Tuesday, June 4, 2013

ቤተ ክርስቲያን በአደጋ ላይ! የቅ/ሲኖዶሱ ስብሰባ ሂደት በፅልመታዊው ጎጠኛና ሙሰኛ ቡድን ተጽዕኖ እንዳይጠለፍ ተሰግቷል


  • የጠ/ቤ/ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅነት ምርጫ ሊቃነ ጳጳሳቱን እርስ በርስ አደፋፍጧል
  • ርእሰ መንበሩ ስብሰባውን በአግባቡ ለመምራትና ለመጠቅለል ተስኗቸዋል ተብሏል
  • በሙሰኝነትና ጎጠኝነት በተዘፈቁበት ተግባራቸው ከሚመጣባቸው ተጠያቂነት ራሳቸውን ለማዳን የተባበሩ ጳጳሳትለተቋማዊ ለውጡ ስጋት ደቅነዋል፤ የፓትርያሪኩን የተቋማዊ ለውጥ ይኹንታዎች ተፈታትነዋል፤ አቡነ ሳዊሮስ፣ አቡነ ማርቆስ፣ አቡነ ፋኑኤል፣ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ አቡነ ቄርሎስ እና አቡነ ሕዝቅኤል ይገኙበታል
  • ምክትል ዋ/ሥራ አስኪያጁን ጨምሮ ልመታዊውን ቡድን በብርቱ የተቋቋሙ የተቋማዊ ለውጡ አውራዎችከሓላፊነታቸው እንዲነሡ መወሰኑ ተሰምቷል፤ራሳቸውን በሙሰኛና ጎጠኛ አሠራር ከመጠየቅ ለማዳን የሚረባረቡ ጳጳሳት ቡድናዊነትና ለዋ/ሥራ አስኪያጅነት ምርጫው የተያዘው መደፋፈጥ በሰፈነበት አጋጣሚ በአጀንዳው ዝርዝር ሳይካተት ም/ዋ/ሥራ አስኪያጁን ከሓላፊነት የማንሣት ውሳኔ የተላለፈበት ኹኔ ተኰንኗል
  • ምክትል ዋ/ሥራ አስኪያጁ አቶ ተስፋዬ ውብሸት ከሓላፊነት የተነሡበት ምክንያት ‹‹ክህነት የላቸውም››  በሚል ቢኾንም ቄስ አይሏቸው መነኵሴ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ቦታውን ለመረከብ አሰፍስፈዋል፤ የአራት መኖርያ ቤቶችና አንድ የንግድ ቤት ባለቤት መኾናቸው የተረጋገጠው ንቡረ እዱ የፀረ – ሙስናውን እንቅስቃሴ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ለማክሸፍ ተነሣስተዋል
  • ‹‹የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ስብከተ ወንጌል ነው›› በሚል የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ እንዲፈርስ ተወስኗል፤ የጠ/ቤ/ክህነቱ አስተዳደር መምሪያ ዋና ሓላፊ ታግደዋል፤ ውሳኔው ‹‹በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ድንጋጌ መሠረት ደረጃውን ጠብቆ ያልተወሰደ፣ በፅልመታዊው ቡድን ጎጠኝነት የተገፋና የፀረ – ሙስና ትግሉን የሚያደናቅፍ የቂም በቀል ርምጃ ነ፤›› በሚል ተተችቷል
  • የፀረ – ሙስና እርምት ርምጃዎችን፣ የአስተዳደራዊ መዋቅር እና ፋይናንስ ሥርዐት ለውጦችን አጥንቶ የሚያቀርብበሁለት ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ የባለሞያዎች ኮሚቴ እንዲቋቋም ተወስኗል፤ ሕጉንና ቃለ ዐዋዲውን የማሻሻል ጅምርሥራዎች የማስፈጸምና የስልታዊ ዕቅዱ ዝግጅት በኮሚቴው ይከናወና
  • የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት በአንድ ረዳት ሊቀ ጳጳስና በአራት ሥራ አስኪያጆች እንዲመራ የቀረበው ሐሳብእያከራከረ ነው
የርክበ ካህናት ቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሁለተኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ ከተጀመረ አራተኛ ቀኑን አስቆጥሯል፡፡ ግንቦት ፳ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. የመክፈቻ ጸሎት ያካሄደው ምልአተ ጉባኤው 18 ያህል አጀንዳዎችን በማጽደቅ ዛሬን ጨምሮ በሥራ ላይ በቆየባቸው አራት ቀናት 13 ያህል አጀንዳዎችን ተመልክቶ ውሳኔ ማስተላለፉ ተዘግቧል፡፡

ምንጭ: ሐራ ዘተዋህዶ
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment