Friday, December 5, 2025

መምህር ዲ/ን ዮሴፍ ዛሬም በግፈኞች እሥር እንዲቀጥል ተደጓል! እግዚኦ ለዳኝነት!!

መምህር ዮሴፍ ዛሬም አልተፈታም፡፡ ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ የተቀጠረ የነበረ ቢሆንም አሁንም ፖሊስ ይግባኝ በማለቱና ወንጀል
መምህር ዲ/ን ዮሴፍ

ሊያገኝበት ስላልቻል ለቀጣይ ማክሰኞ ቀጥረውታል፡፡ ለቀጣይም ዮሴፍ ላይ ወንጀል ማግኘት አይችልም፡፡ የማራዘሚያ ዘልዛላ ምክንያት ግን ይፈበርክ ይሆናል፡፡

ዮሴፍ እንዳይፈታ እየታገለ ያለው ታጋይ የሚባለው ቤተ ክርስቲያንን ይታገልና ሥርዓቱን ያገለግል ዘንድ በቤተ ክርስቲያን ስም የሆነ ተቋም ''እመራለሁ'' የሚል ሰው ነው፡፡ 

ምንም እንኳን አሁን እንደተገለጠው ዮሴፍ አንድ ታጋይ የሚባል የቀድሞ ደረሳ እስረኛ ቢሆንም ለዮሴፍ መንገላታት ግን ዋና ተጠያቂው የቤተ ክርስቲያን ጠላት የሆነው ሥርዓቱ ነው፡፡ እንደ ታጋይ ያሉ አረመኔዎች የግል ታሳሪዎቻቸውን ያለ ምንም ወንጀል በመንግሥት ማረሚያ ቤት የሚያጉሩ ከሆነ ተጠያቂው ሥርዓቱ ነው፡፡ 

ይኸ ሥርዓት ገና ከጥንስሱ የቤተ ክርስቲያን ጠላትነቱን ያስመሰከረና ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ጥራዝ ነጠቆችን፣ ሆዳሞችንና ከሐዲዎችን በመሰብሰብ በራሷ ልጆች በሚመስል መልኩ በተደጋጋሚ እያቆሰላት ይገኛል፡፡ ሥርዓቱን የሚያገለግሉ፣ ቋንቋዋን የሚናገሩና አልባሳቷን የሚለብሱ ሰዎችን የሚፈልጋቸው ከውስጥ ያለውን መከራ ለማጽናት ነው፡፡ 

Thursday, December 4, 2025

✍️መንግሥት በወንድማችን ዮሴፍ አንጻር ቤተ ክርስትያን ላይ የሚያደርገውን ቀልድ ቀጥሎበታል፡፡

ሁላችንም እንደምናውቀው መምህር ዮሴፍ የታፈነው ዕለተ ቅዳሜ ከሥራ ገበታው ላይ እጅግ አጸያፊ በሆነ መልኩ፣ መታሰሩን እንኳን
ዲ/ን ዮሴፍ ፍሰሐ 

ለቤተሰብ እንዲናገር ሳይፈቅዱለት ነበር፡፡ ከዚያም በወንድሞች የየማጎሪያ ቤት ዳሰሳ ከብዙ ድካም በኋላ በማእከላዊ የቶርቸር ቻምበር ውስጥ ለብቻው ጨላማ ክፍል ውስጥ አስረውት የከረሙ መሆኑ ተደረሰበት፡፡ በጨለማ ቤት ባሰሩባቸው ቀናት ማንም ሳያውቅ ፍርድ ቤትም አቅርበውትም ነበር፡፡ ልብ አድርጉ! ያንን ያደረጉት ጠበቃ እንዲቆምለትም ሳይፈቅዱ፣ ቤተሰብ እንዲጠይቀውም ሳያደርጉ ነበር፡፡ 

ከሳንንት እንግልት በኋላ ቤተሰብ እንዲጠይቀው ፈቀዱ፣ ከዚያም የታሰረበትን ወሕኒ ቤትና የፈርድ ቤት ቀጠሮው ከታወቀ በኋላ ጠበቆች ቆሙለት፡፡ ባለፈው ፍርድ ቤት አቅርበውት ምንም በደል ስላላገኙበት ፖሊስ ተጨማሪ 10 ቀናት ያስፈልገኛል በማለቱ ለታኅሳስ 2 ቀጥረውት ነበር፡፡

 የታሰረው በፌስቡክ በለጠፈው ሆኖ ሳለ ሌላ በደል ፍለጋ ትርጉም የማይሰጥ ስለሆነ ቀጠሮው ማጠር አለበት የሚል ይግባኝ ጠበቆቹ ስላስገቡ ትናንት ከቀኑ ሰምንት ሰዓት ላይ በድጋሜ ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር፡፡ አሳፋሪው የፖሊስ መከራከሪያ 'ላይክና ሼር ያደረጉ አባላቱን እያፈላለኩ ነውና ከወጣ ተፈለጊዎቹን ይሰውርብኝል' የሚል በዐለም ላይ ተሰምቶ የማይታወቅን ደደብ ካልሆንክ ብቻ ልትናገረው የማትችለውን መከራከሪያ ቢያቀርብም ፍርዱ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ 8፡30 ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡ 

ወልዲያ ከተማ ውስጥ የሚገኙ በርካታ የዓብነት ተማሪዎች ከቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ታፍሰው መወሰዳቸው ታወቀ

DEC 01, 2025
የጠለፋ ወንጀል በኢትዮጵያ ተባብሷል
(መሠረት ሚድያ)- በቅርብ ወራት በበርካታ ከተሞች ውስጥ ወጣቶች ከየመንገዱ እና ከስራ ቦታ እየታፈሱ ለስልጠና ወደ ካምፖች እየገቡ 
እንደሆነ በተደጋጋሚ ያወጣናቸው መረጃዎች ጠቁመዋል። 
አሁን ከወደ ወልዲያ የደረሰን መረጃ እንደሚጠቁመው በርካታ የዓብነት ተማሪዎች ባሳለፍነው ሳምንት ከቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ታፍሰው ተወስደዋል። 
ስልካቸውን ከተቀሙ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት በሚሊሻዎች የተወሰዱት የዓብነት (የቤተክርስቲያን) ተማሪዎቹ በወልዲያ ከተማ የሚገኘው የቲንፋዝ ደብረ በረከት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርሰቲያን እና የሌሎች ቤተክርስቲያኖች ተማሪዎች መሆናቸው ታውቋል። 

"ዓራት ዓይናው ታላቁ አባት መላከ ገነት አምደብርሃን የኔታ ይባቤ በላይ ትላንት ምሽት ለዛሬ ሌሊት አጥቢያ አርፈዋል " - ቤተክርስቲያኗ

➡️ " የስኳር ህመም በፊትም አለባቸው፤ ግን አሞኝም ብለው ከጉባዔ አልወረዱም፤ ከተኙ በኋላ ነው ገደማያውያኑ 'ምን ነው'? 
መልአከ ገነት አምደብርሃን የኔታ ይባቤ በላይ

ሲሏቸው ማውራት አልቻሉም' ነው ያሉን" - የሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት

በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት፣ "ክብረ ደናግል ናዳ ቅድስት ማርያም ገዳም" አበምኔት፣ የአራቱ ጉባዔያት መምህር መላከ ገነት አምደብርሃን የኔታ ይባቤ በላይ ማረፋቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ረፋድ ገልጻለች።

የቤተክርስቲያኗ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ መላከሰላም ሰለሞን ቶልቻ በሰጡን ቃል፣ " ዓራት ዓይናው ታላቁ አባት መላከ ገነት አምደብርሃን የኔታ ይባቤ በላይ ትላንት ምሽት ለዛሬ ሌሊት አጥቢያ አርፈዋል " ብለዋል።

በምዕራብ ሐረርጌ የታፈነው ጩኸት እና በአርሲ የቀጠለው ዘር ፍጅት!

ምዕራብ ሐረርጌ ዞን፣ ጭሮ ወረዳ፣ ላሎ ጉዶ ቀበሌ፣  ኢፈ ባስ (ifabaas) በምትባል የገጠር መንደር ውስጥ በኅዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም 
እናት ፓርቲ

ከምሽቱ 3:00 እልፌ ተስፋ ወሌ የሚባሉ እናት በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። በዚኹ ቀበሌና በአጎራባች ቀበሌዎች ያብዶ ሸንበቆ፣ ረብሱ፣ ሼክ አደም፣ ሉጎ በርካታ ሃይማኖትና ማንነትን ማዕከል ያደረጉ ጭፍጨፋዎች የሚካሄዱባቸው ናቸው። ብንናገርም ሰሚ የለም። ሕዝቡና ሚዲያውም እኛን ረስቶናል ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች በምሬትና በፍርኃት ተውጠው። 

በወረዳው በቅርቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት የኾኑ ተፈሪ መንገሻ ከነ ባለቤቱ ቀለሟ በለጠ ጋር፣ ባለው መንገሻ፣ አሳምነው አባይነህ የተባሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በአሰቃቂ ኹኔታ በስለትና በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል፤ በርካቶችም ቆስለዋል። ግድያውን የሚፈጽመው በአካባቢው ሰዎች አጠራር ኦነግ ሸኔ(ራሱን ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ኃይል) ነው። 

ይኽን መረጃ እያጣራን ባለንበት አፍታ በአርሲ ዞን በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ፣ በቀቅሳ ቀበሌ በአጨዳ ላይ የነበሩ ከ19 በላይ ገበሬዎች ኅዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ታፍነው መወሰዳቸውን ከቦታው ለማረጋገጥ ችለናል። በዚኹ አካባቢ በቅርቡ ወንድማማቾችን ጨምሮ ሦስት ንጹሓን እንደተገደሉ ይታወሳል። 

Wednesday, December 3, 2025

ይድረስ ለኦርቶዶክሳውያን ሚዲያዎች



ይኽ ሰው አብደላ አማን(አብደላ ማይክሮ) ይባላል።በምሥራቅ አርሲ ዞን የ ሽርካ ወረዳ የምክር ቤት አባል ነው።የሽርካ  የኦርቶዶክሳውያን

ላይ በሚፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ከወረዳው አስተዳዳሪ እስከ ቀበሌ ድረስ ያሉ ካድሬዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጃቸው እንዳለበት የታወቀ ነው አቶ አብደላ ግን ትልቅ ሚና ያለው ሰው ነው፦

፩  አራጁን ቡድን(የኦሮሞ ኢስላማዊ መንግሥት ታጣቂዎችን) የሚያንቀሳቅሰው እርሱ ነው

፪  መቀመጫውን ባሌ በረሃ ካደረገው አል ሸባብ  Al shabab ቡድን  ጋር በቀጥታ ግኑኝነት አለው

Tuesday, December 2, 2025

“ ስንዴውን እየሸከፈ ነው”

      “ስንዴውን እየሸከፈ ነው”

ጌታ ራሱን ከመሰለበት ምሳሌዎች ንጹሕ ዘር በሚዘራ ገበሬ ነው።እርሻውም ይህ ዓለም፣ ዘሩንም ወንጌል ነው።እንክርዳድም ክፉት
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ 

ዘሪውም ዲያብሎስ ነው።እንክርዳዱም የሚዘራው  ሰዎቹ ሲተኙ ነው። ሰዎቹ ያላቸው ታላላቁ የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸው። ማንቀላፋታቸው ዕረፍታቸው ሲሆን ሰዎቹ ሲተኙ እንክርዳድ መዘራቱ ታላላቆቹ ሲያርፉ በዲያብሎስና ግብር አበሮቹ አዲስ እንክርዳድ ሥርዓት ይዘራልና።አብረውም እስከ መከር ይቆያሉ።መከሩ የዚህ ዓለም ማለቅ ሆኖ አጫጆቹም መልእክት ናቸው።ያን ጊዜ ንጉሥ ስንዴውን ከእንክርዳዱ የሚያበጥርበት የማያሳስት ሥልጣን የተባለ ነፋስ አለው።እንክርዳዱን በእሳት አቃጥሎ ስንዴውን በመንግሥተ ሰማያት ጎተራ ይሰበስባል ነበር የተማርነው።ማቴ፲፫፥፴፱-፵፪

የሥጋ ዓይን ሳይኖራቸው በነፍሳቸው  የሚያዩት የኔታ መጋቤ ምሥጢር ተሾመ ደግሞ አሁንም “ስንዴውን እየሸከፈ ነው አሉ”።በ፳፲፫ ዓም መጽሐፈ መነኮሳትን ከእርሳቸው እያሄድኩ ሳለ ወንበር እንዳበቃ አንድ ትልቅ ሰው እንዳረፉ ሰማን።የኔታም ካዘኑ በኋላ “ አይ እግዚአብሔር እኮ እንክርዳዱን ለማቃጠል ስንዴውን አስቀድሞ እየሸከፈ  ነው” አሉ። ምን ማለት ነው የኔታ ስላቸው፦ “ ሰዉ ከፍቷል፤አልመለስ ብሏል፤ ስለዚህ ወዳጆቹን አስቀድሞ ሸካክፎ በመከራ እሳት ሊገርፈን ይመስለኛል አሉ” ያን ጊዜም ጦርነት ውስጥ ነበርን። አሁንም እንደዚያው የመከራው እሳት እየገረፈን አለን።በጊዜው ተጨንቄ አሁንም የሚሆነውን ሁሉ እያየሁ እያሰብኳቸው ሳለ  እንዳረፉ ሰማሁ። 

Saturday, November 29, 2025

ቆመኽ አንገትኽን ተቆረጥ

የአርሲ ሰማዕታት ደም ይጮኻል 

ዛሬ ባለንበት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መከራ የቀደመ የአስተሳሰባችን ውጤት ነው። በሃገሩ ሽማግሌ አለ፣
መንግሥት አለ ብሎ ያምናል። በዚያም ሲተዳደር የኖረ ነው። በተለይ በሃይማሞት ረገድ ብዙም የከፋ ነገር አይቶ አያውቅም። በብልጽግና ዘመን መከራ አይነቱን ከመቁጠር በዝቶ መስማት ሰልችቶናል። ሰምተን እንዳልሰማን ለመኾን እንሞክራለን። 

አኹን አስተሳሰባችን ሙሉ በሙሉ ነው መቀየር ያለበት። ነጠላ ለብሶ ከበሮ የሚያሽከረክረው እንዲኽ አይቀጥልም። ልፍስፍስ ወጣት ማምረት መቆም አለበት። አራሽ ቀዳሽ ተኳሽ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰ መኾን። የቀደመ አባቶቹን መምሰል ግድ ይላል። 
“አትግደል” ተብሏል እያለ ቆሞ አንገቱን እንደ ሸንበቆ የሚሰጥ ጅል ትውልድ አፍርተናል። ይኽ ነው እያስገደለን ያለው። 

አውሮጳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ «ይፈፀማል» ያሉትን ግድያ በሠልፍ አወገዙ

ኢትዮጵያውያን በአውሮጳ
ጀርመን እና በአጎራባች የአውሮጳ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ  ውስጥ በተለይ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ክርስቲያኖች ላይ ይፈፀማል ያሉትን ግድያ፣ ግፍና ማፈናቀል ዛሬ በርሊን-ጀርመን ውስጥ ባደረጉት የአደባባይ ሠልፍ አወገዙ። ሰልፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት አስተባባሪነት የተጠራ ሲሆን በተለያዩ የጀርመን ከተሞች፤ እንዲሁም በጀርመን አጎራባች የአውሮጳ ሃገራት ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያ ተሳትፈዋል።

ሰልፈኞቹ እንደሚሉት የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ አካባባቢዎች «በተደጋጋሚና ሆን ተብሎ» የሚፈፀመውን ግድያና ግፍ እስካሁን ማስቆም አልቻለም። «ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ የሚፈጸመው በቃላት ተገልጾ የሚያልቅ አይደለም» ያሉት ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ከተሰላፊዎቹ አንዱ የሆኑት በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሥራችና የኮሎኝ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል አስተዳዳሪ ሊቀካህናት ዶክተር መርዓዊ ተበጀ፤ «ሰዎች በቋንቋቸው፤ እንደዚሁም በሃይማኖታቸው ተለይተው እየታረዱ፣ እየተጨረሰ ይህን ያህል ግፍ ሲፈጸምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ተብዬ ይህን ሰቆቃ ሊያስቆም አልቻለም» በማለት ዛሬ ድምጻቸውን በዓለም ሸንጎ ለማሰማት መውጣታቸውን ገልጸዋል። የሰልፉ ተሳታፊዎች ኢትዮጵያውያን ካህናትና ምዕመናን ብቻ ሳይሆኑ የሌሎች ሃገራት ዜጎችም አብረዋቸው ድምጻቸውን እያሰሙ እንደሆነም አመልክተዋል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል አርሲ፤ ጅማ፤ ወለጋ፣ ሻሸመኔ፣ እንዲሁም በሐረር ክርስቲያኖች መገደላቸውን የገለጹት ሊቀካህናት ዶክተር መርዓዊ፤ ባጠቃላይ «በሀገሪቱ ግፍ እየተፈጸመ ነው» በማለት በጀርመንዋ ዋና ከተማ በርሊን ለሰልፍ ያስወጣቸውን ምክንያት ዘርዝረዋል።

ወንጌለ ናዚዝም

የኦሮሙማው ክንፍ
"ብዙዎች ግን ወተታችንን ይወዳሉ ፣ሥጋችንን ይወዳሉ፣ፍየሎቻችንን ይወዳሉ፣በጎቻችንን ይወዳሉ፣በሬዎቻችንን ይወዱታል፣መሬታችንን
ይወዳሉ፣ከተሞቻችንን ይወዳሉ እኛን ግን......???"

ይኽ የናዚዝም  (የጥላቻ የወንጌል ) የሚሰበከው  በዘር ተቋቋመው በወልዳ ዱካ ቡኦታ ማኅበር በተዘጋጀው  መርሐ ግብር ላይ ነው። በአራት ኪሎ።እኝህ ሰው "ምንም ቅልቅል ዘር የሌለባቸው ተንጹህ ኦሮሞ ጳጳስ(Organic Oromo)"  ተብለው የጰጰሱት ነገር ግን አንገታቸው በአክራሪ እስልምና ስለሚቀላው  ኦሮሚኛ ተናጋሪ ኦርቶዶክሶች ትንፍሽ የማይሉ በአንጻሩ ደግሞ የኦሮሞ ብሔርተኝነት ዋና አቀንቃኝ ናቸው።"ድንግል ማርያም ቤዛዊተ ዓለም አትባልም "የሚል የምንፍቅና ትምህርት አስተምረው "ኦሮሞ በመሆኔ ተዘመተብኝ" ማለታቸውም የሚታወስ ነው።እኔ የሚያዝኑኝ እኝህንና መሰሎቻቸውን "አባት" ብለው እየተከተሉ የመታረጃ ቀናቸውን የሚጠባበቁ ኦሮሞች ናቸው። እባካችሁ ዘረኝነትን እየተጸየፍን በኦርቶዶክሳዊ ኅብረታችንን እንበርታ ።በልዩ ወንጌል በልዩ ትምህርት አንወሰድ። ማንም ይሁን ማን ከምሥራቅ ይምጣ ከምዕራብ፣ከሰሜን ይምጣ ከደቡብ መለያየትን፣ዘረኝነትን የሚሰብክ እንኳንስ አባታችን ኦርቶዶክስ ሊባል አይገባውም።


የሰሜን አሜሪካ ማኅበራት የጋራ መግለጫ

የሰሜን አሜሪካ ማኅበራት የጋራ ማግለጫ
ቀን ኅዳር ፲፩/፳፻፲፰ ዓ/ም (November 20, 2025)

 

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

 

ምሥራቅ አርሲ በምዕራብ ሐረርጌ እንዲሁም በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገደሉ እና መከራ እየተቀበሉ ያሉ ኦርቶዶክሳውያንን አስመልክቶ የተሰጠ የጋራ መግለጫ

 

ü    የሰሜን አሜሪካ ካሪቢያንና ላቲን አሜሪካ የሰንበት ት/ቤቶች ኅብረት፣

ü    በኢ/ኦ/ተ/ሰ/ት/ቤ/ማ/መ ማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል፣

ü    በኢ/ኦ/ተ/ቤ የማኅበረ በዓለ ወልድ በሰሜን አሜሪካ

ü    ዋልድባን እንታደግ ሰሜን አሜሪካ

 

Wednesday, November 26, 2025

የዘጸአት ነገረ መለኮት ትርጓሜ

ጉዞ ወደ ከነዓን 

ከነዓን በትርጉሙ ዝቅ ያለ ትኁት የሚል ትርጉም ሲኖረው የሸንበቆ ምድር ማለት ነው የሚልም አለ። ነገር ግን የኖኅ የልጅ ልጆች የካም
ስንቶች ምንደኞች አሉን ይሆን? 

