Sunday, November 13, 2011

አባ ፋኑኤል እና ጉዞዋቸው!

  • አቡነ ፋኑኤልን ለምን የአሜሪካን ክርስቲያኖች አይቀበሏቸውም?
  • አቡነ ፋኑኤል የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዴት ተሾሙ?
  • አቡነ ፋኑኤል ከዚህ በፊት ምን አይነት አቋም ነበራቸው? አሁንስ?
  • የአቡነ ፋኑኤል ከነ ወ/ሮ እጅጋየሁ እና በጋሻው ጋር ያላችው ግንኝነት ምንድነው?
  • አቡነ ፋኑኤልን እና የመናፍቃኑ ድምጽ የሆነው "አባ ሰላማን" ምን አገናኛቸው?
በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ከተመሰረተች ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ ቢሆናትም እንደ አሁኑ ያለ ከፍተኛ ፈተና የገጠማት ለመጀመሪያ በታሪኳ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ባስቆጠረው ጉዞዋ ያሁኑ በጣም አስቸጋሪ እና ከፈተናዎች ሁሉ የከፋ እንደሆነ በቤተ ክርስቲያኗ ጥላ ስር ያሉት አብያተ ክርስቲያናት፣ ካህናት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መዕመናን እና ምዕመናት በምሬት ይናገራሉ። ከዛሬ ሃምሳ አመት በፊት በቅዱስ ፓትሪያሪክ ሊቀጳጳስ ዘኢትዮጵያ በሆኑት ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሊዎስ ተባርካ በብሩክላን ኒው ዮርክ ከተማ ከተመሰረተች ጊዜ ጀምሮ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ልካ ሐዋሪያዊት አገልግሎቷን ስትፈጽም ቆይታለች፥ በዚህ በነበራት ጉዞዋ ብዙ ውጣ ውረዶች በተለያየ ጊዜ የገጠማት ቢሆንም ካለፈው አምስት ዓመት በኃላ በሰሜን አሜሪካ ሦስት ሀገረ ስብከቶች ሆነው እንዲሰሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ባዘዘው መሠረት ከተመሠረተ ጀምሮ ግን አመርቂ እና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይዞታዋን ከማስመለሱም በላይ ታላላቅ ገዳማትን እና አድባራትን መሥርታ በላከቻቸው ብፁዓን አባቶች አማካኝነት ታላላቅ የሆኑ ይዞታዎችን ቤተ ክርቲያኗ እንድትይዝ እና ሐዋሪያዊት ተልዕኮዋን ስትፈጽም ስታስፈጽም ቆይታለች።


የዛሬ አስራ አምስት እና አስራ ስድስት ዓመት ገደማ ተመድበው ወደ ሰሜን አሜሪካ ያመሩት ብፁዕ አቡነ ማትያስም የዚህ ፈተና ተቋዳሽ እና የችግሩ ገፈት ቀማሽ የሆኑበት የመጀመሪያ ጅምር ነበር፥ የአሁኑ አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) ለብፁዓን አባቶችን በማዋረድ ክብራቸውን በመንካት እስከ ፍርድ ቤት በመሄድ፣ የታክሲ ነጂዎችን የእለት አበላችሁን እንከፍላለን በማለት በወቅቱ በራሳቸው አካሄድ የተመሰረቱትን አብያተ ክርስቲያናት በማስተባበር ብዙ እንግልት እና በደል ሲፈጽሙ ኖረው፣ከዚህ በተጨማሪም በሰሜን አሜሪካ ዋነኛው እና ቀንደኛው የገለልተኛ መስራች እና ሰሪ ሆነው፣ "አባ ጳውሎስን እና ወያኔን ለይተን አናይም" በማለት የቤተ ክርስቲያኗን ፓትሪያሪክ በአደባባይ እስከ መሳደብ እና እስከ ማዋረድ፣ የቤተ ክርስቲያኗንም ህጋዊ ወኪል የኖኑትን ብፁዕ አቡነ ማቲያስን እርሶንም ሆነ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን አናውቅም አንከተልም እኛ በራሳችን እምንባርከው፣ እምንናዝዘው እራሳችን ነን ወደሚለው አካሄድ ያደረሱ እና የሰሩት አባት ዛሬ ያንን ሁሉ በተናገሩት አፍ ደግሞ እኔ ነኝ የቤተ ክርስቲያኗ ህጋዊ ወኪል ብለው ቢመጡ በምን መመዘኛ ነው ሕዝበ ክርስቲያኑ ሊቀበላቸው የሚችለው? እርሱም ይሁን ቢባል እንኳ የራሴ የግሌ የሚሉትን ደብረ ምሕረትን በቅዱስ ሲኖዶስ አስተዳደር ሥር ሳያደርጉ እንዴት ሌላውን ና በእናት ቤተ ክርስቲያን ተመራ ብለው ሠርተው ሊያሠሩት ይችላሉ መልሱን ለአንባቢያን እንተወው።

ሌላኛው የአቡኑ አካሄድ ደግሞ "እኔ የሁሉም አባት ነኝ" የሚሉት የሞኝ ፈሊጥ አለ፣ እረ ለመሆኑ ፕሮቴስታንቱም፣ እስላሙም ናና ባርከን ቢሏቸው ሄደው ሊባርኩ ነው ማለት ነው? ይህ አይነት አካሄዳቸውን ከሌሎቹ መናፍቃን ጋር የአካሄድ አንድነት እንዳላቸው ያሳያል፣ እንደ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ከሆነ ግን ለቤተ ክርስቲያን ገለልተኛ የሚባል አካሄድ የነ አባ መላኩ አካሄድ ነው፣ ፈጽሞ ለቤተ ክርስቲያን አይስማማትም የማይሞከር አካሄድ ነው፥ እስከምናውቀው ድረስ ገለልተኛ የፕሮቴስታንት አካሄድ ነው የፕሮቴስታት መስራቿ ሉተር እና ጆን ካልቪን ያደረጉት የካቶሊካዊቷ ቤተ ክርስቲያን አካሄድ አልተስማማንም እነሱ ሮም ላይ ብቻ ነው ሊሰራ የሚችለው በማለት ማርቲን ሉተር በጀርመን፣ ጆን ካልቪን ደግሞ በፈረንሳይ የራሳቸውን የገለልተኛ እና የመናፍቃንን አካሄድ ያመጡ በዘመኑ የነበሩ ሃሳዊያን መሪዎቻቸው ናቸው፣ ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ደግሞ ከመሥራቿ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ በአንብሮተ ዕድ በመጀመሪያ ከጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ እና ረድዑ ለሆኑት ሐዋሪያት በአንብሮ ዕድ ከዚያ ጀምሮ እኛ እስካለንበት ዘመን ድረስ ያ ሐዋሪያዊ ቅብልሎሽ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ሥርዓት እና ትውፊት ትተን "ገለልተኛ ነን" ማለት የእኛ አይደለም እኛን እኛን አይልም፥ ይህንን አካሄዳቸውን ቤተ ክርስቲያንም ፈጽማ ትጸየፈዋለች፣ ሕዝበ ክርስቲያኑም ፈጽሞ አይፈልገውም። በሌላ በኩል እኝህ አባት ከሲመተ ጵጵስናቸው ጀምሮ በሦስት የተለያዩ ቦታዎች ተመድበው ያደረሱት በደል፣ ግፍ፣ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ያልሆነውን አሰራራቸውን የጀመሩት ገና በጠዋት ነው፣ እስቲ ለአብነት ከነበሩባቸው ቦታዎች ጥቂቶቹን እናንሳን እንነጋገር።

አባ ፋኑኤል በሐዋሳ
አባ ፋኑኤል ገና ከአሜሪካ እንደገቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ፊት ቀርበው በአሜሪካን ዋና ከተማ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ወጥቼ ወርጄ ሰው አስተባብሬ ያሠራሁትን የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስረክቤያለሁ ብለው አስጨብጭበው ቤተ ክርስቲያኑም ለሚመደበው ሊቀ ጳጳስ መቀመጫ መንበረ ጵጵስና ይሆናል ብለው አውጀው የስብሰባውን ታዳሚ ሁሉ (deceive) አድርገው ነበር ያጭበረበሩት፣ በመቀጠልም ወደዚህ ሀገረ ስብከት ተሹመው መጥተው ነበር ነገር ግን እንኳን ሌላውን ሊመሩ ቀርቶ የራሴ ነው ያሉት ደብረ ምሕረት እንኳን ይህው እስካሁን እልባት ያላገኘለትን የአምስት ዓመት የፍርድ ቤት መዘዝ ያመጣው እሳቸው ይሆነኛል ብለው የዘረጉት መረብ ነው ቤተ ክርስቲያኑን እስከ አሁን ብቻ ከ $250,000.00 በላይ ለጠበቃ ከ $ 95,000.00 በላይ ለአካውንታንት እና ለprivate investigator ወጪ የተዳረገው፣ ያም ሆኖ እኚሁ አባት በሚቀጥለው ያሰብኩት አልተሳካም፣ የጠበኩን አላገኘሁትም ብለው ሌላ ሀገረ ስብከት እንዲሰጣቸው ጠይቀው ሐዋሳ ሲመደቡ ገና በዓመታቸው መጥተው ለደብረ ምሕረት ሕዝብ "እንግዲህ ወደ ሐዋሳ አካባቢ መሬት ከፈለጋችሁ መጥታችሁ አናግሩኝ" ብለው በዓውደ ምሕረቱ ላይ ሲደሰኩሩ ቆይተው ተመለሱ ከዚያም የሆነውን ሁሉ በሐዋሳ እና አካባቢዋ ላይ ያደረሱትን በደል እና ግፍ ሁላችንም የምናውቀው የአደባባይ ሚስጥር ስለሆነ እንለፈው፣ በመቀጠል በሐዋሳ ሕዝበ ክርስቲያን እንባ እና ትግል እንደ መዥገር ተጣብቀው ከነበሩበት ሕዝብ እና ቤተ ክርስቲያን ተገልለው የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ሆነው ተሾሙ፣ ያው የተለመደው ሥራቸው ተከትሏቸው ከቀ መዛሙርቱ ወጥተው ጊቢያችን አይግቡ ብሎ አበረራቸው፣ በመቀጠልም ወደ ሐረር ተመድበው አንድ ቀንም ሳይሄዱ እና ሳያዩት ወደ አሜሪካ በፓትሪያሪክ ጳውሎስ ሥርዓቱን እንዲያፈርሱ፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን ወደ ጎን ትተው እንደሚመቻቸው እንዲሠሩ ከ$400,000.00 ጋር ተልከው ተልዕኮዋቸውን እንደታዘዙት ሲፈጽሙ እና ሲያስፈጽሙ ቆይተው ሐዋሪያዊ ሥራቸውን ሲወጡ ከቆዩት ብፁዓን ሊቀ ጳጳሳን ጎን ቁጭ ብለው ያንኑ የዛሬ አምስት ዓመት አልቻልኩም ከአቅሜ በላይ ነው ያሉትን ሀገረ ስንከት የሀሰት ምሥክሮችን እነ ሊቀ መምዕራን ቀሲስ አማረን (ደብረ ሰላም ቅድስት ማሪያም ዲሲ) የሐሰተኛ ምስክሮችን አስቁመው ለቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ፊት ከቤተ ክርስቲያኑቷ መዋቅር ውጪ በሆኑ እራሳቸውን "ገለልተኛ" ብለው በሚጠሩ አብያተ ክርስቲያናት የተፈረመ የ8 አብያተ ክርስቲያናት ደብዳቤ ይዘው በመቅረብ
የፈራሚዎቹ አድባራት እና አስተዳዳሪዎች ሥም

፩ኛ/ ሊቀ መምዕራን ቀሲስ አማረ ካሳዬ (ደብረ ሰላም ቅድስተ ማሪያም ዲሲ)
፪ኛ/ ቀሲስ ታደሰ (ሐመረ ኖሕ ኪዳነ ምሕረት ቨርጂኒያ)
፫ኛ/ አባ እስጢፋኖስ ባሕሩ (ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ዲሲ)
፬ኛ/ ቀሲስ ሚስጥሩ (ኢየሱስ ቤ/ክርስቲያን ውድ ብሪጅ ቨርጂኒያ)
፭ኛ/ ቀሲስ ኢስሐቅ (ቅድስት ሥላሴ ቨርጂኒያ)
፮ኛ/ ቀሲስ አቡኑ (ለቀሲስ ዘበነ) (ደብረ ገነት መድኅኒዓለም ሜሪላንድ)
፯ኛ/ አባ ጽጌድንግል (ፍኖተ ጽድቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቨርጂኒያ)
፰ኛ/ አባ መዓዛ (ቅዱስ ገብርኤል ዲሲ)


እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት በሙሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አንመራም እራሳችን ባወጣነው መተዳደሪያ ነው የምንመራው በሚሉ ሰዎች የተፈረመ ደብዳቤ አስይዘው ለሦስተኛ እና አራተኛ ጊዜ የቅዱስ ሲኖዶስን አባላት ዋሽተው እና አታለው ሀገረ ስብከቱ እንዲሰጣቸው ከፓትሪያሪኩ ጋር ቀድመው በተዋዋሉት መሠረት አብዛኛው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሳያምኑበት እና ሳይመክሩበት በፓትሪያሪክ ጳውሎስ ትዕዛዝ ምክንያት ተፈፃሚ ሆኗል፣ አንድ ያልተመለሰው ጥያቄ ቢኖር "ለምን አቡነ አብረሃምን በአሜሪካን ሥራቸውን እንዳይሰሩ ተፈለገ? ለምንስ በገለልተኛ አስተዳደር ስር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት አብረዋቸው መስራትን አልፈለጉም? ይልቁንም እነ ሊቀ መምዕራን ቀሲስ አማረን አዲስ አበባ ድረስ ልከው አቤቱታ ለማቅረብ አስፈለገ? ሲጀመርም ጀምሮ እነዚህ ሰዎች የቤተ ክርስቲያኗን መዋቅር ተቃውመው ወይም ስላልፈለጉት ነበር እኮ ገለልተኛ መሆንን የመረጡት ታዲያ በዚህ ፈታኝ በሆነ ወቅት ሊሰሩ የሚችሉ አባቶችን ተባብረው ለማሳደድ ለምን ተፈለገ? ጥያቄውን አሁን ልንመልሰው እንደማንችል እርግጠኞች ነን፥ ነገር ግን ኢፌክቱን ግን መቅርብ ማየት የምንችል ይመልለናል እና ያንን ጊዜ መጠበቅን መርጠናል እና የዛ ሰው ይበለን ብለን ወደሚቀጥለው ነጥብ እንለፍ።
በሰሜን አሜሪካ ባደረጓቸው የመጨረሻ ጉዞዋቸው መሠረት በፍትሕ መንፈሳዊ መጽሐፍ ላይ እንደሚናገረው ሥልጣነ ክህነትን ሊያሽር የምችል ሥራ ሲሰሩ ቆይተው፣ ያለ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ "እኔ የሁሉም አባት ነኝ" በሚለው አቋማቸው በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በመከኘት ሥልጣነ ክህነትን ሲሰጡ፣ ቤተ ክርስቲያን ሲባርኩ (ገለልተኛን) ማዕረግ ሲሰጡ እና ሲሾሙ፣ ከቤተ ክርስቲያኑቷ ሕግና ቀኖና ውጪ የሆነውን "የውጪ ግንኙነት ጽ/ቤት" የተባለውን ሲያደራጁ እና ሲያዘጋጁ ቆይተው ተመልሰው በዚህ ሁሉ በደላቸው መወገዝ ቀርቶ መወቀስ ሲገባቸው እንደገና መሾማቸው የፓትሪያሪኩን የመጨረሻ ቤተ ክርስቲያንን የማፍረስ እና የማጥፋት ሕልማቸውን በትክክል ያሳወቁበት እና ያስገነዘቡበት ጊዜ ቢኖር ይህ የመጀመሪያው ነው ብለን እናምናለን።

