- ቃጠሎው ለአትክልት ልማት ከተደረገ ምንጣሮ ጋራ የተያያዘ መኾኑ ተጠቁሟል
በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም ደን ውስጥ ዛሬ፣ ጥር ፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡30 ላይ የተቀሰቀሰው እሳት በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ፡፡
ቃጠሎው በቁጥጥር ሥር የዋለው ከቀኑ በ9፡00 ገደማ ሲኾን ይኸውም ከቤተ ክርስቲያኑ በግምት ከመቶ ሜትር ባነሰ ርቀት ላይ በደረሰበት ኹኔታ ነው ብለዋል – እሳቱን በማጥፋት የተራዱ የዐይን እማኞች፡፡
የዳጋ እስጢፋኖስን ጨምሮ ከሌሎች የደሴቱ ገዳማት የመጡ መነኰሳት፣ የአቅራቢያው ነዋሪዎች፣ ከባሕር ዳር ከተማ በጀልባ ተጓጉዘው የደረሱ አገልጋዮችና ምእመናን፣ የክልሉ መስተዳድር ተወካዮችና የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሓላፊዎች፣ የባሕር ዳር ዙሪያ ፖሊስና የምዕራብ እዝ ኃይሎች በጋራ ቃጠሎውን በማጥፋት ከፍተኛ የጋራ ርብርብ ማድረጋቸው ተገልጧል፡፡