
Friday, August 16, 2013
‹‹ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በእግዚአብሔር››

Wednesday, August 14, 2013
“በ22 ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ያስተዳደረ ሙስሊም የለም” የሙስሊሞች የተቃውሞ ድምጽ

አዲስ አበባ በለውጥ አመራር ያብባል ገና
- በምደባ ቅር የተሰኙ ሓላፊዎች በየሆቴሉና ሬስቶራንቱ የዐመፅ ምክክር ይዘዋል
- ‹‹የቋሚ ሲኖዶሱ ምደባ በአተገባበር በደላሎች ተጠልፏል›› የሚል ቅሬታ አላቸው
- የረዳት ሊቀ ጳጳሱና ጽ/ቤታቸው ድርሻ የቋሚ ሲኖዶሱን ምደባ ማስፈጸም ብቻ ነው
- በዘላቂው የሀ/ስብከቱ መዋቅር ስፍራ የሚኖራቸው በጊዜያዊ ምደባቸው ብቃት ያሳዩ ሓላፊዎችና ሠራተኞች መኾናቸው ተገልጧል
የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ለአደረጃጀትና አሠራር ለውጥ በሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት ለዘረጋው የሽግግር ጊዜ መዋቅር የሓላፊዎችና ሠራተኞች ምደባ አካሂዷል፡፡ እስከ ጥቅምት ወር መጨረሻ ፳፻፮ ዓ.ም ድረስ ለሦስት ወራት በሚቆየው የሽግግር መዋቅር 133 የሀ/ስብከቱ ሐላፊዎችና ሠራተኞች በምደባው ታቅፈዋል፡፡ ከእኒህም ውስጥ 57 በሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት፣ 76 ያህሉ ደግሞ ለአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ቅርበት ባላቸው ሰባት የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቶች የተመደቡ ናቸው፡፡
ምደባውን ያካሄደው በቋሚ ሲኖዶስ የተሠየመውና በመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አባ ኀይለ ማርያም መለሰ የሚመራ መዳቢ ኀይለ ግብር ነው፡፡ ኀይለ ግብሩ ሰብሳቢውን ጨምሮ አምስት አባላት ያሉት ሲኾን እነርሱም የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ አስተዳደር መምሪያ፣ የሒሳብና በጀት መምሪያ፣ ጠቅላላ አገልግሎት ሓላፊዎችንና የቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ተወካይን በአባልነት የያዘ ነው፡፡ መረጣና ምደባው (selection and placement) የተሠራበት መነሻ በቋሚ ሲኖዶሱ የጸደቀው የሀ/ስብከቱ አስተዳደራዊ መዋቅርና ከእያንዳንዱ የሥራ መደብ ጋራ ተነጻጽሮ የቀረበው ዝርዝር የመመዘኛ መስፈርት ነው፡፡ በመስፈርቱ መሠረት የትምህርት ዝግጅት እና የሥራ ልምድ ዋነኛ መመዘኛ መደረጉ የተገለጸ ሲኾን ‹‹የብሔር ተዋፅኦ››ም ከግንዛቤ ገብቷል ተብሏል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)