Tuesday, May 8, 2012

የሊቀ ስዩማን ኀ/ጊዮርጊስና አቡነ ፋኑኤል ሴራ ሪፖርታዥ(ክፍል አንድ)

-(የጆቢራዎቹ ደብዳቤ) መስከረም 12/2004 . ተወሰኑ የሚላቸውን ጉዳዮችን ጠቅሶ ማኅበረ 
  ቅዱሳን 10 ቀን ውስጥ ተግባራዊ እንዲያደርግ የሚያሳስብ ሲሆን ይህንን ተግባራዊ የማያደርግ 
   ከሆነ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ያስጠነቅቃል፡፡
- (ሰበር ዜና) የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ ከሓላፊነታቸው ተነስተዋል
- የማኅበረ ቅዱሳንን ህልውና ሊቋረጥበት ስለሚችልበት መንገድ ረዘም ያለ ሰዓት ወስደው መክረዋል
- (ኃ/ጊዮርጊስ) ቅዱሰ ሲኖዶስ በደራሽ ችግሮች አንዲጠመድና ጊዜ እንደይኖው በማድረግ ለቀጣይ 
 የጥቅምቱ ስብሰባ አጀንዳዎቹን እንዲያሳድራቸው ለማድረግ በመጣር ላይ ይገኛል ፤ ለዚህም የተመረጠው
 ስስ ርእሰ ጉዳይ” (sensitive issue) የማኅበረ ቅዱሳንን ህልውና ላይ አደጋ መጋረጥ የሚል ይገኝበታል ፤

ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን
(አንድ አድርገን ሚያዚያ 30 ፤ 2004ዓ.ም)፡- ይህን ወሬ ማህበረ ቅዱሳን ድረ-ገጽ ላይ ላይ ላዩን አንበውት ሊሆን ይችላል ፤ እኛ ግን በጆቢራዎቹ እየተደረገ ያለውን ነገር ያሰቡትንና ያለሙትን ነገር ልንነግርዎ ወደድን ፤ አጣብቂን ውስጥ የገቡት አቡነ ፋኑኤል ከ“አማካሪያቸው” ኃ/ጊዮርጊስ ጋር በመሆን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የግንቦት የርክበ ካህናት ስብሰባ ከመድረሱ በፊት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተጽእኖ ለማሳደር እየጣሩ ነው፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ ተጽህኖ ለመፍጠርና ዓላማቸውን ለማሳካት ሲወጡ ሲወርዱ በቤተክህነቱ ውስጥ ተስተውለዋል ፤ ህጋዊ መሳይ ህገወጥ ደብዳቤ አርቅቀው ዓላማቸውን ለማሳካት መንኳኳት ያለበትን ቢሮ ሲያንኳኩ ሰንብተዋል ፤ የተጻፈው ደብዳቤው ዋነኛ ዓላማ ቅዱስ ሲኖዶስ የማኅበረ ቅዱሳን ህልውና ዋንኛ አጀንዳ አድርጎ እንዲነጋገር በማድረግ ሌሎች ከቤተክርስቲያኗ አንድነትና ህልውና ጋር የሚገናኙትን የተሃድሶ መናፍቃንና አሜሪካ ያለውን የአቡነ ፋኑኤል አፍራሽ አካሄድ ጋር የተገናኙ ጉዳዮች እንዳይታዩ ለማድረግ የትኩረት አቅጣጫ ማስቀየር ነው፡፡
ዝርዝሩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል
 


ዲያቆን /ጊዮርጊስ በኑፋቄው ለመግፋት ቢሞክርም በወቅቱ የሀገረስብከቱ ሊቀጳጳስ በነበሩት በብጹእ  
አቡነ አብርሃም፣ በቀናዒ ኦርቶዶክሳዊ መምህራንና ምእመናን ብርታት ሳይሳከለት በመቅረቱ ሌላ  
ቤተክርሰቲያኒቱን ሊጎዳበት የሚችልበት ዘዴ ይዞ አዲስ አበባ ተመለሰ፡፡ ቅዱስነታቸውን የሲአኤ 
agent መሆኑን፤ የኢህአዴግ አባልም እንደሆነ  በመንግስት ዘንድ ይሁን በዲፕሎማቶች ዘንድ  
ተቀባይነት እንዳለውና ሁሉንም ማድረግ እንደሚችል ያሳምናቸዋል፤ በዚህም ለቅዱስነታቸው 
 ቤተኛ መሆን ችሏል፡፡

ዲያቆን /ጊዮርጊስ መንበረ ፓትሪያሪክ ቤተኛ ከሆነ በኋላ ኑፋቄው የተቃወሙትን፣ እንዳያስተምር  
የከለከሉትን ብጹአን አባቶችን፣ሊቃውንተ ቤተክሰቲያንን፤ መምህራንና ማኅበራትን ጥሩ መካሪ  
በመምሰል  ፓትሪያሪኩ በበቀል ዱላ እንዲደበድቧቸው ማድረጉን ተያያዘው፡፡ ለዚህም  
በቃለዋዲው  የሌለ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ያልመከረበት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን  
የአሜሪካ ልዩ /ቤት እንዲቋቋም በማድረግ የካሊፎርኒያ አገረስብከትና የዋሽንግተን ዲሲ  
ሀገረስብከት ለመቆጣጠር የጽፈት ቤቱ ሓላፊ ሆኖ ቅዱስነታቸው የሊቀ ስዩማን ማዕረግ  
ሰጥተውት ወደ አሜሪካ አቅንቷል፡፡

የጥምቅቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ልዩ /ቤቱን በመኖርና ባለመኖር መካከል እንዲሆን(በሁለቱ አሕጉረ 
ስብከቶች ሊቃነጳጳሳት ስር እንዲሆንበመወሰኑ ምክንያት ሊቀስዩማን /ጊዮርጊስ የቆመጠለት ሁለቱን 
አገረ ስብከት የተሀድሶ መናፍቃን ዋሻ ለማድረግ የነበረው ህልም ቅዠት ሆኖ ቢቀርም ቅዱስ ሲኖዶስ 
 የአሕጉረ ስብከቶች ሊቃነጳጳሳት ምደባና ዝውውር የካሊፎርኒያ አገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብጹእ  
አቡነ  ኤውሰጣጥዮስ እና የዋሽንግተን ዲሲ አገረስብከት ሊቀጳጳስ ብጹእ አቡነ አብርሐምን   
በማዛወር  ሁለቱን አሕጉረስብከቶች ደርበው እንዲያስተዳድሩ በፈጸሙት አስተዳደራዊ  በደል  
ምክንያት ከሐዋሳ በምእመናን ብርቱ ተቃውሞ ቅዱስ ሲኖዶስ ያነሳቸው አቡነ ፋኑኤል መመደቡ  
ይታወሳል፡፡
ብጹነታቸው “የሐዋሳን ህዝብ ያሳመጸብኝ ማኅበረ ቅዱሳን ነው፤ ማኅበረ ቅዱሳን የሌለበት ቦታ  
መድቡኝ፡፡” በማለት አደረሱት የተባለው በደል ለማረም ቀኖና ቤተክርስቲያን ይከበር ብሎ  
ጥያቄ የሚያነሳውን ሁሉ “ማኅበረ ቅዱሳን” ነው ብሎ ለማሸማቀቅ ከጉዳዩ ይልቅ የባለጉዳዩ  
ማንነት ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግ ያደረጉት ጥረትብዙ ምእመናን አሳዝኖ ነበር፡፡ ባገኙት አጋጣሚ 
አገልግሎት ከሚነቅፉ ከአጉራ ዘለል ህገወጥ ሰባኪያንና ዘማሪያን እንዲሁም ለተሃድሶ መናፍቃን  
ሽፋን በመስጠት ይነሳባቸው የነበረውን ተቃውሞ እንዲባባሰ አደረጉት፡፡
 

2004 . የጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ብጹነታቸው ከሐዋሳ ወደ ሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ 
መንፈሳዊ ከሌጅ ሊቀጳጳስነት ተዛወሩ፡፡ በግንቦቱ ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ደግሞ ወደ የኪራይ ቤቶች
አሰተዳደር መምሪያ ሊቀጳጳስነት ተዛወሩ፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ብጹነታቸው ሀገረስብከት ባይሰጣቸውም 
በአወዛግቢነታቸው ገፍተውበት ነበር፡፡ ያደረሱትን አሰተዳደራዊ በደል የተቃወሙትን ምእመናንን በሙሉ 
ከማኀበረቅዱሳን ጋር ለማገናኘት በመሞከር ቤተክርስቲያኒቱ ለማፍረስ ከሚጥሩት አጉራ ዘለል ሰባክያንንና 
የተሃድሶ ኑፋቄ አራማጆች ምክርና ውትወታ በመስማት ማኅበረቅዱሳንን ላይ አቄሙ፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የአዋሳ 
ምእመናን ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ያስከተለባቸውን አስተዳደራዊ በደልን ወደ አሜሪካ በተደጋጋሚ 


በማቅናት ያለ አህጉረስብት ሊቃነጳጳሳት ፈቃድ ክህነት በመሾም፣ ማዕረገ-ሥም በመስጠትና 
 ቅዳሴ ቤት በማክበር ገለልተኛ አብያተክርስቲያናት ዘንድ ድጋፍ ለማግኘት በሚል ያደረጉት  
በዚህ መልኩ ያሳዘኑትን ምእመን “ለማገልገል” 
በዚህ ሳይወሰኑ አዲስ አገረ ስብከት ከቃላዋዲው ትእዛዝ ውጭ ማቋቋማቸውን ገለጹ፡፡ ይህ ተግባራቸው 
በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መዋቅር ስር ያሉትን አብያተክርስቲያናት በይፋ ተቃወሙት፡፡ ይህንን አጋጣሚ 
ተጠቅሞ ሊቀስዩማን /ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያኗን ለመከፋፈል የነበረውን ህልም እውን ያደርግልኛል ብሎ 
የሚያስበውን ሴራ ብጹእነታቸውን በመጠቀም ይፈጽም ገባ፡፡
ብጹእነታቸው በሊቀስዩማን /ጊዮርጊስ አቀነባባሪነትና ደብዳቤ አርቃቂነት ቀኖና ቤተክርስቲያን እንዲከበር 
ሲጠይቁ የነበሩትን የአገረስብከቱ ዋና ጸሐፊ የቀሲስ ዶክተር መስፍን ተገኝ ሥልጣነ ክህነት መያዛቸውን አሳወቁ፡፡ደብዳቤው የተሓድሶ መናፍቃን ልሳን በሆነ ድረ-ገጽ(አባ ሰላማ) በኃ/ጊዮርጊስ አማካኝነት እንዲወጣ ተደረገ፡፡ይህን ተከተሎ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መዋቅር ስር ያሉትን አብያተክርስቲያናት ቁጣ ቀሰቀሰ፡፡ ቅዳሜ መጋቢት
 22/2004 .ም፤ ማርች 31/2012 የተሰበሰቡት በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ 
አብያተ ክርስቲያናት፤ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት  የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፤ ምክትል ሰበካ 
ጉባኤ ሊቃነ መናብርት፤ የሰንበት /ቤት፤ የካህናትና የምእመናን ተወካዮች የተገኙበት ባወጡት የአቋም መግለጫ
‹‹አብያተ ክርስቲያናቱ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር ይጠበቅ›› በማለታችን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ነኝ የሚል አባት 
ሊደሰት ሲገባው፤ ይህንን አቋም በመጥላት፤ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ለማዳከም መነሳሳት ከብፁዕ አቡነ ፋኑኤል
በተግባር እያገኘነው ያለ ምላሽ ነው። ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በተደጋጋሚ ከሀገረ ስብከቱ ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤና 
አብያተ ክርስቲያናት የቀረበላቸውን "ወደ መንበርዎ ይመለሱየሚል ጥያቄ አልቀበልም በማለት፤ በተቃራኒ መልኩ
 የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ጠብቀው የሚያገለግሉ ካህናትን በመደወልና በስሜታዊ ንግግር በመናገር የቤተ 
ክርስቲያንን አገልግሎት እንዲያከናውኑ የተሰጣቸውን ክህነት የፈለጉትን መፈጸም የሚችሉበት የግል ሥልጣን 
አድርገው በመውሰድ የቤተ ክርስቲያን መመሪያ ከሚፈቅደው ውጭ "እውነትን ይዘው የተከራከሩ ካህናትን 
ሥልጣነ ክህነት እይዛለሁበሚል መስመር በመጓዝ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

በተለይም ብፁዕነታቸው "ሥልጣነ ክህነታቸውን ይዣለሁያሏቸውን ቀሲስ / መስፍን ተገኝን በተመለከተ 
የአብያተ ክርስቲያናቱ ተወካዮች ባሰሙት ሐሳብ በአንድ ድምጽ ከቀሲሱ አገልግሎት ጋር መሆናቸውን አበክረው
 የገለፁ ሲሆን ስብሰባ በተደረገ ማግስት ሊቀ ጳጳሱ በቃል ያሰሙት የነበረውን ማስፈራሪያ ወደ ጽሑፍ በመቀየር 
የውግዘት ደብዳቤያቸውን ሥልጣነ ክህነትን በማይቀበሉ ተሐድሶያውያን ድረ-ገጽ ላይ አውጥተዋል። ሥልጣነ ክህነቱ መሻር ከነበረበት ነገሩ መዞር የነበረበት ወደ ራሳቸው ወደ ሊቀ ጳጳሱ መሆኑን ያወሳው ጉባኤው "ሰዎችን ሊያሳዝናቸውና ፈርተው እንዲገዙለት ፈልጎ በማይገባ ቢያስር ቢያወግዘውም እርሱ (ጳጳሱ) ከእግዚአብሔር ዘንድ የታሰረ ይሁን። ካህናትም በእውነት ይቋቋሙት" አንቀጽ ፻፹፬ ረስጠብ ፳፬) የሚለውን ሕገ ቤተክርስቲያን የመግለጫው መሪ ቃል በማድረግ” አስታወቁ፡፡(ከደጀ ሰላም የተዋሰደ)

በዚህም የተነሳባቸውን ‹‹ቀኖና ቤተክስቲያን ይከበር›› የሚለውን ጥያቄ ለማዳፈን እንደ ማስፈራሪያ ያሰቡት የአገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ የቀሲስ ዶክተር መስፍን ተገኝ ሥልጣነ ክህነት መያዝ ፤ የርሳቸው ስልጣነ ክህነት 
በእግዚአብሔር ዘንድ የታሰረ እንዲሆን በሚል ተቀየረ ፤ ጉዳዩ ከቀናት በኋላ የሚጀመረው  የቅዱስ ሲኖዶስ
 ስብሰባ ላይ እልባት ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡አጣብቂን ውስጥ የገቡት አቡነ ፋኑኤል መጀመሪያወኑም ወደ /ጊዮርጊስ 
/ጊዮርጊስ የሠንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ጸሀፊ ከሆነው መኮነን ጋር ቅዱስነታቸውን የማኅበረ ቅዱሳንን ህልውና ሊቋረጥበት ስለሚችልበት መንገድ ያለ ሰዓት ወስደው ማማከራቸውን  ለማወቅ ችለናል ፡፡ዋንኛው ማጠንጠኛቸው ‹‹የመስከረም 12/2004 ውሳኔ ይከበር›› የሚል ነው፡፡ምንም እንኳን ይህ የምክክር 
ጉባኤ የማኅበሩን ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው ደንብ መመራትን፤ የማኅበሩ ከሳሽ የነበሩት አባ ሠረቀብርሀን፣ ንቡረእድ
ኤሊያስ፣ መጋቤ ካህናት /ሥላሴ (በአሁኑ ሰዓት ከማኅበሩ ጋር ተግባብተው በመስራት ላይ የሚገኙሀሳዊነት 
እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱን የውስጥ ጉዳይ ራሷ ልትፈታው የሚገባውን ጉዳይ ለሦስተኛ ወገን (ለመንግስት
ማስተላለፍ ጥፋት መሆኑን ስብሰባው ላይ የተገኙት 17ቱም ሊቃነ ጳጳሳት በሙሉ ድምጽ የተስማሙበት ጉዳይ 
ቢሆንም ዛሬም ጆቢራዎች ከሁለት አመት በኋላ እንደ አዝማች ያነሱታል፡፡ ቅዱስነታቸው በሃሳቡ የተስማሙበት 
ቢመስሉም እጃቸው ማስገባት ስላልፈለጉ ‹‹ይሄንን ጉዳይ ከአቡነ ገሪማ ጋር ተነጋገሩ›› ብለው ሊሸኟቸው ችለዋል፡፡ lአቡነ ጳውሎስ ከተማሪ ቤት ጀምረው ጓደኛ እንደሆኑ የሚነገረላቸው አቡነ ገሪማ ጆቢራዎቹ 
‹‹ቅዱስነታቸው ከእርስዎ ጋር ጨሩስ ብለውን›› ነው በማለት ያዘጋጁትን ደብዳቤ ይሰጧቸዋል፡፡ ደብዳቤው 
መስከረም 12/2004 . ተወሰኑ የሚላቸውን ጉዳዮችን ጠቅሶ ማኅበሩ 10 ቀን ውስጥ ተግባራዊ 
እንዲያደርግ የሚያሳስብ ሲሆን ይህንን ተግባራዊ የማያደርግ ከሆነ ግን አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድ 
ያስጠነቅቃል፡፡

