ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማውያንን ጉባኤ ልታዘጋጅ ነው
"እግዚአብሔርም ሰዶምንና ገሞራን ባፈረሰ ጊዜ እንደ ነበረው፥ የመንግሥታት ክብር የከለዳውያንም ትዕቢት ጌጥ ባቢሎን እንዲሁ ትሆናለች። "
ትንቢተ ኢሳያስ ፲፫ ፥ ፲፱
"ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተምች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ እንዲሁ ሰው በዚያ አይቀመጥም የሰውም ልጅ አይኖርባትም። "
ትንቢተ ኤርሚያስ ፶ ፥ ፵
"ሰዶምንና ገሞራን እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፥ እንዲሁ ገለበጥኋችሁ፥ እናንተም ከእሳት ውስጥ እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ ነገር ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥ ይላል እግዚአብሔር፦ "
ትንቢተ አሞጽ ፬ ፥ ፲፩
"ኃጢአትንም ያደርጉ ዘንድ ላሉት ምሳሌ አድርጎ ከተማዎችን ሰዶምንና ገሞራን አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎና ገልብጦ ከፈረደባቸው፥ "
፪ኛ የጴጥሮስ መልዕክት ፪ ፥ ፮
ወገኖቼ እናስተውል ዛሬ እንዲህ ዓይነት በዓይናችን ላይ የሚሰራው ነገር ከምዕራባዊያን የመጣ ባሕል እና ህይወት ነገ የእያንዳንዳችን ቤት ማንኳኳቱ አይቀሬ ነው፣ ሰዶማውያንን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አጥብቃ ትቃወማለች፣ ትጸየፈዋለችም እንዲህ ዓይነቱን በሽታም በህዝባችን የእለት ተዕለት ኑሮውን እንዲያበላሸው ወይንም እንዲበርዘው የማናችንም ምኞት አይደለም ስለሆነም፣ ሕፃን፣ ወጣት፣ አዋቂ፣ ሽማግሌ እና አሮጊት እንዲሁም ክርስቲያን፣ እስላም፣ ወይንም ሃይማኖት የለሹም ቢሆን ይሄንን ኢ - ኢትዮጵያዊ የሆነውን ምግባረ ብልሹነት የምዕራባውያን ቅብጠትን ወይም ሰይጣናዊነት አጥብቀን ልንቃወመው የሚገባ ወቅታዊ ጉዳይ ነው ብለን የዚህ ዝግጅት ክፍል ያምናል፡
"የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም"