Thursday, October 16, 2014

በመጭው ሰንበት/እሁዶች አዲስ አበባ ማህበረ ቅዱሳንን በመደገፍ ታላቅ እና ደማቅ የአጋርነት ንቅናቄ ሊደረግ ነው ማህበረ ቅዱሳንን በመደገፍ ታላቅ እና ደማቅ የአጋርነት ንቅናቄ ሊደረግ ነው።



ንቅናቄው በጩሐት ሳይሆን ብልሃት እና ብስለት የተሞላበት መሆኑ ታውቋል።
የኢሕአዴግ መንግስት እና በቤተክህነት ውስጥ የተሰገሰጉ ካድሬዎች የተዋህዶ እምነትን የፖለቲካ አሽከር ለማድረግ የጀመሩትን ሴራ እና በማህበረ ቅዱሳን ላይ የተሰነዘረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በመቃወም በድምጻችን ይሰማ ዘኦርቶዶክስ እና በእኔም ለእምነቴ በብስለት እና ብልሃት በተሞላበት ሁኔታ በጋራ የተዘጋጀ ታላቅ እና ደማቅ የአጋርነት ንቅናቄ ማህበረ ቅዱሳንን በመደገፍ ሊካሄድ እንደሆነ እና ምእመናን ለዚሁ ንቅናቄ እንዲዘጋጁ ጥሪው ተላልፏል።
===============================
የመጀመሪያው ዙር ዝርዝር መግለጫ እንደሚከተለው ነው።
ለማኅበረ ቅዱሳን እመሰክራለው :: ለቀጣዩ የአደባባይ ምስክርነት በተጠንቀቅ እንዘጋጅ።
ምእመናን ምን ማድረግ እንዳለብን በቀጣይ ቀናት የሚገለፅ ይሆናል፡፡

††† #ድምጻችንይሰማዘኦርቶዶክስ - #እኔም_ለእምነቴ ! ††† የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆነ እና ስለማኅበረቅዱሳን በጎ ሥራ ለመመስከር እንዲቻል ይህ መልዕክት ለሁልም ማዳረስ ሐይማኖታዊ ግዴታችን ነው ፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !
እኔም ለእምነቴ የማህበራዊ ድረ ገፅ ተጠቃሚ ምንጮቻችን መሰረት፤ በማኅበረቅዱሳን ላይ አሁን እየተፈፀመ ያለው የስም ማጥፋት እና ውግዘት፤ ገና ከጥንስሱ ከማንም በፊት መረጃው ለሁሉም እንዲደር ጥረት ተደርጓል፡፡

ይሁን እንጂ ያስተላለፍ ነው መልዕክት ከቁምነገር ሳይቆጠር አብዛኛው ሰው ጉዳዩን በቸልታ አልፏታል፡፡ ሆኖም ግን በእኔም ለእምነቴ መረጃው ከተላለፈ 1 ቀን በኋላ ሪፖርተር ጋዜጣ በጉዳይ ዙሪያ ሰፊ ዘገባ ይዞ ወጥቷአል፤ ከዚያ ቀን ጀምሮ እስካሁን ስለማኅበረ ቅዱሳን መልካም የሆነ ነገር እየተሳማ አይደለም፡፡



የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ አሁን ላይ ከጫፍ የደረሰ አሳሳቢ የቤተክርስቲያናችን ጭንቀት ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ/ እጅግ በጣም ለቁጥር የሚታክት መንፈሳዊ አገልግሎት የሰጠ እና እየሰጠ የሚገኝ መኅበር ነው፡፡

ይሁንእንጂ ጥቅምት፯ቀን፳፻፯ዓ.. በጠቅላይ ቤተክህነት የስብሰባ አዳራሽ በተጀመረው ፴፫ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ላይ የጉባኤ መክፈቻ ቃለ በረከት እንዲሰጡ የተጋበዙት ፓትርያርክ አባማትያስ፣ ማኅበረቅዱሳንን ‹‹የቤተ ክርስቲያን ቅኝገዥ›› ነው ‹‹እኔ ብቻዬን የምሠራው ነገር የለም፤ በዚኽ መግለጫ እንድትሠሩበት ነው የምነግራችኹ፤ አባ ማትያስ አላበደም፤ መልእክቴን እያስተላለፍኹ ነው ያለኹት፤መልእክቴን ተቀበሉ ብዬ እማፀናችኋለኹ፡፡››አስከትለውም ‹‹ቤተክርስቲያን ከቅኝ ተገዥነት ትውጣ፤ ካህናቱ ከመከራ ይውጡ›› በማለት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የመጨረሻ አስደንጋጭ እና አሳዛኝ ትዕዛዘቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመሆኑም የፊታችን እሁድ ጥቅምት 9 ቀን 2007 ዓም በቅድስትሥላሴ ካቴድራል ቤተ/ዝክረ አቦ ሊቀነጳጳሳትመንፈሳዊ መራሃ-ግብር ይካሄዳል፡፡ በዕለቱም የአባጳውሎስ የሐውልት ምረቃ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ነገር ግን የዚህ መረሃ-ግብር ዋንኛ ዓላማ ቀደምት ቅዱስ ጳጳሳት እና ብፁዓንሊቃነጳጳሳትን በሥጋሞት የተለዩትን በማስብ የፀሎት እና የፍትሐት ስነ-ስርዓት ይደረጋል፡፡

ይህም የሚሆነው የቅ/ሲኖዶሱ ዓመታዊ ስብሰባ ከመካሄዱ የመጀመሪያው እሁድ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ መንፈሳዊ መረሃ-ግብር 1998 . ጀምሮ እየተካሄድ የሚገኝ ነው፡፡
ስለዚህም የፊታችን እሁድ ጥቅምት 9 ቀን 2007 ዓም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ/ ከሥርዓተ ቅዳሴ በኋላ፤ ፓትርያርክ አባ ማትያስ፣ በአገር ውስጥ እና በውጪ የሚገኙ በሙሉ ብፁዓን ሊቃነጳጳት፣ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ገዳማትና አድብራት አስተዳደሪዎች እና ፀሐፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የውጪሀገር ብፁዓን ሊቃነጳጳሳት በሚገኙበት ታላቅ መንፈሣዊ ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡

በዕለቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆነ ሁሉ በመረሃ-ግብሩ የመሣተፍ ሓይማኖታዊ ምግባር ነው፡፡ በዚህ ታላቅ ሐይማኖታዊ መረሃ-ግብር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ በሙሉ መገኘት አለብን፡፡ በዕለቱም ስለማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት 17 ዓመታት ማኅበሩ በቤተክርስቲያናችን የሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት እንጂ ‹‹የቤተክርስቲያን ቅኝ ገዥ›› አለመሆኑ የምንመሰክርበት መልካም አጋጣሚ ነው፡፡

በዕለቱም ምእመናን ምን ማድረግ እንዳለብን በቀጣይ ቀናት የሚገለፅ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ የሆነ እና ስለማኅበረቅዱሳን በጎ ሥራ ለመመስከር እንዲቻል ይህ መልዕክት ለሁልም ማዳረስ ሐይማኖታዊ ግዴታችን ነው ፡፡


ወስብህትለእግዚአብሔር !!!

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

2 comments:

  1. እኔ ይሄንን እቃወማለሁ፡፡ የማኅበሩ ሀሳብ ነው ብየም አላምንም፡፡ መቅደም ያለበትን (ጾም፣ ጸሎት…) ሳያቀድሙና ሌሎች መንፈሳዊ መፍትሔዎችን ሳይወስዱ ለተቃሞ ሰልፍ መውጣት የኦርቶዶክሳውያን መገለጫም አይደለም፡፡ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የመረጋትና የትዕግሥት ሃይማኖት ናት፡፡ በክርስትና ሲኖሩም ከፈተና የጸዳ ሕይወት እንደሌለ ተማርን እንጂ ፈተና ሲገጥምህ/ሲፀናብህ ተቃወም፣ ተሰለፍ፣ የዓለምን መፍትሄ ውሰድ የሚል አስተምህሮ አልሰማሁም፡፡ ለማኅበሩ ያለንን አጋርነትም ማኅበሩ በሚያከናውናቸው አገልግሎቶች ሁሉ ተግባራዊ እገዛና ድጋፍ በማድረግ እንጂ በሰልፍ መሆን አለበት ብዬ አላምንም፡፡ ሁሉም በተረጋጋ መንፈስና በትዕግሥት ይሁን፡፡ የእግዚአብሔር እንጅ የሰው ድጋፍ የትም አያደርስም፤ የእግዚአብሔር እንጅ የሰው ተቃውሞም ምንም ዓይነት ውጤት አይኖረውምና ዓለማዊ መፍትሄ ከመውሰድ እንቆጠብ….

    ReplyDelete
  2. አደራ እባካችሁ ማህበረ ቅዱሳንን ደገፍን ብለን ቅዱሳን አባቶችን ወደመዝለፍ፣ እንድናመራ የሚያደርግ አካሔድን አታበረታቱ፣ ለህዝበ ክርስትያኑ ቅዱሳን አባቶችም/ ሲኖዶሱም፣ ማህበረቅዱሳንም ያስፈልጉናል፡፡ በተቻለ መጠን ችግሮቻቸውን በምክክር ፈትተው በጋራ የሚሰሩበትን እንጂ አቧራ የሚነሳበትን ፣ የሚወጋገዙበትን አካሄድ አትከተሉ፡፡

    ReplyDelete