- ‹‹ለዚህ መረጃ አቡነ ማቲያስ የቀድሞ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ በአሁን ሰዓት 6ተኛው ፓትርያርክ፣ አቡነ ሣሙኤልና አቡነ ኢሳይያስ ህያው ምስክሮች ናቸውና›› መረጃውን የላኩልን የሎሳንጀለስ ምዕመን
- ‹‹አባ›› ሰረቀ ታቦት ሰርቀው ተይዘዋል፡፡ ከገዛናቸው 12 ጸናጽል ያስረከቡን ስድስቱን ሲሆን፤ ከ 12ቱ መቁዋሚያም 6ቱን ይዘውብን ሄደዋል፡፡
- ‹‹አቡነ አረጋዊም የሚባል ቤተክርስቲያን የለም፡፡›› ‹‹አባ›› ሰረቀ ብርሃን በአንድ ወቅት የሰበኩት ስብከት
- ‹‹በወቅቱ የአሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት አቡነ ማቲያስ ማኅተም ወስደው በነጭ ወረቀት ላይ እያተሙየኔን ፊርማ እያስቀመጡ ሰዎችን ብር እየተቀበሉ ከኢትዮጵያ ወደዚህ ሲያመጡተደርሶባቸው..........››በወቅቱ አባ ሰረቀ ከጓደኛቸው ጋር ሲሰሩት የነበረ ሥራ የምዕመኑ ቃል
ከአንድ የሎስ አንጀለስ ምዕመን የደረሰን መልዕክት
(አንድ አድርገን የካቲት 11 2006 ዓ.ም)፡- በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት ሊካሄድ የታሰበው የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ በአባ ሰረቀ ብርሃን አማካኝነት ከቅዱስ ፓትርያርኩ በተሰጠ መመሪያ መሠረት ሳይካሄድ መቅረቱ ይታወቃል፡፡ የአባ ሰረቀን የቀድሞ ተግባር በርካታ ምዕመን ቢያውቀውም ብጹዕ አቡነ ማቲያስ የሚያውቁትን እና በሎስአንጀለስ ምዕመናን ላይ ያደረሱትን በደል የደረሰንን መልዕክት ለእናንተው ለማድረስ ወደድን፡፡ ‹አባ› ሰረቀን ከአመታት በፊት በታቦት ሌብነት ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ዘንድ ቀርበውም እንደነበርም መረጃው ያመለክታል፡፡ ስለዚህ ቅዱስነታቸው አሁን እየሰሩ የሚገኙት ቀድሞ ለሰሚ ጆሮ የሚከብድ ዝርፊያ በቤተ ክርስቲያን ላይ ካደረገ ሰው ጋር መሆኑን ነው፡፡ እስኪ በወቅቱ የነበሩ ህያው ምስክሮች የላኩልንን መረጃ ይህን ይመስላል፡፡
አባ ሰረቀ ማን ናቸው? ከዚህ በፊት ያልተሰሙ ወሬዎችን ያንብቡት
ምንም እንኳን የሰሩት ሥራ ያደረጉት አሳዛኝና አሳፋሪ ተግባር አንቱ ለማለት ቢያስቸግርም የቤተ ክርስቲያናችንሥርዓት ፣ የሀገራችን ባህል አስገድዶኝ አንቱ በማለቱ እቀጥላላልሁ ። አባ ሰረቀ ብርሃን (እዚህ ባለሁበትሎሳንጀለስ ከተማ) ታቦታቸውንና ንዋያት ቅዱሳታቸውን ዘርፈው ስለሄዱ አባ ሰራቂ በማለት ይጠሯቸዋል ።አንዲት የቤተክርስቲያናችን አዛውንት ስማቸው እንኳን ሲጠራባቸው የሚያንገሸግሻቸው አውቃለሁ።
ወደ ዋናው ቁም ነገር ልግባና አባ ሰረቀ በሎሳንጀለስ እንዴት ነበሩ የሚለውን እስኪ እንመልከት፦
አባ ሰረቀ ብርሃን በ1993 መስከረም ላይ ከኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት ይህንን መረጃ የሰጡን አባት እንዲህያጫውቱናል። ‹‹አባ ሰረቅ ብርሃንን ለማስመጣት ሂደቱን የጀመእኩት እኔ ነኝ። በ1993 እ.ኤ.አ. የእህቴን ባልእባክህ ጥሩ ካህን የተማረና ሰዎችን የሚያስተምር ሰው ፈልግልን ብዬ ነገርኩት። እርሱም ወዲያው አንድ በጣምየተማሩ ሰው አግኝቸልሃልሁ ብሎ አጫወተኝና (በኢትዮጵያም ክረምት አካባቢ ነው) ደስ አለኝ። ደውዬምእንዳነጋግራቸው አመቻቸልኝና ፤ አባ ሰረቀን ድውዬ አገኘኋቸው። እርሳቸውም ለመምጣት እፈልጋለሁ ግንለመጉዋጓዣ 2000 ዶላር ያስፈልገኛል ብለው ነገሩኝ። እኔም ቦርዱን አስፈቅጀ የመምጫቸውን ሁኔታጀመርን።2000 ዶላርም ተላክላቸው። ››
በኋላም ስለመምጫቸው ተነጋግረን ንዋያተ ቅዱሳት (ጽናጽልና መቋሚያ ) እንዲሁን ጽላትም ጭምር እንደሌለንስነግራቸው፤ ሁሉንም ማግኘት እንደሚችሉ፤ ነገር ግን ተጨማሪ 1000 ዶላር እንደሚያስፈልግ ነገሩኝ። ያንንምቦርዱን አስፈቅጀ ላኩላቸው። መስከረም 1993 እ.ኤ.አ. 12 ጸናጽል፣ 12 መቋሚያና ጽላት ይዘውልን ሎሳንጀለስገቡ። እኛም አባት ናፍቆን ስለነበረ ምንም እንኳን ያወጣነው ወጭ ብዙ ቢሆንም በደስታ ተቀበልናቸው።ስላሁሰንና ዌስት (between Slauson and West) ላይ አንድ የአድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ተከራይትንአገልግሎት ማግኘት ጀመርን።
ትንሽ ቆይቶም አባ ተከስተ የሚባሉ መነኩሴ (የዛሬው ብጹእ አቡነ ሣᎀኤል) ወደዚህ እነደሚመጡ ተነገረንናእኔው ተቀብዬ አብረው መኖር ጀመሩ። የሚገርመው ግን አባ ሰረቀ ከሰው ጋር ተስማምቶ መኖርን ስለማይፈልጉ፤አባ ተከስተ ጋር አለመግባባት ፈጠሩና አባ ተክስተ ወደ ሌላ ስቴት ሄዱ።
ከዚያም እርሳቸውም ብቻቸውን እንዳይሆኑ በማለት “ሳንሆዜ የነበረ አንድ ይሥሐቅ የሚባል አገልጋይልናመጣልዎት ነበር” ብንላቸው ያሉንን እስከ አሁን አስታውሰዋለሁ ‹‹እኔ ቤት አንድ ሰው አይገባም›› ነበር በወቅቱ ያሉት። ያን ጊዜ ነበር አባ ሰረቀ ላይ የነበረው እምነታችን እየተሸራረፈ የመጣው። እንደምንምአግባብተን ልጁን ብናመጣውም አሁንም እርሱም የአባ ተክስተ እጣ ደርሶት አባረሩትና ሄደብን።
መቼም የኛ ቤተክርስቲያን ታሪካዊ ነችና ከአሪዞና አባ ወልደ ሰንበት የሚባሉ አንድ መነኩሴ ደግሞአስመጣንላቸው። ለካስ ሁለቱም መሰሪ ነበሩና የሚከተለውን ምእመናን የማይረሱትን አሳዛኝ ሥራ ሰሩ።
‹‹ቀኑ እሁድ ነው አስታውሳለሁ ፤ አባ ስረቀና አባ ወልደ ሰንበት ቅዳሴ ቀድሰው ሲያበቁ አባ ሰረቀ ለእኔናለጓደኞቸ “አባ ወልደ ሰንበት ወንድሙ ስላረፈ ልናረዳው ነው ምን ትላላችሁ” አሉ። እኛም አዝነንአሁን ቅዳሴ ቀድሰው ከምንነግራቸው ለምን ሳምንት ወይንም ነገ አንነግራቸውም አልናቸው።እርሳቸውም እሺ ብለው እኛን ከላኩ በኋላ ረድተዋቸው ነበርና ወዲያው ደውለው አርድቻቸዋለሁና ኑተባልን በጣም ሁላችንም ተመልሰን መጣን ። እውነት መስሎን በጣም አዝነን አባ ወልደ ሰንበትንምአጽናንተን ተመለስን። ከዚያም ወደ ሀገራቸ መመልስ እንደሚፈልጉ አባ ሰረቀ ነገሩን እኛም አዝነን ያለንንአዋጥተን ላክናቸው። ትዝ የሚለኝ ለቤተሰቦቻቸውም አምነዋቸው ብር አድርሱልንም ያሉ ሰዎች ነበሩ።ግን አባ ወልደ ሰንበት ሳያደርሱላቸው ብራቸውን በዚያው በልተው ቀርተዋል።
ከትንሽ ጊዜ ቆይታ በኋላ የአባ ወለደ ሰንበትን እህት ወይዘሮ አብርኸትን የሚያውቅ አንድ የቤተክርስቲያናችነ አባል፤ አዲስ አበባ ሄዶ ወይዘሮ አብርኸትን ያገኝና ‹‹እባክሽ የወንድማችሁን መሞትሰምተን እኮ አባን አጽናናቸው ቢሏት›› የምን ወንድም ነው የምታወራው? ትለዋለች። ለካስ አባ ወልደሰንበት ወድማቸው ሞተ ትብሎ የተነገረው የውሸት ኑሯል። አባ ሰረቀና እርሳቸው የፈጠሩት ውሸት መሆኑን አወቅን። ከዚያ በኋላ ይኸው አባ ወልደ ሰንበት በወቅቱ ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ እንደዘገበውበወቅቱ የአሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት አቡነ ማትያስ ማኅተም ወስደው በነጭ ወረቀት ላይ እያተሙ የኔንፊርማ እያስቀመጡ ሰዎችን ብር እየተቀበሉ ከኢትዮጵያ ወደዚህ ሲያመጡ ተደርሶባቸው መጀመርያ ወደጀርመን አሁን ደግሞ መቼም ጅብ በማያውቁት ሀገር እንደሚባለው በገለልትኞች ሲኖዶስ ጳጳስ ሆነውካናዳ ይኖራሉ።
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ፤ አባ ሰረቀ አባ ወልደ ሰንበትን እንዲህ አድርገው ከአጠገባቸው ካራቁ በኋላከቤተ ክርስቲያን አባልት ጋር መግባባት አልቻሉም። ከእለታት አንድ ቀን እንደውም ‹‹ቤተክርስቲያን የለችም ፤አቡነ አረጋዊም የሚባል ቤተክርስቲያን የለም ፤›› በማለት ሲስብኩ አስታውሳለሁ። ይህ በእምነታችን የሌለኑፋቄ ነው። ከዚያም በኋላ ከቤተክርስቲያናችን ተለይተው ‹‹የአቡነ ጳውሎስ እንደራሴ ነኝ ፤ እኔ ማንንምመነኩሴ ጳጳስ እንዲሆን አስደርጋለሁ›› ከሚለውና እዚሁ ሎሳንጀለስ ከሚኖረው ቄስ ጋር ገጠሙና ከእኛ ጋርመጣላት ጀመሩ። ከዚያም አቡነ ማትያስ ለጥቅምት አቡነ አረጋዊ ሲመጡ ምእመናን ክስ አቀረቡ። ውይይቱየተደረገው በወዳጃችን በ አቶ ዕቁበ ጽዮን ቤት ነበር። ብጹእ አባታችንም ቢመክሩዋቸው አልሰማ አሉ። አባሰረቀንም ብጹእ አቡነ ማትያስ ምእመናኑ ምንም አልበደሉምና ‹‹ተሳስባችሁ አብራችሁ ኑሩ›› ቢሉዋቸው አባሰረቀ ‹‹ከአሁን በኋላ እዚህ አላገለግልም›› ብለው ካበቁ በኋላ ትንሽ ቆይተው ለአቡነ ማትያስ “ብርሌ ከነቃ…”የሚል መልስ ሰጧቸው።
ብጹእ አቡነ ማቲያስም ‹‹እንግዲያውስ እናንተም ሌላ ካህን ፈልጉ እርሳቸውንም መጓጓዣ ከፍላችሁ ላኳቸው ፤እርሳቸውም ንዋያተ ቅዱሳቱን ፤ ታቦቱን ጭምር ያስረክቧችሁ›› ተባለ (ይህንንም በዚያን ጊዜ አባ ኢሳይያስ-የሳንዲያጎ ገብርኤል አስተዳዳሪ የነበሩ- የአሁኑ ብጹእ አቡነ ኢሳይያስ ያረካክቡዋችሁ ተባለ)። እኛም አዝነን እሺብለን 700 ዶላር ከምዕመናን ሰበሰብንና ዶ/ር ኃይሉ ፤ አቶ ጥላሁንና አንድ ሌላ ሰው ወክለን አባ ኢሳይያስንይዘው እንዲረከቡ ላክናቸው።
ከዚያም አባ ሰረቀ በለመዱት አንደበታቸው የተወከሉ ምእመናንን ታቦቱን ነው የያዝኩት ብለው ብሪፍ ኬዝይዘው መጡና ፤ ይህንን ለመነኩሴው ለአባ ኢሳይያስ ብቻ ነው የማስረክበው በማለት ወደ ውስጥ ሁለቱ ብቻገቡ። ብዙ ቆይተው ሲወጡ አባ ኢሳይያስን የተወከሉት ሰዎች ‹‹ታቦቱን ተረከቡ ወይ?›› ሲሉዋቸው “ታቦትተረከብኩም አልተረከብኩም አይባልም” አሏቸው።
ተወካዮችም ግራ ግብቷቸው ሲመለሱ አባ ኢሳይያስም ፤ ለብጹእ አቡነ ማቲያስ ደውለው ታቦቱን እንዳልተረከቡእንደውም ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ አባ ሰረቀ ብሪፍ ኬዙን ሳይከፍቱ ይረከቡ ይሏቸዋል። አባ ኢሳይያስም‹‹ይክፈቱት እንጂ እንዴት ዝም ብዬ እረከባለሁ›› ይሉና ተቀብለው ቢከፍቱት የተገኘው ታቦት ሳይሆን መጽሐፍቅዱስ እንደሆነ፤ ከዚያም አባ ሰረቀ እግራቸው ላይ ወድቀው ‹‹እባክዎን አልተቀበልኩም ብለው ለተወካዮችአይንገሩብኝ ፤ ታቦቱን ዲሲ ልኬዋለሁ እዚያ ሄጄ ለአቡነ ማትያስ እሰጣለሁ ወይንም እልከዋለሁ››ብለዋል ይሏቸዋል።
ይህንን ነገር አቡነ ማቲያስ ሲሰሙ በጣም አዝነውና ተናድደው ነገሩን ምእመናን እንዲሰሙ ያደርጋሉ። ሁለቱምአባቶች (አቡነ ማቲያስና አቡነ ኢሳይያስ በሕይዎት ስላሉ ህያው ምሥክር ናቸውና ስለ እውነትነቱ እነሱውሊጠየቁ ይችላሉ።) ከገዛናቸው 12 ጸናጽል ያስረከቡን ስድስቱን ሲሆን ፤ ከ 12ቱ መቁዋሚያም 6ቱን ይዘውብንሄደዋል። ምእመናንም በዚህ ተናድደን ያዋጣነውን ገንዝብ ሳንሰጣቸው ቀርተናል። ከሁሉ የሚገርመኝ ሲሄዱአንዲት ምዕመን ለቤተ ክርስቲያን የሰጠችውን ሰንና ብርን ይስጡን ብለን ስንጠይቃቸው ፤ ‹‹መልሳወስዳዋለች›› አሉን። ይህ ሁሉ እንግዲህ በሎሳንጀለስ የነበራቸው ታሪክ ነው።
አንድ መነኩሴ ከሰረቀ ፤ ከዋሸ ፤ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ስልጣን ፤ ገንዝብና ፤ ክብርን ከፈለገ እንዴት መነኩሴይሆናል። በአሁኑ ሰዓት የሚያደርጉት ብጥብጣ እኔ ከአባ ሰረቀ የማልጠብቀው አይደለም። እርሳቸው፤ ከሰው ጋርተስማምተው የማይሰሩ ፣ የሚዋሹና ፤ በሃሰት ማንኛውንም ኃጢያት ሁሉ ሊሰሩ የሚችሉ ሰው ናቸው። ለዚህደግሞ አቡነ ማቲያስ ቀድሞ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ አሁን 6ተኛው ፓትርያርክ ፣ አቡነ ሣሙኤል፤ አቡነ ኢሳይያስህያው ምስክሮች ናቸውና ፡፡ እነሱን በመጠየቅ ወይንም ለእኔም በመደወል የበለጠ መረጃ ማግኝት ይቻላልብለውናል።
በአጠቃላይ አባ ሰረቀ ማለት ለእምነታቸው ሳይሆን ለሆዳቸውና ለገንዘብ የሚኖሩ ፤ ካለ ፍርኃት የሚዋሹ ፤ ካለ ሃፍረት የሚሰርቁ ፤ ከሰው ጋር ተባብረውና ተግባብተው መኖርን የማያውቁ ሰው ናቸው።
እርሳቸው ከሄዱ በኋላ ስድስት ወራት ሙሉ ካለ ካህን እሁድ እሁድ ምእመናን ብቻችንን ተሰብስበን አቶ እቁባይመጽሐፍ ቅዱስ እያነበቡልን እንበተን ነበር። በኋላ ይኼው እስከ አሁን የሚያገለግሉንን ታላቅ አባቶች አግኝተንእንገለገላለን፡፡ እንደውም ባለፈው ዓመት ቤተ ክርስቲያን ገዝተን ገብተናል። በአሁኑ ሰዓትም ከልብ የሚያገለግሉካህናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት አባላትና ታላላቅ ም ምእመናን ያላት ቤት ክርስቲያን በማግኘታችን ደስትኞችነን። በማለት አባ ሰረቀ ቤተክርስቲያን ላይ ያደረሱትን በደል ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ አቅርበውልናል፡፡
እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን
ምንጭ: አንድ አድርገን
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
No comments:
Post a Comment