Thursday, July 18, 2013

ዜና ብሥራት ዘሥላሴ! ሐኬተኛው እና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲወገድ ቋሚ ሲኖዶስ ወሰነ!

  • መ/ር ፍሥሐ ጽን ደመወዝ በማስተማር ሥራ ብቻ ይወሰናሉ
  • የአቡነ ጢሞቴዎስ ቀጣይነት እየተጤነ ነው
  • የቅ/ሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ ነገ እንደሚካሄድ ይጠበቃል
ጥቅመኛው፣ ሐኬተኛው (ክፋተኛው) እና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከያዘው የቀን መደበኛ መርሐ ግብር አስተባባሪነት እንዲወገድ ቋሚ ሲኖዶስ ከስምምነት ላይ ደረሰ፡፡
ቋሚ ሲኖዶሱ ከዚህ ዐቢይ የስምምነት ውሳኔ ላይ የደረሰው በኮሌጁ አስተዳደርና በደቀ መዛሙርቱ መካከል ላለፉት ስድስት ወራት እየተባባሰ የመጣውን ውዝግብ ለማጣራት የተቋቋመው ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ ከኮሌጁ መምህራንና የደቀ መዛሙርቱ መማክርት አመራሮች ጋራ ከመከረ በኋላ ነው፡፡


ትላንት እና ዛሬ ቋሚ ሲኖዶሱ በወቅታዊ የኮሌጁ ኹኔታ ላይ ሲያካሂድ በዋላቸው ተከታታይ ስብሰባዎች፣ አጣሪ ኮሚቴው የኮሌጁንአካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ይዞታ ለማሻሻል ከአጭር እና ረጅም ጊዜ አኳያ በመፍትሔነት ያቀረባቸውን የውሳኔ ሐሳቦች መርምሯል፡፡ በዚህም መሠረት በኮሌጁ መደበኛ ደቀ መዛሙርት ቅሬታ ከቀረበባቸው መካከል አንዱ የኾነውና ተደራራቢ ሓላፊነቶችን የያዘው ዘላለም ረድኤት ከሐላፊነቱ መነሣት እንዳለበት ተስማምቷል፡፡
በአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ላይ እንደተገለጸው፣ ዘላለም ረድኤት ‹‹መምህር፣ የቀን መርሐ ግብር ሓላፊ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽንና የአስተዳደር ጉባኤ አባል›› ነበር፡፡ በሐኬተኛውና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት ላይ የታዩበትን ጉድለቶችና ድክመቶች ኮሚቴው በሪፖርቱ ገጽ 14 ላይ  እንደሚከተለው ዘርዝሮታል፡-
  • ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ በማስተርስ መርሐ ግብር ሞያቸው ያልኾነውን ትምህርት ማስተማር፡፡ በኮሌጁ ከመጀመሪያ ጀምሮ ለዲግሪ መርሐ ግብር የምርምር ዘዴ /Research Method/ የሚያስተምሩት በሞያው ልምድና ዕውቀት ያላቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚመጡ መምህራን ናቸው፡፡ ለማስተርስ ፕሮግራም ደግሞ የበለጠ ስፔሻላይዝድ ያደረገ መምህር መኾን ይኖርበታል፡፡ በኮሌጁ የተደረገው ግን÷ በሞያው ልምድና ዕውቀት ያላቸው መምህር ተነሥተው መ/ር ዘላለም ያጠኑት ነገረ መለኰት ኾኖ ሳለ ምርምር ዘዴን ለማስተርስ ፕሮግራም ያስተምራሉ፡፡
  • የቀን መርሐ ግብር አስተባባሪ ኾነው ሳለ ተማሪውንና መምህሩን አስተባብሮ አለመምራት፤
  • መደበኛ ደቀ መዛሙርት በኩል ግን ‹‹ለሚያስተምሩት ትምህርት ብቁ አይደሉም›› ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ እርሳቸው በኮሚቴው ፊት ከተማሪዎች ለሚቀርቡባቸው ቅሬታዎች እንዲከራከሩ ቢጠየቁም ኮሚቴውን ረግጠው ወጥተዋል፡፡ በዚህም ‹‹ብቁ መምህር አይደሉም›› የሚለውን ቅሬታ የተቀበሉት አስመስሏል፡፡
  • ለአጣሪ ኮሚቴው ሥራ ተባባሪ ተባባሪ አለመኾን፡፡ ኮሚቴው ለሚያቀርብላቸው ጥያቄዎች ቀና ምላሽ አለመስጠትና እንዲስተካከሉ በኮሚቴው ለተሰጣቸው ሥራዎች ተባባሪ ኾኖ ከመገኘት ይልቅ ሥራዎቹ እንዳይሠሩ መሞገት፤
  • በክፍል ተገኝቶ አለማስተማር፤ በደቀ መዛሙርቱና በአስተዳደሩ መካከል አለመግባባት ከተፈጠረ በኋላ ተማሪዎች፣ ‹‹መምህር ዘላለም ረድኤት አያስተምረንም›› እያሉ ጥያቄ ሲያቀርቡ እርሳቸው ግን ‹‹ማስተማር አለብኝ.› በማለት ይናገሩ ነበር፡፡ በአጣሪ ኮሚቴው ከፍተኛ ጥረት ተማሪዎች ጥያቄያቸውን አንሥተው እንዲያስተምሩ ከተስማሙ በኋላ ግን መምህር ዘላለም ረድኤት አንድ ክፍል እንደገቡ ‹‹ተማሪዎች እንዳላስተምር መሰናክል ኾነውብኛል›› በማለት ደብዳቤ ለአስተዳደሩ አስገብተው ማስተማራቸውን አቁመዋል፡፡ መ/ር ዘላለም ረድኤት ለማስተማር ፈቃደኛ አለመኾናቸውን ገልጸዋል፡፡ የመማር ማስተማሩን ሥራ ወደነበረበት ለመለሰው ለኮሚቴው ግን በግልባጭ አላሳወቁም፡፡ ይህም ለኮሚቴው ሥራ ተባባሪ አለመኾናቸውን ያሳያል፡፡
  • በደቀ መዛሙርቱ በኩል መ/ር ዘላለም ረድኤት በክፍል ውስጥ የሃይማኖት ሕጸጽ ያስተምራሉ ሲሉ ይከሳሉ፡፡ ይህን የቀረበባቸውን ክሥ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ፊት ለፊት ተገናኝተው እንዲያስረዱ ቢጠየቁም ፈቃደኛ ኾነው አልተገኙም፡፡
  • በቅርብ ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ነገሮችን ማባባስ፤ መ/ር ዘላለም ከአጣሪ ኮሚቴው ጋራ በቅርብ ከመሥራት ይልቅ የኮሚቴውን ጥረት በመልካም ጎን ተቀብሎ በክፍል ተገኝቶ አለማስተማር፤ ችግር ተፈጥሮብኛል በሚል ሰበብ ደብዳቤ ለአስተዳደሩ ማስገባት፤ ከዚያም የሥራ መልቀቂያ ማቅረብ ወዘተ ናቸው፡፡
  • የቀን አስተባባሪ እንደመኾናቸው መጠን መምህራን ማስተማራቸውን፣ ተማሪዎችም መማራቸውን በቅርብ ኾነው መከታተልና መቆጣጠር ሲገባቸው ይህን አላደረጉም፡፡
  • በተማሪዎች በኩል ግሬድ ተበላሽቶብናል ሲባሉ አፋጣኝና ተገቢ የኾነ መልስ አለመስጠት፤
አጣሪ ቡድኑ ከዚህ የሐኬተኛው፣ ሓካዩ እና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት ‹‹ክፍተቶች›› በመነሣት በመፍትሔነት ያቀረበው የውሳኔ ሐሳብበአጭር ጊዜ መወሰድ ከሚገባቸው የማስተካከያ ርምጃዎች ጋራ የሚደመር ነው፡፡ ስለኾነም በሪፖርቱ ገጽ 17 ተ.ቁ 8 ላይ በዘላለም ረድኤት ላይ መወሰድ የሚገባው የማስተካከያ ርምጃ እንደሚከተለው ነው የተገለጸው፤
  • መ/ር ዘላለም ከላይ እርሳቸውን በተመለከተ በተዘረዘሩት ምክንያቶች ከኮሌጁ ተነሥተው ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በሚመድባቸው ቦታ እንዲመደቡ ቢደረግ፣ የቀረበባቸው የሃይማኖት ሕጸጽ ጉዳይ በሚመለከት እንዲጣራ ቢደረግ፤
በዚህም መሠረት ቋሚ ቅ/ሲኖዶስ የኮሌጁን መምህራንና የደቀ መዛሙርቱን መማክርት አመራሮች በመያዝ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ባደረገው ስብሰባ የአጣሪ ኮሚቴውን የመፍትሔ ሐሳብ ከሚያጸድቅ የስምምነት ውሳኔ ላይ ደርሷል! ጥቅመኛው፣ ሐኬተኛው(እኵዩ)፣ ሓካዩ(ሰነፉ) እና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት ከኮሌጁ ተወግዷል!
ሐኬተኛው ዘላለም የሰሞኑ ውሎውን እንደተለመደው በኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ መኖሪያ ቤት አድርጎ ሊቀ ጳጳሱን ወደ በለጠ ክፋትና ስሕተት የሚያስገቡ የከሣሽነትና የነገረ ሠሪነት ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉ ተነግሯል፡፡
በዚህ ተግባሩ ለደቀ መዛሙርቱ ጥያቄዎች ሽፋን የሰጡ የሳምንቱን ጋዜጣዎች ሰብስቦ ይዞ ገብቶ በንባብ ያሰማቸዋል፤ ከዚሁ ጋራ በተያያዘም የኮሌጁ አካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ችግሮች እንዲቀረፉና እንዲሻሻሉ በሚደረገው ጥረት ግንባር ቀደም ሚና ይጫወታሉ ያላቸውን መምህራንንና ደቀ መዛሙርትን በስም እየለየ ለሊቀ ጳጳሱና ሊቀ ጳጳሱ ለሚያውቋቸው የፖሊቲካና የጸጥታ ሓላፊዎች እንደ ኦፕሬተር በሞባይል ስልክ እያገናኘ ያስጠቁራል፤ ይወነጅላል፤ ይከሣል፡፡
መምህራኑ ከሳምንቱ መጀመሪያ አንሥቶ፣ ከሊቀ ጳጳሱ ዕርግናና ከጤንነትም አኳያ አጥርቶ ለማየትና ለመስማት ካለባቸው እክል በመነሣት ኮሌጁን በበላይ ሓላፊነት ሊመሩ እንደማይችሉ በመግለጽ፣ የወቅቱ አመራራቸውም እንደ ዘላለም ላሉት ሐኬተኞችና የማይገባቸውን ጥቅም ለሚያገኙ ድጋፍ ሰጭዎች ተንኰል በመጋለጡ የኮሌጁን አስተዳደር ወደ አደገኛ አቅጣጫ እየገፋው መኾኑን በዝርዝር በማስረዳት ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ ወይም የፈላጭ ቆራጭነት ሥልጣናቸው እንዲገደብ የአቤቱታ ፊርማ ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ማስገባታቸው ተዘግቧል፡፡
ይኸው የመምህራኑ ጥያቄ የደቀ መዛሙርቱንም ጠንካራ ድጋፍ ያገኘ ሲኾን ቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ በነገው ዕለት ለመንበረ ፓትርያሪኩ መቀመጫ በቅርበት ከሚገኙ አህጉረ ስብከት የጠራቸውን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በመጨመር በሚያደርገው አስቸኳይ ስብሰባ ጉዳዩን ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚነጋገርበት ይጠበቃል፤ በውጤቱም ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪክ አቡነ ማትያስ ጋራ ባላቸው የቆየና የጠበቀ ወዳጅነት ‹‹ኮሌጁ ሀገረ ስብከቴ ነው፤ በሀ/ስብከቴ ጣልቃ አትግቡብኝ›› በማለት ሥልጣናቸውን ሲከላከሉ በቆዩት አቡነ ጢሞቴዎስ ቀጣይነት ላይ ዐቢይ ውሳኔ ሊተላለፍ እንደሚችል ተገምቷል፡፡
በሌላ በኩል ቋሚ ሲኖዶሱ ባሳለፈው ውሳኔ ቅሬታ ከቀረበባቸው ሓላፊዎች አንዱ የኾኑት የኮሌጁ አካዳሚክ ምክትል ዲን መ/ር ፍሥሓ ጽዮን ደመወዝ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡና የተመጠኑ ኮርሶችን ይዘው በማስተማር ሥራ እንዲቀጥሉ በአጣሪ ኮሚቴው የቀረበውን የመፍትሔ ሐሳብ አጽንቷል፡፡ በኮሚቴው ሪፖርት ገጽ 13 ላይ እንደተገለጸው መ/ር ፍሥሓ ጽዮን የሚከተሉት ክፍተቶች ተገኝቶባቸዋል፡፡
  • ተደራራቢ ሓላፊነት መያዝ፤ በኮሌጁ ያሉትን መምህራን እና ሠራተኞች በልዩ ልዩ ሥራዎች ማሳተፍ ሥራዎችና በተቀላጠፈ እና በአጭር ጊዜ እንዲሠሩ ያደርጋል፡፡ አንድ ሰው ብዙ ሥራዎችን ከያዘ ግን ሥራዎች በተቀላጠፈና በጠራ ኹኔታ መካሄዳቸውን ጥርጥር ውስጥ ይከታል፡፡ በሌሎች መምህራንና ሠራተኞች ዘንድም ቅሬታን ይፈጥራል፡፡ መ/ር ፍስሃፅየን ደመወዝ÷ መምህር፣ የቦርድ ጸሐፊ፣ የአካዳሚክ ምክትል ዲን፣ የአካዳሚክ ኮሚሽን ምክትል ሰብሳቢና የአስተዳደር ጉባኤ አባል በመኾን በኮሌጁ ውስጥ እያገለገሉ ናቸው፡፡ የኮሌጁ ደቀ መዛሙርት እንደሚናገሩት፣ መምህሩ በብዙ ሥራ በመጠመዳቸው ከዝግጅት ጊዜ ማነስ የተነሣ እና በልዩ ልዩ ስብሰባዎች ስለሚያዙ ከእርሳቸው ማግኘት የሚገባንን ትምህርት አላገኘንም ይላሉ፡፡
  • ተማሪዎች ለሚያቀርቡት ትምህርት ነክ ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ አለመስጠት
  • ተማሪው መማር አለመማሩን፤ መምህራኑም በተገቢው ኹኔታ ማስተማራቸውን አለመቆጣጠርና አለመከታተል፡፡ ምንም እንኳ ከመምህራንና ከተማሪዎች መካከል በክፍል የማይገኙ ቢኖሩም በዚህ በኩል ተገቢው እርምት አለመወሰዱን ተገንዝበናል፡፡
  • በቤተ መጻሕፍቱ ለደረሰው ችግር መፍትሔ አለመፈለግ፤
  • መምህራኑም ኾኑ ተማሪዎች አስተዳደራዊ ጥያቄዎች ሲጠይቋቸው በቁጣ መመለስ፤
  • ካሪኩለሙ ሲከለስ መምህራኑን አለማሳተፍ፤
  • ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋራ ተቀናጅቶና ተናቦ አለመሥራት፤
ኮሚቴው ከእኒህ ዋነኛ ‹‹ክፍተቶች›› አንፃር በአጭር ጊዜ እንዲወሰድ ባቀረበው የማስተካከያ ርምጃ መሠረት መ/ር ፍሥሓ ጽዮን ከተደራራቢ ሓላፊነታቸው ተነሥተው የተመጠኑ ኮርሶችን ብቻ ይዘው እንዲያስተምሩ ሐሳብ አቅርቧል፤ በዛሬው ዕለትም ቋሚ ሲኖዶሱ በስምምነቱ ያስረገጠው ይህንኑ የመፍትሔ ሐሳብ ነው፡፡ እዚህ ላይ ሳይጠቀስ የማይታለፈው አጣሪ ኮሚቴው ከሐኬተኛው ዘላለም ረድኤት በተለየ መ/ር ፍሥሓ ጽዮንን ያመሰገነበት ኹኔታ ነው፡-
  • የመምህር ፍሥሓ ጽዮን ጠንካራ ጎን ተማሪዎች እንደመሰከሩላቸው ብቁ መምህር ናቸው፡፡ ለአጣሪ ኮሚቴው የሥራ ትብብር በማድረግ ለሥራው መቃናት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ አስፈላጊውን ትብብር አድርገዋል፡፡ ከተማሪዎች የቀረቡባቸውንም ቅሬታዎች ፊት ለፊት ተገኝተው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በተማሪዎቹ እና በመምህሩ መካከል በተደረገው ክርክርም ሪፖርቱ እንደገለጸው፣ ‹‹የአጣሪ ኮሚቴው አባላት እውነት እማን ዘንድ እንዳለች ለመረዳት አስችሏቸዋል፡፡››
ዜናው የተገኘበት ምንጭ: http://haratewahido.wordpress.com/ 
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም

No comments:

Post a Comment