Friday, May 31, 2013

ጀብራሬው ‹‹ኢህአዴግ›› በአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ላይ


የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ሲነሳ

(አንድ አድርገን ግንቦት 23 2005 ዓ.ም)፡- ‹‹ ከምሽቱ 1፤30 ላይ አንድ ሞቅ ያለው የተበሳጨ ጀብራሬ አቡነ ጴጥሮስ  ሃውልት ላይ ሽንቱን እየሸና  ‹አንተ ድንጋይ ጓደኞችህ  ተመችቷቸው በማርቼዲስ ሲንሸራሸሩ ይህው አንተ ድንጋይ ሆነህ ቀረህ ድንጋይ አሸናብሃለሁ › ሲል በልጅነት ደም ፍላት  ዘልዬ  ከጀብራሬው ጋር ግብ ግብ ገጠምኩኝ ፡፡ ድንጋይ አይደለም፡  ‹ድንጋይ ነው› በሚል በቡጢም  ተቃመስን ፡፡ ከስብሰባው የተበተኑ ሰራተኞች ገላገሉንና እየተበሳጨሁ ቤቴ ገባሁ፡፡ ሌሊቱን አልተኛሁም፡፡ ጴጥሮስ ሕያው ነህ ለማለት ፤ ጴጥሮስ ድንጋይ አይደለም ለማለት ይመስለኛል ‹ጴጥሮስ ያችን ሰዓት› ስጭር አደርኩ ›› ጸጋዬ ገብረ መድህን

ሃሙስ ሚያዚያ 24 ቀን 2004 ዓ.ም  ጠዋት ሳተና የሆኑ ወጣቶችና ጎልማሶች የአቡነ ጴጥሮስን ሃውልት ልክ እንደ አስቸጋሪ ኮርማ በገመድ ጠልፈው አንዳች የሚያህል ክሬነር አስረው ከነበረበት ለመንቀል ደፋ ቀና ይላሉ፡፡
አላፊ  አግዳሚው ወጪ ወራጁ እንደ ዘበት እያየ ያልፋል፡፡ ከፊሉም ሞባይሉን አውጥቶ ፎቶ ሊያነሳ እና ሊቀርጽ ይሞክራል፡፡ ‹‹የሰውየው›› (ሁነኛ ሰው) ሃውልት (የእኛ የእውነተኝነት) ዋቢ ከውስጥ በአቡጀዲ ተጠቅልሎ ፤ ከውጭ በጣውላ ተጠፍንጎ ፤ በብረት ዘንግ ተደግፎ ሊነቀል ትዕዛዝ ይጠብቃል፡፡
 

ቅ/ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያን ስልታዊ ዕቅድ ላይ ይወያያል


  • ምልአተ ጉባኤው 18 የመነጋገሪያ አጀንዳዎችን ለይቶ ውይይቱን ቀጥሏል
ምልአተ ጉባኤው በዋናነት ከሚነጋገርባቸው ጉዳዮች ውስጥ፡-
  • ቤተ ክርስቲያኒቱ በመሪ ዕቅድ መመራት እንዳለባት የታመነበት በመኾኑ መሪ ዕቅዱ ‹‹ተዘጋጅቶ ሲቀርብ›› ተመርምሮ ውሳኔ ይሰጥበታል፡፡
  • የሕገ ቤተ ክርስቲያን እና ቃለ ዐዋዲ ማሻሻያ ረቂቆች በኮሚቴው ቀርበውና ተደምጠው ተጨማሪ ሐሳብ ይሰጥባቸዋል፤
  • በቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደርና ሙስና ችግሮች ላይ ‹‹መጠነ ሰፊ›› ውይይት ተደርጎ ውሳኔ  ይተላለፋ በጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያዎችና ድርጅቶች፣ በሁሉም አህጉረ ስብከት መዋቅሮች ሙስናን የመከላከያውና መቆጣጠርያው አግባብ ከሚያሰፍነው ጥብቅ ሥርዐት አንጻር አጀንዳው አነጋጋሪና አከራካሪ እንደሚኾን ይገመታል፡
  • የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የጠ/ቤ/ክህነት ዋና ሥ/አስኪያጅ ምርጫ ይካሄዳል በቂ የሰው ኀይልና በበጀት ተደግፎ በሦስት ዴስኮች እንዲደራጅና የራሱ ወርኃዊ መጽሔት እንዲኖረው የተወሰነለት የውጭ ግንኙነት መምሪያ አዲስ ሓላፊና ሊቀ ጳጳስ ይሾምለታል፤ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የቅድሚያ ግምት የተሰጣቸው ቢኾንም ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስና ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ይጠበቃሉ፤

Thursday, May 30, 2013

የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተጀመረ፤ ‹‹ሙስና ቤተ ክህነት››ን ያጠፋሉ የተባሉ የእርምት ርምጃዎች ይፋ ተደረጉ

  • ሙሰኛ እንክርዳድ ሁሉ በፀረ – ሙስና ዐቢይ ኮሚቴ ተለይቶ ሕጋዊ ርምጃ ይወሰድበታል!
  • የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር፣ ሕግና ደንብ በውጤት ተኮር ማሻሻያ ይዘጋጃል
  • ከመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ እስከ አጥቢያ የፋይናንስ ሥርዐቱ በዘመናዊ አሠራር ይደራጃል
  • የቤተ ክርስቲያንን ርእይና ተልእኮ የሚያሳይ የስትራተጂያዊ አመራር ሥርዐት ይነደፋል
  • በሁሉም የለውጥ ርምጃዎች የባለሞያ ምእመናን ተሳትፎ ይረጋገጣል
  • በእግዚአብሔር፣ በታሪክና በትውልድ ፊት ለሚመዘነው የለውጥ ርምጃ በጋራ እንነሣ!
  • ‹‹በዚህ ትልቅ የሓላፊነት ወንበር ላይ ስታስቀምጡኝ÷ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ፣ የምእመናንን የልብ ትርታ እያዳመጥኹ ለእናንተ ለብፁዓን አባቶች ሳቀርብ ይኹንታውንና እገዛውን እየለገሣችኹኝ የጋራ ሓላፊነታችንን እንድንወጣ መኾን አለበት፡፡››/የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ንግግር/
ቢሮክራሲው በእጅጉ በተንዛዛውና ከሚያስፈልገው በላይ የሠራተኛ ቁጥር በተሸከመው÷ ለመንፈሳዊነት፣ ሞያና ልምድ ቦታ በማይሰጠው÷ የሰው ኀይል አመዳደቡም ከመሠረታዊ ተልእኮው ጋራ ባልተቀናጀው፣ ከዚህም የተነሣ ሙስናና ወገንተኝነት በሰፈነበት የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ላይ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሊወሰድ የሚገባውን የእርምት ርምጃ የሚያመላክቱ ሦስት የይኹንታ ሐሳቦችበዛሬው ዕለት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ ይፋ ተደርገዋል፡፡
Abune Matyas Looking Forward
ወደፊት፤ በእግዚአብሔር፣ በታሪክና በትውልድ ፊት ለሚመዘነው የለውጥ ርምጃ!
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ዛሬ ጥዋት የተጀመረው የርክበ ካህናት ቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ትኩረት ሊሰጥባቸው ይገባል ባሏቸው መሠረታዊ የለውጥ ርምጃ ይኹንታቸው እንደገለጹት÷ በቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር የሚታየው የሥነ ምግባር ብልሹ አሠራር ከቤተ ክርስቲያን ክብርና ቅድስና ጋራ የማይጣጣም ነው፤ በምእመናን ላይ ባሳደረው ከፍተኛ ቅሬታ ምእመናኑ በቤተ ክርስቲያን አመራር ላይ ያላቸውን እምነት እያሳጣ ነው፤ አሳፋሪውና አሳዛኙ ብልሹ አሠራር ሥር ከመስደዱ የተነሣ ሳይታረም ቢቀጥል ቤተ ክርስቲያኒቱን ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚጥል በግልጽ እየታየ ነው፡፡
ብልሹ አሠራሩን ለማረምና ለማስወገድ፣ አስተዳደሩን በአዲስ መልክ ለማዋቀርና የፋይናንስ አያያዝና አጠቃቀሙን ግልጽ በኾነና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ለማደራጀት የሚወሰደው የእርምት ርምጃ÷ የቤተ ክርስቲያንን ስምና ክብር በማስጠበቅ ቤተ ክርስቲያንን የሚታደግ፣ ካህናትና ምእመናን የተባበሩበትና ተሳትፎቸው የተረጋገጠበት፣ አመራሩንም ከታሪክ ፍርድና ወቀሳ የሚያድን ሊኾን ይገባል፡፡
የፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ የመሠረታዊ ለውጥ ርምጃ ይኹንታዎች፡-

Friday, May 24, 2013

ኦርቶዶክሳዊ መምህር


ከታምራት ፍሰሐ
"በሃይማኖት ብርኖሩ፥ እራሳችሁን መርምሩ" ፪ኛ ቆሮ. ፲፫ ፥ ፭

ይድረስ ኦርቶዶክሳዊ ምላሽ አዘጋጅተው በልዩ ልዩ መንገድ ለህዝብ ለሚያደርሱ ኦርቶዶክሳውያን መምህራን

         ብዙወች መምህራን ተብለው ይጠሩ ዘንድ ይሾማሉ፡ አንዳንዶቹ ስለመልካም ግብር አንዳንዶቹም ስለዋዛ ፈዛዛ ብዙወች መምህራን ተብለው እንዲያስተምሩ ወደ ምእመናን ይላካሉ ፡አንዳንዶቹ ከመንፈስ ቅዱስ አንዳንዶቹ ከዲያቢሎስ አንዳንዶቹ መምህራን ከማስተማራቸው አስቀድመው ለራሳቸው ጥበብን ይማሯታል፡ ይተረጉሟታል ይኖሯታል አንዳንዶች ግን ያልገባቸውን ጥበብ ለሌሎች ሊያስረዱ ይደክማሉ፡፡

በምዕራብ አ/አ ሀ/ስብከት ‹ያልጠለቀችው› የሙስናና የጎጠኝነት ጀንበር ‹እየቀላች› ነው


  • በሀ/ስብከቱ የአቡነ ሕዝቅኤል አስተዳደር ሙስናና ጎጠኝነት ባስነሣው ቀውስ ተዘፍቋል
  • የሊቀ ጳጳሱ ዘመዶች ከደብር እልቅና እስከ ዕቅብና በከፍተኛ ደመወዝ ተቀጥረዋል
  • ሊቀ ጳጳሱ ሥራ አስኪያጁን ያገዱበት ርምጃ የሀ/ስብከቱን አድባራት ተቃውሞ ቀስቅሷል
  • ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በታገዱት ሥ/አስኪያጅ ምትክ ለመመደብ ከሊቀ ጳጳሱ ጋራ እየተሸማገሉ መኾናቸው ተሰምቷል
  • ፓትርያሪኩ እግዱ ተነሥቶ ሥ/አስኪያጁ ወደ ሓላፊነታቸው እንዲመለሱና የእግዱ አግባብነት እንዲጣራ ለጠ/ቤ/ክህነቱ ጽ/ቤት የሰጡት መመሪያ አልተፈጸመም፤ /ሥ/አስኪያጁ እግዱን ለማስፈጸም ዳተኛ ሲኾኑ ሊቀ ጳጳሱ ደግሞ ላልተገባ ርምጃቸው ድጋፍ ለማግኘት የሀ/ስብከቱን አጥቢያ አብ/ክርስቲያን ሓላፊዎች ነገ ስብሰባ ጠርተዋል
  • አቡነ ሕዝቅኤል በዕጩነት በቀረቡበት የስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ድጋፍ ነፍገውኛል ያሏቸውን እየተበቀሉ ነውን?
metering the sunsetየጥቅምት 2005 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በአራት አህጉረ ስብከት እንዲከፈል ሲወስን በሀ/ስብከቱ የተንሰራፋውን የሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር በዘላቂነት እንደሚፈታው በመታመኑ ነበር፡፡ ምልአተ ጉባኤው ስለ ውሳኔው ያወጣው መግለጫ ቃል የሚከተለውን ይላል፡-
በቅ/ሲኖዶስ የተቋቋመው ኮሚቴ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከትን ችግር ለመፍታት አጥንቶ ያቀረበውን ጥናታዊ ጽሑፍ የመረመረው የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጥናቱ መሠረት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በአራት አህጉረ ስብከት ቢከፈል ለአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ቅርበት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚችል ከመኾኑም በላይ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አካባቢ የሚታየው የአስተዳደር ችግር በዘላቂነት እንደሚፈታው በመታመኑ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በምሥራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜን፣ በደቡብ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት እንዲደራጅ ወስኗል፡፡
የምልአተ ጉባኤውን ውሳኔ አስመልክቶ የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከብዙኀን መገናኛ ለቀረበላቸው ጥያቄ በወቅቱ በሰጡት ምላሽ÷ ‹‹አቤት ባዩ በዛ፤ ጩኸት በዝቷልና ሁሉም በአካባቢው እንዲስተናገድ በሊቃውንትም በአባቶችም ተጠንቶ ቀጠሮ ተይዞበት የቆየ ነው፤›› ብለው ነበር፡፡

ሰበር ዜና – ጠቅላይ ቤተ ክህነት በአጥማቂ ነኝ ባዩ ግርማ ወንድሙ ላይ የተላለፈውን እግድ አጸና!


  • ውሳኔው የአጥማቂ ነኝ ባዩን ሥርዐተ አልበኝነት ሲቃወሙና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ለማስከበር ሲጋደሉ ለቆዩት የደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ሰንበት ት/ቤት አባላትና ምእመናን ታላቅ ድል ነው፡፡
  • ሰንበት ት/ቤቱ እና ምእመናኑ የውሳኔውን አፈጻጸም በቀጣይነትና በጋራ ሊከታተሉ ይገባል
  • ሕገ ወጥ ሰባክያንና አጥማቂ ነን ባዮች ችግር የሚፈጥሩባቸው ሌሎች አጥቢያዎችስ ከዚህ ምን ይማራሉ?BeteKihnet banned Girma

Tuesday, May 14, 2013

ስመ ‹‹መቲራ››ው ሲመተር! ቀንደኛው ፅልመታዊና ሙሰኛ ‹‹አባ›› ገ/መድኅን ገ/ጊዮርጊስ ወደ መንበረ ፓትርያሪኩ እንዳይገቡ ታገዱ!


  • ጀብደኛው ሙሰኛ ‹‹አባ›› ገብረ መድኅን በመንበረ ፓትርያሪኩ አሠራር ጣልቃ በመግባት፣ ከሥ ሓላፊዎችና ከጥበቃ አባላት ጋራ ሁከት በመፍጠር አቤቱታ ቀርቦባቸዋል
  • Abba Gebre Medhin banned
  • ከምስጉን አቋማቸው በመንሸራተት ከሙሰኞች ጋራ መተቃቀፍ የጀመሩት አቡ ሕዝቅኤል በሙሰኛው ‹‹መነኩሴ›› ላይ የተላለፈውን እግድ በጣልቃ ገብነት መቃወማቸው አስገራሚ ኾኗል

Thursday, May 2, 2013

ስለ ሃይማኖት ተቋማት ምዝገባ አንዳንድ ነጥቦች


*ቀለመ ወርቅ ሚደቅሳ
ምንጭ፡- ዕንቁ መጽሔት፣ ቅጽ 6 ቁጥር 90፣ ሚያዝያ 2005 ዓ.ም
መንደርደሪያ
የሃይማኖት እና የእምነት ነጻነት መብት መሠረታዊ የሰብአዊ መብት አካል ነው፡፡ የሃይማኖት ነጻነት መብት የምንለው አንድ ሰው ፈጣሪ መኖሩን በመሰለው መልክ በመበየን ብቻውን ወይም ከሌሎች ጋር የሚኖረውን የማምለክ መብት የሚገልጽ ነው፡፡ የእምነት ነጻነት ደግሞ ፈጣሪ የለም ብሎ ከማመን ጀምሮ አንድ ሰው የእምነት ጉዳይን በሚመለከት ያለውን ነጻነት የሚመለከት ነው፡፡
በቅርብ ዓመታት ውስጥ በተደረገ የሕዝብ ቆጠራ ከአጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ 97% የሚኾነው ‹‹ሃይማኖተኛ›› መኾኑን ከብሔራዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የተገኘ መረጃ ይገልጻል፡፡ ከዚህ ነጥብ በመነሣት በኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ጉዳይ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው ማኅበራዊ ጉዳይ መኾኑን መደምደም ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የእምነት ነጻነት ጉዳይ ያለው ሽፋን አነስተኛ መኾኑን ማየት ይቻላል፡፡ በመኾኑም የዚህ ጽሑፍ ትኩረት የሃይማኖት ጉዳይ ላይ ይኾናል፡፡
የሃይማኖት ነጻነት መብት በግል የሚያምኑበትን ሃይማኖት መምረጥን ወይም መያዝን፣ ሃይማኖትን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመኾን ማምለክን፣ መተግበርን፣ ማስተማርን ወይም መግለጽን ያጠቃልላል፡፡ በእነዚህ ዝርዝር መብቶች በጋራ ተጠቃሚ ለመኾን አንድ ቡድን የሃይማኖት ተቋሙ የሕግ ዕውቅና እንዲያገኝለት ያስፈልገዋል፡፡ ይህ ጽሑፍ ከሃይማኖት ተቋማት ምዝገባ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን አንዳንድ ነጥቦች ለማንሣት ይሞክራል፡፡
የሃይማኖት ነጻነት መብት የሕግ ማዕቀፍ  

የሕማማት ዋዜማው ሕማም! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ተቋማዊ ህልውና እና የክህነታዊ ሥልጣን ማእከላዊነት በምዝገባና ፈቃድ ዕድሳት በሚሸረሽር እና በሚያፋልስ የመመሪያ ረቂቅ ላይ እየተመከረ ነው

Sebeka Gubae General Structure
  • ቤተ ክርስቲያን ፍትሐ ብሔር ሕጉ ያገኘችውን ሕጋዊነት የሚከልስ፣ ታሪካዊ ክብሯን የሚያንኳስስ፣ ማኅበራዊ እሴቷን የሚቀንስና አሐቲነቷን የሚያፈርስ በምትኩ የመንግሥትን የቁጥጥር አቅም የሚያፈረጥምና የሚያነግሥ ነው፡፡
  • የሃይማኖትና መንግሥት ግንኙነትን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ የሚጥስ መመሪያ ነው
  • የሃይማኖት ተቋማትን ልዩ መንፈሳዊና ድርጅታዊ ጠባይ ያገናዘበ መመሪያ አይደለም
  • መመሪያው ለአድልዎና ብልሹ አሠራር የመጋለጥ ዕድሉ የሰፋ ነው
  • መመሪያው የአሐቲ ቤተ ክርስቲያንን መርሕ በመጣስ የፕሮቴስታንቲዝምን ራስ በቀል ዘይቤ የሚያስፋፋ ነው፡፡
  • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ያሳዘነውና የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን ጨምሮ የሕግ ምሁራንን ያነጋገረው የመመሪያው ረቂቅ ከቅዱስ ሲኖዶሱ ዐበይት አጀንዳዎች አንዱ እንደሚኾን ተጠቁሟል
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ‹‹የሃይማኖት ተቋማትን ለመመዝገብ›› በሚል በቅርቡ ለውይይት የዘረጋው የመመሪያ ረቂቅ፣ በአገራችን ታላቅ ፋይዳ ያላቸውን የሃይማኖት ተቋማት ልዩ መንፈሳዊ ጠባይ እና ድርጅታዊ አሠራር ያላገናዘበ በተለይም ጥንታዊትና ብሔራዊት የኾነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ ሰውነት የሚከልስና ማእከላዊ አሠራሯን የሚያፈርስ እንደኾነ እየተገለጸ ነው፡፡
የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በዐዋጅ ቁጥር 691/2003 አንቀጽ 14/1/ሸ የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር ለመወጣት በሚል መዘጋጀቱ የተገለጸው የመመሪያው ረቂቅ፣ አስፈላጊ የኾነባቸው አራት ነጥቦች በመግቢያው ላይ ተመልክተዋል፡፡ ከእኒህም ዋነኛው ‹‹ለሃይማኖት ወይም እምነት ተቋማት በሕገ መንግሥቱ የተረጋገጠው÷ የሃይማኖት ነጻነት፣ እኩልነትና የመደራጀት መብት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለማስቻልና ነጻነታቸው እንደተጠበቀ ኾኖ አሠራራቸው ከሕገ መንግሥቱና ከሌሎች የአገሪቱ ሕጎች ጋራ በተጣጣመ ኹኔታ እንዲቀጥል ለማድረግ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ነው፤›› በሚል ሰፍሯል፡፡