የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም ድምጽ: አባ ፋኑኤል እና የሐሰት ስርጭታቸው: ባለፈው ቅዳሜ ጥር ፲፪ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. አባ ፋኑኤል በቪኦኤ የአማርኛው ዝግጅት በአቶ አዲሱ አበበ አማካኝነትክፍል አጭር ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር፣ በቃለ ምልልሱም በርካታ የሆኑ ውሸት አዘል መልዕክቶችን በአ...
የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
Thursday, January 26, 2012
Wednesday, January 25, 2012
ጸብአቴ የማነ ብርሃን ማናቸው?
በዚህ ሰሞን በአትላንታ ጆርጂያ እራሱን ገለልተኛ ብሎ የሚጠራው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቦርድ አባላትና የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ የነበሩት ጸብአቴ የማነ ብርሃን ከረር ያለ ውዝግብ ምዕመናኑን ለሁለት ከመክፈሉ ባሻገር፥ የምዕመናንን ጆሮ ጭው የሚያደርግ ነገር መፈጸሙን ስንሰማ፣ ከአካባቢው የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ሞክረን በጉዳዩ ተሳታፊ ከሆኑት ምዕማን ጋር ግንኙነት በማድረግ ስለተፈጠረው ሁኔታ እንዲያብራሩልን ጠይቀናቸው ሙሉ መረጃውን ሰጥተውናል። የእኛ አላማ አንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓቷ፣ ቀኖናዋ፣ ትውፊቷ ተጠብቆ አገልግሎቱን መፈጸም ሲሆን አንዳንድ ጥቅም ዓይናቸውን ያሳወራቸውን አባት ተብዬዎች ግን፣ ዝም ብለን አናልፍም ሕዝበ ክርስቲያኑን ስለማንነታቸው በማሳወቅ መለየት። የበግ ለምድ ለብሰው በውስጣችን የገቡትን ነጣቂ ተኩላዎች ማውጣት የኛ አነሳስ ነው።Monday, January 23, 2012
አባ ፋኑኤል እና የሐሰት ስርጭታቸው
ጥያቄ: አባታችን አሁን የመጡበት ሹመቶ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው?
መልስ፡ አዎ፣ ከዚህ በፊት መጥቼ ቅዱስ ፓትሪያሪኩንም ነግሬያቸው ነበር እኔ የመጣሁት ሀገሬን ለማገልገል ነው እና በተቻለ መጠን እዚሁ ቢያረጉኝ ብዬ ነበር ነገር ግን በቅዱ ሲኖዶስ ስለታዘዝኩኝ ትዕዛዙን አክብሬ መጥቻለሁ፣ በመቀጠም እራሴው ደብዳቤ ጽፌ ወዳገሬ እንዲመልሱኝ ያለምንም ችግር በመጣሁ በሦስት ወሬ ወዳገሬ ተመልሻለሁ ነበር ያሉት።
እርምት: እኛ እስከምናውቀው ድረስ ከዚህ በፊት በመጡበት ወቅት ትልቅ ችግር ተነስቶ እንደውም በቅዱስ ሚካኤል ደብር መቀመጥ እንደማይችሉ ተነግሯቸው፣ እንደዛ ከሆነ የቤቱ ባለቤት እራሴው ነኝ እስቲ የምታደርጉትን እናያለን ብለው ከጥቂት የቤተክርስቲያኑ አባላት ጋር አምባጓሮ ጀምረው በዛው ጊዜ የተጀመረው የፍርድ ቤት ክስ እስከ አሁን ድረስ ሕዝበ ክርስቲያኑን ለሁለት ከፍሎት ይገኛል፣ ቤተክርስቲያኑንም ላላስፈላጊ የ$200000 ብር ወጪ ተዳርጓል ለምን ይሄን ሸሸጉ?ሌላው በዚሁ በመጡበት ጊዜ በተለምዶ እራሳቸውን ገልልተኛ ብለው የሚጠሩ አብያተ ክርስቲያናት ስብስብ ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለንም ብለው በዛው ጊዜ ከገለልተኞች አንድነት የወጡበት እና ባይተዋር የተደረጉበት ጊዜ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።
Thursday, January 19, 2012
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም በጤና አደረሳችህ አደረሰን
"በፍሰሐ ወበሰላም ወረደ ወልድ ውስተ ምጥማቃት"
እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን አሜን
![]() |
| እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሰዎት |
ይህን ድምጽ ሰምተው ምላሽ ለመስጠት ከቤታቸው የወጡ በግብርና የሚኖሩ፣ በባሕር የነበሩ አሳ አጥማጆች እንዲሁም በገዥው መደብ ስር በተለያየ ማዕረግ እና ስም የሚጠሩና የሚሠሩ ሰዎች ሁሉ ነበሩ፤ በጥሪው ምክንያት ሁሉም በአንድ ሥፍራ ተሰብስበዋል ጥሪውም እንዲህ የሚል ነበር "የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፤ ዐዘቅቱ ሁሉ ይሙላ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል፥ ጠማማውም የቀና መንገድ ይሁን፥ ሸካራውም መንገድ ትክክል ይሁን፤ ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ ተብሎ እንደ ተጻፈ ለኃጢአት ስርየት የንስሐን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለችው አገር ሁሉ መጣ። " ሉቃስ ፫ ፥ ፫ - ፮ ለዚህ ድምጽ ምንነትና ማንነት ለማየት እና ለመስማት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ የወረደው ሕዝብ ስፍር ቁጥር አልነበረውም፥ ተናጋሪው ከየት እንደመጣ ያልታወቀ ነገር ግን በበረሃ ሲኖር ከኅብረተሰቡ ተለየቶ የበረሃ ማር እና አንበጣ እየበላ በጸጋ ያደገው የካህኑ ዘካሪያስ ልጅ መጥምቁ ዮሐንስ ነበር።
Wednesday, January 11, 2012
የተዋሕዶ ቤተሰቦች ለምን?
በተደጋጋሚ ከተለያዩ የዝግጅታችን ተከታታዮች
የተዋሕዶ ቤተሰቦች ማናቸው?- የናንተ የጡመራ መድረክ ለምን አስፈለገ?
- ለቤተክርስቲያን መቆማችሁን በምን እናውቃለን?
- ዓላማችሁ ምንድነው? እና የመሳሰሉት ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን ከአንባቢያን ስለመጡ ሙሉም ባይሆን በመጠኑ የመልሳሉ ያልናቸውን ነጥቦች ከዚህ በመቀጠል አስቀምጠናቸዋል እና ጥያቄያችሁን ወይም አስተያየታችሁን በተለመደው መልኩ በኢሜል ወይም በፊስ ቡክ ልታደርሱልን ትችላላችሁ፤ የቻልነውን መልሰን ያልቻልነውን ሊቃውንቱን ጠይቀን መልሶቻችሁን ለመስጠት ከወዲሁ ተዘጋጅተናል።
እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለዘመናት ከውስጥም፣ ከውጪም በሚመጡ ወራሪዎች እና ሃይማኖት እና ትውፊት ለዋጮች ስትታመስ ኖራለች፤ ምንም እንኳ ቤተክርስቲያኒቱ በጠላቶቿም ሳይቀር "ስንዱ እመቤት" እየተባለች እስከመጠራት ብትደርስም ፈተናው በየደረጃው መስራቿ ኢየሱስ ክርስቶስን አይሁድ በቅናት ተነሳስተው ከሰቀሉበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ በዘመናችን እስከተነሱት ሃይማኖት ለዋጮች፣ ትውፊት ከላሾች ድረስ በብዙ ተፈትናለች፥ ዲያብሎስም ፆሩን መወርወሩን አያቆምም በተክርስቲያንም በክርስቶስ ደም ጸንታ ትቆማለች፡፡ ለዘመናት የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማ፤ቀኖናና ትውፊት ሲያስተላልፉ የነበሩ ሁለት አይና ሊቃውንትን በአብነት ት/ቤቶች ስታፈራ ኖራለች፡፡ ከዚህም በላይ ቤተክርስቲያኒቱ ራሷን የምታስተዳድርበት የራሷ የሆነ ሥርዓት ለሺህ ዓመታት የነበራት ሲሆን ይህም አንድነቷን በመጠበቅ ከፍተኛ ሚና ሲጫወት ኖሯል፡፡ በተጨማሪም ቤተክርስቲያኒቱ ለሀገሪቱ ዘመናዊ አስተዳደር፤ ቋንቋ፤ ባህል፣ ስነ-ጽሁፍ፣ ስነ-ስዕል እና ስነ-ህንፃ ወዘተ ከፍተኛ የልማት አስተዋጽኦ አድርጋለች፡፡ ይሁንና የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ዘመናት ብዙ ፈተናዎችን ስትጋፈጥና በእግዚአብሄር እርዳታም ስትወጣ ኖራለች ከነዚህም ዋነኞቹ የዮዲት ጉዲት ጭፍጨፋ፣ የግራኝ መሃመድ ህንፃ ቤተክርስቲያንና ቅርስን የማውደም ዘመቻ እንዲሁም የነገስታት እና የመሪዎች የሀይማኖት ጥላች አፄ ሱስዮስ በመካከለኛው ዘመን ያደረሱት በደል፣ የደርግ መንግስት የቤተክርስቲያኒቱን አንጡራ ሀብት መውረስ የመሳሰሉት በአብነት የሚጠቀሱ ፈተናዎች ናቸው፡፡
Thursday, January 5, 2012
ቤተ ክርስቲያናችን በሀገረ አሜሪካን በይበልጥ ውስብስብ የሆነ ችግር ውስጥ እየገባች ነው
ይህ ጽሁፍ አሐቲ ተዋሕዶ ከሚባል ፌስ ቡክ የተገኘ ነው፤ ይጠቅማል ብለን ስላሰብን እንደሚከተለው አቅርበነዋል መልካም ንባብ ይሁንልዎ።
ባለን መረጃ በሰሜን አሜሪካ በ26 ግዛቶች(እስቴቶች) ውስጥ 106 አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ:: በሁሉም እስቴቶች ቢቆጠር የአጥቢያዎቹ ብዛት ከ106 በላይ ይሆናል ማለት ነው:: እነዚህ አጥቢያዎች ሁሉ በውጫዊ እና በውስጣዊ ተጽኖዎች ምክንያት በፖለቲካ፣ በዘር እና በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች የተከፋፈሉ ናቸው:: በአስተዳደር መዋቅር ደግሞ ስደተኛ ሲኖዶስ፣ ገለልተኛ፣ በግለሶዎች፣ እና በኢትዮጵያ ሲኖዶስ በማለት የተለያዩ ናቸው:: በአስተዳደር ብቻ ሳይሆን በሃይማኖታዊ ሥርዓት ጭምር የተላያየ አቋም ያላቸው አጥቢያዎች አሉ:: ለምሳሌ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአዳም ኀጢአት ወርሳለች በማለት በግል የመሠረቱት አጥቢያቸው ውስጥ የሚያስተምሩ እነ አባ መዓዛ በየነ እና ቀሲስ አስተራየ ጽጌ የሚጠቀሱ ናቸው:: እንዲሁም ደግሞ አንዳንድ አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት በይፋ በኦርጋን መዘመር ተፈቅዶዋል በማለት ወደ መቅደሱ ኦርጋን አስገብተው የሚዘምሩ አሉ::
ይህ በአስተዳደር፣ በፖለቲካ፣ በዘር፣ በተለያዩ ጥቅማ ጥቅም እና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የተለያዩት አጥቢያዎች እንዴት አንድነት ማምጣት ይቻላል? የተወጋገዙት የጳጳሳት መታረቅስ ይህንን ችግር ይፈታው ይሆን? ጊዜ ይፍታው ተብሎስ የሚተው ጉዳይ ነውን? አሐቲ ተዋሕዶ የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ መዋቅር ከተጠበቀ ለዚህም መዋቅር መጠበቅ በጋራ ከሰራን አንድነት ይመጣል ብላ ታምናለች:: የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ መዋቅሯ ከግንዱ ተለይቶ እዚህ ሀገረ ቅርጫፎች ብቻቸውን ከተስፋፉ ወደፊት ከፕሮስቴንታንቶቹ የሚለየን ነገር አይኖርም የሚል ስጋት አለን:: የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ መዋቅር መጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው ብለንም እናምናለን::
ይህ በአስተዳደር፣ በፖለቲካ፣ በዘር፣ በተለያዩ ጥቅማ ጥቅም እና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የተለያዩት አጥቢያዎች እንዴት አንድነት ማምጣት ይቻላል? የተወጋገዙት የጳጳሳት መታረቅስ ይህንን ችግር ይፈታው ይሆን? ጊዜ ይፍታው ተብሎስ የሚተው ጉዳይ ነውን? አሐቲ ተዋሕዶ የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ መዋቅር ከተጠበቀ ለዚህም መዋቅር መጠበቅ በጋራ ከሰራን አንድነት ይመጣል ብላ ታምናለች:: የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ መዋቅሯ ከግንዱ ተለይቶ እዚህ ሀገረ ቅርጫፎች ብቻቸውን ከተስፋፉ ወደፊት ከፕሮስቴንታንቶቹ የሚለየን ነገር አይኖርም የሚል ስጋት አለን:: የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደራዊ መዋቅር መጠበቅ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው ብለንም እናምናለን::
Wednesday, January 4, 2012
የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት ሥራ አስፈጻሚ የብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን እንቅስቃሴ እየተቃወመ ነው
(ደጀ ሰላም፣ ታኅሣሥ 24/2004 ዓ.ም፤ January 3/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ለዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ተመድበው ቢላኩም ሀ/ስብከቱን ማስተዳደር ያልጀመሩት አቡነ ፋኑኤልን በተመለከተ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ቀጥሎ ሀ/ስብከቱን እንዲያስተዳድር የተመረጠው ሥራ አስፈጻሚ “ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን” 1ኛ ቆሮ 14፡40 በሚል ርእስ ኅዳር 29 ቀን 2004 ዓ. ም ባወጣው መግለጫ በሀ/ስብከቱ ያለው ዋነኛ ችግር “የውስጥ የቤተ ክርስቲያን ፈተናና እና ችግር የሆነው የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት በማክበርና ባለማክበር፤ እውነታን በመናገርና ባለመናገር፤ የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም በማስጠበቅና የግል ጥቅምን ከቤተ ክርስቲያን በማስቀደም፤ መዋቅርን በመጠበቅና ባለመጠበቅ፤ ጽኑ መንፈሳዊ አቋም በመያዝና ባለመያዝ መካከል” መሆኑን ጠቅሷል።
መግለጫው አክሎም “በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር የምንገኝ አብያተ ክርስቲያናት እያሳሰበን የመጣው የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ጠብቆና አስጠብቆ የመጓዝ ሁኔታ በመሆኑ በሀገረ ስብከታችን ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከዚህ ቀደም ያሳሰብን ቢሆንም፤ እውነት ሊደበቅ ስለማይገባ ያለውን እና ተጨባጭ የሆነውን ጉዳይ ለቅዱስ ሲኖዶስና ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በድጋሚ ማሳሰብ እንዳለብን በመረዳት ይህንን የአቋም መግለጫ አዘጋጅተናል” ብሏል።
Tuesday, January 3, 2012
አክራሪ ሙስሊሞች የወራቤ ደብረ ኃይል ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያንን ሊያቃጥሉ ሲሉ ተያዙ
‹‹ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን፡፡ ስለ ቤተ ክርስቲያን ጸልዩ››
ሰበር ዜና - ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደ
- READ THIS ARTICLE IN PDF.
- በየአህጉረ ስብከቱ ለሚፈጠሩት ችግሮች የአቡነ ጳውሎስ ግፊት እንዳለበት ቅዱስ ሲኖዶስ ገለጸ።
- አስቸኳይና ድንገተኛ ስብሰባ የተጠራው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ፓትርያርኩ ያቀረቧቸው አጀንዳዎች “ለአስቸኳይ ስብሰባ የማይበቁ ናቸው” በሚል አጣጥሏቸዋል::
- በፓትርያርኩ እልከኝነትና ተንኮል ላይ ያመረሩት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት “የቤቱ ችግር ተጣርቶ መወገዝ ያለበት ይወገዝ፤ ስለ ወንጌል አገልግሎት፣ መልካም አስተዳደር፣ ሰላም እና ልማት መነጋገር ሲገባን ቤተ ክርስቲያን በእርስዎ የተነሣ ስትበጠበጥ እና ስትናጥ መኖር የለባትም” በሚል አቡነ ጳውሎስን ሲገሥጹ እና ሲያስጠነቅቁ አርፍደዋል::
- ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከሲዳማና ጌዲኦ ዞኖች አማሮና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት እንዲነሡ ‹በ15,000 ምእመናን ፊርማ› ቀርቧል የተባለው ‹አቤቱታ› ስድነት የተሞላበትና በአቡነ ጳውሎስ ግፊት የቀረበ የተሐድሶ መናፍቃን ሤራ መሆኑን ሲኖዶሱ ገልጧል፡፡ በሕገ ወጥ አድመኞች የቀረበውን ይህንኑ ስድ አቤቱታ በመቃወም 20,000 የሐዋሳ እና ዲላ ምእመና ያሰባሰቡት የተቃውሞ ፊርማ አቤቱታ ለሲኖዶሱ ጽ/ቤት ደርሷል::
- አቡነ ጳውሎስ “ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም” የሚለውን ስመ ማዕርጋቸውን በመጠቀም በአኵስም ሀገረ ስብከት ላይ ሥልጣናቸውን የሚያጠናክር አጀንዳ አቅርበዋል፡፡ አጀንዳው አቡነ ጳውሎስ አስገነባዋለሁ ከሚሉት ሙዚዬም አገልግሎት ጋራ በተያያዘ አጠያያቂ ገጽታዎች እንዳሉበት ተነግሯል::
Saturday, December 31, 2011
አባ ፋኑኤል በዋሽንግተን ዲሲ ላይ የተናገሩት ያማፍረስ ሥራ
የተወደዳችሁ አንባቢዎቻችን ባለፈው ስለ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ያቀረብነው ዘገባ መሠረት አቡነ ፋኑኤል በዲሲ ደብረ ምሕረት ተገኝተው ይህ ደክሜ የሰራሁት ቤቴ ነው ከዚህ ማንም ውጣ ሊለኝ አይችልም "ደርግ እንኳን ሁለት ያለውን ነው የሚነጥቀው፣ እኔ ግን ያለኝ አንድ ቤቴን ነጥቃችሁ የት ልሂድ" ብለው አስገርመውናል፣ አሁንም ከፋፋይ ሥራቸውን ቀጥለውበት ይገኛሉ በፍትሕ መንፈሣዊ ላይ እንደተገለጸው ቤተክርስቲያንን በደሙ የመሠረታት ክርስቶስ እንጂ አባ ፋኑኤል እንደሚሉት እርሳቸው አልሰሩትም። አሁንም ይህንን ሥርዓት አልበኝነታቸውን በመቀጠል በአካባቢው ከሚገኙት እራሳቸውን ገለልተኛ ብለው የሚኖሩትን የቦርድ እና የካህናት ስብሰባ ጠርተው በቦታው ግምቱ ከ15 ሰው የማይበልጥ ተገኝቶ በጥያቄ ሲያወዛግባቸው ታይተዋል የውሽታቸው ብዛት ደግሞ ከአንድ የስብሰባው ተከታይ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር ጥያቄውም እንደሚከተለው ነው።
እዚህ አካባቢ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሥም የተቋቋመ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሚባል ተቋቋሞ ነበር እና ድጋሚ ለማቋቋም ለምን አስፈለገ? ተብለው ሲጠየቁ. . .
መልሳቸው: እኔ እስከማውቀው ድረስ ከወሬ ውጪ የሰማሁት ነገር የለም የተሰራም ወይም የታየ ምንም የማውቀው ነገር የለም ብለው ነበር የሸመጠጡት በጣም የሚያስገርም ነው። ለመቋቋሙም የመጀመሪያው የሀገረ ስብከቱም ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሹመው መጥተው ነበር እርሱንም እራሳቸው በዚህ ቪዲዮ ላይ ተናግረውታል።
ሌላው ከስብሰባው ተሳታፊዎች የቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ እንደሚከተለው ነው
በዚህ አካባቢ የሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት አለ ሲባል ሰምተናል ግዢውም ከሦስት ዓመት በፊት መገዛቱንም ይታወቃል ስለዚህ ለምን ሌላ ለመግዛት ወይም ለመመስረት አስፈለገ ተብለው ሲጠየቁ. . .
መልስ: ለሀገረ ስብከቱ ደብዳቤ ጽፈናል ነገር ግን መልስ አላገኘንም ብለው በሚያሳፍር ሁኔታ "በአንድ ራስ ሁለት ምላስ" እንደሚባለው ሆነው ነበር ነበር ያሳለፉት።
በአጠቃላይ ፍርዱን ለአንባቢያን እንተወዋለን።
እዚህ አካባቢ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሥም የተቋቋመ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት በሚባል ተቋቋሞ ነበር እና ድጋሚ ለማቋቋም ለምን አስፈለገ? ተብለው ሲጠየቁ. . .
መልሳቸው: እኔ እስከማውቀው ድረስ ከወሬ ውጪ የሰማሁት ነገር የለም የተሰራም ወይም የታየ ምንም የማውቀው ነገር የለም ብለው ነበር የሸመጠጡት በጣም የሚያስገርም ነው። ለመቋቋሙም የመጀመሪያው የሀገረ ስብከቱም ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሹመው መጥተው ነበር እርሱንም እራሳቸው በዚህ ቪዲዮ ላይ ተናግረውታል።
ሌላው ከስብሰባው ተሳታፊዎች የቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ እንደሚከተለው ነው
በዚህ አካባቢ የሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት አለ ሲባል ሰምተናል ግዢውም ከሦስት ዓመት በፊት መገዛቱንም ይታወቃል ስለዚህ ለምን ሌላ ለመግዛት ወይም ለመመስረት አስፈለገ ተብለው ሲጠየቁ. . .
መልስ: ለሀገረ ስብከቱ ደብዳቤ ጽፈናል ነገር ግን መልስ አላገኘንም ብለው በሚያሳፍር ሁኔታ "በአንድ ራስ ሁለት ምላስ" እንደሚባለው ሆነው ነበር ነበር ያሳለፉት።
በአጠቃላይ ፍርዱን ለአንባቢያን እንተወዋለን።
Wednesday, December 21, 2011
አስኬማው የለንም እንጂ እኛም ጳጳስ መሆን እንችላለን (የትዝታው ሳሙኤል ግሩፓች)
![]() |
| የሥርዓት አልበኞቹ ግሩፕ ቀንደኛ መሪዎች |
(አንድ አድርገን ታህሳስ 11 ፤ 2004)፡- በዲላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ህገወጥነት እና ስርዓት አልበኝነት በፊት እነ በጋሻው ደሳለኝ እና ትዝታው ሳሙኤል ባስመረጧቸው የሰበካ ጉባኤ አባላት እየተከናወነ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ አሁን በስራ ላይ የሚገኝውን የሰበካ ጉባኤ እንዲበተን እና በምትኩ ህዝቡ ይሆኑኛል ፤ ቤተክርስትያኗን ለማተዳደር እውቀቱም ሆነ ብቃቱ አላቸው ያላቸውን ሰዎች እንዲመርጡ የሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የተፃፈ ደብዳቤ ከሳምንት በፊት በእጃቸው ደርሶ ነበር፡፡ ነገር ግን ፓትርያርኩም ሆነ የሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አያገባቸውም በሚል እሳቤ ሰውን ለሌላ ብጥብጥ ለማነሳሳት የቤተክርስትያ አስተዳዳሪው የኛ የሚሏቸውን ሰዎች እየሰበሰቡ ይገኛሉ፡፡
ብፁዕ አብነ አብርሃም ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ
የአቡነ ገሪማ አምላክ አባ ጳውሎስ ይሆኑ?
በሉልሰገድ እረታ lulsegedrt@gmail.com
ክርስትና የመከራ ህይወት ነው እንደሚባለው ሆኖ እንደሆነ እንጃ በየትኛውም ዘመን የተፃፈ የትኛውንም የታሪክ መጽሐፍ የተመለከተ ሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከፈተና እና ከመከራ የተላቀቀችበት ዘመን እንደሌለ በቀላሉ መረዳት ይችላል፡፡ በ10ኛው መቶ ክ/ዘመን የዮዲት ወረራ፣ በ16ተኛው ክ/ዘመን የአህመድ ግራኝ ጭፍጨፋ፣ በ17ተኛው ክ/ዘመን የሱስንዮስ ካቶሊካዊ ወረራ፣ በ18ኛው ክ/ዘመን የዘመነ መሳፍንት የእርስ በርስ ክፍፍል፣ በጣም በቅርብ ጊዜ እንኳን የወታደራዊ መንግስት ደርግ ኮሚንስታዊ ተጽእኖ በግምባር ቀደምነት የሚጠቀሱ የቤተክርስቲያን ፈተናዎች ናቸው፡፡ መሰረታዊው ጥያቄ ግን ቤተ-ክርስቲያን እነዚህን ሁሉ መከራዎች በምን መንገድ እና በማን መስዋዕትነት ተወጣቻቸው የሚለው ሲሆን ለዚህ ጥያቄ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ በጋራ የሚሰጠው ምላሽ አንድ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም ፡፡
እነዚያ ሁሉ መከራዎች ታሪክ ሆነው የቀሩት ቤተ-ክህነቷ ባፈራቻቸው ልጆቿ በተለይም ደግሞ በአስተዳዳሪዎቿ ብርታት እና መስዋዕትነት መሆኑን ማንም የማይክደው ሐቅ ነው፡፡ በቅርብ ጊዜ ምናልባትም ከአንድ ሰው እድሜ ባልዘለለ አመት ውስጥ እንኳን በአንባገነኑ የደርግ መንግስት ስለ እምነታቸው እና ስለሀገራቸው ሰላም መስዋዕት የሆኑትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን፣ ወይም ለፋሽስት ሐገሬን ባርኬ አልሰጥም በማለት ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡትን ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን የሚዘነጋቸው ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡
ዛሬስ ———
Wednesday, December 14, 2011
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ ፈጣሪ ትዘረጋለች
በዚህ እኛ በተፈጠርንበት ዘመን በጣም ለጆሮ የሚቀፉ፣ ለማየት የሚያስደነግጡ፣ የሰሚን ጆሮ ጭው የሚያደርጉ ብዙ ክስተቶች ተከስተዋል እየተከሰቱም ነው። በተለይ በእኛ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ዙሪያ ይልቁንም ባለፉት ፳ ዓመታት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና የተለያዩ አስደንጋጭ ክስተቶች ተከስተዋል፣ የብዙ ኦርቶዶክሳውያንን አንገት አስደፍቷል፣ ለብዙዎች ኦርቶዶክሳውያን መሰደደ እና ሕልፈት እንደሆነ የአደባባይ ሚስጢር ነው ብለን እናምናለን። ለምን በዘመነ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ ዘመን በቤተክርስቲያን ላይ ይህ ሁሉ ፈተና በዛባት? ፈተነውስ ከየት የመጣ ፈተና ነው? እንደሚታወቀው በፓትሪያሪክ ጳውሎስ ዘመን ብዙ ክፍተቶች፣ ግድፈቶች፣ ቀኖና ጥሰቶች፣ ግድያዎች፣ አፈናዎች፣ ስም ማጥፋቶች፣ እንዲሁም ብዙ መጠነ ሰፊ ዘረፋዎች እና ሙስናዎች ተፈጽመዋል እነዚህ ሁሉ ግፎች እና በደሎች ሲፈጽሙ ማንም የቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ወይም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጭምር "ይደልዎ" ከማለት በስተቀር ምንም ዓይነት ተቃውሞ ያቀረቡም ሆነ የተለያዩ አቤቱታዎችን ለሚመለከተው የቤተክርስቲያን አካል ከዚያም ባሻገረ የሚመለከተው የመንግስት አካል ጥያቄ ያቀረቡ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አሉ ብሎ ለመናገር አያስደፍርም።
Monday, December 12, 2011
አባ ፋኑኤል እስከ መቼ ቤተክርስቲያንን እያመሱ ይኖራሉ?
ይህንን ጽሁፍ እንድናዘጋጅ ያስገደደን አንድ አንባቢያችን ያደረሱን መልዕክት ነው፣ መልዕክቱም አባ ፋኑኤል እንደተለመደው የመከፋፈል ሥራቸውን በዋሽንግተን ዲሲ እና ካሊፎርኒያ ግዛት ጀምረዋል። በቅርቡ የደረሰን ደብዳቤ እንደሚያመለክተው አባ ፋኑኤል እኔ በሕጋዊ መልኩ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወክዬ የመጣሁ ወኪል ነኝ ካሉ በኃላ፣ በመቀጠል በተለያዩ የዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ለሚገኙ ይልቁንም በገለልተኛ አስተዳደር ስር ላሉ አብያተ ክርስቲያናት የስብሰባ ጥሪ ደብዳቤ ልከዋል፥ ደብዳቤው እንደሚያብራራው እያንዳንዱ ቤተክርስቲያን (ደብር) ያለው መተዳደሪያ ደንብ እንደተከበረ ሆኖ ሃይማኖት እንዳይበረዝና ቀኖና ቤተክርስቲያን እንዳይፋለስ ለመጠበቅ እንድንመካከር አብረን ተነጋግረን ልንሰራ የምንችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በሚል ይጀምራል። በመቀጠል የደብራችሁ አስተዳዳሪዎች፣ የቦርድ ተወካዮች፣ እና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮች እንድትገኙልን በአክብሮት እንጠይቃለን ይላል። ሙሉውን ደብዳቤ ለማንበብ ይጫኑThursday, December 1, 2011
እንኳን ለጽዮን ማርያም በዓል አደረሳችሁ
"ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።" መዝ ፻፴፮ ፥ ፩ "የእግዚአብሔርንም ታቦት ወስዳችሁ በሰረገላው ላይ አኑሯት፤ ስለበደል መባእ ካሳ አድርጋችሁ ያቀረባችሁትን የወርቁንም ዕቃ በሣጥን ውስጥ አድርጋችሁ በታቦቷ አጠገብ አኑሯት፤ ትሄድም ዘንድ ስደዱአት።"
፩ኛ ሳሙ ፮ ፥ ፩
የእመቤታችን የቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ጣዒሟንና ፍቅሯን በልባችን ጽላት ያሳድርብን ከበዓሉ ረድሄት በረከት ያካፍለን። አሜን!!!
፩፦ «ሰው እናታችን ጽዮን ይላል»«እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ፥ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ፤ ወውእቱ ልዑል ሣረራ። ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጧም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።» ይላል። መዝ ፹፮፥፭። ቅዱስ ዳዊት ጽዮንን እናት ብሏታል። እናት፦ ወላጅ፥ መገኛ፥የአባት ሁለተኛ ናት። እግዚአብሔር በአሠርቱ ትእዛዛት፦ «አክብር አባከ ወእመከ፤ ከመ ይኩንከ ጽድቀ፥ ወይኑኅ መዋዕሊከ በውስተ ምድር ዘይሁበከ እግዚአብሔር አምላክከ። አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ (ቸርነቱ ረድኤቱ ይደረግልህ ዘንድ) ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚስጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም፤ » እንዳለ፦ እናት ከአባት እኲል ክብር ይገባታል። ዘጸ ፳ ፥፲፪። ጽዮን ማለት ደግሞ አምባ መጠጊያ ማለት ነው።
Wednesday, November 30, 2011
ዝምታው እስከመቼ ነው?
ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማውያንን ጉባኤ ልታዘጋጅ ነው
"እግዚአብሔርም ሰዶምንና ገሞራን ባፈረሰ ጊዜ እንደ ነበረው፥ የመንግሥታት ክብር የከለዳውያንም ትዕቢት ጌጥ ባቢሎን እንዲሁ ትሆናለች። "
ትንቢተ ኢሳያስ ፲፫ ፥ ፲፱
"ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተምች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንዲሁ ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰውም ልጅ አይኖርባትም። "
ትንቢተ ኤርሚያስ ፶ ፥ ፵
"ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ እንዲሁ ገለበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር፦ "
ትንቢተ አሞጽ ፬ ፥ ፲፩
"ኃጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥ "
፪ኛ የጴጥሮስ መልዕክት ፪ ፥ ፮
ወገኖቼ እናስተውል ዛሬ እንዲህ ዓይነት በዓይናችን ላይ የሚሰራው ነገር ከምዕራባዊያን የመጣ ባሕል እና ህይወት ነገ የእያንዳንዳችን ቤት ማንኳኳቱ አይቀሬ ነው፣ ሰዶማውያንን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አጥብቃ ትቃወማለች፣ ትጸየፈዋለችም እንዲህ ዓይነቱን በሽታም በህዝባችን የእለት ተዕለት ኑሮውን እንዲያበላሸው ወይንም እንዲበርዘው የማናችንም ምኞት አይደለም ስለሆነም፣ ሕፃን፣ ወጣት፣ አዋቂ፣ ሽማግሌ እና አሮጊት እንዲሁም ክርስቲያን፣ እስላም፣ ወይንም ሃይማኖት የለሹም ቢሆን ይሄንን ኢ - ኢትዮጵያዊ የሆነውን ምግባረ ብልሹነት የምዕራባውያን ቅብጠትን ወይም ሰይጣናዊነት አጥብቀን ልንቃወመው የሚገባ ወቅታዊ ጉዳይ ነው ብለን የዚህ ዝግጅት ክፍል ያምናል፡
"የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም"
ቤተክርስትያናችንን አፈረሱብን
ቤተክርስትያናችንን አፈረሱብን
- በስልጤ ዞን ቅበት ከተማ በአካባቢው ሙስሊሞችና ፖሊሶች የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን አፈረሱ
- ፓትሪያሪኩስ እንዴት ዝም ይላሉ? ለምን ለመንግስት አካላት አያሳውቁም፣
- ቋሚ ሲኖዶሱስ እንዴት ዝም ይላል፣ ቤተ ክርስቲያን ስትፈርስ ለምን ዝም ይባላል
- በዓለም ዙሪያ ያለ እያንዳንዱ የተዋሕዶ ልጆች ይህንን ጉዳይ በዝምታ ማለፍ የለብንም
- የከተማው ሕግ ቢፈቅድ እንኳ የቤተ ክርስቲያን የበላይ አባቶች እና ተጠሪዎች ይህንን እንዴት ዝም ብለው ይመለከታሉ?
(አንድ አድርገን ህዳር 19 ፤2004 ዓ.ም November 29 2011 ) በስልጤ ዞን ከቅበት ከተማ 2 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኝው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን አርብ በ15 /03/04 በሙስሊም ፖሊስ አባላትና እነርሱን ከሚመስሏቸው ማህበረሰብ አካላት ጋር ሆነው ቤተክርስትያኗን ያፈረሷት ሲሆን ፤ በአካባቢው የሚገኝ ታማኝ ምንጭ ለማወቅ እንደቻልነው የቤተክርስትያኒቷ ጉልላት በፖሊስ አዛዡ ግቢ ውስጥ መገኘቱን በዓየይናቸው ተመልክተዋለል ፤ በዞኑ ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ አማኞች የሚደርስባቸው ግፍ አስመክቶ ከስልጤ ዞን ቅበት ከተማ ትናንት በ18/03/2004 ዓ.ም ማለዳ በደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ፅ/ቤት ክርስቲያኖች ለአቤቱታ በአምስት መኪና የሄዱ ሲሆን :: አቤቱታ አቅራቢዎች የደቡብ ክልል ርዕሠ መስተዳድር ቃል አቀባይ የሆኑት እስከ 10 ሠዓት ድረስ ሲሳለቁባቸው ውለው ያለ ምንም መፍትሄ ሸኝተዋችዋል:: አቤቱታ አቅራቢዎቹ ተመልሠው ወደመጡበት አካባቢ ቢመለሱ የመኖር ህልውናቸውናቸው አስጊ በመሆኑ በመጀመሪያ የደቡብ ክልል ፍትህ እና ፀጥታ ቢሮ ከዞኑ ፖሊስ ለሚደርስባቸው ጫና ገለልተኛ በሆኑ ፖሊስ እንዲጠበቁ ለማድረግ ቀጥሎም ለፌደራል መንግስት ለማሳወቅ አዲስ አበባ እንደሚያመሩ በባዶ ሆዳቸው መሪር እንባ እያነቡ ሲናገሩ ላያቸው ያስለቅሱ ነበር፡፡›› በማለት ዘግቦልናል ፡፡ጉዳዩን አስመልክቶ የሀገረሥብከቱ ሊቀጳጳስ አቡነ ቀሌምጦሰም ለሚመለከታቸው ደብዳቤ እንደፃፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
Tuesday, November 29, 2011
ከደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ምዕመን ምልከታ
Subscribe to:
Posts (Atom)