የአቡነ ፋኑኤል እና የወ/ሮዋ ግንኙነት
ወ/ሮዋ እና አቡነ ፋኑኤል ግንኙነት ማድረግ የጀመሩት ገና በጠዋሩ ወደ ሰሜን አሜሪካ ተመድበው ለመምጣት በዝግጅት ላይ እያሉ ነበር፣ በዚያን ጊዜ የጎላ ተሳትፎም ስላልነበራቸው፣ እውቅናም ስላልነበራቸው፣ ከርሳቸው የሚያገኙት ጥቅምም እምብዛም ስለነበረ ወይዘሮዋ ብዙም ክትትል አላደረገችባቸውም ነበር፣ ነገር ግን ተመልሰው ወደ ሐዋሳ ሲመደቡ ወይዘሮዋ በግንባር ተገኝታ በጋሻውን እና ያሬድ አደመን በመያዝ የጥቅም ትስስራቸውን በዚያው ጀምረዋል፣ በመቀጠልም ቃል በገቡት መሠረት ያሬድ አደመን የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊ አድርገው ሹመው ሕዝበ ክርስቲያኑን በአወደ ምሕረት ላይ በማሰደብ፣ የሰንበት ት/ቤት ቢሮዎችን በማሰበር፣ ቀናዪ አባቶችን እና አገልጋዮችን በማሳደድ ካስወጡ በኃላ የምንፍቅና ሥራቸውን በአደባባይ ጀምው ልክ እንደ ግብር አባታቸው ፓትሪያሪክ ጳውሎስ ፎቶዋቸውን ከቤተ ክርስቲያን በላይ በቢል ቦርድ በመለጠፍ ቤተ ክርስቲያንን በደሙ የመሠረታትን መዳኅኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስን ዝቅ አድርገው የራሳቸውንን ፎቶ ከበላይ አድርገው ሕዝቡን ደም እንባ አስለቅሰው የራሔልን እንባ የቆጠረ እግዚአብሔር ቆጥሮላቸው እስኪነሱ ድረስ ቆራጥ ተጋድሎ አድርገው አስወጥተዋቸዋል በመጨረሻም ልክ በዚህ ባለፈው ምልዓተ ጉባኤ ላይ እንዳቀረቡት "ለመንበረ ፓትሪያሪኩ ተጠሪ የምትሆን ቤተ ክርስቲያን ይመስረትልን"  ብለው ለፓትሪያሪክ ጳውሎስ አቅርበዋል። የወይዘሮዋ እና የአኑነ ፋኑኤል ግንኙነት በቀጣይነት የጥቅም ትስስራቸውን በመቀጠል ዛሬ ወደ ሰሜን አሜሪካ ለመምጣት በዝግጅት ላይ ባሉበት ወቅት የወይዘሮዋን ወኪል በጋሻውን ቢችሉ በሕጋዊ መንገድ በፓትሪያሪክ ጳውሎስ ተባባሪነት ይዘውት ሊመጡ፣ እሱ ባይመቻቸውም በሻንጣቸውም አጣጥፈው ሊያመጡት ለወይዘሮዋ ቃላቸውን ሰጥተዋል። ታዲያ ወይዘሮዋን እና አቡነ ፋኑኤልን ምን ዓይነት ጥቅም ሊያቆራኛቸው እንደቻለ የደረሰንን እንቅርብ፥ በመጀመሪያ የወይዘሮዋ አካሄድ አቡነ ፋኑኤል ውዳሴ ከንቱ ወዳጅ መሆናቸውን በደንብ ጠንቅቃ ስላወቀች ስታግባባቸው "ቅዱሱ አባታችን እንደሚያውቁት ቅዱስ አባታችን እድሜያቸው እየገፋ እንደሆነ ያውቃሉ፣ በዛ ላይ ሕመማቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ስለመጣ በቅርቡ መሞታቸው አይቀሬ ነው" "እንደሚያውቁት በአሁን ሰዓት እርሶን የመሰለ ምሁር አባት ስለሌለ እርሶን ፓትሪያሪክ ለማድረግ የቅዱስ አባታችንም ምርጫ ነዎት" ብለዋቸው ልባቸው በፈንጠዚያ ላይ እያለ " ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ እርሶ አሜሪካ ላይ ሆነው የቤተ ክርስቲያኑ ሕጋዊ ወኪል እንደመሆኖት መጠን እኔ ከዚህ ከ $30,000.00 እስከ $ 40,000.00 እየተቀበልኩ እርሶ እዛ እየተቀበሉ ወደ ዋናው እና ወደ ተመረጡበት ሥራዎ ድረስ" እንደዚህ እያደረግን ቤተ ሰቦቻችንን እንዲሁም ሕብረተሰባችንን እንጠቅማለን በማለት በውል እና በጥቅም ትስስር አድርገው እንደሚመጡ የደረሱን መረጃዎቻችን ያሳያሉ።

የአቡነ ፋኑኤል እና የአባ ሰላማ ብሎግ ግንኙነት
እራሱን "አኑነ ሰላማ" ብሎ የሚጠራው ብሎግ ማንነት በጥቂት ጊዜ ውስጥ የተረዳነው
ይመስለናል እነዚህ ሰዎች ሥራቸው በቀጥታ ከፕሮቴስቲያዊ አስተምህሮዋቸው በግልጽ በሚያወጡት ጽሁፎች ተምልክተዋል። እነዚህ ቡድኖች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ላይ የጽርፈት ቃላትን በየጊዜው ይናገራሉ፣ በቅዱሳን ሰማዕታት ላይ፣ በመላዕክቱ ላይ እንዲሁ የስድብ ድምጻቸውን እያሰሙ ይገኛሉ፣ ሰማይና ምድር የዘረጋውን መድኅኒዓለም ክርስቶስ እንኳ ላከበራቸው ቅዱሳን እንኳን ያልሳሱ እና ያለፈሩ አንደበቶች ዛሬ ታዲያ በምን መመዘኛ ነው አቡነ ፋኑኤልን ''ብፁዕ አባታችን" ብለው ሊጠሯቸው የቻሉት እንደእውነቱ ከሆነ አንድም የአላማ አድነት ቢኖራቸው ነው የማፍረስ፣ የመበረዝ፣ የማደስ ምኞት እና ጥማት ቅድም ከላይ እንደገለጽነው እነዚህ ሰዎች ከወይዘሮዋም ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንዲሁም ከአባ ሰረቀ ጋርም የጠበቀ የሥራ ግንኙነት እንዳላቸው በተለያየ ሚዲያዎች ተዘግበዋል። ከዚህ በፊት አንድ ሊቅ ነበሩ አሉ፣ እኝህ ሊቅ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ነበሩ ይባላል፣ እስሳቸው የተቀኙትን ቅኝት እንዲህ በቀላሉ ማንም አይፈታውም ነበር ይባላል ታዲያ አንድ ቀን በአገልግሎት ላይ ቅኔ ይቀኙና አንድ ደብተራ ነበርና፣ የኔታ ፍቺው ለካ እንዲህ ማለት ነው ብሎ ፈታላቸው ይባላል፥ እኚም ሊቅ በጣም አዝነው ልክ ነህ ነገር ግን ባንተ ከተፈታ ምኑን ቃኘሁት ብለህ ነው አሉት እና አረፉት ይባላል።

እንደ ቀደሙት አበው ሕይወት በእውነት በእንዲህ አይነቶቹ መመስገን ለአባው ውድቀት ከውድቀትም በላይ መሆኑ ከወዲሁ ማወቅ ይቻላል፣ አንድም የአባ ፋኑኤልን አካሄድ ጠንቅቆ ማወቅ ይገባል፣ ሌላው ደግሞ አወዳደቃቸው እንደ ብልጣሶር አወዳደቅ እንዳይሆን ከወዲሁ ስጋታችን ሳንገልጽ አናልፍም። ለተጠሩበት ለተመረጡበት ሐዋሪያዊ ሥራ በቅንነት አገልግሎ ማለፍ ለታሪክም፣ ለክብርም፣ በመረጣቸው አምላክ ፊትም ሞገስን እና ቅድስናን የሚያስገኝ እንደሆነ ሳያውቁ ቀርተው ሳይሆነ
 ነገር ግን ለምድራዊው ዝና እና ሞገስ የበለጠውን ቦታ በመስጠታቸው አሁን የደረሱበት ደርሰዋል ቀሪ ጊዜያቸውንም የንስሐ ጊዜ እንዲያገኙ እና የበደሉትን ሕዝብ እና ቤተ ክርስቲያን ይቅር ብለው ቀሪ ዘመናቸውን በገዳም እየመከሩ እና እያስተማሩ እንዲኖሩ ምኞታችን  ለዛም እንዲያበቃቸው የአምላክ ቅዱስ ፈቃድ እንዲሆን እንመኛለን።

ቸር ወሬ ያሰማን!


የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ

3 comments:

  1. merejaw asfelagi yemehonun yahil bedenb tetsifo bikerb sefi meliekt mastelalef slemichal berttachihu astekaklut, tiru jimir new Amlak yirdachihu!

    ReplyDelete
  2. Egzio min aynet zemen lay deresin! Egziabher hoy bete mekdesihin atsida jirafihinm ansa difret betam beza.

    ReplyDelete
  3. የሐዋርያት ሥራ 20፦28 በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።

    29-30 ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።

    31 ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ።

    32 አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ።

    33 ከማንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤----------------የተነገረውን፡ ትንቢት፡አስፈጻሚ፡ከሆኑ፡የእኛ፡ማልያ፡ለብሰው፡ለመናፍቃን፡የሚጫወቱ፡ሀሰተኛ፡አገልጋዮችን፡ሀያሉእግዚአብኤር፡በደሙየመሰረታትን፡ቅድስቲቱ፡ቤተክርስቲያንን፡በማወቅም፡ሆነ፡ባለማወቅ፡የማጣሉዋትን፡ጠላቶችዋን፡ያስታግስልን፡እንደቅዱስአባታችን፡አትናትዮስ፡እና፡እንደቅዱስአባታችን፡ጊዮርጊስ፡ሀቢብ፡ያሉ፡አባቶች፡ያሰነሳልን፡እናታችን፡ቅድስት፡ድንግል ማርያምበምልጃዋ፡አትለየን፡ለዘላለሙ፡አሜን።

    ReplyDelete