ዘሮች ሲሆን መጀመሪያ የተስፋይቱን ምድር የኖሩ የጥንቷ ከነዓናውያን ሕዝቦች መጠሪያ ነው። በጥቅሉ የተስፋይቱ ምድርን ያመለክታል። በዮርዳኖስና በሜዲትራንያን መካከል ያለ ነው። ዘፍ.9 እና 10

 የነዌ ልጅ ኢያሱ እንጂ ሙሴ የእስራኤልን ልጆች ዮርዳኖስን እንዳላሻገራቸው እንዲሁ ክርስቶስ ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚገቡባትን ጥምቀት ለአዳም ልጆች አልሰጣቸውም ይኽንን መንፈስ ቅዱስ ሰጣቸው እንጂ። ይኽውም ከእርሱ ጋር ያለ የክርስቶስ መንፈስ ነው። (ዘቦቱ ለከ ምስሌሁ ወምስለ ቅዱስ መንፈስ) እንዲል) ሊጦን።

እርሱም ከሁሉም ሐዋርያት ጋር ይኖራል እነዚኽም በእውነት መንግሥቱን እስኪወርሱም ድረስ በዲያብሎስ ሠራዊት ላይ ድል መንሳትን አሸናፊነትን ይሰጣቸዋል። 

Monday, November 24, 2025

የነቢያት ጾም- እንኳን አደረሰን።

በዘመነ ብሉይ ነቢያት እግዚአብሔር ወልድ ከንጽሕተ ንጹሐን፤ ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ
ለአዳም የገባለትን ቃል ይፈጽም ዘንድ  ትንቢት በመናገር ለሕዝቡ የምሥራችን ቃል ያበሥሩ ነበር፡፡ አምላካችን ከድንግል ተወልዶ ከእናቱ ጋር ወደ ግብፅ ምድር እንደሚሰደድ፣ በባሕረ ዮርዳኖስ እንደሚጠመቅ፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል መከራና ስቃይ እንደሚቀበል፣ እንደሚሰቀል፣ እንደሚሞት፣ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፣ እንደሚያርግና ዳግም ለፍርድ እንደሚመጣ  በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አስቀድመው ትንቢት ተናግረዋል፡፡

ነቢያቱም የትንቢቱን መፈጸም በተስፋ ይጠብቁ፣ በጾምና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ይማጸኑ ነበር፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ አስቀድሞ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ‹‹ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኃል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች›› በማለትም እንደተናገረ ትንቢት ኢሳይያስ ላይ ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡ (ኢሳ. ፯፥ ፲፬)

Friday, November 21, 2025

ኅዳር ሚካኤል

ቅዱስ ኤጲፋንዮስ “ሚካኤል ሥዩም በዲበ ኃይላት፤ በኃይላት ላይ የተሾምክ ሚካኤል” ሲል ያመሰገነው ቅዱስ ሚካኤል በኃይላት መላእክት ላይ የተሾመ ሊቀ መላእክት እንደመሆኑ በዓለ ሢመቱ ኅዳር ፲፪ ቀን በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ይከበራል፡፡ (መጽሐፈ አክሲማሮስ)
ኃይላት የተባሉት መላእክትም ሰዎች በዓለም ፈተና ውስጥ ሆነው ሰይጣን ሊያደክማቸው ሲፈልግ ኃይልን ብርታትን የሚሰጡ፣ ይህን ዓለም ንቀው በበርሃ ወድቀው ከሥጋ ምኞት ጋር የሚጋደሉትን፣ በከተማም እየኖሩ መንፈሳዊ ትሩፋት የሚያደርጉትን ደግሞ የሚያበረቱ ናቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ በመልእክቱ “እርሱም ወደ ሰማይ ያረገ እግዚአብሔርም ተቀምጦ ያለ መላእክትና ሥልጣናት ኃይላትም የተገዙለት ነው” ሲል  “ኃይላት” በማለት ያነሣቸው በኢዮር አራተኛይቷ  ከተማ  የሚኖሩትን  ነው፡፡ በእነዚህ ላይ እግዚአብሔር  ቅዱስ ሚካኤልን አለቃቸው አድርጎ ሾሞታል፡፡ (፩ኛጴጥ.፫፥፳፪)
ሊቀ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል

የቅዱስ  ሚካኤል  ሢመት  በነገደ  መላእክት  ላይ ብቻም ግን  አይደለም፤  የእግዚአብሔር  ሕዝብ  በሆኑት  ላይም ጭምር ነው፡፡ ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ትርጓሜ በዕብራይስጥ “እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠቅሳሉ፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ላይ እንዳሰፈሩት ደግሞ የስሙን ፊደላት በመተንተን እንዲህ ተርጉመውታል፤ ሚ-መኑ፣ ካ-ከመ፣ ኤል-አምላክ፤ “መኑ ከመ አምላክ፤ እንደ አምላክ  ማን ነው”  (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ)
የሰማይ ሠራዊት ሁሉ አለቃቸው  ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ  ይኽ ኃያል መልአክ  ቅዱስ  ሚካኤል በብሉይ  ኪዳን  የእግዚአብሔር  ሕዝብ  የተባሉትን  እስራኤል  ዘሥጋን  ሲረዳና  ሲጠብቅ  እንደነበረ ተጽፎልን  እናገኛለን፡፡  ለምሳሌ  መልአኩ  ቅዱስ  ሚካኤል  ለኢያሱ  በኢያሪኮ  ምድረ  በዳ  እንደተገለጠለት  “… ዐይኑን  አንሥቶ  ተመለከተ፤  እነሆም፥  የተመዘዘ  ሰይፍ  በእጁ የያዘ  ሰው  በፊቱ  ቆሞ አየ፤  ኢያሱም  ወደ  እርሱ  ቀርቦ፥  “ከእኛ  ወገን  ወይስ  ከጠላቶቻችን  ወገን  ነህ?”  አለው፡፡  እርሱም “እኔ  የእግዚአብሔር  ሠራዊት  አለቃ  ነኝ፤  አሁንም  ወደ  አንተ መጥቼአለሁ፡፡” ሲል ተናግሯል፡፡ (ኢያ.፭፥፲፫)
እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነፃ ሲያወጣቸው ይመራቸው የነበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ “በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ፥ ወዳዘጋጀሁልህም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ ፥እኔ መልአኬን በፊትህ እልካለሁ”  እንዲል፤  ሹመቱ  በእግዚአብሔር  ሕዝብ  ላይም  በመሆኑ  ስለ  እነርሱ ከእግዚአብሔር ምሕረትን ይለምንላቸው  ነበር፡፡ (ዘፀአት.፳፫፥፳)

“እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ”

“እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ”
  ኢያ.፭፥፲፫

በቅድስና፣ በውዳሴ፣ በኅብረ ቀለም በመላእክት ዝማሬ በደመቀው በዓለመ መላእክት ውስጥ ቅዱሳን መላእክት በነገድ ተከፍለው
መኑ ከመ እግዚአብሔር

ይኖራሉ፡፡ እነርሱም የዘወትር ምግባራቸው እንዲያውም ምግባቸው ፈጣሪን ማመስገን ነው፡፡ ስፍራ ቁጥር የሌላቸው መላእክቱም በሦስቱ የመላእክት ከተሞች ኢዮር፣ ራማ እና ኤረር በአለቃቸው ስር ሆነው ዘወትር አምላክን ያገለግላሉ፡፡ ለዚኽም ድንቅ ሥራው ክብረ ምስጋና ይድረሰውና፣ በኢዮር ከተማ የኃይላት አለቃ አድርጎ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ሾሞታል፤ ይኽም የሆነበት ኅዳር ፲፪ ቀን የከበረ በዓል ነው፡፡ ስለዚኽ የዚህን የከበረና የገናና መልአክ በዓሉን እንድናደረግ ቅዱሳን አባቶች ሥርዓት ሠሩልን፡፡

የስሙ ትርጓሜ “ማን እንደ እግዚአብሔር” የሆነው የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል፣ እንደ አምላክ ኃያል፣ ቸርና ርኅሩኅ ነው፤ በቅዱሱ መጽሐፍ ላይ ይኽንን ነገር ራሱ መልአኩ ለነቢዩ ኢያሱ እንዲህ ሲል ገልጾለታል “እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ” ኢያ.፭፥፲፫

ሊቀ መለእክት ቅዱስ ሚካኤል፣ ለእኛ ሰዎች አምላጅ ሲሆን ለቅዱሳና ሰማዕታት ደግሞ አጋዣቸው የሆነው ነው፤ በሕይወታቸውና በተጋድሏቸውም እስከ መጨረሻው ይረዳቸዋል።

እግዚአብሔርን የሚወድ  ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዎብስታ ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያደርጉ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ ለቅዱስ ሚካኤልም ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን እስኪያጡ ድረስ ቸገራቸው፡፡ ዱራታዎስም ሸጦ ለመልአኩ በዓል መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱንና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡

Thursday, November 20, 2025

በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ውሃቢያ እና ጂሃዲስት ምን ላይ እንዳሉ ያየም የሰማም የለም




