- ተማሪዎች÷ አካዳሚክ ምክትል ዲኑ እና የቀን መርሐ ግብር አስተባባሪው ከሓላፊነታቸው ካልተነሡ ያቋረጡትን ትምህርት እንደማይቀጥሉ አስታውቀዋል
- አስተዳደሩ÷ ተማሪዎች ትምህርት ካልጀመሩ ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፤ ለውዝግቡ መባባስ የተማሪዎች መማክርትን ተጠያቂ አድርጓል
- የመደበኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ትምህርት ከተቋረጠ ዘጠነኛ ቀኑን አስቆጥሯል
- ደቀ መዛሙርቱ አካዳሚያዊና አስተዳደራዊ ሓላፊነቶችን ደራርበው የያዙ መምህራን በሚታይባቸው የማስተማር ዝግጅት ማነስ ተማርረዋል
- የቀን መርሐ ግብር አስተባባሪው÷ መ/ር ዘላለም ረድኤት÷ በሸውከኛነት (ነገረ ሠሪነት) ኰሌጁን ሰላም በመንሳት ተከሠዋል
- ለ14 ዓመታት ያህል በኮሌጁ የበላይ ሓላፊነት የቆዩት ሊቀ ጳጳስ ‹‹በቃዎት›› ተብለዋል
- ውዝግቡ ከመ/ፓ/ጠ/ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሓላፊዎች አቅም በላይ ኾኗል
- ‹‹ትምህርት የምንጀምረው የዛሬም የሁልጊዜም ጥያቄዎቻችን የነበሩት ችግሮች ተፈተው ተገቢ ምላሽ ስናገኝ ብቻ ነው›› /ደቀ መዛሙርቱ/
- ‹‹ችግራችሁን እናስተካክላለን፤ ጥያቄዎቻችሁን እንመልሳለን፤ ነገር ግን ወደ ክፍል ገብታችኹ ትምህርታችሁ ቀጥሉ›› /የኮሌጁ አስተዳደር/
Source: http://haratewahido.wordpress.com/
የተዋሕዶ ቤተሰቦች በመላው ዓለም
No comments:
Post a Comment