Tuesday, May 14, 2013

ስመ ‹‹መቲራ››ው ሲመተር! ቀንደኛው ፅልመታዊና ሙሰኛ ‹‹አባ›› ገ/መድኅን ገ/ጊዮርጊስ ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ እንዳይገቡ ታገዱ!


  • ጀብደኛው ሙሰኛ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በመንበረ ፓትርያሪኩ አሠራር ጣልቃ በመግባት፣ ከሥ ሓላፊዎችና ከጥበቃ አባላት ጋራ ሁከት በመፍጠር አቤቱታ ቀርቦባቸዋል
  • Abba Gebre Medhin banned
  • ከምስጉን አቋማቸው በመንሸራተት ከሙሰኞች ጋራ መተቃቀፍ የጀመሩት አቡ ሕዝቅኤል በሙሰኛው ‹‹መነኩሴ›› ላይ የተላለፈውን እግድ በጣልቃ ገብነት መቃወማቸው አስገራሚ ኾኗል


  • ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤና በክልል ትግራይ ስድስት አህጉረ ስብከት በሕገ ወጥነት ከተፈረጀው ‹‹አቡነ ሰላማ ምትሕግጋዝ ማኅበር›› የተባለ የጥፋት ቡድን ጋራ በመቀናጀት÷ የኑፋቄ ትምህርት ሲያሰራጩ፣ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ካህናቱና ምእመናኑ መካከል ሰላም አደፍራሽ ቅስቀሳ ሲያካሂዱ፣ የጥንታውያን አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችን በጥቅም በመደለል ቅርሶችን ለባዕዳን አሳልፈው ለመስጠት ሲሰናዱ የነበሩ ናቸው፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ገዳማት መምሪያ ዋና ሓላፊ ለመኾን እየተፍጨረጨሩ ያሉትም ይህን ተልእኳቸውን በማሳካት ሕገ ወጥ ጥቅም ለማካበት ነው!!
  • ከፕትርክና ምርጫው በፊት በነበረው የሽግግር ወቅት የዐቃቤ መንበሩን ቲተር በመያዝ በርካታ ሕገ ወጥ ደብዳቤዎችን አዘጋጅተዋል፤ በዚህ አጋጣሚ ጀብደኛው ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ዐቃቤ መንበሩን በመደለል ባጻፉት አሠራሩን የጣሰ ሕገ ወጥ የቅጥር ደብዳቤ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ገዳማት መመሪያ ዋና ሓላፊ ኾነው ለመሾም ያደረጉት ሙከራ በማኔጅመንት ኮሚቴው ውድቅ ተደርጎባቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ‹‹መነኩሴ›› ነኝ ባዩ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን የማኔጅመንት ኮሚቴውን አባላት ስም በማጥፋት ከመጠመዳቸውም በላይ ዋና ሥራ አስኪያጁን ብፁዕ አቡነ ፊልጶስን በተደጋጋሚ ዘልፈዋቸዋል
  • ኪራይ ሰብሳቢው ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በምሥራቅ ትግራይ – ዓዲ ግራት ሀ/ስብከት በሚገኘው ለሀ/ስብከቱ በማይታዘዙበት የደብረ ዐላማ ኢሲራ መቲራ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም በሰበሰቧቸው ትጉሃን መነኰሳትና አሳድጋቸዋለኹ በሚሏቸው ምስኪን ጓለ ሙታን ሰበብ÷ ከዩኔስኮ፣ ዩኒሴፍ እና ሌሎች በጎ አድራጊዎች ያገኙትን ርዳታ ለግል ጥቅማቸው በማዋል በስማቸው የሸመቷቸውን ኮድ – 05 ላንድ ክሩዘር እና ዶልፊን ሞዴል መኪኖች በአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች ያሽከረክራሉ፤ በአምባሳደር ሕንፃ የመንግሥት አፓርታማ ቤት ቁልፍም በብር 350,000 እጅ መንሻ ገዝተዋል፤ በሲ.ኤም.ሲ ቪላ ቤት መሥራታቸውም ይነገርላቸዋል!!
  • በሀ/ስብከታቸው መዋቅር የማይታዘዝ ገዳም አበምኔት ነኝ የሚሉት ነውጠኛው ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በሀ/ስብከታቸው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ላይ ሽጉጥ በመምዘዝ ፍላጎታቸውን በጉልበት ለማስፈጸም እስከ መሞከር ደርሰዋል!!
  • ርካሽ ተወዳጅነት ለማግኘት በማሰብ በአዲሱ ፓትርያሪ  በዓለ ሢመት ወቅት ያለፓትርያሪኩ ፈቃድ በብር ኀምሳ ሺሕ ወጪ አሠርተው ያሰራጩት ፖስተር በፓትርያሪኩ ትእዛዝ ከመንበረ ፓትርያሪኩ ቅጽር እንዲወገድ ተደርጓል
  • ጎጠኛው ሙሰኛ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን የንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ እና አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ጉዳይ አስፈጻሚ በመኾን በከፍተኛ የፖሊቲካና የደኅንነት ባለሥልጣናት ስም መነገዳቸውንና ማስፈራራታቸውን ቀጥለዋል፡፡ በስማቸው ከሚነግዱባቸው ባለሥልጣናት መካከል÷ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕርግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ሥዩም መስፍን እና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ም/ሥራ አስኪያጅ አቶ ኢሳይያስ ወልደ ጊዮርጊስ ይገኙባቸዋል፡፡
  • መነኵሴ ነኝ ባዩ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን÷ የቅዱሳን አበውን አርዑተ ምንኵስና በመናቅና ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ካህናት አለባበስና ገዳማውያን ሥርዐት ያስተላለፈውን መመሪያ በመጣስ በዋና ዋና ከተሞች በተለይም በመዲናይቱ አዲስ አበባ ለመነኰሳት በማይገቡ ሕገ ወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ምንኵስናንና ኦርቶዶክሳዊነትን በአጠቃላይ የሚያስነቅፉ በርካታ ስመ መነኰሳት ምሳሌ ናቸው፡፡
  • ‹‹አባ›› ነኝ ባዩ ገብረ መድኅን በመቐለ ከሁለት ሴቶች የወለዷቸውን ልጆች ሜዳ ላይ በትነው በአዲስ አበባ የተለያዩ ሴቶችን /ዝሙት አዳሪዎችንና መሰል መነኰሳዪያትን ጨምሮ/ በሕገ ወጥ መንገድ ባካበቱት ገንዘብ እየደለሉ ይማግጣሉ፡፡ ከመሰል ድሉል ስመ መነኰሳዪያቱ መካከል÷ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎጎች የሚያቀብሉትን መረጃ በማሾለክ የምትተባበር አንዲት የፓትርያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት መዝገብ ሠራተኛ እንደምትገኝበት ተጠቁሟል፡፡ ምንኩስናው ይቅርና ‹‹አባ›› ነኝ ባዩ ግለሰ በአሁኑ ወቅት ከኤች.አይ.ቪ ጋራ የሚኖሩና የመድኃኒት ተጠቃሚ መኾናቸውን እያወቁ ከሴሰኛ ተግባራቸው አለመቆጠባቸው ፍጹም ሓላፊነት የማይሰማቸው፣ ለአንዳችም ሓላፊነት የማይበቁ መኾናቸውን ያረጋግጣል!!

የዜናው ዝርዝር ከአባሪ ማስረጃዎች ጋራ ይቀጥላል፡፡

የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment