·
አባ ጳውሎስ በጉባኤው ላይ እንዲቀርቡ ለተጠሩት አዘጋጆች በተፈለጉበት ጉዳይ ዙሪያ ሲመክሩና
ነገር ሲያስጠኑ አምሽተዋል፤ አዘጋጆቹን አቅርቦ ለመጠየቅ የነበረው ዕቅድ ተሰርዞ እንዳይገቡ ተደርገዋል::
·
“እኔ የግል ቤት የለኝም፤ መኪና የለኝም፤ ሲኖዶሱ መወሰንና ርምጃ መውሰድ አለበት” (ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)
·
“ለቤተ ክርስቲያን አደጋ ነው፤ መወሰን አለብን” (ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ)
(ደጀ ሰላም፤
ግንቦት 7/2004 ዓ.ም፤ May 15/ 2012/ READ THIS IN PDF)፦ ዛሬም ለተከታታይ ሁለተኛና ሙሉ ቀን በዜና ቤተ ክርስቲያን
ጽሑፎች ላይ ሲወያይ የዋለው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ
የጽሑፎቹን ይዘት ከሕግ እና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር
መርምሮ ውሳኔ የሚያቀርብ ሰባት አባላት ያሉት የምሁራን፣ ባለሙያዎችና የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ኮሚቴ አቋቋሟል፡፡ የኮሚቴው አባላት ኾነው የተመረጡት ሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፡- ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ እና ብፁዕ
አቡነ ያሬድ ናቸው፡፡ የሕግ ባለሙያዎቹና ምሁራኑ
ደግሞ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ፣ ዶ/ር ተክለ ሃይማኖት አንተነህ፣ አቶ ፊልጶስ ዓይናለም እና አቶ በፍርዱ መሠረት ናቸው፡፡ተጨማሪ ዜናዎችን ከቆይታ በኋላ እናቀርባለን፡፡
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
No comments:
Post a Comment