Thursday, October 16, 2014

ሰበር ዜና – የቅ/ሲኖዶሱን ልዕልናና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን መፃረራቸውን የቀጠሉት አቡነ ማትያስ ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ›› አሉት – ‹‹አባ ማትያስ አላበደም፤ በዚኽ መግለጫ እንድትሠሩበት ነው የምነግራችኹ›› ሲሉም በማኅበሩ ላይ የጥፋት መልእክታቸውን ዐዋጁበት!

  • ጥቂት አማሳኞች በማንጨብጨብ ሲከተሏቸው፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ጨምሮ ብዙኃን ጉባኤተኞች በድንጋጤና በተደምሞ አዳምጠዋቸዋል፡፡ ፓትርያርኩ በቀቢጸ ተስፋ ውስጥ እንዳሉም አመላካች ኾኗል፡፡
  • ማኅበረ ቅዱሳን÷ በጉባኤያት፣ በኅትመትና በኤሌክትሮኒክስ የስብከተ ወንጌል ስርጭት፣ በቅዱሳት መካናት ልማት፣ በአብነት ት/ቤቶችና በካህናት ማሠልጠኛዎች ድጎማና ሞያዊ እገዛዎች ያከናወናቸው ተግባራት በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፖርት በስፋት ተዳስሰዋል፤ ጉባኤተኞች ማኅበሩ ላስመዘገባቸው የሥራ ፍሬዎች ደማቅ ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡
his-hholiness00ዛሬ፣ ጥቅምት ፭ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብሰባ አዳራሽ በተጀመረው ፴፫ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ላይ የጉባኤ መክፈቻ ቃለ በረከት እንዲሰጡ የተጋበዙት ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ›› በማለት ‹‹በቁጥጥር ሥር እንዲውል›› ቅስቀሳ እንዳካሔዱበት ተሰማ፡፡
ፓትርያርኩ የጉባኤ መክፈቻ ‹ቃለ በረከታቸው› ማሳረጊያ ላደረጉት ቅስቀሳ መሰል ንግግራቸው መግቢያ ያደረጉት፣ ‹‹ስለ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ኹኔታ ልገልጽ እፈልጋለኹ፤ ይህ ጉባኤ በዓመት አንዴ የሚገኝ ነው፤ ዕድሉ እንዲያመልጠኝ አልፈልግም፤›› በሚል ቃለ አጽንዖት ነበር፡፡
ከዚያም ‹‹ቤተ ክርስቲያናችን በቅኝ ገዥዎች ተይዛለች›› ካሉ በኋላ ‹‹ቅኝ ገዥው ማን ነው?››ሲሉ ጠይቁ፡፡ ምላሹን ራሳቸው ሲሰጡ፣ ‹‹ኹላችኁም የምታውቁት አንድ ማኅበር ነው›› ሲሉ ጠቆሙ፡፡ ‹‹በምን?›› ሲሉ ዳግመኛ ጠየቁና ‹‹በገንዘብ፤ በራስዋ ገንዘብ፤ ይኼን እንድታውቁ እፈልጋለኹ›› ሲሉ መለሱ፤ ‹‹እኔ ይኽን ጉዳይ ከራሴ አወርዳለኹ፤ የቤተ ክርስቲያናችን ገንዘቧ፣ ክብሯ ተወስዷል፤›› በማለትም አስረገጡ፡፡
በአምናው ዓመታዊ ስብሰባ፣ ‹‹ማኅበሩ በቁጥጥር ሥር እንዲውል›› አጠቃላይ ጉባኤው ውሳኔ አሳልፎ ነበር ያሉት ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ ‹‹ገንዘቡ፣ ንብረቱ በቁጥጥር ሥር እንዲውል የወሰናችኁት አንድም አልተፈጸመም፤ እነርሱም ፈቃደኛ አልኾኑም፤ ማን ጠይቆ?›› ሲሉ ኹኔታው ከአቅማቸው በላይ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡
አስከትለውም ‹‹ቤተ ክርስቲያን ከቅኝ ተገዥነት ትውጣ፤ ካህናቱ ከመከራ ይውጡ›› በማለት መልእክታቸውን በማንኛውም ቦታ እንደሚያስተላልፉ ከተናገሩ በኋላ፣ በሓላፊነት የተቀመጡት ‹‹ይህችን ቤተ ክርስቲያን ለመጠበቅ፤ አንዷን ቅድስት፣ ኦርቶዶክሳዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን ልመራ እንጂ ኹለት ቤተ ክርስቲያን የለችም፤›› ብለዋል፡፡
እሾም ባዩ ቄስ ዘካርያስ (ከአጨብጫቢዎቹ አንደኛው)

በመጭው ሰንበት/እሁዶች አዲስ አበባ ማህበረ ቅዱሳንን በመደገፍ ታላቅ እና ደማቅ የአጋርነት ንቅናቄ ሊደረግ ነው ማህበረ ቅዱሳንን በመደገፍ ታላቅ እና ደማቅ የአጋርነት ንቅናቄ ሊደረግ ነው።



ንቅናቄው በጩሐት ሳይሆን ብልሃት እና ብስለት የተሞላበት መሆኑ ታውቋል።
የኢሕአዴግ መንግስት እና በቤተክህነት ውስጥ የተሰገሰጉ ካድሬዎች የተዋህዶ እምነትን የፖለቲካ አሽከር ለማድረግ የጀመሩትን ሴራ እና በማህበረ ቅዱሳን ላይ የተሰነዘረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በመቃወም በድምጻችን ይሰማ ዘኦርቶዶክስ እና በእኔም ለእምነቴ በብስለት እና ብልሃት በተሞላበት ሁኔታ በጋራ የተዘጋጀ ታላቅ እና ደማቅ የአጋርነት ንቅናቄ ማህበረ ቅዱሳንን በመደገፍ ሊካሄድ እንደሆነ እና ምእመናን ለዚሁ ንቅናቄ እንዲዘጋጁ ጥሪው ተላልፏል።
===============================
የመጀመሪያው ዙር ዝርዝር መግለጫ እንደሚከተለው ነው።
ለማኅበረ ቅዱሳን እመሰክራለው :: ለቀጣዩ የአደባባይ ምስክርነት በተጠንቀቅ እንዘጋጅ።
ምእመናን ምን ማድረግ እንዳለብን በቀጣይ ቀናት የሚገለፅ ይሆናል፡፡

††† #ድምጻችንይሰማዘኦርቶዶክስ - #እኔም_ለእምነቴ ! ††† የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆነ እና ስለማኅበረቅዱሳን በጎ ሥራ ለመመስከር እንዲቻል ይህ መልዕክት ለሁልም ማዳረስ ሐይማኖታዊ ግዴታችን ነው ፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !
እኔም ለእምነቴ የማህበራዊ ድረ ገፅ ተጠቃሚ ምንጮቻችን መሰረት፤ በማኅበረቅዱሳን ላይ አሁን እየተፈፀመ ያለው የስም ማጥፋት እና ውግዘት፤ ገና ከጥንስሱ ከማንም በፊት መረጃው ለሁሉም እንዲደር ጥረት ተደርጓል፡፡

ይሁን እንጂ ያስተላለፍ ነው መልዕክት ከቁምነገር ሳይቆጠር አብዛኛው ሰው ጉዳዩን በቸልታ አልፏታል፡፡ ሆኖም ግን በእኔም ለእምነቴ መረጃው ከተላለፈ 1 ቀን በኋላ ሪፖርተር ጋዜጣ በጉዳይ ዙሪያ ሰፊ ዘገባ ይዞ ወጥቷአል፤ ከዚያ ቀን ጀምሮ እስካሁን ስለማኅበረ ቅዱሳን መልካም የሆነ ነገር እየተሳማ አይደለም፡፡

Thursday, July 31, 2014

የብፁዕ አቡነ ዳንኤል የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ ተቃውሞ በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ላይ



የሚከተለውን አስተያየየት መሐሪ Mulugeta Maranatha ከተባሉ ግለሰብ ፌስ ቡክ(facebook) ገጽ ያገኘነው ነው።
+++
ሰሞኑን እንዲያውም በቅርቡ የቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ዳንኤል በደብረ ሰላም መድኃኒዓለም ቤ/ክ
ውስጥ ከሚገኙ ከተወሰኑ ምእመናን ጋር እና ከተወገዙት ካሕናት መካከል ከመሪጌታ ቀሲስ ጌታሁን ጋር በአደረጉት የስልክ ንግግር ላይ
የተናገሯቸው ብዙ ስህተቶች እርሳቸውንም ሆነ የቆሙለትን "ሥርዓተ ቤተክርስቲያን" ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው። ሲጀመር ከእነዚህ ሰዎች
ጋር ከመነጋገራቸው በፊት በመዓረግም ሆነ በሥልጣን ከሚቀርቧቸው አባት ከብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ጋር መጀመሪያ ቢነጋገሩ መልካም ነበር ያንን ግን የአደረጉ አይመስልም።

+ ሌላው ከስልክ ንግግራቸው እንደተረዳነው የብፁዕ አቡነ ዘካርያስን ርምጃ በተመለከተ ወደፊት ርሳቸው ከብፁዕነታቸው ጋር ተነጋግረው ሊፈቱት እንደሚችሉ
መናገራቸው መልካም ቢሆንም ርምጃው ግን ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን አንፃር ትክክል እንዳይደለ መናገራቸው በዛ በኩል "ስለ እኔ ጠይቃችው" ብሎ ለሌላ
ሰው ሹክ ያሉትን መሪጌታ ጌታሁንን እና ጥቂት ግለሰቦችን ብቻ ለማስደሰት እንደሆነ የሚያስረዳ ነው።

+ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ሀገረ ስብከታቸው ሌላ ቦታ፤ እረኝነታቸው ለሌላ ሥፍራ ሆኖ ሳለ ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ በሀገረ ስብከታቸው ውስጥ በአሉት አብያተ
ክርስቲያናት የሚወስዱትን ርምጃ መከላከልም ሆነ ትክክል እንዳልሆነ መናገራቸው ተገቢ አልነበርም።

+ በመጨረሻም ብፁዕ አባታችን ጥቂት ሰዎችን ለማስደሰት ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን መሻርና መጣስ የሚያስከትለው ችግርና መዘዝ ብዙ እንደሆነ እያወቁ፤
ስለ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን መከበር ግድ ከሌላቸው ሰዎች ጋር የሚነጋገሯቸውን ንግግሮች መጀመሪያ በሚገባ ቢያጤኗቸውና ከሚመለከታቸው አባቶች ጋር መክረውና ተመካክረው ቢያወሯቸው መልካም ነው ብዬ አስባለሁ።

+ ለመሪጌታ ቀ/ ጌታሁን፦ ውግዘቱ የመጣቦ ከብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ነበር። መፍትሔ ማግኘትም የሚችሉት ከርሳቸው ዘንድ ሆኖ ሳለ
በሌላ አቅጣጫ ሌላ ሰውን ሄዶ ፍረድልኝ ማለት እርሶን ሚዛን ላይ የሚጥል በእውነትም ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ የወሰዱት ርምጃ ትናንትናም ሆነ ዛሬ አማናዊ የነበረና፤
ሆኖ የሚቀጥል መሆኑን አስረግጦ ያለፈ ትዝብት ላይ የጣሎት አጋጣሚ ነበር የስልኩ ውስጥ ንግግሮት።

ነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን። አሁንም ሆነ ወደፊት የጥቂት ፓለቲከኞች ፈቃድ ሳይሆን፤ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ለማስከበር የሚደርስብንን
ፈተና ለመቀበል ዝግጁዎች ነን።





የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

Monday, April 7, 2014

በተጠርጣሪ የፕሮቴስታንታዊ ኑፋቄ ኅቡእ አራማጆች ላይ ዛሬ ምስክሮች ይሰማሉ

holy trinity building
  • ከሓላፊነታቸው ውጭ የሚንቀሳቀሱ ፕሮቴስታንትና ጉዳዩን ፖሊቲካዊ ያደረጉ የደኅንነት አባላት ነን ባዮች የኮሌጁን ሓላፊዎች በመጫን ተጠርጣሪዎቹን ከተጠያቂነት ለማዳን እየሠሩ ነው፤ ተጠርጣሪዎቹ በኮሌጁ አስተዳደር የተከለከለ ስብሰባ በግቢው እንዲያካሒዱ ረድተዋቸዋል፡፡
  • በ‹ደኅንነት አባላቱ› የሚደገፉትና ‹‹የኢሕአዴግ ተወካዮች ነን›› የሚሉት ተጠርጣሪዎቹ፣ ለሃይማኖታቸው የቆሙትን ብዙኃኑን የኮሌጁን ደቀ መዛሙርት በስለትና በፌሮ ብረት የታገዘ ዛቻና ማስፈራራት እያደረሱባቸው ነው፤ ደቀ መዛሙርቱና የኮሌጁ አስተዳደር ጉዳዩን ለጸጥታ አካላት አስታውቀዋል፡፡
  • ተጠርጣሪዎቹ÷ ‹‹ጽንፈኝነትን ታስፋፋለች›› በማለት ቤተ ክርስቲያንን የከሰሱ ሲኾን ዋና ዲኑን ጨምሮ አንዳንድ የኮሌጁን ሓላፊዎች ደግሞ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንና ፖሊቲከኞች ናችኹ›› በሚል ውንጀላ በምርመራው ሒደት እንዳይሳተፉና ከቦታቸው ለማስነሣት እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡፡
  • ኅቡእ የኑፋቄ አንቀሳቃሾችን በመመልመልና በማደራጀት የሚታወቁ ግለሰቦች (አሳምነው ዓብዩ፣ ደረጀ አጥናፌ እና ታምርኣየሁ አጥናፌ) ተጠርጣሪዎቹ ጥፋታቸውን እንዳያምኑ ከመገፋፋት ጀምሮ ደቀ መዛሙርቱን በጎጠኝነት በመከፋፈል አንድነታቸውን ለማሳጣትና ክሡን ለመቀልበስ እያሤሩ ነው፡፡

የመቐለ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መ/ኮሌጅ ኹለት የፕሮቴስታንታዊ ኑፋቄ ኅቡእ አንቀሳቃሾችን አባረረ፤ ለሰባት ተጠርጣሪዎች ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ በቅ/ሥላሴ መ/ኮሌጅ በዐሥር የኑፋቄው ኅቡእ አቀንሳቃሾች ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች ዛሬ መመርመር ይጀምራሉ

HOLY TRINITY THEOLOGICAL COLLEGE LOGO
  • የኮሌጁ የደቀ መዛሙርት ም/ቤት ችግሩ በአስቸኳይ እንዲጣራ ከኹለት ወራት በፊት ያስገባው ደብዳቤ ለተጠርጣሪ ደቀ መዛሙርት ሽፋን በሚሰጠውና ተጠርጣሪዎችን በቢሮው እየጠራ በሚያበረታታው የአስተዳደር ዲኑ ያሬድ ክብረት ተቀብሮ መቆየቱ ተገልጦአል፡፡
  • በቅ/ሲኖዶስ ከተወገዙ ግለሰቦችና ፕሮቴስታንታዊ ድርጅቶች የኑፋቄ አስተምህሮና ተልእኮ የሚሰጣቸው ኅቡእ አንቀሳቃሾችትኩረታቸውን በአዲስ ገቢ ደቀ መዛሙርት ላይ አድርገዋል፤ በመምህራን ምደባ ተጽዕኖ እስከመፍጠር፣ በነግህ ጸሎት ቤት ተራ ወጥቶላቸው ለስብከተ ወንጌል የሚመደቡ ቀናዒ ደቀ መዛሙርትን በማሸማቀቅ መርሐ ግብሩን እስከማስተጓጎልና መደበኛ የትምህርት ክፍለ ጊዜዎችን በጋጠ ወጥነትና በአካዳሚያዊ ነጻነት ስም እስከማወክ የደረሱት ኅቡእ አንቀሳቃሾቹ፣ ከየአህጉረ ስብከቱ ተልከው የመጡበትን የኮሌጁን ትምህርት በክፍል ተገኝተው በመደበኛነት አይከታተሉም፤ ቤተ መጻሕፍቱንማ ጨርሶ አያውቁትም!!
  • በተጠርጣሪነት ክትትል ከሚደረግባቸው ኻያ ያህል የስም ደቀ መዛሙርት መካከል የድምፅ፣ የጽሑፍና የሰው ምስክሮች የቀረቡባቸው ዐሥር ተማሪዎች፡- ጥበቡ ደጉ(፬ኛ ዓመት ከደብረ ማርቆስ)፣ መለሰ ምሕረቴ(፬ኛ ዓመት ከራያና ቆቦ)፣ ያሬድ ተስፋዬ(፫ኛ ዓመት ከሃላባ)፣ ኤርሚያስ መለሰ(፫ኛ ዓመት ከባሌ)፣ ታቦር መኰንን(፫ኛ ዓመት ከወሊሶ)፣ በኃይሉ ሰፊው(፫ኛ ዓመት ከቤንች ማጂ)፣ ተመስገን አዳነ(፪ኛ ዓመት ከሐዋሳ)፣ ይስፋ ዓለም ሳሙኤል(፫ኛ ዓመት ከሰቆጣ)፣ ገብረ እግዚአብሔር ተስፋ ማርያም(፫ኛ ዓመት ከአሶሳ)፣ ሀብታሙ ወልድ ወሰን(፫ኛ ዓመት ከወለጋ) ናቸው፤ የኑፋቄ ተልእኳቸውና ማስረጃዎቹ ከየስማቸው ዝርዝር በአንጻሩ ሰፍሯል፡፡
  • ከተጠርጣሪ ደቀ መዛሙርት መካከል የአጫብር አቋቋም ዐዋቂ ነው የተባለው መሪጌታ ጥበቡ ደጉ የደቀ መዛሙርት ም/ቤት አባል ሲኾን በፈረንሳይ ለጋስዮን ገነተ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በስብከተ ወንጌል እያገለገለ እንደሚገኝ ተዘግቧል፤ ግለሰቡ በግልጽ በሚናገረው ኑፋቄው፣ ‹‹እያንዳንድህ የበላኸውን ትፋ! ያለነው በጫካ ውስጥ ነው፤ ክርስቶስን ለማወቅ ካለንበት ጫካ መውጣት አለብን፤ መስቀል ዕንጨት ነው፤ ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ለመልአክ የምሰግደው ተገልጦ ሲታየኝ ብቻ ነው፤ ለማርያም የጸጋ ስግደት የሚለው በመጽሐፍ ቅዱስ የቱ ላይ ነው፤›› በሚል ግልጥ ኑፋቄ የቤተ ክርስቲያንን የነገረ ድኅነትና ክብረ ቅዱሳን አስተምህሮ በመጋፋት ይታወቃል፡፡
  • በኤቲክስና ሶሲዮሎጂ መምህሩ ተሾመ ገብረ ሚካኤል ‹‹ታዲያ ለምን ኤቲክስ ትማራለኽ?›› በሚል የተጠየቀው መለሰ ምሕረቴ፡-‹‹ኢየሱስ አማላጅ ነው፤ በጸጋው ድነናል፤ ሥራ(ምግባር) አያስፈልግም፤›› በማለት ይታወቃል፡፡ ያሬድ ተስፋዬ፡- በነግህ ጸሎት ቤት ነገረ ማርያምንና ክብረ ቅዱሳንን ማእከል አድርገው የሚያስተምሩ ቀናዒ ደቀ መዛሙርትን ትምህርት አስቁሞ ከመድረክ እንዲወርዱ በማስገደድ፤ ተመስገን አዳነ፡- አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ‹‹የተሻለ ሥልጠና የምታገኙበት ቦታ አለ›› በሚሉ የጥቅም ማባበያዎች እየመለመሉ በመውሰድ፣ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ትራክቶችንና መጽሐፎችን በኅቡእ በማሰራጨት፤ ‹‹እኔ የመንግሥት የደኅንነት አካል ነኝ፤›› የሚለው ታቦር መኰንንና ገብረ እግዚአብሔር ተስፋ ማርያም ቀናዒ ደቀ መዛሙርትን ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንና ፖሊቲከኞች ናችሁ›› እያሉ በማስፈራራት፣ መምህራን በምደባቸው እንዳያስተምሩ በውጤት አሰጣጥ ያኮረፉ ተማሪዎችን ለዐመፅ በማነሣሣት፣ በክፍል እያስተማሩ በሚገኙ መምህራን ላይ ከውጭ በር በመቀርቀርና በማንጓጠጥ፣ ዋናው ዲን የኮሌጁን ማኅበረሰብ በመንፈስ ለማስተሳሰር የጀመሯቸውን ጥረቶች (በጋራ እንደማስቀደስና እንደመመገብ ያሉ) በመቃወም በተለያዩ ስልቶች ወንጅሎ ለማስነሣት በሚፈጽሟቸው ሤራዎች ይታወቃሉ፡፡
  • ኅቡእ አንቃሳቃሾቹን እየመለመሉና ከኮሌጁ ውጭ በተለያዩ መንደሮች እያደራጁ ተልእኮና ጥቅም በመስጠት ወደ ኮሌጁ መልሰው ከሚያሰማሩት ግለሰቦች መካከል፡- በ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. በቅ/ሲኖዶስ ተወግዞ ከሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተባረረው ግርማ በቀለ፣ በግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. በቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተወገዘው አሸናፊ መኰንን፣ የታገደው ጥቅመኛና ጥራዝ ነጠቅ ተላላኪ አሰግድ ሣህሉ በዋናነት ተጥቅሰዋል፤ ከኮሌጁ ተመርቀው ምደባ ቢሰጣቸውም በአዲስ አበባ ተቀምጠው የማደራጀት ሥራውን የሚመሩትም አሳምነው ዓብዩ፣ ታምርአየኹ አጥናፌ፣ አብርሃም ሚበዝኁ፣ ጋሻው ዘመነ፣ ‹አባ› ሰላማ ብርሃኑ፣ እሸቱ ሞገስና በድሬዳዋ የሚገኘው በረከት ታደሰ እንዲኹም በኮሌጁ የድኅረ ምረቃ ትምህርት በመከታተል ላይ የሚገኙት አእመረ አሸብርና ደረጀ አጥናፌ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው፡፡
  • የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር በጽሑፍ፣ በድምፅና በሰው ምስክሮች ተደግፈው የቀረቡ ማስረጃዎችን ከቅዱሳት መጻሕፍት፣ ከትምህርተ ሃይማኖትና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ለመመልከት የሚያግዙትን ሦስት መምህራን መርጦ ዛሬ ምርመራውን ይጀምራል፤ የተመረጡት መምህራን፡- የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና ታሪከ ሃይማኖት መ/ር ፍሥሓ ጽዮን ደመወዝ፣ የሥርዓተ ቅዳሴ መ/ር ሐዲስ ትኩነህና የትምህርተ ሃይማኖትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን መ/ር ዶ/ር ሐዲስ የሻነህ ናቸው፡፡

አማሳኞች ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት የፈረጁበት ስብሰባና መግለጫ ሊቃነ ጳጳሳቱን አስቆጣ

  • ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች ገልጸዋል
  • የቤተ ክርስቲያንን እንጀራ እየበሉና በጀቷን አውጥታ እያስተማረቻቸው የሌላ እምነት በሚያራምዱ የስም ደቀ መዛሙርት ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ
(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፵፩፤ መጋቢት ፳ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)
Admas logoየኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ የኾኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዐት እንዲማሩ፣ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በማቀናጀት ሞያዊ ድጋፍ እንዲያበረክቱ በማስተባበር ላይ የሚገኘውን ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት በመፈረጅ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካይነት ጠቅላላ ሀብቱና ንብረቱ የሚታገድበት ውሳኔ እንዲተላለፍ በመንግሥትም በኩል እርምትና ርምጃ እንዲወሰድበት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአድባራት አስተዳዳሪዎች መግለጫ አውጥተውበታል በተባለው ስብሰባ ጉዳይ ኹለት ሊቃነ ጳጳሳት ለከፍተኛ የመንግሥት ሓላፊዎች ቅሬታቸውን ማሰማታቸው ተገለጸ፡፡
የቅ/ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስንና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን በስም የጠቀሱት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች፣ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ያቀረቡት ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች እንደኾነ ቢገልጹም የሓላፊዎቹን ስም ከማሳወቅ ተቆጥበዋል፡፡
Lukas
ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና በክልል ትግራይ የምዕራብ ሰቲት ሑመራ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ማኅበረ ቅዱሳን የደረሰበት ፈታኝ ወቅት

FACT magazine Megabit 3rd cover(ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፱፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.)
ተመስገን ደሳለኝ
  • በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም አዝማችነት በማኅበሩ ላይ የደቦ ዘመቻ ከተከፈተ ሰነባብቷል፡፡ በጥናት ስም በተከታታይ የሚወጡና በየመድረኩ የሚቀርቡ ወረቀቶች ማኅበሩን የኦርቶዶክስ አክራሪከማለት አሻግረው ‹‹የግንቦት ሰባት መንፈሳዊ ክንፍ/የግንቦት ሰባት ከበሮ መቺ/›› ሲሉ ይወነጅሉታል፡፡
  • የማኅበሩ አመራሮች እንዲኽ ዓይነቱን ውንጀላ በተመለከተ በተለያየ ጊዜ ከአቶ በረኸት ስምዖን እስከ ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም፣ ከአዲስ አበባ የጸጥታ ሓላፊዎች እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ አቶ ፀጋይ በርሀ ድረስ ያሉ ባለሥልጣናትን በቢሯቸው ተገኝተው ውንጀላው ተቀባይነት ያለው ማስረጃ የማይቀርብበት የሐሰት እንደኾነ ቢያስረዱም መፍትሔ እንዳላገኙ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
  • በግልባጩ በመንግሥት ተቋማት ያሉ የፋክት መጽሔት መረጃ አቀባዮች፣ በግንቦት ወር ከሚካሔደው የሲኖዶሱ መደበኛ ዓመታዊ ጉባኤ በፊት፣ ከኻያ የሚበልጡ የማኅበሩ አመራሮችን ከሽብርተኝነት ጋራ በማያያዝ ለመክሰስና ማኅበሩንም እንደተለመደው በዶኩመንተሪ ፊልም ለመወንጀል ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
  • በዚኽ አስቸጋሪ ወቅት ደግሞ መነሣት የሚኖርበት አስቸጋሪ ጥያቄ፣ እንዴት ይህን ማኅበር ወደ ቀጣዩ ትውልድ ማሻገር ይቻላል? የሚለው ሲኾን ምላሾቹም ኹለት ናቸው፡፡ ‹‹ችግሮች ኹሉ የየራሳቸው በጎ ገጾች አሏቸው›› እንዲሉ፣ ማኅበሩ የደረሰበትን ይህን ፈታኝ ጊዜ ተከትለው የሚመጡ ኹለት ወቅቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው፣ በቀጣዩ ወር የሚታሰበውየስቅለት ቀን ነው፡፡ ኹለተኛና በእጅጉ የተሻለ ነው ብዬ የማስበው ጊዜ ደግሞ ቀጣዩ የ2007 ዓ.ም. ምርጫ ነው፡፡
  • የሃይማኖቱ ተከታዮች በሙሉ በየቤተ ክርስቲያኑ የሚውሉበት የስቅለት በዓል የትኞቹም የሕገ መንግሥቱ ሐሳቦች አልያም የሞራል ዕሴቶች የማይገዛው ሥርዓት እጁን ከማኅበሩና ከቤተ ክርስቲያን በአጠቃላይ እንዲያነሣ ለመጠየቅ ብሎም ሕያውነታቸውን የመሠረቱበትን ሃይማኖት ለማስከበር የተመቸ ቀን ስለመኾኑ ማስታወስ አባላቱን አሳንሶ መገመት እንዳይኾን ተስፋ አደርጋለኹ፡፡

Friday, February 21, 2014

አባ ሰረቀ ብርሃን ‹‹በታቦት ዝርፊያ›› ክስ ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ዘንድ ቀርበው ነበር

  • ‹‹ለዚህ መረጃ አቡነ ማቲያስ ቀድሞ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ በአሁን ሰዓት 6ተኛው ፓትርያርክ፣ አቡነ ሣሙኤልና አቡነ ኢሳይያስ ህያው ምስክሮች ናቸውና›› መረጃውን የላኩልን የሎሳንጀለስ ምዕመን
  • ‹‹አባ›› ሰረቀ ታቦት ሰርቀው ተይዘዋል፡፡ ከገዛናቸው 12 ጸናጽል ያስረከቡን ስድስቱን ሲሆን  12 መቁዋሚያም 6ቱን ይዘውብን ሄደዋል፡፡
  • ‹‹አቡነ አረጋዊም የሚባል ቤተክርስቲያን የለም፡፡›› ‹‹አባ›› ሰረቀ ብርሃን በአንድ ወቅት የሰበኩት ስብከት
  •  ‹‹በወቅቱ የአሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት አቡነ ማቲያስ ማኅተም ወስደው በነጭ ወረቀት ላይ እያተሙየኔን ፊርማ እያስቀመጡ ሰዎችን ብር እየተቀበሉ ከኢትዮጵያ ወደዚህ ሲያመጡተደርሶባቸው..........››
    በወቅቱ አባ ሰረቀ ከጓደኛቸው ጋር ሲሰሩት የነበረ ሥራ የምዕመኑ ቃል
ከአንድ የሎስ አንጀለስ ምዕመን የደረሰን መልዕክት 


(አንድ አድርገን የካቲት 11 2006 ዓ.ም)፡- በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት ሊካሄድ የታሰበው የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ በአባ ሰረቀ ብርሃን አማካኝነት ከቅዱስ ፓትርያርኩ በተሰጠ መመሪያ መሠረት ሳይካሄድ መቅረቱ ይታወቃል፡፡ የአባ ሰረቀን  የቀድሞ ተግባር በርካታ ምዕመን ቢያውቀውም  ብጹዕ አቡነ ማቲያስ የሚያውቁትን እና በሎስአንጀለስ ምዕመናን ላይ ያደረሱትን በደል የደረሰንን መልዕክት ለእናንተው ለማድረስ ወደድን፡፡ ‹አባ› ሰረቀን ከአመታት በፊት በታቦት ሌብነት ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ዘንድ ቀርበውም እንደነበርም መረጃው ያመለክታል፡፡ ስለዚህ ቅዱስነታቸው አሁን እየሰሩ የሚገኙት ቀድሞ  ለሰሚ ጆሮ የሚከብድ ዝርፊያ በቤተ ክርስቲያን ላይ ካደረገ ሰው ጋር መሆኑን ነው፡፡ እስኪ በወቅቱ የነበሩ ህያው ምስክሮች የላኩልንን መረጃ ይህን ይመስላል፡፡

Saturday, February 15, 2014

የሃይማኖት ተቋማት ምዝገባን መቃወም የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌ ነው ተባለ

  • ሐዋሳው ስብሰባ የተጠበቀው የምዝገባ ዐዋጁ ረቂቅ ለውይይት ሳይቀርብ ቀረ
  • የዐዋጁ ጉዳይ በቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ደረጃ ሊመከርበትና አቋም ሊያዝበት ይገባል
  • የሰላም ዕሴት ግንባታ ሰነዱ በአወዛጋቢ ይዘቱ ለተጨማሪ ግምገማ እንዲዘገይ ተደረገ
Dr. Shiferaw Hawassa
ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም
የሃይማኖት ወይም እምነት ተቋማትን ለመመዝገብና የዕድሳት አገልግሎት ለመስጠት በሚል መዘጋጀቱ የተገለጸውን የዐዋጅ ረቂቅና አሠራሩን በመቃወም የሚካሔድ እንቅስቃሴ የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌ መገለጫ መኾኑን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም ተናገሩ፡፡
ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት፣ በሐዋሳ ለሁለት ቀናት በተካሔደውና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ‹‹ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ›› ጋራ በመተባበር ባዘጋጀው ዐውደ ትምህርት ላይ ‹‹አክራሪነትና ጽንፈኝነት ከሕገ መንግሥታችን ጋራ ያለው የማይታረቅ መሠረታዊ ቅራኔና መፍትሔው›› በሚል ርእስ ባቀረቡት ጽሑፍ ነው፡፡
ይኸው የሚኒስትሩ ጽሑፍ ‹‹አክራሪነትና ጽንፈኝነት ማብራሪያና መፍትሔዎቻቸው››ተብሎ በስላይድ ታግዞ የቀረበ ሲኾን መንግሥትና የሃይማኖት ተቋማት በሰላምና ልማት ጉዳይ ጭምር መደራረስ የለባቸውም በሚል የሚካሔድ እንቅስቃሴ ስለመኖሩ ይገልጻል፡፡
ይኸው እንቅስቃሴም የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌ እንደኾነ የሚኒስትሩ ጽሑፍ ያመለክታል፡፡ ‹‹የአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌዎች የጋራ ጉዳዮች›› በሚል የጽሑፉ ንኡስ ርእስ ሥር የተካተተው ይኸው የሚኒስትሩ ምልከታ፣ በስም ለይቶ ያነሣው አካል ባይኖርም ‹‹የሃይማኖት ተቋማት ምዝገባ ጉዳይ እና የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ›› የሚሉ ሁለት ጉዳዮችን በማውሳት ‹‹ለአክራሪነትና ጽንፈኝነት ዝንባሌው›› በማሳያነት ማቅረቡ ተዘግቧል፡፡

ከመመሪያ ወደ ዐዋጅ ከፍ የተደረገው ‹‹የሃይማኖት ተቋማት ምዝገባና የዕድሳት አገልግሎት›› ረቂቅ በሐዋሳ ለውይይት ይቀርባል

  • የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ከ‹‹ኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ›› ጽ/ቤት ጋራ በመተባበር ያዘጋጀውና ከጥር ፴ – የካቲት ፪ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. በሐዋሳ – ሌዊ ሪዞርት በሚካሔደው ውይይት ላይ፣ በፓትርያርኩ የሚመራ ኻያ ያህል የቤተ ክርስቲያናችን ልኡክ ይሳተፋል፤ ልኡኩ በዛሬው ዕለት ከቋሚ ቅዱስ ሲኖዶሱ የሥራ መመሪያ ይቀበላል፡፡
  • የዐዋጁን ረቂቅ ከውይይቱ አስቀድሞ ለመመልከትና የቤተ ክርስቲያናችንን አስተያየትና አቋም ለመወሰን ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የቀረበው ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ አላገኘም፡፡
  • ‹‹የሃይማኖት ወይም እምነት ተቋማትን ለመመዝገብና የዕድሳት አገልግሎት ለመስጠት›› በሚል በፓርላማው ጸድቆ እንደሚወጣ የተመለከተው ዐዋጅ÷ የእምነት ተቋማትና ከእምነት ጋራ የተሳሰሩ መንግሥታዊ ያልኾኑ አደረጃጀቶች‹‹ፀረ ሕገ መንግሥታዊ ተግባር ላይ እንዳይሳተፉ ለመከላከልና ተጋላጭ ከሚያደርጉ አሠራሮች እንዲቆጠቡ ለመደገፍ እንዲሁም ሕገ ወጥ የፋይናንስ ዝውውር አካል እንዳይኾኑ ለመጠበቅ ያስችላል›› ተብሏል፡፡
  • የ‹‹ኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ›› አባል ከኾኑ ሰባት የእምነት ተቋማት በተውጣጡ ምሁራን እንደተዘጋጀና በአገር አቀፍ ደረጃ በየአብያተ እምነቱ ተግባር ላይ እንደሚውል የተገለጸው፣ የሃይማኖት ተቋማት የሰላም ዕሴት ማሠልጠኛ መመሪያ ረቂቅም የመጨረሻ ይዘት ተገምግሞ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል፡፡
  • ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ጋራ በቅርበት በሚሠራው ‹‹የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ›› የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ፣ የቀበሌና ንኡስ ቀበሌ መዋቅሮች በቋሚነት የሚመደቡ ተወካዮቻችንና ጽ/ቤቱ በሚያዘጋጃቸው የምክክር መድረኮች፣ ዐውደ ጥናቶችና የኅትመት ውጤቶች ላይ የሚሳተፉ ልኡኰቻችን፣ የአስተሳሰብና ሞያዊ ብቃት፣ የውክልና አግባብነትና የተሳትፎ ፋይዳ ከሽርሽር ጉዞ፣ ከፖሊቲካ ቅኝትና አድርባይነት ይልቅ የቤተ ክርስቲያናችንን መብቶችና ጥቅሞች በማስጠበቅ ለአገራዊ የጋራ ጉዳይ ለመሥራት የሚያስችል ስለመኾኑ በጥንቃቄና በጥልቀት መገምገም እንደሚገባው እየተጠየቀ ነው፡፡

ጥንታዊው የደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ ገዳም ተፈታ

  • ገዳሙ ጨርሶ ሳይጠፋ ጉዳያቸው በቅዱስ ሲኖዶሱ እንዲታይ መናንያኑ ጠይቀዋል
  • በገዳሙ ህልውና ላይ የተጋረጠው አደጋ በሀ/ስብከቱ የተንሰራፋው ችግር የከፋ መገለጫ ነው
(አዲስ አድማስ፤ ጥር ፳፬ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀ/ስብከት ሞረትና ጅሩ ወረዳ የሚገኘው የመካከለኛው መቶ ክፍለ ዘመን የደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ አንድነት ገዳም ተፈትቶ፣ መናንያኑና መነኰሳቱ መበተናቸውን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ገለጹ፡፡
ጥንታዊውን ገዳም ለመፈታት፣ ማኅበረ መነኰሳቱንም ለመበተን ያበቃቸው፣ በአካባቢ ተወላጅነት የገዳሙን መሬት በተለያዩ ጊዜያት ተቆጣጥረው ለግላቸው ይጠቀሙ ከነበሩ ግለሰቦች ጋር ተፈጥሮ የቆየውና በተለያዩ ምክንያቶች እየተካረረ የመጣው አለመግባባትመኾኑን ምንጮቹ ተናግረዋል፡፡
በኅዳር ወር 2006 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ገዳሙን ለቀው የወጡት በቁጥር ከ50 – 80 የሚገመቱ መናንያኑ ከተለያዩ አህጉረ ስብከትና ክልሎች የተሰባሰቡና በጸሎት ተወስነው የራስ አገዝ ልማት እያለሙ በአንድነት የኖሩ መነኰሳትና መነኰሳዪያት ሲኾኑ በሀገረ ስብከቱ ውሳኔ ከአስተዳዳሪነት የተነሡትን አበምኔቱን መ/ር አባ ተክለ ብርሃን ሰሎሞንን ጨምሮ ከፊሎቹ በአሁኑ ወቅት በደነባ በኣታ ለማርያም ገዳምተጠልለው እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ የወረዳው መንግሥታዊ አስተዳደር፣ ከእነዋሪና ደነባ ከተሞች የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ገዳማውያኑንና ግለሰቦቹን በተለያየ ጊዜ በማገናኘት ለአለመግባባቱ የመፍትሔ ሐሳብ ሲሰጡና ውሳኔ ሲያሳልፉ እንደቆዩ ያስታወሱት መነኰሳቱ፤ ‹‹ተሰዳጅና መጤ›› ከሚል በቀር ግለሰቦቹ በገዳሙ አበምኔትና በመናንያኑ ላይ የሚያቀርቧቸው ክሦች መሠረተ ቢስ መኾናቸው ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

Tuesday, February 4, 2014

የሐመረኖህ ኪዳነ ምህረት በላስቬጋስ የተደበቀና የደረስኩበት የውስጥ ችግር

 አንድ የዘወትር አንባቢያችን ከላስቬጋስ አካባቢ በተለይ በሐመረ ኖሕ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ በመሆን እያገለገሉ ስላሉት መነኮስ እና ሥራቸው መጠነኛ የሆነ መረጃዎችን ልኮልናል። ምዕመን የማወቅ መብት አለው ብለን ስለምናምን ይኛም የመጣልንን መረጃ እንደወረደ ለእናንተው አቅርበነዋልና ተከታተሉ። መልካም ምንባብ እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ እንመኛለን።
መላከ ሰላም አባ ገብረ ኪዳን ሽፈራው
በጥቂት ምዕመናንና በአንድ ቄስ የዛሬ ስምንት አመት የተቋቋመው የሐመረኖህ ቤተክርስቲያን በመናፈሻ ፣በላይብረሪ ‘በሰርቢያንቸርች ፍላሚንጎና ጆንስ፣ቶሮፓይንስና ትሮፒካና በሚገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ፣በመጨረሻም አሁን ባለበት ቤተክርስቲያን በብዙ ድካምና ትጋት ሲገለገል ቆይቷል አራት ወራት ያህል በካህን እጦት ከዲሲ፣ከሎሳንጀለስና ከሳንዲያጎ ፣ከዳላስ ቴክሳስ ካህናት እየተመላለሱ ሲያገለግሉ ቆይተዋል እለዚህ ቤተክርስቲያኑን በየሳምንቱ እየተመላለሱ ሲያገለግሉ የነበሩት ባለውለታ ካህናት ቀሲስ ከፈለኝ፣ አባ ሀይለስላሴ፣አባ ገብረ ማርያም፣አባ ገብረ መድህን ፣ቀሲስ ብርሀኑ፣ቀሲስ ሰብስቤ በመሀል ስማቸውን የረሳኋቸው የመጡ ካህናት ይኖራሉ እነዚህ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በባእል ቀን ሲያገለግሉን ነበር ከአራት ወር በኋላ በአቡነ ማትያስ ሽዋሚነጽ ዲ/ሳሙኤል ደጀኔ ቅስና ተቀብለው ለአራት አመታት ያህል ብቻቸውን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አንድምቀን አገልግሎቱ ሳይቋረጥ ከአራት አመት በኋላ ዲ/ዮሐንስን ቅስና ከአቡነ ማርቆስ ተሸሙ ቀሲስ ሳሙኤልን እያገዙ ብዙም ሳይቆይ አባ ገብረኪዳን መጡ አንድ ሆነው በፍቅር በሰላም ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ አዲስ የሰበካ ጉባኤ ከተመረጠ ወዲህ ሰለም እየደፈረሰ መጣ በጉባኤው ውሰት አባ ገብረ ኪዳንን ጨምሮ ሦስት የማህበረ ቅዱሳን አባላት አሉበት እንደምንሰማው ውሳኔዎች በግሩፕ መወሰን ጀመሩ በሞቀበት ፈላ የሆነው ዲ ምስክርም ወደሞቀበት ሲያጫፍር ቆየ ይህ በእንዲህ እንዳለ አባ ገብረ ኪዳን ለአራት ወር ወደሀገርቤት ሲሄዱ