Monday, April 7, 2014

በተጠርጣሪ የፕሮቴስታንታዊ ኑፋቄ ኅቡእ አራማጆች ላይ ዛሬ ምስክሮች ይሰማሉ

holy trinity building
  • ከሓላፊነታቸው ውጭ የሚንቀሳቀሱ ፕሮቴስታንትና ጉዳዩን ፖሊቲካዊ ያደረጉ የደኅንነት አባላት ነን ባዮች የኮሌጁን ሓላፊዎች በመጫን ተጠርጣሪዎቹን ከተጠያቂነት ለማዳን እየሠሩ ነው፤ ተጠርጣሪዎቹ በኮሌጁ አስተዳደር የተከለከለ ስብሰባ በግቢው እንዲያካሒዱ ረድተዋቸዋል፡፡
  • በ‹ደኅንነት አባላቱ› የሚደገፉትና ‹‹የኢሕአዴግ ተወካዮች ነን›› የሚሉት ተጠርጣሪዎቹ፣ ለሃይማኖታቸው የቆሙትን ብዙኃኑን የኮሌጁን ደቀ መዛሙርት በስለትና በፌሮ ብረት የታገዘ ዛቻና ማስፈራራት እያደረሱባቸው ነው፤ ደቀ መዛሙርቱና የኮሌጁ አስተዳደር ጉዳዩን ለጸጥታ አካላት አስታውቀዋል፡፡
  • ተጠርጣሪዎቹ÷ ‹‹ጽንፈኝነትን ታስፋፋለች›› በማለት ቤተ ክርስቲያንን የከሰሱ ሲኾን ዋና ዲኑን ጨምሮ አንዳንድ የኮሌጁን ሓላፊዎች ደግሞ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንና ፖሊቲከኞች ናችኹ›› በሚል ውንጀላ በምርመራው ሒደት እንዳይሳተፉና ከቦታቸው ለማስነሣት እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡፡
  • ኅቡእ የኑፋቄ አንቀሳቃሾችን በመመልመልና በማደራጀት የሚታወቁ ግለሰቦች (አሳምነው ዓብዩ፣ ደረጀ አጥናፌ እና ታምርኣየሁ አጥናፌ) ተጠርጣሪዎቹ ጥፋታቸውን እንዳያምኑ ከመገፋፋት ጀምሮ ደቀ መዛሙርቱን በጎጠኝነት በመከፋፈል አንድነታቸውን ለማሳጣትና ክሡን ለመቀልበስ እያሤሩ ነው፡፡

የመቐለ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መ/ኮሌጅ ኹለት የፕሮቴስታንታዊ ኑፋቄ ኅቡእ አንቀሳቃሾችን አባረረ፤ ለሰባት ተጠርጣሪዎች ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ በቅ/ሥላሴ መ/ኮሌጅ በዐሥር የኑፋቄው ኅቡእ አቀንሳቃሾች ላይ የቀረቡት ማስረጃዎች ዛሬ መመርመር ይጀምራሉ

HOLY TRINITY THEOLOGICAL COLLEGE LOGO
  • የኮሌጁ የደቀ መዛሙርት ም/ቤት ችግሩ በአስቸኳይ እንዲጣራ ከኹለት ወራት በፊት ያስገባው ደብዳቤ ለተጠርጣሪ ደቀ መዛሙርት ሽፋን በሚሰጠውና ተጠርጣሪዎችን በቢሮው እየጠራ በሚያበረታታው የአስተዳደር ዲኑ ያሬድ ክብረት ተቀብሮ መቆየቱ ተገልጦአል፡፡
  • በቅ/ሲኖዶስ ከተወገዙ ግለሰቦችና ፕሮቴስታንታዊ ድርጅቶች የኑፋቄ አስተምህሮና ተልእኮ የሚሰጣቸው ኅቡእ አንቀሳቃሾችትኩረታቸውን በአዲስ ገቢ ደቀ መዛሙርት ላይ አድርገዋል፤ በመምህራን ምደባ ተጽዕኖ እስከመፍጠር፣ በነግህ ጸሎት ቤት ተራ ወጥቶላቸው ለስብከተ ወንጌል የሚመደቡ ቀናዒ ደቀ መዛሙርትን በማሸማቀቅ መርሐ ግብሩን እስከማስተጓጎልና መደበኛ የትምህርት ክፍለ ጊዜዎችን በጋጠ ወጥነትና በአካዳሚያዊ ነጻነት ስም እስከማወክ የደረሱት ኅቡእ አንቀሳቃሾቹ፣ ከየአህጉረ ስብከቱ ተልከው የመጡበትን የኮሌጁን ትምህርት በክፍል ተገኝተው በመደበኛነት አይከታተሉም፤ ቤተ መጻሕፍቱንማ ጨርሶ አያውቁትም!!
  • በተጠርጣሪነት ክትትል ከሚደረግባቸው ኻያ ያህል የስም ደቀ መዛሙርት መካከል የድምፅ፣ የጽሑፍና የሰው ምስክሮች የቀረቡባቸው ዐሥር ተማሪዎች፡- ጥበቡ ደጉ(፬ኛ ዓመት ከደብረ ማርቆስ)፣ መለሰ ምሕረቴ(፬ኛ ዓመት ከራያና ቆቦ)፣ ያሬድ ተስፋዬ(፫ኛ ዓመት ከሃላባ)፣ ኤርሚያስ መለሰ(፫ኛ ዓመት ከባሌ)፣ ታቦር መኰንን(፫ኛ ዓመት ከወሊሶ)፣ በኃይሉ ሰፊው(፫ኛ ዓመት ከቤንች ማጂ)፣ ተመስገን አዳነ(፪ኛ ዓመት ከሐዋሳ)፣ ይስፋ ዓለም ሳሙኤል(፫ኛ ዓመት ከሰቆጣ)፣ ገብረ እግዚአብሔር ተስፋ ማርያም(፫ኛ ዓመት ከአሶሳ)፣ ሀብታሙ ወልድ ወሰን(፫ኛ ዓመት ከወለጋ) ናቸው፤ የኑፋቄ ተልእኳቸውና ማስረጃዎቹ ከየስማቸው ዝርዝር በአንጻሩ ሰፍሯል፡፡
  • ከተጠርጣሪ ደቀ መዛሙርት መካከል የአጫብር አቋቋም ዐዋቂ ነው የተባለው መሪጌታ ጥበቡ ደጉ የደቀ መዛሙርት ም/ቤት አባል ሲኾን በፈረንሳይ ለጋስዮን ገነተ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በስብከተ ወንጌል እያገለገለ እንደሚገኝ ተዘግቧል፤ ግለሰቡ በግልጽ በሚናገረው ኑፋቄው፣ ‹‹እያንዳንድህ የበላኸውን ትፋ! ያለነው በጫካ ውስጥ ነው፤ ክርስቶስን ለማወቅ ካለንበት ጫካ መውጣት አለብን፤ መስቀል ዕንጨት ነው፤ ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ለመልአክ የምሰግደው ተገልጦ ሲታየኝ ብቻ ነው፤ ለማርያም የጸጋ ስግደት የሚለው በመጽሐፍ ቅዱስ የቱ ላይ ነው፤›› በሚል ግልጥ ኑፋቄ የቤተ ክርስቲያንን የነገረ ድኅነትና ክብረ ቅዱሳን አስተምህሮ በመጋፋት ይታወቃል፡፡
  • በኤቲክስና ሶሲዮሎጂ መምህሩ ተሾመ ገብረ ሚካኤል ‹‹ታዲያ ለምን ኤቲክስ ትማራለኽ?›› በሚል የተጠየቀው መለሰ ምሕረቴ፡-‹‹ኢየሱስ አማላጅ ነው፤ በጸጋው ድነናል፤ ሥራ(ምግባር) አያስፈልግም፤›› በማለት ይታወቃል፡፡ ያሬድ ተስፋዬ፡- በነግህ ጸሎት ቤት ነገረ ማርያምንና ክብረ ቅዱሳንን ማእከል አድርገው የሚያስተምሩ ቀናዒ ደቀ መዛሙርትን ትምህርት አስቁሞ ከመድረክ እንዲወርዱ በማስገደድ፤ ተመስገን አዳነ፡- አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ‹‹የተሻለ ሥልጠና የምታገኙበት ቦታ አለ›› በሚሉ የጥቅም ማባበያዎች እየመለመሉ በመውሰድ፣ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ትራክቶችንና መጽሐፎችን በኅቡእ በማሰራጨት፤ ‹‹እኔ የመንግሥት የደኅንነት አካል ነኝ፤›› የሚለው ታቦር መኰንንና ገብረ እግዚአብሔር ተስፋ ማርያም ቀናዒ ደቀ መዛሙርትን ‹‹ማኅበረ ቅዱሳንና ፖሊቲከኞች ናችሁ›› እያሉ በማስፈራራት፣ መምህራን በምደባቸው እንዳያስተምሩ በውጤት አሰጣጥ ያኮረፉ ተማሪዎችን ለዐመፅ በማነሣሣት፣ በክፍል እያስተማሩ በሚገኙ መምህራን ላይ ከውጭ በር በመቀርቀርና በማንጓጠጥ፣ ዋናው ዲን የኮሌጁን ማኅበረሰብ በመንፈስ ለማስተሳሰር የጀመሯቸውን ጥረቶች (በጋራ እንደማስቀደስና እንደመመገብ ያሉ) በመቃወም በተለያዩ ስልቶች ወንጅሎ ለማስነሣት በሚፈጽሟቸው ሤራዎች ይታወቃሉ፡፡
  • ኅቡእ አንቃሳቃሾቹን እየመለመሉና ከኮሌጁ ውጭ በተለያዩ መንደሮች እያደራጁ ተልእኮና ጥቅም በመስጠት ወደ ኮሌጁ መልሰው ከሚያሰማሩት ግለሰቦች መካከል፡- በ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. በቅ/ሲኖዶስ ተወግዞ ከሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተባረረው ግርማ በቀለ፣ በግንቦት ፳፻፬ ዓ.ም. በቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተወገዘው አሸናፊ መኰንን፣ የታገደው ጥቅመኛና ጥራዝ ነጠቅ ተላላኪ አሰግድ ሣህሉ በዋናነት ተጥቅሰዋል፤ ከኮሌጁ ተመርቀው ምደባ ቢሰጣቸውም በአዲስ አበባ ተቀምጠው የማደራጀት ሥራውን የሚመሩትም አሳምነው ዓብዩ፣ ታምርአየኹ አጥናፌ፣ አብርሃም ሚበዝኁ፣ ጋሻው ዘመነ፣ ‹አባ› ሰላማ ብርሃኑ፣ እሸቱ ሞገስና በድሬዳዋ የሚገኘው በረከት ታደሰ እንዲኹም በኮሌጁ የድኅረ ምረቃ ትምህርት በመከታተል ላይ የሚገኙት አእመረ አሸብርና ደረጀ አጥናፌ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው፡፡
  • የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር በጽሑፍ፣ በድምፅና በሰው ምስክሮች ተደግፈው የቀረቡ ማስረጃዎችን ከቅዱሳት መጻሕፍት፣ ከትምህርተ ሃይማኖትና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ለመመልከት የሚያግዙትን ሦስት መምህራን መርጦ ዛሬ ምርመራውን ይጀምራል፤ የተመረጡት መምህራን፡- የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና ታሪከ ሃይማኖት መ/ር ፍሥሓ ጽዮን ደመወዝ፣ የሥርዓተ ቅዳሴ መ/ር ሐዲስ ትኩነህና የትምህርተ ሃይማኖትና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን መ/ር ዶ/ር ሐዲስ የሻነህ ናቸው፡፡

አማሳኞች ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት የፈረጁበት ስብሰባና መግለጫ ሊቃነ ጳጳሳቱን አስቆጣ

  • ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች ገልጸዋል
  • የቤተ ክርስቲያንን እንጀራ እየበሉና በጀቷን አውጥታ እያስተማረቻቸው የሌላ እምነት በሚያራምዱ የስም ደቀ መዛሙርት ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ
(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፫ ቁጥር ፯፻፵፩፤ መጋቢት ፳ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.)
Admas logoየኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ የኾኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዐት እንዲማሩ፣ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በማቀናጀት ሞያዊ ድጋፍ እንዲያበረክቱ በማስተባበር ላይ የሚገኘውን ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት በመፈረጅ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካይነት ጠቅላላ ሀብቱና ንብረቱ የሚታገድበት ውሳኔ እንዲተላለፍ በመንግሥትም በኩል እርምትና ርምጃ እንዲወሰድበት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአድባራት አስተዳዳሪዎች መግለጫ አውጥተውበታል በተባለው ስብሰባ ጉዳይ ኹለት ሊቃነ ጳጳሳት ለከፍተኛ የመንግሥት ሓላፊዎች ቅሬታቸውን ማሰማታቸው ተገለጸ፡፡
የቅ/ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስንና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን በስም የጠቀሱት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች፣ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ያቀረቡት ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች እንደኾነ ቢገልጹም የሓላፊዎቹን ስም ከማሳወቅ ተቆጥበዋል፡፡
Lukas
ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና በክልል ትግራይ የምዕራብ ሰቲት ሑመራ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ማኅበረ ቅዱሳን የደረሰበት ፈታኝ ወቅት

FACT magazine Megabit 3rd cover(ፋክት፤ ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፱፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.)
ተመስገን ደሳለኝ
  • በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም አዝማችነት በማኅበሩ ላይ የደቦ ዘመቻ ከተከፈተ ሰነባብቷል፡፡ በጥናት ስም በተከታታይ የሚወጡና በየመድረኩ የሚቀርቡ ወረቀቶች ማኅበሩን የኦርቶዶክስ አክራሪከማለት አሻግረው ‹‹የግንቦት ሰባት መንፈሳዊ ክንፍ/የግንቦት ሰባት ከበሮ መቺ/›› ሲሉ ይወነጅሉታል፡፡
  • የማኅበሩ አመራሮች እንዲኽ ዓይነቱን ውንጀላ በተመለከተ በተለያየ ጊዜ ከአቶ በረኸት ስምዖን እስከ ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም፣ ከአዲስ አበባ የጸጥታ ሓላፊዎች እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደኅንነት አማካሪ አቶ ፀጋይ በርሀ ድረስ ያሉ ባለሥልጣናትን በቢሯቸው ተገኝተው ውንጀላው ተቀባይነት ያለው ማስረጃ የማይቀርብበት የሐሰት እንደኾነ ቢያስረዱም መፍትሔ እንዳላገኙ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
  • በግልባጩ በመንግሥት ተቋማት ያሉ የፋክት መጽሔት መረጃ አቀባዮች፣ በግንቦት ወር ከሚካሔደው የሲኖዶሱ መደበኛ ዓመታዊ ጉባኤ በፊት፣ ከኻያ የሚበልጡ የማኅበሩ አመራሮችን ከሽብርተኝነት ጋራ በማያያዝ ለመክሰስና ማኅበሩንም እንደተለመደው በዶኩመንተሪ ፊልም ለመወንጀል ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
  • በዚኽ አስቸጋሪ ወቅት ደግሞ መነሣት የሚኖርበት አስቸጋሪ ጥያቄ፣ እንዴት ይህን ማኅበር ወደ ቀጣዩ ትውልድ ማሻገር ይቻላል? የሚለው ሲኾን ምላሾቹም ኹለት ናቸው፡፡ ‹‹ችግሮች ኹሉ የየራሳቸው በጎ ገጾች አሏቸው›› እንዲሉ፣ ማኅበሩ የደረሰበትን ይህን ፈታኝ ጊዜ ተከትለው የሚመጡ ኹለት ወቅቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው፣ በቀጣዩ ወር የሚታሰበውየስቅለት ቀን ነው፡፡ ኹለተኛና በእጅጉ የተሻለ ነው ብዬ የማስበው ጊዜ ደግሞ ቀጣዩ የ2007 ዓ.ም. ምርጫ ነው፡፡
  • የሃይማኖቱ ተከታዮች በሙሉ በየቤተ ክርስቲያኑ የሚውሉበት የስቅለት በዓል የትኞቹም የሕገ መንግሥቱ ሐሳቦች አልያም የሞራል ዕሴቶች የማይገዛው ሥርዓት እጁን ከማኅበሩና ከቤተ ክርስቲያን በአጠቃላይ እንዲያነሣ ለመጠየቅ ብሎም ሕያውነታቸውን የመሠረቱበትን ሃይማኖት ለማስከበር የተመቸ ቀን ስለመኾኑ ማስታወስ አባላቱን አሳንሶ መገመት እንዳይኾን ተስፋ አደርጋለኹ፡፡