በደብዳቤው ላይ የተጠቀሱት ስድሰቱ ጉዳዮች መስከረም 12/2004 . ሊቃነጳጳሳት፣ ከፍተኛ የመንግስት 
ባለሥልጣናትና የማኅበሩ አመራሮች ባሉበት በተደረገው የምክክር ጉባኤ በሦስቱ ከሳሾች ቀርበው በማኅበሩ በቂና 
አሳማኝ መረጃ አቅርቦ መሰረተ ቢስ ክስ እንደሆኑ በተሳታፊዎች ዘንድ የታመነባቸው ነበሩ፡፡ታዲያ አሁን ላይ ለም ማንሳት ፈለጉ ? የደብዳቤው ዋነኛ ዓላማ ‹‹በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማኅበሩ 
የታዘዘውን ብጹእ አቡነ ገሪማ ደብዳቤው አይተው ይኸ ደብዳቤ ወውጣት የሚችለው በሠንበት 
ሊያቀርብ ባለመቻሉ፤ ማህበሩ ታግዷል›› በማለት ቅዱስ ሲኖዶስ የማኅበሩ ህውልና ዋነኛ አጀንዳ አድርጎ 
እንዲነጋገር በማድረግ ሌሎች ከቤተክርስቲያኗ አንድነትና ህልውና ጋር የሚገናኙትን የተሃድሶና መናፍቃንን ጉዳይ ወደ ኋላ ማስባል ፤ አሜሪካን ያለውን የአቡነ ፋኑኤል አፍራሽ አካሄድ ጋር የተገናኙ ጉዳዮች እንዳይታዩ 
ለማድረግ የቅዱስ ሲኖዶስንና የማኅበረ ቅዱሳን ትኩረት አቅጣጫ ማስቀየሪያነት ታስቦ የተደረገ መሆኑኑን 
መረዳት አይከብድም፡፡ ለዚህም በደብዳቤው ላይ የተቀመጠው ቀነ ገደብ (አስር ቀንየሚጠናቀቀው የቅዱስ ሲኖድስ ስብሰባ የሚጀርበት ዋዜማ ላይ መሆኑ ድግሞ ጉዳዩ የበለጠ ትኩረት እንዲያገኝ ያስችላል ብለው 
አምነውበት ነበር፡፡
/ቤቶች ማደራጃ መምረያ ሃላፊ ስለሆነ እርሳቸውን ቢሯቸው ድረስ አስጠርተው ያዘጋጁት ደብዳቤ እንዲፈርሙ 
ሲጠይቋቸው ኃላፊው ደብዳቤውን ተመልክተው ካበቁ በኋላ በደብዳቤው ሃሳብ እንደማይስማሙ ፤ መፈረምም እንደማይፈልጉ ፤ ችግር እንኳን ቢኖር በውይይት ሊፈታ እንደሚችል ይነግሯቸዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ‹‹ይህንን 
ደብዳቤ ቅዱስነታቸው ናቸው ፈርሙ ያሉዎት ፤ እንዴት የቅዱስነታቸውን ትእዛዝ አልፈጽምም ይላሉ?›› 
በማለት አጣብቂኝ ውስጥ ያስገቧቸዋል::‹‹ፊርማውን ብፈርም እንኳ በሚዲያ ሳላምንበት ነው የፈረምኩበት 
ብዬ እገልጻለሁ›› ቢሉም ጆቢራዎቹ አሁንም የቅዱስነታቸው መመሪያ እንደሆነ በተለያየ መንገድ ያሳስቧቸዋል፡፡ 
እያመነቱ መፈረም ከጀመሩ በኋላ ቢሮዬ ብቻዬን አስቤበት ነው የምፈርመው ብለዋቸው ደብዳቤዎቹን ይዘው 
ወደ ቢሯቸው አመሩ፡፡  በዚህ መሃል የማኅበሩ አመራሮች አካባቢው ደርሰው ብጹእ አቡነ ገሪማ ሲያናግሯቸው 
ጉዳዩን እንደማያውቁት ጆቢራዎቹ እንዳሳሳቷቸው ይናጋራሉ፡፡ ቅዱስነታቸውም እንደዚህ እንዲደረግ እንዳላዘዟቸው
በመግለጽ እንደተለመደውን ስልታዊ ማፈግፈግ ካደረጉ በኋላ ደብዳቤዎቹ እንዲመጡላቸው በማዘዝ ከሠንበት 
/ቤቶች መመሪያ ኃላፊው በመልክተኞች ያስወስዱታል፡፡ በዚህ ሁኔታ ደብዳቤው ጆቢራዎቹ እጅ ከገባ ወጭ 
እንዳያደርጉት የሚያዝ ደብዳቤ ለመምሪያው መዝገብ ቤት ሹም ለወ/ሪት አለምፀሀይ በጻፉት 
ደብዳቤ በመጻፍ አስበው ሀገር አቋርጠው የመጡበትን  ሴራ ሊያከሽቡባቸው ችለዋል፡፡

በቁጥር 168/127/2004 በቀን 24/8/2004 . የተጻፋ ደብዳቤ ይዘቱ ስካን አድርገን ማቅረብ ባንችልም ወረቀቱ ላይ የሰፈረው ነገር እንደሚከተለው  እንደሚከተለው ይነበባል፡፡


 /ሪት ዓለምፀሃይ ጌታቸው


 
18/8/2004 . ማታ ከምሽቱ 100 ተኩል ሲሆን ማሕበረ ቅዱሳንን በተመለከተ በብጹዕ አቡነ ገሪማ ቢሮ በአስቸኳይ ከጠሩኝ በኋላ እኔ ያላረቀቁትና በቢሮ ያልተጻፈ 
ደብዳቤ አስቸኳይ መፈረም አለብህ ፤ ቅዱስ አባታችን አዘዋል በማለት ስላሳሰቡኝ እንድፈርም ተደርጓል፡፡
ስለዚህ፣
1. የስንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያውን ወረቀት ከጸሃፊዋ አጅ በግድ በቅዱስ አባታችን አማህኝተው የተወሰደ
 በመሆኑ፣
2. ከሕጉ ውጭ ሌላ ቢሮ የተረቀቀ በመሆኑ፣
3. ቅዱስ አባታችን ጻፉ ሳይሉ በስማቸው የተነገደ በመሆኑ፣
4. የፈረምኩት በጨለማ ተጠርቼ በመሆኑ ደብዳቤ ወጭ አድርጉልኝ ብሎ የሚመጣ ቢኖር ደብዳቤውን ወጭ 
እንዳታደርጊ አሳስባለሁ፡፡ በተጨማሪም በደብዳቤው ግልባጭ ለተደረገለት መሥሪያ ቤት ሁሉ በግልባጭ አሳውቃለሁ፡፡

ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር
   
በማለት የጆቢራዎቹ ህገወጥ እንቅስቃሴ ያከሸፉት ቢሆንም ቆሞስ መላእከ ጽዮን አባ ሕሩይ ወንድይፍራው ላይ 
ተጽእኖ ለማሳደር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ሲሆን ባለፈው አርብ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ ለመፈፀም ታስቦ 
የነበረና ይህ ዘገባ እሰከተጠናቀረበት ድረስ ሴራውን ለመቀልበስ በብጹዓን ሊቃነ በማኅበሩ አመራሮች ጥረት 
እያደረጉት ያለበትን ጉዳይ ተከታትለን በክፍል ሁለት ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን
ከዚህ በታች ያለው ‹‹ደጀ ሰላም›› የዘገበችው ነው

(ሰበር ዜና) የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ ከሓላፊነታቸው ተነሡ
  • የዋና ሓላፊው መነሣት በቤተ ክህነቱ የጨለማ ቡድን የተቀነባበረ ነው፤ የአቡነ ጳውሎስ ስውር ትእዛዝና የአቡነ ገሪማ የተለመደ አድርባይነት እንዳለበትም ተረጋግጧል
  • የመምሪያው ሊቀ ጳጳስእኔ በማላውቅበት ኹኔታ የመምሪያው ሓላፊ ሊቀየሩ አይችሉምበማለት ርምጃውን ተቃውመዋል
  • ተግባሩ በቤተ ክህነታችን እየኾነ ያለው አሳሳቢ ኹኔታ መገለጫ ነው” /ማኅበረ ቅዱሳን/

(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 29/2004 .ም፤ May 7/2012) ከአሿሿማቸው እና ከተሾሙበት ጥቅምት ወር 2003 . አንሥቶ መነጋገርያ የኾኑት በመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት /ቤት የሰንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንድይፍራው ከሓላፊነታቸው መነሣታቸው ተሰማ፤ የመምሪያው ምክትል ሓላፊ የኾኑት / ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ በቦታቸው የተተኩ ሲኾን የመምሪያው ጸሐፊ የኾኑት / መኰንን ወልደ ትንሣኤ ደግሞ የመምሪያ ምክትል ሓላፊ ኾነዋል፡፡ ከዋና ሓላፊነት የተነሡት መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሠራተኞችና በፓትርያሪኩ ሳይቀርመጋዘንእየተባለ ወደሚጠራው መንፈሳዊ ፍርድ ቤት አባል ኾነው እንዲሠሩ ተዘዋውረዋል፡፡
መልአከ ጽዮን አባ ኅሩይ ከሓላፊነታቸው ለመነሣት ያበቃቸው በቀድሞው ዋና ሓላፊ አባ ሰረቀ አማካይነት ሲገፋ ለቆየው÷ ማኅበረ ቅዱሳንንና ሰንበት /ቤቶችን አሽመድምዶ በማዳከምና በመቆጣጠር የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶን ፕሮጀክት ለማሳከት፣ የግልንና የቡድን ጥቅምን ለማስፈን ምቹ ኹኔታ ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ለሚገኘው የቤተ ክህነቱ የጨለማ ቡድን ሤራ አልመች፣ አልታዘዝ በማለታቸው እንደ ኾነ ተዘግቧል፡፡
የጨለማ ቡድኑ ዋነኛ መሪዎች ለረጅም ጊዜ የመምሪያው /ሓላፊ ኾኖ ሲሠራ የነበረውና የግል ጥቅሙን በማሳደድ የሚታወቀው ዕንቍ ባሕርይ ተከሥተ፣ ከቀድሞው ዋና ሓላፊ በሚሰጠው ጥቅምና ተስፋ ሥጋዊ ኑሮውን ሲያደላድል የቆየው የመምሪያው ጸሐፊ መኰንን ወልደ ትንሣኤ እና አንዴኢሕአዴግ ነኝ፤ ተሰሚነት አለኝሌላ ጊዜየሲ.አይ. አባል ነኝ፤ ከዲፕሎማቶች ጋራ እገናኛለሁእያለ የሚያጭበርበረው የአቡነ ፋኑኤል ተስፈኛ ኃይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ናቸው፡፡
ካለፈው ሳምንት ዐርብ ምሽት ጀምሮ የጨለማ ቡድኑ ሲያካሂድ የቆየውንና ዛሬ ጠዋት ገሃድ የኾነውን አስከፊ ማፊያዊ ተግባር የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል፡፡ ሊቀ ጳጳሱ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስእኔ በማላውቅበት ኹኔታ የመምሪያው ዋና ሓላፊ ሊቀየሩ አይችሉምየሚል ተቃውሞ ማሰማታቸው ተገልጧል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ሚያዝያ 24 ቀን 2004 .ሕገ ወጥ ሕግ አስከባሪዎችበሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ የጨለማ ቡድኑን አባላትጆቢራዎች እና ወሮበሎችበማለት የገለጻቸው ሲኾን ድርጊቱምበቤተ ክህነታችን እየኾነ ያለው አሳሳቢ ኹኔታ መገለጫ ነውሲል ማጋለጡ ይታወሳል፡፡
የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች ለደጀ ሰላም እንደገለጹት በዚህ ሕገ ወጥ ተግባር የፓትርያሪኩ አቡነ ጳውሎስ ቀጥተኛ ይኹንታ እንዳለበት ያመለከቱ ሲኾን ጸሐፊያቸው አቡነ ገሪማ ከጨለማ ቡድኑ አባላት ጋራ ኾነው እንዲያስፈጽሙም ማዘዛቸው ተረጋግጧል፡፡
በአሁኑ ወቅት የጨለማ ቡድኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማኅበረ ቅዱሳንን ከአክራሪዎች ጋራ በመደመር በፓርላማ የተናገሩትን ውንጀላ እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም መስከረም 12 ቀን 2002 . ከቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣንና ከማኅበረ ቅዱሳን መተዳደሪያ ደንብ በሚጋጭ አኳኋን የተላለፉ ውሳኔዎችን ለማስፈጸም እየጣረ መኾኑ ተገልጧል፡፡ በሌላም በኩል ኹኔታውን ፓትርያሪኩ በቅርቡ በሚጀመረው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ከትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያን፣ ከገዳማት ህልውና እና ክብር መጠበቅ ጋራ ተያይዞ ለሚነሡባቸው አጀንዳዎች እንደ ትኩረት ማስቀየሻ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ እየተነገረ ነው፡፡
ከዜናው ጋራ የተያያዙ ዝርዝር መረጃዎችን እንደ ደረሰን እናቀርባለን፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
 

የሰንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ


  ግልባጭ
  • ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
  • ለብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያሪክ ልዩ ጽ/ቤት
  • ለመንበረ ፓትሪያሪክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
  • ለሕግ አገልግሎት መምሪያ
  • ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር
  • ለብሔራዊ ደህንነት አገልግሎት
  • ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
  • ለአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ
  • አዲስ አበባ
ቆሞስ መላአከ ጽዮን አባ ሕሩይ ወንድይፍራው
 
አዲስ አበባ


ጉዳዩ፡ወጭ መሆን ስለማይገባው ደብዳቤ በተመለከተ ይሆናል
የስንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ መዝገብ ቤት




አሜሪካ ሲመደቡ እንደ አዋሳው የህዝብ ተቃውሞ እንደሚገጥማቸው ሥጋት የነበራውቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ 
አባላትን የግንቦት የርክበ ካህናት ስብሰባ ከመድረሱ በፊት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተጽእኖ ለማሳደር ከሁለት
ሳምንት በፊት አዲሰ አበባ ገብተዋል፡፡ “አማካሪያቸው” /ጊዮርጊስ ደግሞ ይሄንን ለማመቻቸት እርሳቸውን 
በአስር ቀን ቀድሞ አዲስ አበባ የገባ ሲሆን የጆቢራውን ቡድን ሲያስተባብር ንብቷል፡፡
ከጆቢራዎቹ ጋር በመሆን በቀጣይ ሐሙስ ይጀመራል ተብሎ በሚጠበቀው የግንቦቱ ርክበ ካህናት የቅዱስ 
ሲኖዶስ ስብሰባ በአሜሪካ ከአቡነ ፋኑኤል ጋር ተያይዞ የተከሰተው ውዝግብና የተሐድሶ መናፍቃንን በተመለከተ 
የቀረበለት መረጃ መርምሮ አንዲያቀርብ የተሰየመው ስድስት ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳትና ሁለት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን ያካተተው ኮሜቴ ሪፖርት አቅርቦ ውሳኔ እንዳይሰጥ ለማድረግ ቅዱሰ ሲኖዶስ በደራሽ ችግሮች 
አንዲጠመድና ጊዜ እንደይኖው በማድረግ ለቀጣይ የጥቅምቱ ስብሰባ አጀንዳዎቹን እንዲያሳድራቸው ለማድረግ 
በመጣር ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህ የተመረጠው “ስስ ርእሰ ጉዳይ” (sensitive issue) የማኅበረ ቅዱሳንን ህልውና ላይ አደጋ መጋረጥ ነው፡፡ ለአሁኑ በኃ/ጊዮርጊስ አስተባበሪነት ተቀነባብሮ በቆሞስ መልዓከ 
ጽዮን አባ ሕሩይ ወንድይፍራው የሠንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሓላፊ አማካኝነት የከሸፈውን ሴራ 
እናቀርባለን፡፡
 


ቀኖናዊ ጥሰት በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መዋቅር ስር ያሉትን አብያተክርስቲያናት አሳዘነ፡፡
ባለፈው የጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ሁሉቱን አህጉረ ስብከት ደርበው እንዲያስተዳድሩ  
ተመደቡ፡፡ብጹነታቸው ወደ አሜሪካ እንደሄዱ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መዋቅር ስር ያሉትን አብያተክርስቲያት 
ሊያደርጉላቸውን የነበረውን አባታዊ አቀባበል እንዲሁም በብጹእ አቡነ አብርሐም የተገዛውን መንበረ ጵጵስናውን
እንዲረከቡ የቀረበላቸውን ጥያቄ ወደ ጎን በመተው ቀድሞውንም ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ ክህነት በመሾም፣ማዕረገ-ሥም በመስጠትና ቅዳሴ ቤት በማክበር ገለልተኛ አብያተክርስቲያናት ዘንድ ድጋፍ ለማግኘት ሲሞክሩ 
ወደ ነበሩበት ፊታቸውን አዞሩ፡፡ “የሁሉም አባት ነኝ” በሚል ሽፋን ከገለልተኛ አብያተክርስቲያናት ጋር ያለውን 
የቀኖና ቤተክርስቲያን ልዩነት ግምት ውስጥ ያላስገባ አካሄድ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መዋቅር ስር ያሉትን 
አብያተክርስቲያናት ካህናትን፣ምእመናን፣የአገረ ስብከት ኃላፊዎች፣ መምህራን ዘንድ ተቃውሞ ገጠማቸው፡፡በገለልተኛ አብያተክርስቲያናት በኩል ደግሞ የጠበቁትን ምላሽ ማግኘት አልቻሉም፡፡


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማት ኮሚሽን በመደበኛነት ተቀጥሮ በሰራባቸው ጊዜ 
ለፈጸማቸው ሙስናዎችና ላለበት ሐይማኖታዊ ኑፍቄ መረጃ ይዞብኛል ብሎ የሚሰጋውን ማኅበረ ቅዱሳንን ለማጥቃት (ተቋማዊ ቀብር ለመፈጸምላለፉት አስራ አምስት ዓመታት የዓላማ አንድነት 
ካላቸው ጆቢራዎች ጋር ግንባር በመፍጠር በርካታ ጥረቶች እንዳደረገ ይታወቃል፡፡ ይሄ መሰሪ አካሄዱ 
የበለጠ እንዲገልጠው ምቹ ሁኔታ የፈጠረለት ልማት ኮሚሽንን ለቆ ወደ አሜሪካ ኢምባሲ USAID  
ሲቀጠር ነው፡፡የሚሰራበት ድርጅት አሜሪካ ሃገር የሚተገብረው ፕሮጀክት ስለነበር በጊዜው ወደ አሜሪካ
ልኮት ነበር፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ (phaseout ሲያደርግወደ ኢትዮጵያ  
መመለስ የነበረበት ቢሆንም አሜሪካ ለመሰንበት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ  
ቤተክርስቲያን  አገልጋይ በመሆን ያደረገው ጥረት ብዙም አልሰመረም፡፡


ዲያቆን /ጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ psychology በመጀመሪያ ዲግሪ መመረቁን፤ ዩንቨርስቲ ተማሪ 
በነበረበት ወቅት በስድስት ኪሎ ግቢ ጉባኤ ከተመረቀ በኋላ ማኅበረ ቅዱሳን ማገልገል ጀምሮ የነበረ ቢሆንም 
1989 . ያራምደው በነበረው ፕሮቴስታንታዊ የተሃድሶ አስተምሮ በወንድሞችና በአባቶች ቢመከርም በኑፋቄው 
ስለገፋባትም በማኅበሩ አባልነት ሊቀጥል እንደማይችል በሚገልጽ ደብዳቤ ከአባልነት እንደተሰናበተ በቅርብ 
የሚያውቁት ይናገራሉ፡፡
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
ኃይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን


No comments:

Post a Comment