ዛሬ ዛሬ በሃገራችን ኢትዮጵያ ያለው መንግሥትም ሆነ ሕዝቡ በጣም ያልተገነዘበው አንድ ትልቅ አደጋ ለሃገራችንም፣ ለሕዝባችንም ብሎም ለቀጠናው ከፍተኛ የሆነ አደጋ የጋረጠ ነገር ቀስ በቀስ እግር አውጥቶ እየተንሰራፋ ባለበት በአሁኑ ወቅት፤ ከሁሉም በላይ በሃላፊነት ስሜን የሕዝቦችን ደህንነት እና ሁኔታ መጠበቅ ማስጠበቅ፤ የሕግ የበላይነትን ማስፈን ያለበት መንግሥት ቢሆንም ያንን ሥራውን ለሌሎች አሳልፎ የሰጠበት እና ዋናውን ሥራውን ትቶ ብዙ በማይመለከተው እና ባልበላው ቦታ ላይ ገብቶ ሕዝብን ከሕዝብ ሲያጫርስ እና እራሱም መሣሪያ ሆኖ አንድን ማኅበረሰብ ለመጨረስ ወይም ቁጥር ለመቀነስ በሚል ብዙ ድካም ሲደክም እና ነገሮችም ሳይሳኩለት እየታየ ነው፤ ከመንግሥትም አካላት ተው የሚለውም ያለ አይመስልም፤ ለነገሩ ብዙዎቹም የመንግሥት አካላት አብረው ተከትለው እንደ ነፋስ መንፈስ እንጂ ቆም ብሎ የሚያስብ የሚያመዛዝን የጠፋበት ዘመን ነው፤ ብዙዎቹ ገና ሙቀት ላይ ናቸው የተለየ የሚንፈላሰስበት መኪና አለው፣ መንግሥት የሚሰጠው የመኖሪያ ቤት አለው፣ ወጪውንም በሙሰኝነት የለመደው ስለሆነ ኑሮውም አይሰማውም፣ ምቾት ላይ ነው ብዙው በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉት ሰዎች ከሆኑ ሰዎች እንበላቸው እና፤ ሰዎች ከሆኑ ማለት ነው፤ ብዙዎች እየሆነ ያለውን አያስተውሉም፤ "እኔ ከሞላልኝ፤ . . ." በሚል ብሂል ይመስላል ብዙም አይመለከታቸውም፤ እንደ ኢትዮጵያ የሰው ልጅ በየቀኑ እንደ በግ የሚታረድበት ሃገር ያለ እስከማይመስል ድረስ ዛሬ ዛሬ እማ አምስት አሥር ሰው ሲታረድ ወይም ሲገደል ብዙም ቦታ ሰጥቶ የሚያይ ሰው የለም፤ መንግሥትም የመንግሥትም ሰዎች ብዙም አይመለከታቸውም እስከ መቼ ይሆን?

Wednesday, November 19, 2025

" ሦስት ዓመት ተከራክረን በፍርድ ቤት ያስወሰንነውን ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ወረዳው ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆነም " - ጤና ባለሙያዎች

ውዝፉን በአንዴ ለመክፈል በጀት የለውም ወረዳው " - የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ 
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ኪንዶ ዲዳዬ ወረዳ ሃላሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያሉ 128 ጤና ባለሙያዎች በፍርድ ቤት የወሰነላቸው #ከ3_ሚሊዮን ብር በላይ የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንዳልተፈጸመላቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

ጤና ባለሙያዎቹ ምን አሉ ?

" ወላይታ ዞን ሃላሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለሶስት ዓመት ሙሉ ተከራክረን በፍርድ ቤት ያስወሰንነውን 17 ወራት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ወረዳው ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆነም።

Tuesday, November 18, 2025

ቅዱስነታቸውን በተመለከተ የሚሰማው ምንድነው?

"…ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በቅዱስነታቸው ጤንነት ዙሪያ እንዲህና እንዲያ ሆነ እያተባሉ የሚወሩ ወሬዎችን በሰማሁ ጊዜ በቀጥታ ወደ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ

ወፎቼ ነው የደወልኩት። ወፎቼም እዚያና እዚህ ገብተው አገኘነው ያሉትን መረጃ እነሆ ጀባ ብያችኋለሁ። 

• የሆነው እንዲህ ነው ይላሉ ወፎቼ… 

"…የጥንታዊቷ፣ የቀኖናዊት፣ ሐዋርያዊቷና ብሔራዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ የሆኑት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በገጠማቸው ድንገተኛ አደጋ ምክንያት በሕክምና ላይ እንደሚገኙ ታማኝ የመረጃ ምንጮቼ የሆኑት ወፎቼ ከአዲስ አበባ መረጃውን አድርሰውኛል። 

"…ቅዱስነታቸውን ለሕክምና ያበቃቸውም ጉዳይ የመረጃ ምንጮቼ እንደነገሩኝ ከሆነ "በማረፊያ ክፍላቸው ዎክ ሲያደርጉ የታጠፈ የመሬት ምንጣፍ ጠልፎ ስለጣላቸው በድንገት ወድቀው" እንደሆነ እና በዚህም ምክንያት ድንጋጤ ተጨምሮበት በአደጋው በአንደኛው እግራቸው ዳሌ ላይ ስብራት እንደረሰባቸውና በዚህም ምክንያት በሀኪሞች በተደረገላቸው ከፍተኛ ርብርብ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸው ሕክምና እየተከታተሉ መሆናቸውን ነው የመረጃ ምንጮቼ የሚገልፁት። በአደጋው ወቅት በተጨማሪ የአልጋ ጠርዝም ሆነ ሌላ አደጋውን ከፍ የሚያደርግ ተጨማሪ ምት ስላልገጠማቸውና ሙሉ ለሙሉ ከመሬቱ ላይ ብቻ በመውደቃቸው የደረሰባቸው አደጋ ቀላል ባይባልም ነገር ግን ለክፉ የማይሰጥ በመሆኑ በዚህ ሁለትና ሦስት ቀናት ውስጥ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ማረፊያ ቤታቸው እንደሚመለሱም ነው የወፎቼ መረጃ የሚያመለክተው። 

በምስራቅ አርሲ አዋሳኙ በምዕራብ ሐረርጌ የሰባት ልጆች እናት መገደላቸውን ስምዓ ተዋሕዶ ዘገበ፡፡

የኦርቶዶክሳውያኑ ደም መፍሰስ በአስቸኳይ ይቁም!!
ምዕራብ ሐረርጌ ዶባ ወረዳ ኢፋ ጀነቴ ቀበሌ ላይ ታግተው ከአንድ ቤተሰብ 4 ሰው አባት አቶ ደበበ እና እናት ወ/ሮ ገነት (የሰባት ልጆች እናት)፣ ወንድ ልጃቻው እና የልጃቸው ባል አግተው ከወሰደዋቸው በኃላ ብዙ ድብደባና እንግልት ደርሶባቸዋል::  ከእነዚህ ኦርቶዶክሳውያን ውስጥም በድብደባው ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈው የሰባት ልጆች እናት የሆኑት ወ/ሮ ገነት  ስርዓተ ቀብራቸውም  በዶባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል። 

ኦርቶዶክሳውያኑን ሲያሰቃዩ የነበሩ አጋቾች በድካም እንቅልፍ ላይ መሆናቸውን እንደአጋጣሚ  በመጠቀም ከታጋቾች መካከል የነበሩት አቶ አበበ አምልጠው በመውጣትና ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠታቸው  በአካባቢው የሚገኙ ፖሊሶች ባደረጉት ጥረት አስከሬን ለማንሳትና  እና የቀሩ ታጋቾችን ለማዳን መቻሉን ከአካባቢው የደረሰን ጥቆማ ያመለክታል፡፡  ይሁንና አሁንም በእገታ ውስጥ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን የ3.5 ሚሊዮን ብር ካሳ ተጠይቆባቸዋል ።

የኦርቶዶክሳውያን ሞት ይቁም!!!

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

Sunday, November 16, 2025

የምዕራብ ሐረርጌ ኦርቶዶክሳዊየ ሥጋት ላይ ናቸው።

ምዕራብ ሐረርጌ አደጋ ላይ ናቸው!

 የአርሲው ኦርቶዶክሳዊ ግድያ ወደ ሐረርጌ የተሻገረ ይመስላል ።
 ለማንኛውም ሁላችንም ኦርቶዶክሳዊያን ባለቹበት መሰባሰብ መደራጀትይጠበቅብና ! 
በምዕራብ ሐረርጌ ዶባ ወረዳ አንድ (1 )ኦርቶዶክስ ሲገደል  አራቱ (4)ደግሞ ታፍነው ተወስደዋል ። በዳሮለቡ ወረዳ  የተገደሉት ተገድለው ከቀያቸው ተፈናቅለው የቀሩት በሰቀቀን  ነው ያሉተ። ሰዎች እንዳያስጠጋቸው በፖሊስ ለሁሉም ታዝዘዋል። ስጋት ውስጥ ያሉት ወረዳዎች ዳሮለቡ ፣ አንጫር ጭሮ ወረዳ ለሞት የታጩ ናቸው።

በአሰቦት ገዳም አካባቢ እንደሚታወቀው በአክራሪ ዋሃቢያውያን የተከበበ እንደሆነ ይታወቃል፤ በተለያየ ጊዜ ተደጋጋሚ ጥቃት ግድያ ማዋከብ እያደረሱ እንደሆነ ይታወቃል፤ በተደጋጋሚ ለአካባቢው የመንግሥት ተቋማት ጥቆማው ተሰጥቶ ነበር፤ ከመከላከል ይልቅ ሁኔታዎችን አቅልሎ የመመልከት እና ጉዳቱ እንዲባባስ እና እንዲከፋ የሚያደርጉት ብዙ ነገሮች እንዳለ አብዛኛው ኦርቶዶክሳዊ የሚረዳው ነገር ነው፤ ላለፉት በርካታ ዓመታት የእርሻ ቦታቸው ላይ መነኮሳት ተገልዋል፣ የአብነት ተማሪዎች በጥይት ተደብድበዋል፣ ሌሎችም ብዙ በርከት ያሉ ጥቃቶችን በገዳሙ ላይ ሲያደርሱ ቆይተዋል፤ እንደተባለው በአርሲ፣ በወለጋ፣ በምዕራብ ሐረርጌ፣ በአሰቦት፣ በምዕራብ አርሲ በሁሉም አካባቢዎች ብቸኛው አማራጭ መደራጀት እና እራስን መከላከል ብቸኛው እና አይነተኛ አማራጭ መሆኑን ልብ ይሏል፤ "የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም" እንደሚባለው የሄ መንግሥት በምንም መልኩ መፍትሄ ያመጣል ብሎ መጠበቅ "ከዝንብ ማር " እንደመጠበቅ ነው



የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም