- ‹‹ለዚህ መረጃ አቡነ ማቲያስ የቀድሞ የኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስ በአሁን ሰዓት 6ተኛው ፓትርያርክ፣ አቡነ ሣሙኤልና አቡነ ኢሳይያስ ህያው ምስክሮች ናቸውና›› መረጃውን የላኩልን የሎሳንጀለስ ምዕመን
- ‹‹አባ›› ሰረቀ ታቦት ሰርቀው ተይዘዋል፡፡ ከገዛናቸው 12 ጸናጽል ያስረከቡን ስድስቱን ሲሆን፤ ከ 12ቱ መቁዋሚያም 6ቱን ይዘውብን ሄደዋል፡፡
- ‹‹አቡነ አረጋዊም የሚባል ቤተክርስቲያን የለም፡፡›› ‹‹አባ›› ሰረቀ ብርሃን በአንድ ወቅት የሰበኩት ስብከት
- ‹‹በወቅቱ የአሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት አቡነ ማቲያስ ማኅተም ወስደው በነጭ ወረቀት ላይ እያተሙየኔን ፊርማ እያስቀመጡ ሰዎችን ብር እየተቀበሉ ከኢትዮጵያ ወደዚህ ሲያመጡተደርሶባቸው..........››በወቅቱ አባ ሰረቀ ከጓደኛቸው ጋር ሲሰሩት የነበረ ሥራ የምዕመኑ ቃል
ከአንድ የሎስ አንጀለስ ምዕመን የደረሰን መልዕክት
(አንድ አድርገን የካቲት 11 2006 ዓ.ም)፡- በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት ሊካሄድ የታሰበው የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ በአባ ሰረቀ ብርሃን አማካኝነት ከቅዱስ ፓትርያርኩ በተሰጠ መመሪያ መሠረት ሳይካሄድ መቅረቱ ይታወቃል፡፡ የአባ ሰረቀን የቀድሞ ተግባር በርካታ ምዕመን ቢያውቀውም ብጹዕ አቡነ ማቲያስ የሚያውቁትን እና በሎስአንጀለስ ምዕመናን ላይ ያደረሱትን በደል የደረሰንን መልዕክት ለእናንተው ለማድረስ ወደድን፡፡ ‹አባ› ሰረቀን ከአመታት በፊት በታቦት ሌብነት ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ዘንድ ቀርበውም እንደነበርም መረጃው ያመለክታል፡፡ ስለዚህ ቅዱስነታቸው አሁን እየሰሩ የሚገኙት ቀድሞ ለሰሚ ጆሮ የሚከብድ ዝርፊያ በቤተ ክርስቲያን ላይ ካደረገ ሰው ጋር መሆኑን ነው፡፡ እስኪ በወቅቱ የነበሩ ህያው ምስክሮች የላኩልንን መረጃ ይህን ይመስላል፡፡