ ነው።
![]() |
| አቡነ ፋኑኤልን እና "አባ ሰላማን" ምን አገናኛቸው??? |
በደብዳቤው ላይ እንደተገለጸው አቡነ ፋኑኤል ቀሲስ ዶ/ር መስፍን የጀመሩትን ሥራ ካላቆሙ እርምጃ እወስዳለው በማለት ማስፈራሪያን ጨምረው በደብዳቤው ገልጸዋል የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ያገኙታል እንደ አቡነ ፋኑኤል ከሆነ ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ቤተክርስቲያን ፣ በሀገረ ስብከቱ ሥር ያሉት አጥቢያዎች፣ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ እንዲሁም ሕዝበ ክርስቲያኑ የጣለችባቸውን ሃላፊነት ባስቸኳይ ካላቆሙ እርምጃ እንደሚወስዱ ዝተዋል። እረ ለመሆኑ የሚሰሩት መንፈሳዊ ሥራ ነው ወይስ ሌላ የፓለቲካ ሥራ ነው? አቡነ ፋኑኤል ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ከመጡ ጊዜ ጀምሮ በሀገረ ስብከቱ ታቅፈው ከነበሩት አጥቢያዎች ወደ አንደኛው እንኳን በመሄድ ለማግባባት አለመሞከራቸው፣ የነበረውንም ሥራ አስፈጻሚ እንደ ቤተክርስቲን መዋቅር እኔ አላውቅህም ከማለት የፍትህ መንፈሳዊ በሚያዘው መሠረት ሰብስቦ ሥርዓት ባለው መንገድ መሥራት አለበለዚያም በሌላ መተካት ሲቻል፥ ጭራሽ መኖሩንም አላውቅም ሲሉት የነበሩትን ሥራ አስፈጻሚ ማስፈራራት ምን የሚሉት አካሄድ ነው።
የዋልድባ ገዳማት ህልውና እና ክብር ለአደጋ ተጋልጧል
የዋልድባ ገዳማት ህልውና እና ክብር ለአደጋ ተጋልጧል
· በገዳሙ ክልል እና ዙሪያ (በዓዲ አርቃይ ወረዳ በኩል) የፓርክ ይዞታ ለመከለል እና የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም በሚል በሚካሄደው የጥርጊያ መንገድ ሥራ (ከማይ ፀብሪ እስከ ዕጣኖ ማርያም) የቅዱሳን አበው ዐፅም እየፈለሰ መሬቱ እየታረሰ ነው።
· የሦስቱ ገዳማት ማኅበረ መነኮሳት ዕቅዱ የገዳሙን ክብር የሚጋፋ ህልውናውንም የሚያጠፋ በመሆኑ እንዲቆምላቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል።
· መንግሥት ካቀዳቸው 10 ግዙፍ የስኳር ፋብሪካ ግንባታ ፕሮጀክቶች አንዱ በዋልድባ ገዳም ክልል እና ዙሪያ (ወልቃይት - መዘጋ) የሚቋቋም ሲሆን በዛሬማ ወንዝ ላይ 3.8 ቢልዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ የመያዝ አቅም ያለውና 40,000 ሄ/ር የሸንኮራ ተክል የሚለማበት ግድብ ይቆምለታል፤ ግድቡ በሚሸፍነው ስፍራ (ማይ ዲማ) የሚገኙ አራት አብያተ ክርስቲያን የሚነሡ ሲሆን ለ10,000 የፕሮጀክቱ ጊዜያዊ እና ቋሚ ሠራተኞች የመኖሪያ ካምፕ ግንባታ እየተካሄደ ነው።
· “በቅድስት ገዳማችን ዋልድባ ውስጥ ለሚደረገው አግባብ ያልሆነ እንቅስቃሴ አበው ቅዱሳን አባቶቻችን ልዩ ሥራ እንዳይሠራባት የውግዘት ቃል (እንበለ ፈላሲ ኢይባዕ ነጋሲ) ያሳለፉባት ቦታ በመሆኗ ማኅበረ መነኮሳቱ ባደረግነው ምልአተ ጉባኤ መሠረት ለሚሠራው ሥራ ፈጽሞ ፈቃዳችን አለመሆኑንና የአባቶቻችን ቅዱሳንን ፈለግ ሕግና ሥርዐት ተከትለን የምንሄድ መሆናችንን በጥብቅ እናሳውቃለን”።
Wednesday, February 8, 2012
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከመንፈሳዊ የአስተዳደር ጉባኤ የተሰጠ መግለጫ ከሀገረ ስብከቱ ድረ ገጽ ላይ አግኝተናል::
ለብጹዕ አቡነ ፋኑኤል
![]() |
| "ታላቅ ምክር" |
የብፁዕነትዎን ይቅርታ እየጠየቅሁ እንደ መንፈሳዊ ልጅነቴ በግሌ ላሳስብዎት የምሻውን ከዚህ እንደሚከተለው አቀርባለሁ። እድሜዬ በ30ዎቹ ሲሆን በውጭ ሃገር ተወልደው አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነትን በባለቤትነትና በኩራት የሚከተሉ ሁለት ልጆችን እግዚአብሔር ሰጥቶኛል። ዕድሜያቸው በአስራዎቹ ሲሆን በእምነታቸው ግን በጣም በመብሰላቸው ለዘመኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ንትርክ ሳይወዱ ተካፋይ ሆነዋል። ለዚህም የዳረጋቸው በየአብያተ ክርቲያናቱ ዶግማና ቀኖና ሥርዓት ነው። ዝርዝሩን እዚህ ላይ ባላሰፍረውም የሁሉም የእምነቱ ተከታይ የሆኑት ምእመናን ቤት ጠንቅቆ ያውቀዋል።
Tuesday, February 7, 2012
ለብጹዕ አቡነ ፋኑኤል
- ቤተ ክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አይደለችም፤ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ናት” ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል
READ IN PDF
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጋዜጠኛ ከአቶ አዲሱ አበበ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በሀገረ አሜሪካን ስለምትገኘው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ግንዛቤ ለሌላቸው አድማጮች እውነት የሚመስሉ፤ ነገር ግን በመሬት ላይ ካለው እውነት ጋር ፍጹም የማይገናኙ ትንታኔዎችን ሰጥተዋል:: “የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጵጵስና በተቀበሉበት ወቅት ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዳስረከቡ መረጃዎች አሉን የሚሉ ወገኖች አሉ፤ ነገር ግን አሁንም ድረስ ቤተ ክርስቲያኑ በእርሶ እጅ እንዳለ ይወራል” በማለት አቶ አዲሱ አበበ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ቤተ ክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አይደለችም፤ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ናት” ብለው ነበር:: ይህ አነጋገር በሰሜን አሪሜካ ስላለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናን በቂ መረጃ ለሌላቸው ሰዎች እውነት ቢመስልም ሐቁ ግን ከዚህ የራቀ ነው::
ለብፁዕ አባታችን አሁን ደግሞ እኛ አንድ ጥያቄ እናቅርብ እስኪ፤ እውነት በሰሜን አሜሪካን ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ናትን?
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጋዜጠኛ ከአቶ አዲሱ አበበ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በሀገረ አሜሪካን ስለምትገኘው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ግንዛቤ ለሌላቸው አድማጮች እውነት የሚመስሉ፤ ነገር ግን በመሬት ላይ ካለው እውነት ጋር ፍጹም የማይገናኙ ትንታኔዎችን ሰጥተዋል:: “የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጵጵስና በተቀበሉበት ወቅት ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዳስረከቡ መረጃዎች አሉን የሚሉ ወገኖች አሉ፤ ነገር ግን አሁንም ድረስ ቤተ ክርስቲያኑ በእርሶ እጅ እንዳለ ይወራል” በማለት አቶ አዲሱ አበበ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ቤተ ክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አይደለችም፤ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ናት” ብለው ነበር:: ይህ አነጋገር በሰሜን አሪሜካ ስላለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናን በቂ መረጃ ለሌላቸው ሰዎች እውነት ቢመስልም ሐቁ ግን ከዚህ የራቀ ነው::
ለብፁዕ አባታችን አሁን ደግሞ እኛ አንድ ጥያቄ እናቅርብ እስኪ፤ እውነት በሰሜን አሜሪካን ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ናትን?
Monday, February 6, 2012
የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ
· በስብሰባው ያልተገኙት አቡነ ፋኑኤል ከአካባቢው ለሰበሰቧቸው ካህናት አዲስ ሹመት ሰጥተዋል፤
(ደጀ ሰላም፤ ጥር 28/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 6/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አስቸኳይ አጠቃላይ ጉባዔውን በኖርዝ ካሮላይና ሻርለት በማካሄድ እና መሠረታዊ ውሳኔዎችን በማሳለፍ እንደተጠናቀቀ ምንጮች ለደጀ ሰላም ገልጸዋል። ጥር 25 እና 26/ 2004 ዓ.ም በሀ/ስብከቱ ሥር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በተገኙበት በተደረገው የምክክር ጉባኤ ላይ “የሀ/ስብከቱን መኖር አላውቅም” ያሉት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አለመገኘታቸው ታውቋል።
Thursday, February 2, 2012
አቡነ ፋኑኤል ሀ/ስብከት በማፍረስ ጎዳና ላይ ይሆኑ?
አቡነ ፋኑኤል ሀ/ስብከት በማፍረስ ጎዳና ላይ ይሆኑ?
(ደጀ ሰላም፣ ጥር 24/2004 ዓ.ም፤ February 2/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በብፁዕ አቡነ አብርሃም ምትክ የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የሀ/ስብከቱን መኖር እንደማያውቁ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ በተናገሩ ማግስት ለቅ/ፓትርያርኩ የላኩት ደብዳቤ ለድረ ገጻችን በአድራሻ ተልኮልናል፡፡ ደብዳቤውን ያደረሱንን ደጀ ሰላማዊ ከልብ እናመሰግናለን።
ሊቀ ጳጳሱ አስቀድሞ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ሀ/ስብከት መኖሩን አላውቅም” ማለታቸውን ሰምተናል። ያንን አስከትለው ደግሞ የለም ያሉትን ሀ/ስብከት “በሕግ ለመጠየቅ” ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ባልሸሸጉበት ሁኔታ በሀ/ስብከቱ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በብፁዕ አቡነ አብርሃም ሰብሳቢነት ባደረጉት ዓመታዊ ጉባኤ የተቋቋመውን የሀ/ስብከቱን ሥራ አስፈጻሚ “ሕገ ወጦች” እና “የግል ጥቅማቸው የተነካባቸው ግለሰቦች” በሚል ጠርተዋል።
Friday, January 27, 2012
አባ ፋኑኤል በዳላስ ቴክሳስ
በስብሰባው ላይ ብዙ ያልተገኙ አድባራት ተወካዮች ያልተገኙ ቢሆንም፥ የተገኙት ግን አባ ፋኑኤል በተለያየ ጊዜ የሚያደርሱትን የሥርዓተ ቤተክርስቲያን መጣስ እና የቀኖና ማፍረስ ሥራዎችን በመቃወም ነበር ስብሰባው የተጀመረው፤ ተሰብሳቢዎቹም የተለያየ የምስል እና የድምጽ መቅረጫዎችን እንዳይጠቀሙ ሊቀ ካህናት አጥብቀው ሲያሰሙ ስለነበር በተከታዮቹ ቀናት በተሰብሳቢዎቹ ካህናት እና የሰበካ ጉባኤ ተጠሪዎች ችግር ሳይገጥማቸው እንደማይቀር ይገመታል።
የስብሰባው ሙሉ ሪፓርት እንደደረሰን እናቀርባለን ተጠባበቁን።
ቸር ወሬ ያሰማን
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
![]() |
| ሥርዓት አልበኛው ጳጳስ አባ ፋኑኤል |
በትላንትናው እለት አባ ፋኑኤል ወደ ዳላስ ቴክሳስ ጉዞ አድርገው ከካሊፎርኒያ እና የምዕራቡ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ካህናት ኃይለሥላሴ እና ለስብሰባው ከተገኙት የደብር ተወካዮች ጋር ንግግር ለማድረግ ትላንት አመሻሹ ላይ ዳላስ ቴክሳስ ገብተው አድረዋል። በደብረ ምሥራቅ አቡነ ተክለሃይማኖት ወአረጋዊ ቤተክርስቲያን የሚደረገው ይህ ከአቡኑ ጋር የሚደረገው ስብሰባ ምንም አይነት ውጤት እንደማያመጣ እና በደጋሚ የአቋም ለውጥ ካመጡ በሚል ቀቢጸ ተስፋ እንጂ ምንም የተለየ ነገር እንደማይጠብዙ የስብሰባው ተሳታፊዎች ከቦታው ገልጸውልናል፥ በተለይ በቦታው የተገኙት የደብር ሃላፊዎች እና የሰበካ ጉባኤ አባላት አቡኑ ሀሳባቸው እንደ ሁልጊዜው ከሆነ በምንም መልኩ አብረዋቸው እንደማይሠሩ ከወዲሁ ሲነጋገሩበት የቆየ ቢሆንም አንድ ቁርጥ ውሳኔ ከአቡነ ፋኑኤል እንደሚጠብቁና ውጤት ሊያመጣ የሚችል ንግግር ካልሆነ ግን ስብሰባውን ጥለው ወደየመጡበት ሀገር እንደሚወጡ አስቀድመው አሳውቀዋል። ለዚህ ስብሰባ መጠራት ትልቅ አስተዋፅኦ ያደረጉት የዴንቨር ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም አስተዳዳሪ የሆኑት ሊቀ ካህናት ኃይለሥላሴ እንደሆኑ እና በባለፈው በ፴ኛው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ወቅትም በብጹዕ አቡነ ኤውስጣቲዎስ እና በብጹዕ አቡነ አብርሃም ላይ ከሊቀ መምሕራን ቀሲስ አማረ ካሣዬ ጋር በመሆን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ አቤቱታ አቅርበው ለአባ ፋኑኤል ወደ አሜሪካን መምጣት አይነተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ይታወሳል።
በስብሰባው ላይ ብዙ ያልተገኙ አድባራት ተወካዮች ያልተገኙ ቢሆንም፥ የተገኙት ግን አባ ፋኑኤል በተለያየ ጊዜ የሚያደርሱትን የሥርዓተ ቤተክርስቲያን መጣስ እና የቀኖና ማፍረስ ሥራዎችን በመቃወም ነበር ስብሰባው የተጀመረው፤ ተሰብሳቢዎቹም የተለያየ የምስል እና የድምጽ መቅረጫዎችን እንዳይጠቀሙ ሊቀ ካህናት አጥብቀው ሲያሰሙ ስለነበር በተከታዮቹ ቀናት በተሰብሳቢዎቹ ካህናት እና የሰበካ ጉባኤ ተጠሪዎች ችግር ሳይገጥማቸው እንደማይቀር ይገመታል።
የስብሰባው ሙሉ ሪፓርት እንደደረሰን እናቀርባለን ተጠባበቁን።
ቸር ወሬ ያሰማን
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
Thursday, January 26, 2012
ተሀድሶያውያን እንደ እባብ የሞተ በመምሰል አፈር ልሰው ለመነሳት እየሞከሩ ነው
![]() |
| ትዝታው እና አቶ በጋሻው |
(አንድ አድርገን ጥር 16 ፤ 2004ዓ.ም)፡- እነዚህ ሰዎች በጥምቅቱ የሲኖዶስ ጉባኤ የታገዱ እና ህገወጥ የተባሉ ሰባኪያን እና ዘማሪያን መሰል የተኩላው ለምድ የለበሱ ሰዎች (አቶ በጋሻው ደሳለኝ ፤ አሸናፊ ገ/ማሪያም ፤ አሰግድ ሳህሉ ፤ ትዝታው ሳሙኤል ፤ ምርትነሽ ጥላሁን ፤ ሀብታሙ ሽብሩ ፤ እና መሰሎቻቸው) በየትኛው በር ገብተው ነው የቤተክርስትያናችን አዳራሽ የተፈቀደላቸው ? እኛ እስከምናውቀው ድረስ ከቅዱስ ሲኖዶስ የትኛውም አውደ ምህረት ላይም ሆነ የትኛውም ቤተክርስትያን ላይ የመስበክ ፍቃድ እንዳይሰጣቸው እና ቤተክርስትያንን የማይወክሉ መሆኑን ገልፆ ቅዱስ ሲኖዶስ ለመላው አዲስ አበባ ውስጥም ላሉ ፤ ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚገኙ አብያተክርስያናት በሀገረስብከታቸው አማካኝነት እንዲደርሳቸው ተደርጎ ነበር ፤ ታዲያ ይህን ጉባዬ ለዛውም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ ማን ፈቀደላቸው?
Subscribe to:
Posts (Atom)









