በቅድሚያ እንኳን ለጌታችን እና ለመድኅኒታች ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት ሁላችንንም በሰላም አድረሰን እንዲሁም ቅዱስ
| አባ ፍቅረማርያም አጣናው |
ሚካኤል ቃና ዘገሊላ ሁላችንንም በያለንበት በስላም አድረሰን እንላለን፤ ባለፈው በአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን አስተዳደር ላይ ሰፋ ያለ ዳሰሳ አዘጋጅተን እንዳስተላለፍን ይታወሳል፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአቡነ ተክለሃይማኖት አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ፍቅረማርያም አጣናው አንተነህ በአቡነ አብረሃም አማካኝነት ከኢትዮጵያ መጥተው አንገታቸውን ደፍተው የተጠጉ እና የሕዝቡን ፍቅር እና አክብሮት ካገኙ በኃላ ሁኔታዎች በሙሉ በእኔ ቁጥጥር ሥር ነው ብለው በአመኑበት ሰዓት ይልቁንም አሁን ባለው አዲስ በተገዛው ሕንጻ ላይ የበላይነታቸውን ይዘው ከዚህ በኃላ ከእኔ በስተቀር ማንም ሰው በዚህ አጥቢያ ላይ ሊያዝም ሆነ ሊናዝዝ አይችልም ብለው አምነው ወይንም ተመኝተው ሕዝቡንምም ሆነ ማኅበረ ካሕናቱን እየበጠበጡት የሚጉኙት የቀበሮው መነኩሴ ዛሬ ላይ በርካታ ካህናትን በማገድ፤ እንዲሁም ብዙ መከራ አይተው በገንዘብ፣ በእውቀት እንዲሁም በሙያ ሲያግዙ የነበሩትን ምዕመናን ከዚህ በኃላ የዚህ አጥቢያ አባል አይደላችሁም በማለት በማገድ ማሕበረ ምዕመናኑን በተለይ ይቃወኛል ወይም እኔ በምለው መንገድ አይሄድም ብለው ያሰቡትን በሙሉ በማገድ፤ ማኅበረ ምዕመናኑን በማወክ ላይ እንደሚገኙ ለመረደት ችለናል፤ በተለይ በዚህ አጥቢያ ላይ ከባድ የሆነ ይልቁንም በመላው አሜሪካ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የማናለብኝነት እና የጎጠኝነት ሥራቸውን እይሰሩ እያ እያስፋፉ እንደሚገኙ መረጃ ያደረሱን ይሄንን ገልጸውልናል።